No summary available.
ጥር 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዓሕመድልሃዱ ካህሳይ - ከጠበቃ ወ/ጊዮርጊስ ማሩ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዓቃቤ ህግ - በላለበት።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ አመልካች በሥራና ሰራተኛ ማገናኘት አገልግልት አዋጅ ቁ. 632/2002 በአንቀጽ 16(1) (መ)፣ 18(1) (ሀ)፣ 20(2) እና 40(3) የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ወንጀል ፈጽሟል በማለት ተጠሪ በመሰረተው ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። የክሱም ዝርዝር ተከሳሽ (አመልካች) ኢትዮጵያውያንን ለሥራ ወደ ውጭ አገር ለመላክ የሚያስችል ፈቃድ አውጥቶ ገልፍ የግል ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የሚል ከፍቶ በሚሰራበት ጊዜ የግል ተበዲይ ወ/ሪት ፊኢዛ ይመር ዘገየን በኤጀንሲው ፀሐፉ አማካኝነት ማሟላት የሚገባትን ቅድመ ሁኔታዎች እንድታሟላ ከተደረገች በኋላ በኤጀንሲው በኩል የአየር ቲኬት እና ቪዛ በኢሜል ተልኮላት በአዋጁ መሰረት ውለን በሚመለከት በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር በኩል ሳያዋውል ሚያዝያ 7 ቀን 2001 ዓ.ም ወደ ባህሬን አገር የላካት በመሆኑ ከተላከችም በኋላ መብቷንና ደህንነቷን መጠበቅ ሲገባው ባለመጠበቁ ተበዲይዋ ለብዙ ስቃይ እንድትጋለጥ በማድረጉ እንዱሁም ተበዲይዋን የስራ ዘመንዋ ሲያልቅ ወይም ሲቋረጥ ወደአገሯ መመለስ ሲገባው ባለመመለሱ ወይም ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በፈጸመው የህግ መጣስ ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ በክሱ የተጠቀሰውን ድርጊት አልፈጸምኩም፤ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ክድ በመከራከሩ ክሱ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በቅድሚያ የዓቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ፣ አመልካች ሉከላከል ይገባል በማለት ብይን ሰጥቷል።
በመቀጠልም የአመልካችን የመከላከያ ማስረጃዎች የሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም አመልካች እንደክሱ አቀራረብ የወንጀል ድርጊቱ ስለመፈጸሙ በማስረጃ ተረጋግጧል የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ በአመልካች ላይ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህም አመልካች በብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር) እንዱቀጣ ወስኗል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበትን ውሳኔ አፅንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሐምል 11 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በስር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቧል።
እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የቀረበው የግል ተበዲይ በአመልካች ኤጀንሲ በኩል መሄድዋ ሳይረጋገጥ እንዱሁም በአካል ቀርባ እንግልት እንደደረሰባት ባላስረዲችበት አመልካች ጥፊተኛ ተብል የመቀጣቱን አግባብነት ሉመረመር ይገባል ተብል ነው። በመሆኑም ከሥር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር ከተሰጠው ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ እንዲመለከትነው ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ በዝርዝር እና በግልጽ ፍሬ ነገሮችን ያመለከተ ከመሆኑም በላይ፤ በአመልካች ድርጊት ተጣሱ የተባለትን የአዋጁ ድንጋጌዎችም እንደዚሁ በዝርዝር ተጠቅሰዋል። ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም እንደክሱ ያስረዲለ ተብለው በዓቃቤ ሕግ የተቆጠሩትን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ሰምቷል። በሰማው ማስረጃ ተበዲይ ወደባህሬን የተላከችው በዓቃቤ ሕግ ክስ ዝርዝር በተገለጸው ሁኔታ አመልካች ባመቻቸው መንገድ መሆኑን፣ የግል ተበዲይ ወደ ባህሬን ከሄደች በኋላ ችግር እንዲጋጠማት ሲነገረው እና ወደሀገርዋ እንዱያስመጣት ሲጠየቅ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን፣በመጨረሻም የግል ተበዲይ በራሷ ወጪ ተሳፍራ ወደ ሀገሯ ብትመጣም፤ ጤንነቷ ግን ደህና እንዲልሆነ በፍሬ ነገር ረገድ ማረጋገጡን በውሳኔው ላይ በዝርዝር እና በግልጽ ማመልከቱን ለመገንዘብ ችለናል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች የግል ተበዲይ ወደውጪ ሀገር የተላከችው ከእሱ እውቀት (እውቅና) ውጪ በኤጀንሲው ፀሐፉ በኩል መሆኑን እንደሚያስረዲ በመግለፅ ባስያዘው ጭብጥ መሰረት የመከላከያ ማስረጃ ማሰማቱን እና ፍ/ቤቱ ግን የተሰማው መከላከያ ማስረጃ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ለማስተባበል አልቻለም ለማለት ክብደት እንዲልሰጠው ተመልክተናል።
እንደምናየው አመልካች በዓቃቤ ሕግ በዝርዝር የተመለከተውን ፍሬ ነገር ክድ በመከራከሩ ፍ/ቤቱ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመመስረት ማስረጃዎን ሰምቷል። በዚህ ሂደት የሰማችውን ማስረጃዎችም መዝኖ መደምደሚያ ላይ ደርሷል። አመልካች ግን አሁንም የግል ተበዲይን ወደ ውጭ ሀገር ስለመላኩ በማስረጃ አልተረጋገጠብኝም በማለት ነው እየተከራከረ ያለው። ጭብጥ ለማስያዝ በሰበር ችልቱ እንዱመረመርለት የጠየቀውም ይህን የፍሬ ነገር ጉዲይ ነው። የግል ተበዲይ ቀርባ እስካልመሰከረችብኝ ድረስ እንግልት ደርሶባታል ተብል ጥፊተኛ መባል የለብኝም የሚል ክርክርም አንስቷል። እንደሚታወቀው ይህ የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት የፍሬ ነገር ጭብጥን በማስረጃ የማጣራትም/የማንጠርም/ ሆነ ማስረጃውን በመመዘን ድምዲሜ ላይ የመድረስ ሥልጣን በሕጉ አልተሰጠውም። በኢፉ.ዱሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(30(ሀ) እና በፋዳራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁ.25/88 አንቀጽ 10 እንደተደነገገው ለሰበር ችልቱ የተሰጠው የዲኝነት ሥልጣን የክርክር ሥርዓቱን ጨርሶ በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ የተፈጸመውን መሰረታዊ የህግ ስህተት በማረም የተወሰነ ነው። በመሆኑም ድርጊቱን ለመፈጸሜ በማስረጃ ሳይረጋገጥ ነው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተላለፈብኝ የሚለውን መነሻ በማድረግ አመልካች ያስያዘውን የፍሬ ነገር ጭብጥ የምንመረምርበት አግባብ የለም። የግል ተበዲይ የሆነ ሰው እስካልመሰከረ በላልች ማስረጃዎች የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ማረጋገጥ አይቻልም የሚል የህግ ፍልስፍናም ሆነ ሕግ ስለላለም የግል ተበዲይ ቀርባ ስለደረሰባት እንግልት ሳታስረዲ ጥፊተኛ መባላ ተገቢ አይደለም የሚለው የአመልካች መከራከሪያም ተቀባይነት ያለው አይደለም። ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው የምንልበት ምክንያት የለም። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.95035 ሰኔ 21 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍቤት በወ/ይ/መ/ቁ. 59774 ግንቦት 10 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕግ/ሥ-ሥ-ሕ-ቁ. 195(2)(ለ) (2) መሰረት ፀንቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
No topics extracted.