No summary available.
ጥር 15 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዱ - ኤም - ሲ ኮንስትራክሽን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ኢብራሂም ኢቲሶ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመደበኛ ጉዲይ ችልትና የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የውል አፈፃጸምና የጉዲት ካሳ ጥያቄን የሚመለከት ነው። በሥር ፍ/ቤት ክስ ያቀረበው ተጠሪ ነው። ተጠሪ በቱላ ክ/ከተማ ቶል ቀበላ ክልል ባለኝ የይዞታ ቦታዬ ላይ የነበረኝን የድንጋይ ማውጫ ካባ ተከሳሽ ለአንድ ዓመት በኮንትራት ይዞ ለመጠቀም ተስማምቷል። ተከሳሽ ለካባው ዋጋ ብር 60,000 (ስድሳ ሺህ ብር) በመጀመሪያ የከፈለ ሲሆን ቀሪውን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ለመክፈል ከተስማማ በኋላ ቀሪውን ክፍያ ያልከፈለኝ ስለሆነ በውለ መሰረት ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) እንዱከፍል ይወሰንልኝ። ከዚህ በተጨማሪ ተከሳሽ ድንጋይ ሲያወጣ በአቅራቢያው የነበረውን የእርሻ መሬት ከጥቅም ውጭ በማድረግ ጉዲት አድርሶብኛል። በይዞታዬ በነበረው የእርሻ መሬት ላይ ላደረሰው ጉዲት ብር120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ለመክፈል የዕርቅ ስምምነት ውል የተዋዋለ በመሆኑ ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) የጉዲት ካሳ እንዱከፍል ይወስንልኝ በማለት አመልክተዋል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርቦ ከሳሽ በውለ መሰረት የካባ ድንጋዩን እንድጠቀም ያላደረገና የውል ግዳታውን ያልፈፀመ በመሆኑ ቀሪውን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የመክፈል ግዳታ የለብኝም። የእርሻ መሬቱ ከሳሽ ድንጋይ እንዱወጣበት የፈቀደና የውል ግዳታ የገባበት ነው።
ለደረሰበት ጉዲትም ብር 9000 (ዘጠኝ ሺህ ብር) ለሰጠሁት ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) የሚጠይቅበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቷል። ጉዲዩን የያዘው ችልትም አመልካችና ተጠሪ ከሚከራከሩበት መሬት ድረስ በመሄድ የእርሻ መሬቱ ላይ የደረሰውን ጉዲት ተመልክተናል።
ከዚህ በተጨማሪ በእርሻ መሬቱ ላይ በነበረው ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዲት እንዱገመት በማድረግ ብር 62,000 (ስድሳ ሁለት ሺህ ብር) ግምት ያለው ንብረት የወደመ መሆኑን በግብርና ባለሞያ ግምት ተሰርቶ ቀርቦለታል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሳሽ በውለ መሰረት የካባ ድንጋዩን በማውጣት የተጠቀመ ስለሆነ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የመክፈል ኃላፉነት አለበት። እንደዚሁም ተከሳሽ የከሳሽን የእርሻ መሬት ከጥቅም ውጭ ያደረገ መሆኑ ተረጋግጧል። ተከሳሽ በእርሻ መሬቱ ላይ ላደረሰው ጉዲት ለከሳሽ ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በካሳ መልክ ለመክፈል የተስማማ መሆኑን የሚያረጋግጥ የፅሁፍና የሰው ማስረጃ ያቀረበ በመሆኑና የተከሳሽ ማስረጃ የከሳሽን ማስረጃ ለማስተባበል የማይችል በመሆኑ ተከሳሽ ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) የመክፈል ግዳታ አለበት። ስለዚህ ተከሳሽ ብር 160,000 (አንድ መቶ ስድሳ ሺህ ብር) ለከሳሽ ይክፈል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካች ሰኔ 8 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የታጠረ የእርሻ መሬቱ ጉዲት የደረሰበት የድንጋይ ካባውን ለአመልካች ከማከራየቱ በፉት ሆኖ እያለ አመልካች ጉዲት አድርሷል መባለ ተገቢነት የለውም። በእርሻ መሬቱ ላይ አመልካች ጉዲት አላደረሰም እንጅ ጉዲት አድርሷል የሚባል ቢሆን የጉዲቱ መጠን ብር 62,000 (ስድሳ ሁለት ሺህ ብር) መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) አመልካች ለተጠሪ እንድከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ተጠሪ የካባ ድንጋይ አመልካች እያወጣ እንዱጠቀም ያደረገው ውል የህገመንግስቱ አንቀፅ 43(3)ን የሚጥስ በመሆኑ ውለ ይፈፀምልኝ በማለት ሉጠይቅ አይችልም። ተጠሪ ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር) መቀበለን ባልካደበት ሁኔታ የሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ገንዘቡን አልተቀበለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ሀምላ 5 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች በእርሻ መሬቱ ላይ ጉዲት ያደረሰ መሆኑ ተረጋግጧል። ስለዚህ በሰበር ጉዲት አላደረስኩም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም ብር 62,000 (ስድሳ ሁለት ሺህ ብር) በመሬቱ ላይ የነበሩ ዛፍችና ላልች ንብረቶች ግምት ነው። በጉዲቱ የደረሰብኝን ኪሣራ የሚያጠቃልል አይደለም። አመልካች ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ለጉዲቱ ካሳ ለመክፈል የተስማማ ስለመሆኑ ማስረጃ አቅርቤያለሁ። አመልካች ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር) ለተጠሪ አልከፈለም። የካባው ድንጋይ ጉዲይ የተጠሪና አመልካች መከራከሪያ ባለመሆኑ አመልካች ተጠሪ የድንጋይ ካባ ለማከራየት አይችልም በማለት ያቀረበው ክርክር ተገቢነት የለውም። የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ሐምል 29 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ አመልካች ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ለተጠሪ የከፈለው በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት እንዱፈፀም ተገድድ በመሆኑ የሰበር መከራከሪያ አይደለም በማለት ተጠሪ ያቀረበው ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች በተጠሪ ይዞታ መሬት ላይ የነበረውን የካባ ድንጋይ አውጥቶ ለመጠቀምና ለዚህም በበኩለ ለመክፈል ከተስማሙበት ገንዘብ ውስጥ ቀሪውን ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደልም?አመልካች በተጠሪ የእርሻ መሬት ላይ ያደረሰው ጉዲት ብር 120,000 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ካሣ ይክፈል በማለት የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
አመልካችና ተጠሪ ውል የተዋዋለበት ድንጋይ "የኮንስትራክሽን ማዕድን" እንደሆነ የኮንስትራክሽን ማዕድን ማለት፣ እብነበረድ ግራናይት፣ ባዛልት፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ድንጋይ፣ የሸክላ አፈር የመሣሰለትና ላልች ሚኒስትሩ በመመሪያ የኮንስትራክሽን ማዕድናት ብል የሚሰይማቸው ብረት ነክ ያልሆኑ መዕድናትን የሚያጠቃልል ነው በማለት በአዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 3 ከተሰጠው ትርጓሜ ለመገንዘብ ይቻላል። ተጠሪ በህጋዊ የይዞታ መሬቱ ላይ ያለውን የኮንስትራክሽን ማዕድን በማምረትና ከላላው ዋጋ እየተቀበለ ለመሸጥ በአዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀጽ 4 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረት ከክልለ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ወይም ከቢሮው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፀና ፈቃድ ሉኖረው ይገባል።
ተጠሪ በህጋዊ መንገድ በያዘው መሬት ላይ የሚገኘውን ለግንባታ ሥራ የሚያገለግል ድንጋይ የመጠቀም መብት ድንጋዩን ለላላ ሰው በውል ገንዘብ ተቀብል ለመሸጥ የሚያስችለው አይደለም። ምክንያቱም ተጠሪ በህጋዊ ይዞታው ላይ የሚገኘውን የኮንስትራክሽን ማዕድን የሆነውን ድንጋይ የመጠቀም መብት በህግ ዕውቅና እና ጥበቃ የተሰጠው እስከምን ድረስ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ 1 "ሕጋዊ የመሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው ሥፍራው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 6 መሰረት የተያዘ ወይም የተከለከለ ካልሆነ በስተቀር የኮንስትራክሽን ማዕድናት በይዞታው ሥር ከሚገኝ ሥፍራ ያለ ክፍያና ፈቃድ ሣያስፈልገው ለንግድ ላልሆነ ዓላማ አምርቶ ለመጠቀም ይችላል። ሆኖም የአዋሳኝ ባለይዞታዎች መሬት ወይም ንብረት አጠቃቀም ማወክ ወይም በእነዚሁ ላይ ጉዲት ማድረስ የለበትም" በማለት በግልፅ ደንግጎታል። ከዚህ ድንጋጌ የምንረዲው ተጠሪ በይዞታው የሚገኘውን ድንጋይ ቤት ለመሥራት፣ አጥር ለመገንባትና ለላልች ግላዊ ለሆኑ አገልግልቶች ያለማንኛውም አካል ፈቃድ አምርቶ ለመጠቀም የሚችል መሆኑን ነው። ከዚህም ተጠሪ ከሚመለከተው አካል ሣይፈቀድለት በይዞታው ሥር ያለውን የግንባታ ድንጋይ በውል ላላ ሰው አውጥቶ እንዱጠቀምበት አሳልፍ መስጠትና የመሸጥ መብት የላለው መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 3፣ አንቀፅ 4 ንዐስ አንቀፅ 1 እና አንቀፅ 21 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። ተጠሪ የፋዳራል መንግስት ባወጣውና የክልል ምክር ቤት ባወጣው አዋጅ መሰረት በይዞታው ሥር ያለውን የግንባታ ድንጋይ የማምረትና የመሸጥ ፈቃድ የተሰጠው ስለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤትም ሆነ በሰበር ያቀረበው ክርክር የለም። ተጠሪ ቀሪውን ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) አመልካች የከፈለኝ በመሆኑ እኔና አመልካች ድንጋዩን በተመለከተ ያደረግነው ውል በሰበር የቀረበው ክርክር አካል አይደለም በማለት ሀምላ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ ሰጥቷል። ተጠሪ አዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀፅ 4 ንዐስ አንቀፅ 1 እና አግባብነት ባለው የክልለ የህግ መዕቀፍ መሰረት ሥልጣን ካለው አካል በይዞታ መሬቱ ላይ ያለውን ድንጋይ ለንግድ ተግባር ለማዋል የተፈቀደለት መሆኑን በመግለፅ ያልተከራከረ በመሆኑ የፀና ፈቃድ ሣይኖረው በይዞታ መሬቱ ላይ ይገኝ የነበረውን ድንጋይ አመልካች እያወጣ እንዱጠቀም በውል የሸጠ መሆኑን እንዲመነ የሚያስቆጥረው እንደሆነ ከፍትሐብሄር ሥነሥርአት ሕግ ቁጥር 235 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም ተጠሪ የፀና ፈቃድ ሣይኖረው በአዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀፅ 4 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 182/1986 አንቀፅ 36 ንዐስ አንቀፅ 1(ሀ) በመተላለፍ በይዞታው ሥር የነበረውን የኮንስትራክሽን መዕድን አመልካች ለአንድ አመት እያወጣ እንዱጠቀምበት የሸጠ መሆኑንና አመልካችም የፀና ፈቃድ ከላለው ከተጠሪ ጋር የኮንስትራክሽን ማዕድኑን እያወጣ ለመጠቀም ውል በመዋዋል ድንጋዩን በመውሰድ የተጠቀመ መሆኑን ተገንዝበናል። ተጠሪና አመልካች የውለ መሰረታዊ ነገር በማድረግ የተዋዋለበት የግንባታ ማዕድን የፀና ፈቃድ ሣይኖር የመሸጥና የመግዛት ውለታ በአዋጅ ቁጥር 52/1985 አንቀፅ 53 ንዐስ አንቀፅ 5፣ በደንብ ቁጥር 182/1986 አንቀፅ 39 እና በወንጀል ህግ አንቀፅ 353(1)(ለ) በወንጀልነት የሚያስጠይቅ ህገወጥ ተግባር እንደሆነ የድንጋጌዎቹን ይዘት በማገናዘብ ለመለየት ይቻላል። የአንዱት አገር ህግ ህገወጥ ተግባር በተለይም ወንጀል መሆኑን በግልፅ በመደንገግ ማንኛውም ሰው ድርጊቱን እንዲይፈፅም የከለከለውን ተግባር ለመፈፀም ውል የተዋዋለ የተስማሙ ሰዎች ውለ በመሰረታዊ ባህሪውና ሞራላዊ ይዘቱ ህገወጥ የሆነውን ውላቸውን በፍርድ ቤት ውሣኔ በማስገደድ ለማስፈፀም አይችለም። ዳኞችም በመሰረታዊ ይዘቱ ሞራላዊ ባህሪው ህገወጥ የሆነ ውል እንዱያስፈፅሙ ያቀረበላቸውን ጥያቄ አንቀበልም ማለት እንደሚችለ ከፍትሀብሓር ሕግ ቁጥር 1718 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪ በህገወጥ መንገድ በይዞታው ላይ ያለውን የኮንስትራክሽን ማዕድን ለመሸጥ ከአመልካች ጋር ያደረገው ውልና አመልካችም የፀና ፈቃድ ከላለው ተጠሪ በመግዛት የኮንስትራክሽን ማዕድን ለመጠቀም የተዋዋለው ውል በመሰረታዊ ይዘቱ ሞራላዊ ባህሪው ህገወጥ ውል ነው። ይህም በመሆኑ ተጠሪ አመልካች በውለ መሰረት ያልከፈለኝ ገንዘብ በማለት የሚያቀርበውን ጥያቄም ሆነ አመልካች ህገወጥ በሆነው ውል መሰረት ክፍያ ፈፅሜ ተጠሪ የውል ግዳታውን አልፈፀመም በሚል ወይም በልላ ምክንያት በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት በህገወጥ ውል የከፈልኩት ክፍያ ይመለስልኝ በማለት የሚያቀርበውን ጥያቄ ፍ/ቤቶች በመቀበል የሚመለከቱበትና ውሳኔ ሉሰጡ የሚችለበት የህግ መሰረት የላለ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/1716 እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ/1718 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም የፀና ፈቃድ ሣይኖረው የኮንስትራክሽን ማዕድን ለአመልካች ለመሸጥ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያደረገውን ህገወጥ ውል በህግ ፉት ምንም አይነት ውጤትና ተፈፃሚነት የላለው ሆኖ እያለ እንደ ህጋዊ ውል በመቁጠር አመልካች ለተጠሪ ቀሪውን የማዕድን ዋጋ ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) ከነወለደ ለተጠሪ እንዱከፍል ውሳኔ መስጠቱና ውሳኔውንም አመልካችን በማስገደድ ማስፈፀሙ ከላይ በዝርዝር የገለፅናቸውን የህግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የሀዋሳ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያደረገው ህገወጥ ውል እንዱፈፀምለት ያቀረበውን ጥያቄ በማስተናገድና በዲኝነት በማየት የሰጠውን ውሳኔ ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ማረምና ማስተካከል ሲገባው የሥር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አመልካች በተጠሪ የእርሻ መሬት ላይ ጉዲት አላደረስኩም በማለት ያቀረበው ክርክር የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት በህግ በተሰጠው ሥልጣንና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 272 መሰረት ከቦታው ድረስ በመሄድ ያረጋገጠውን ፍሬ ጉዲይ ሰበር ችልቱ እንዱለውጥ የቀረበና የሰበር ችልት የህገመንግስቱን አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 3(ሀ) እና የአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 10ን ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
የካሳውን መጠን በተመለከተ አመልካች በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዲት ብር 62,000 (ስድሳ ሁለት ሺህ ብር) ሆኖ እያለ ከደረሰበት ጉዲት በላይ ካሣ እንድከፍል ተወስኖብኛል በማለት ያቀረበውን ክርክር አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። በመርህ ደረጃ ለተጎጂው የሚከፈለው የካሣ መጠን ከደረሰበት ኪሳራ ጋር የተመጣጠነ መሆን እንዲለበት ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 እና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2992 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይችላል። አመልካች በፈፀመው ጥፊት የሆነ ድርጊት ተጠሪ ላይ ያደረሰበት የጉዲት መጠን ምን ያህል ነው? የሚለውን ነጥብ ስንመለከተው የግብርና ባለሙያ ተጠሪ በእርሻ መሬቱ ላይ የተከላቸው የሙዝ፣ የቡና፣ የእንሰትና የዋንዛ ዘፍ እንደዚሁም የበቆል ሰብል በአመልካች አድራጎት የወደሙ መሆኑን ግምታቸውም ብር 62,000 (ስድሳ ሁለት ሺህ ብር) እንደሆነ በማረጋገጥ እንዲቀረበ የሥር ፍርድ ቤት በውሳኔው ገልፆታል።
ሆኖም አመልካች በተጠሪ ላይ ያደረሰው ጉዲት በመሬቱ ላይ የነበረውን ሀብት ግምት ብቻ አይደለም። የተጠሪ መሬት የእርሻ ተግባር ለመቀጠል በማያስችል ሁኔታ ጉዲት የደረሰበት መሆኑ ተረጋግጧል። አንድ አርሶ አደር ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው የእርሻ ሥራውን በይዞታው ላይ ለመሥራት በማይችልበት ሁኔታ በመሬቱ ላይ ባለው የንብረቱ ግምት ብቻ ሣይሆን የመፈናቀያ ካሣ ሉከፈለው የሚገባ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀፅ 8 እና አንቀፅ 9 ድንጋጌዎች በማመሳሰል ትርጉም በመስጠት ለማገንዘብ ይቻላል። ከዚህ አንፃር ስናየው አመልካች ተጠሪ በመሬቱ ላይ የነበረውን አትክልትና ሰብል ግምት ብቻ ሉከፈለው ይገባል በማለት ያቀረበው ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በተጠሪ መሬት፣ ሰብልና አትክልት ላይ ላደረሰው ጉዲት ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ካሣ ለመክፈል ከተጠሪ ጋር የግልግል ውል የተዋዋለ መሆኑን ውለን የሚያረጋግጥ የጽሁፍና የሰው ማስረጃ እንደቀረበ የሥር ፍርድ ቤት በውሳኔው በግልፅ አስፍሮታል። በፍሬ ጉዲይ ረገድ የሥር ፍርድቤት ያረጋገጠውን ይህንን ፍሬ ጉዲይ በመያዝ አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር ስናገናዝበው አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገው የግልግል ውል መሰረት ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) እንዱከፍል የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3312 መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ አመልካች ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) እንዱከፍል መወሰኑ ስህተት አለበት በማለት ያቀረበውን አቤቱታ አልተቀበልነውም።
ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) የጉዲት ካሳ እንዱከፍል የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
በአጠቃላይ አመልካች በተጠሪ መሬት ላይ ለደረሰው ጉዲት ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ካሳ ይክፈል በማለት የሰጡትን የቅጣት ውሳኔ አፅንተናል። በልላ በኩል በተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገውን ህገወጥ ውል ምክንያት በማድረግ ተጠሪ አመልካች ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) እንዱከፍለው ያቀረበውን ክስ ተቀብለው ማየታቸውና መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት አሻሽለን ወስነናል።
ው ሣ ኔ 1.የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የደ/ብ/ብ/ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሸሽሎል።
2.ተጠሪና አመልካች የኮንስትራክሽን ማዕድን ለመሸጥና ለመግዛት ፈቃድ ሣይኖራቸው ያደረጉት ውል ህገወጥ ውል ነው በማለት ወስነናል።
3.በተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገው ውል ህገወጥ ውል በመሆኑ ተጠሪም ሆነ አመልካች የውለን አፈፃፀም ሆነ ከውለ ጋር ተያያዥነት ያለው ጉዲይ በፍ/ቤት ታይቶ ውሳኔ እንዱሰጥላቸው የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቀባይነት የላለው ነው በማለት ወስነናል።
4.የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ ህገወጥ ውል ይፈፀምልኝ በማለት ያቀረበውን ክስ ተቀብለው አመልካች ለተጠሪ ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) እንዱከፍል የሰጡት የውሳኔ ክፍል ተሻሽሎል።
5.የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች በተጠሪ የእርሻ መሬት ላይ የነበረውን ንብረትና በእርሻ መሬቱ ላይ ላደረሰው ጉዲት ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ካሳ እንዱከፍል የሰጡት የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
6.በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.