No summary available.
ጥር ዐ3 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ወርቅነህ ዲቲ ጉዲይ ተከታታይ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ ተስፊዬ አባቡ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘቱም፡- አመልካች በ1996 ዓ/ም የወጣውን በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ወንጀል አንቀፅ 32/1/ሀ/ እና 598/2/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ወደ ውጪ ለመላክ የሚያስችል ምንም አይነት ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሣሽ ከነበረው ከአቶ ሙለጌታ ገ/ማርያም ጋር ግብረ አብር በመሆን የግል ተበዲይ ነፃነት መንግስቴ የተባለችውን ታህሣሥ 27 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 12፡3ዐ ሰዓት ሲሆን በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ2 ክልል በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካይነት ወደ ቤሩት በመላክ ሟች በአሰሪዎቿ ከባድ ድብደባ እየደረሰባት መሆኑን ለቤተሰቦቿ ውጪ አገር ባለችው ዘመዶ አማካይነት ስትናገር ይህ ጉዲይ እየደረሰባት መሆኑን በተመለከተ ለአመልካችና ለግብረ አብሩ ተገልፆ ሟች አገሯ እንድትመለስ እንዱያድርጉ ሲነገራቸው ተከሣሾች መምጣት አትችልም ፣ የሁለት አመት ከአርባ አምስት ቀናት የስራ ኮንትራት አላት በማለት መልስ ከመስጠታቸው ውጪ ወጪ በመክፈል ወደ አገር እንድትመለስ ሁኔታዎችን ጨርሳ ሟች በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጋቢት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡1ዐ ሲሆን ስትደርስ እግሯ በጣም ያበጠና መቆም የማትችል ፣ በአውሮኘላን ሰራተኛ ድጋፍ ወርዲ ወደ ቤቷ ሄዲ መጋቢት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፑታል ተወስዲ ምንም እርዲታ ሳይደረግላት በደረሰባት ጉዲት ከቀኑ 5፡ዐዐ ሰዓት ሲሆን ሕይወቷ ሉያልፍ መቻለን ዘርዝሮ ተከሣሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት በሕገ ወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊን ወደ ውጪ አገር መላክ ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
አመልካች የአቃቤ ክስ ተነቦለት እንዱረዲው ከተደረገ በሁዋላ አለኝ ያላቸውን የክስ ተቃውሞ አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ተገቢ ነው ያለውን ትዕዛዝ በመስጠት ስለድርጊቱ አፈፃፀም የአመልካችን የእምነት ክህደት ቃል በመጠየቅ አመልካች ክድ በመከራከሩ አቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካች በዐቃቤ ህግ ማስረጃ ወንጀለን መፈፀሙ መረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ገልፆ አመልካች እንዱከላከል መብቱን ጠብቆት አመልካችም አለኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን በማስቀረብ አሰምቷል። ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ የአመልካች ማስረጃዎች የአቃቤ ህግን ማስረጃዎችን ሉያስተባብለ የሚችለ አይደለም በማለት ቃላቸውን ውድቅ አድርጎ አመልካችን በተከሰሰበት የሕግ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጓል። ቅጣቱን በተመለከተም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብል ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ጋር በማገናዘብ በእያንዲንደ ክስ ተገቢ ነው ያለውን የእስራት እና የገንዘብ መቀጮ ከአስቀመጠ በሁዋላ በድምሩ ደግሞ 9/ዘጠኝ አመት /ፅኑ እስራት እና በብር 3ዐዐዐ.ዐዐ/ሶስት ሺህ / የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ይግባኙ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195/1/ መሰረት ተሰርዟል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ለግል ተበዲይ መሞት ምክንያት አመልካች ስለመሆኑ ሳይረጋገጥ አመልካች ለድርጊቱ ተጠያቂ መደረጉ ያለአግባብ መሆኑን ፣ ሟችን አመልካች ወደ ውጪ በመላክ ሂደት የተሳተፈ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ሳይረጋገጥና የመከላከያ ምስክሮች ቃልም ውድቅ የተደረገው ያለአግባብ መሆኑን ዘርዝሮ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሣኔው እንዱታረም ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የግል ተበዲይ የሞተችው በበረታ የሳምባ ምች በተሰራጨ የቲቢ በሽታ ታማ ላሆን እንደሚችል የሕክምና ማስረጃ ቀርቦ እያለ አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 598/2/ ስር ጥፊተኛ ተብል የመቀጣቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦም በሰጠው መልስ ሟች ወደ ውጪ አገር አመልካችና ግብረ አበሩ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ልከዋት በውጪ አገር እያለች እግሯ አብጦ መምጣቷና ወደ አገሯ እንደተመለሰች ህክምና ሳታገኝ ሕይወቷ ማለፊ የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ የሳንባ ምች የሚባለው በሽታም ከድብደባ ጋር ተያይዞ ሉከሰት እንደሚችል ሳይንሱ የሚያረጋግጠው ሕቅ መሆኑን ዘርዝሮ አመልካች ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ ሕጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተከሰሰው የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 598/2/ ተጠቅሶበት ሁኖ ይዘቱም ባጭሩ ሲታይ አመልካች ምንም ሕጋዊ የሆነ ፈቃድ ሳይኖረው የግል ተበዲይ ነፃነት መንግስቴን ወደ ውጪ በመላክ የግል ተበዲይ ከተላከችበት አገር ድብደባ ደርሷባት እግሯ አብጦ ወደ አገሯ ከተመለሰች በሁዋላ በበነጋታው ሕይወቷ አልፎል የሚል ነው።
አመልካች ክሱን የካደ ሲሆን አቃቤ ሕግ አለኝ ባላቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች አመልካች የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን ማስረዲቱን የበታች ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል።
አመልካች በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አጠብቆ የሚከራከረውና ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ በሰበር ችልቱ እንዱታይ በጭብጥነት የተያዘው ዋናው ነጥብ የግል ነፃነት መንግስቴ የሞተችው በአመልካች ድርጊት ምክንያት መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። ይሁን እንጂ አመልካች የተጠቀሰበት ድንጋጌ ይዘትም ሆነ የክሱ ዝርዝር ይዘት አመልካች ለግል ተበዲይ ሞት ምክንያት የሆነ ድርጊት ራሱ በቀጥታ ፈፅሟል የሚል ሳይሆን ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ኢትዮጵያዊ ዜጋን ወደ ውጪ በመላክ የግል ተበዲይ ድብደባ የደረሰባት መሆኑንና ይህ ጉዲትም ከዉጪ አገር ስትመለስ የነበረ ስለመሆኑና ከውጪ አገር ከተመለሰች በሁዋላ በሁለተኛው ቀን ሕይወቷ አገሯ ውስጥ አልፎል በሚል ነው። በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 598/2/ ድንጋጌ ስር አንድ ሰው ሉቀጣ የሚችለው ፈቃድ ሳይኖረው ወይም በማናቸውም ላላ ሕገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊ ዜጋን ለስራ ወደ ውጭ የላከ እንደሆነ እና በዚህ ድርጊት ምክንያት የተላከችው ኢትዮጵያዊት በሰብአዊ መብቷ፣ በህይወቷ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት የደረሰባት መሆኑ ከተረጋገጠ ሲሆን ቅጣቱም ከአምስት አመት እስከ ሃያ አመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና ሃምሳ ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ እንደሚሆን ሕጉ ያሳያል። ይኸው ድንጋጌ በተጠቃሹ አንቀፅ ንዐስ አንቀጽ አንድ ስር የተመለከተው ድንጋጌ ቀጣይ ሲሆን ዝርዝር ይዘቱ ሲታይ ቅጣትን የሚያከብደ ምክንያቶች መቀመጣቸውን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ድንጋጌው ማንም ሰው ፈቃድ ሳይኖረው ወይም በማናቸውም ላላ ሕገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊ ዜጋን ለስራ ወደ ውጭ አገር በመላኩ ድርጊት የተላከችው ኢትዮጵያዊት በሰብአዊ መብት ፣ በሕይወቷ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት ከደረሰ የወንጀል ተጠያቂነት አለበት ። ድንጋጌው በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር የተላከች ኢትዮጵዊት ላይ በሰብአዊ መብቷ፣ በሕይወቷ ወይም በአኳሎ ላይ ጉዲት መድረሱ መረጋገጡን እንጂ በሕገ ወጥ መንገድ የላከው ሰው ራሱ በቀጥታ በሚፈፀመው ድርጊት ወይም በልላ ጣልቃ ገብ በሆነ ምክንያት ጉዲቱ መድረሱ መረጋገጡን በወንጀለ ማቋቋሚነት አያስቀምጥም። በልላ አገላለፅ በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጪ አገር የተላከች ኢትዮጵያዊት በሰብአዊ መብቷ ፣ በሕይወቷ ወይም በአካሎ ላይ ጉዲት ከደረሰና ይህም ጉዲት ውጭ አገር የደረሰ መሆኑ ከተረጋገጠ በሕገወጥ መንገድ የላከው ሰው ራሱ በቀጥታ ጉዲዩን ባያደርሰውም በሕገወጥ መንገድ በመላኩና ጉዲቱ በውጪ አገር በመድረሱ ምክንያት ብቻ የወንጀለ ተጠያቂነት ይኖርበታል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ሟችን ወደ ውጪ አገር በመላክ የግል ተበዲይዋ ውጭ አገር እያለች ድብደባ ደርሶባት እግሯ አብጦ ወደ አገሯ ከተመለሰች በሁዋላ ሕይወቷ ማለፈና በአካሎ ላይ ጉዲት መድረሱ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። በመሆኑም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 598/2/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አመልካች ለድርጊቱ ተጠያቂ የማይሆንበት ምክንያት የለም። በዚህም መሰረት በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ቅሬታም ሆነ የተያዘው ጭብጥ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚችል ሁኖ አላገኘንም። ቅጣቱን በተመለከተ የቀረበውን ቅሬታ ስንመለከተውም አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ የሚያስቀጣው የቅጣት መጠን ከአምስት አመት እስከ ሃያ አመት የሚደርስ ፅኑ እስራትና ከሃምሳ ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ሲሆን ቅጣቱ የተጣለው በግራ ቀኙ የቀረቡት የቅጣት አስተያየቶች ተመዛዝነው በወንጀል ሕጉ የተመለከቱትን የቅጣት አጣጣል መርሆችን እንዱሁም የቅጣት አወሳሰን መመሪያውን መሰረት ተደርጎ ነዉ። በመሆኑም በአመልካች ላይ የተጣለው የዘጠኝ አመት ጽኑ እስራትና የብር ሶስት ሺህ የገንዘብ መቀጮ የሚነቀፍ ሁኖ አላገኘውም። ሲጠቃለልም ጉዲዩ ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ ተከተዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 2ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም የተሰጠው ጥፊተኝነት ውሣኔ እና በ26/05/2003 ዓ/ም የተሰጠው የቅጣት ውሣኔ እንዱሁም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/2/ለ-2/ መሰረት ጸንቷል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.