No summary available.
ጥር 15 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ፈለቀ ሉቤ- ቀረበ ተጠሪ፡- የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የስነ- ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐ/ህግ- አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
በስር ከፍተኛ ፍ/ቤት በአሁኑ የሰበር ተጠሪ ከሳሽነት በቀረበው ክስ የአሁኑ አመልካች 3ኛ ተከሳሽ የነበረ ሲሆን ከቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው በ3ኛው ክስ የተላለፈበት የጥፊተኛነት የቅጣት ውሳኔ ነው። የአሁኑን አመልካች ጨምሮ በስር 2ኛ፣9ኛና 14ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበባቸው 3ኛ ክስ ፍሬ ቃለ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ/የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1) (ሀ)፣33 እና 407(1) እና (2) የተደነገገውን በመተላለፍ 2ኛ ተከሳሽ የጠምባሮ ወረዲው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፉ፣ 3ኛ ተከሳሽ የወረዲው ውኃ ሀብት ጽ/ቤት ሀላፉ፣9ኛ ተከሳሽ የወረዲው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ዋና ሀላፉ፣14ኛ ተከሳሽ የግል ኮንትራክተር ሆነው በሚሰሩበት ወቅት 2ኛ ተከሳሽ በቁጥር 1727/ፈ-126/99 በቀን 28/3/99 ዓ/ም እና በቁጥር 2030/ፈ-126/99 በቀን 23/3/99 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤዎች ተሰርቶ ላልተጠናቀቀ ለባዲ ምንጭ ግንባታ ከተያዘው በጀት ብር 90,699.94 ላይ ብር 60,466.83 ያለ አግባብ ወጪ ሆኖ እንዱከፈል ለወረዲው ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ህገ ወጥ ትዕዛዝ በመስጠቱ፤ 9ኛው ተከሳሽ በቁጥር 81/ፈ-126/99 በቀን 14/05/99 ዓ/ም በተጻፈ ደብዲቤ ቀደም ሲል በ2ኛ ተከሳሽ ህገ ወጥ ድርጊት ሲከፈል የቀረውን ብር 30,000 ላልተሰራ ስራ እንዱከፈል ለወረዲው ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ህገ ወጥ ክፍያ እንዱፈጽም ትዕዛዝ በመስጠቱ፤14ኛ ተከሳሽም ከ2ኛ፣ከ3ኛ እና ከ9ኛ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር በማመሳከሪያ ሰነድች በሶስት የተለያዩ ቀናት በድምሩ ብር 90,466.83 ላልተሰራ ወይም ላላተጠናቀቀ ስራ ያለ አግባብ የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ በመወሰደ፣3ኛ ተከሳሽም የአሰሪው መ/ቤት ሀላፉ ሲሆን ከማንም እና ከምንም በላይ ከፍተኛ ሀላፉነት እያለው ላልተሰራ ስራ ወይም ላላተጠናቀቀ ስራ ክፍያ እንዱፈጸም በማመቻቸቱ ሁለም ተከሳሾች ወንጀል ለመስራት በማቀድ እና በማሰብ ለራሳቸው ወይም ላላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በዋና ወንጀል አደራጊነት እና በልዩ ተካፊይነት በፈጸሙት በስልጣን ያለ አግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ተካሳሹም የእምነት ክህደት ቃለን ሲጠየቅ ወንጀለን አለመፈጸሙንና ጥፊተኛ አለመሆኑን ክድ በመከራከሩ የሥር የከምባታና ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የከሳሽን ምስክሮች በመስማትና ተከሳሽ ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች በመመርመር በሰጠው ውሳኔ ተካሳሹ በመከላከያ ማስረጃነት አንደ ያቀረበው የጽሁፍ ማስረጃ በቁ/ጠወ/አስም/ 372/99 በቀን 3/04/99 የወረዲው ውኃ ጽ/ቤት ሀላፉ ሆኖ በውክልና እንዱሰራ የተጻፈለትን ደብዲቤ ሲሆን ለክሱ መነሻ የሆነው የባዲ ምንጭ ግንባታ ውል ደግሞ የተደረገው በ27/3/99 በመሆኑ ውለ ሲደረግ ተከሳሽ ሀላፉነት ላይ አልነበረም።
በውለ መሰረት 1/3ኛ ክፍያ ተከሳሹ የጽ/ቤቱ ሀላፉ ሆኖ እንዱሰራ ከመወከለ በፉት የተፈጸመ ቢሆንም ቀሪ ክፍያ ግን መፈጸም ያለበት ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ መሆን ሲገባው ተከሳሹ ከተወከለ በኋላ ላልተሰራ ስራ ከውለ ስምምነት ውጪ በ25/4/99 ብር 30,233.30 እና በ26/4/99 ብር 30,000 በድምሩ 60,233.30 ክፍያ ተፈጽሟል። ስለሆነም የውክልና ማስረጃው አግባብነት የለውም፤ እንዱሁም ተከሳሽ ያቀረባቸው ላልች ድብዲቤዎች ማለትም በቁ/ጠወ/ውሃ/26/99 በቀን 17/12/99 እና በቁ/307/ጠጠ-35 በቀን 27/2/2000 የተጻፈት የኦዱት ውጤት ከታወቀ በኋላ ከሀላፉነት ለመሸሽ ሲል የጻፊቸው ስለሆኑ ከጉዲዩ ጋር አግባብነት የላቸውም በማለት በወ/ህ/ 32(1)ሀ፣33 እና 407(1)(ሀ)ስር ጥፊተኛ ነው ሲል ወስኗል።
ቅጣትን በሚመለከት የቅጣት ሪከርድ አልቀረበም በሚል በሁለት አመት ጽኑ እስራት እና በብር 500 መቀጮ እንዱቀጣ ወስኖበታል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በበኩለ ተከሳሽ ያቀረበውን ይግባኝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/195 (1) መሰረት የሰረዘ ሲሆን የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔም ሆነ በጠ/ፍ/ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ የህግ ስህተት የለም ሲል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረጉ አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት አቅርቧል።
አመልካች በዋናነት ያቀረበው የቅሬታ ነጥብም፡- ላልተሰራ ስራ ወይም ላልተጠናቀቀ ስራ ክፍያው እንዱፈጸም ያዘዘው የወረዲው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ሀላፉ ሲሆን ክፍያውን የፈጸመው ደግሞ የወረዲው ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ነው። ነገር ግን የወረዲው ውኃ ሀብት ጽ/ቤት ፈጸመ ተብል አንድም የተጠቀሰ ድርጊት በላለበት አመልካች ሁኔታዎችን አመቻችቷል በሚል ብቻ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ የተላለፈብኝ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ/የወንጀል ህግ አንቀጽ 2፣23(2) እና 32 (1) ሀ-ሐ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የሚቃረን በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው።
ተጠሪው በበኩለ አመልካች ላቀረበው ቅሬታ በሰጠው መልስ ያልተሰራውን ወይም ያልተጠናቀቀውን የባዲ ምንጭ ውኃ ፔሮጀክት በሀላፉነት የሚያስገነባውና የሚቆጣጠረው አመልካች በሀላፉነት የሚመራው የውኃ ሀብት ጽ/ቤት ሲሆን አመልካች ስራው ያለበትን ደረጃ የማወቅ ዕድል እንደነበረው ባቀረብናቸው የሰውና የጽሁፍ ማስረጃዎች አስረድተናል። ስለሆነም አመልካች ላልተሰራ ወይም ላልተጠናቀቀ ስራ ክፍያ እንዱፈጸም ሁኔታዎችን ያመቻቸ በመሆኑ የተላለፈበት የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ በአግባቡ ስለሆነ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
አጠቃላይ የክርክሩ ሂደት ከዚህ በላይ እንደተገለጸው አጥሮ የቀረበ ሲሆን እኛም ላልተሰራ ወይም ላልተጠናቀቀ ስራ ክፍያ እንዱፈጸም አመልካች ሁኔታዎችን አመቻችቷል በሚል 32(1)ሀ፣33 እና 407(1)ሀ ስር ጥፊተኛ ነው ተብል የቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት በአግባቡ ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በከፍተኛው ፍ/ቤት ቀርበው ከተሰሙት የተጠሪ ምስክሮች አመሰካከር የተጣራው ፍሬ ነገር ስራው አልተሰራም ወይም አልተጠናቀቀም በሚል ለክሱ ምክንያት በሆነው የባዲ ምንጭ ግንባታ ለኮንትራክተሩ ያለ አግባብ ክፍያ የተፈጸመ መሆኑን፣ ክፍያው እንዱፈጸም ደግሞ ትዕዛዝ የሰጠው የወረዲው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፉ መሆኑንና ክፍያውን የፈጸመው ደግሞ የወረዲው ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት መሆኑን ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከኮንትራክተሩም ጋር ስለ ስራው ውል የገባው የወረዲው ፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት መሆኑ በስር ከ/ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በዚሁ ውል መሰረት ለኮንትራክተሩ ከጠቅላላው የውል ገንዘብ ውስጥ 1/3ኛው ውለ በተገባበት ጊዜ ሲከፍል አመልካች በወረዲው ውኃ ሀብት ጽ/ቤት ሀላፉ እንዲልነበረም የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
አመልካች የውኃ ጽ/ቤት ሀላፉ ሆኖ በሰራባቸው ጊዜያትም ለምንጩ ግንባታ ቀሪ ክፍያዎች እንዱከፈለ ለፊይናንስ ትዕዛዝ ስለመስጠቱ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር አይደለም። ሆኖም ተጠሪው አመልካች ለተፈጸመው ህገ ወጥ ክፍያ ሁኔታዎች አመቻችቷል የሚለው የስራው ባለቤት የአመልካች መ/ቤት በመሆኑ የስራውን መጠናቀቅና አለመጠናቀቅ ሁኔታን የመከታተልና የማወቅ ሀላፉነት አለበት በሚል ነው። ይህንኑ የተጠሪ ክርክር ደግሞ አመልካች ጥፊተኛ ነው ከተባለበት የወንጀል አንቀጽ 32 (1)(ሀ)፣33 እና 407 (1)(ሀ) አንጻር መመርመር ተገቢነት አለው።
በዚሁ በተጠቀሰው ወንጀል ህግ አንቀጽ መሰረት ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በልላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ የተሰጠውን ሹመት ወይም ስልጣን በግልጽ ተግባር ወይም በግድፈት ያለ አግባብ የተገለገለበት እንደሆነ በሥልጣን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ የሚቀጣ ሲሆን እነዚህ በአንቀጹ የተገለጹ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ደግሞ በፍሬ ነገር ደረጃ ሉረጋገጥ ይገባል።
ተጠሪው ምንም እንኳን ገንዘቡ በህገ ወጥ መንገድ እንዱከፈል አመልካች ሁኔታዎችን አመቻችቷል ቢልም አመልካች በተከሰሰበት የወንጀል ህግ አንቀጽ መሰረት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለመስገኘት ወይም በልላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዲት ለማደረስ የተሰጠውን ሹመት ያለ አግባብ ስለመገልገለ በቀጥታም ሆነ ቀጥታ ባልሆነ መንገድ በመላ አሳቡና አድራጎቱ በወንጀለ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን ድርጊቱን የራሱ ያደረገ ስለመሆኑ የተረጋገጠ አንድም ነገር የለም።
ይህ ሆኖ ሳለ አመልካች የውኃ ሀብት ጽ/ቤት ሀላፉ በመሆኑ ብቻ በስልጣን ያለ አግባብ ስለመገልገለ የሚያረጋግጡ ፍሬ ነገሮች በላለበት ደግሞ ጥፊተኛ ነው ብል የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፍ ከወንጀል ህጉ ዓላማና ግብ ውጪ ስለሆነ የስር ፍ/ቤቶች በ3ኛ ክስ አመልካች ጥፊተኛ ነው ሲለ የሰጡት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል ። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ በቀን 15/03/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ በ3ኛ ክስ በአመልካች ላይ ያስተላለፈበት የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ክፍል እንዱሁም የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በቀን 25/6/2002 በዋለው ችልት የሰጠውን የትዕዛዝ ክፍል እንዱሁም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ በቀን 24/10/2002 በዋለው ችልት የሰጠውን የትዕዛዝ ክፍል በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/195 (2) (ለ)(1) መሰረት ሽረናል።
አመልካች ከቀረበበት 3ኛ ክስ በነጻ እንዱሰናበት ወስነናል። የመቀጮ ገንዘብም ከፍል እንደሆነ ሉመለስለት ይገባል ብለናል። ስለሆነም በስር ፍ/ቤት ቀርቦበት ከነበረው 2ኛ ክስም በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 141 መሰረት መከላከል ሳያስፈልግ በብይን መሰናበቱን መዝገቡ ስለሚያመለክት በልላ ወንጀል የማይፈለግ ከሆነ ከሚገኝበት የማረሚያ ቤት ተቋም እንዱለቀቅ ትዕዛዝ ይጻፍ ብለናል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡
No topics extracted.