No summary available.
ታህሣስ 06 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ታደሰ ናማጋ ሀያቱ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ፕሉስ ወ/ምርመራ መምሪያ ዋና ሣጅን ደምሴ ሰጠኝ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ ሰበር አመልካች በስር የፋዳራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረ ሲሆን ተጠሪው ደግሞ ተከሣሽ ነበር። ክሱም እነዲዊት ጸጋዬ የተባለት 23 ተከሣሾች ህዲር 27 ቀን 1992 ዓ.ም ከከሣሽ ብር 250,000 ዘርፈው ከተሰወሩ በኋላ በፕሉስ ታድነው በከፉል ተይዘው ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በጊዜው ከከሣሸ ዘርፈው ከወሰደት ገንዘብ ውስጥ ብር 94,000 በኢግዚቢትነት ተከሣሽ ሲይዝ በተረፈው ገንዘብ እነዚህ በወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች ዓይነታቸውን ባላውቅም የተለያዩ የገዙአቸውንም ቁሳቁሶች ጭምር ተከሣሽ በኢግዚቢትነት ይዟል። ሆኖም በኢግዚቢትነት የተያዙትን ቁሳቁሶች እና ገንዘብ ተከሣሽ እንዱያስረክበኝ ብጠይቅም ለማስረከብ ፍቃደኛ ስላልሆነ ተገድ እንዱያስረክበኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
ተከሣሽም በሰጠው መልስ በጊዜው የውንብድና ወንጀል በፈጸሙ 23 ተከሣሾች ላይ 14 ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን በ2ኛ ክስ ከከሣሽ ብር 250,000 ስለመዝረፊቸው በክሱ ተጠቅሷል። ሆኖም በክሱ ኢግዚቢቶቹ ከ1-8 ተራ ቁጥር ከመዘርዘራቸው በቀር የከሣሽ በኢግዚቢትነት የተያዘው ገንዘብም ሆነ ንብረት ተለይቶ አልተቀመጠም። በልላ በኩል በኢግዚቢትነት የተያዙ ንብረቶችን ፕሉስ የመጠበቅ እንጂ የመመለስ ስልጣን የፕሉስ ሳይሆን የፍ/ቤት በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም በሚል ተከራክሯል።
የስር የመ/ደ/ፍ/ቤትም በሰጠው ፍርድ ገንዘቡም ሆነ ላልች ቁሳቁሶች የከሣሸ ስለመሆናቸው ከሣሸ ያቀረበው ማስረጃ ካለመኖሩም በላይ ላልች ንብረትና ገንዘብ የተወሰደባቸው ሰዎችም ስላለ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብሎል።
ከፍተኛው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ወገኖች በማከራከር በሰጠው ፍርድ የስር የመ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቷል።
አመልካችም በስር ፍ/ቤቶች ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ሲል አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት ያቀረበው የቅሬታ ነጥብም፡- ተጠሪው በስር የመ/ደ/ፍ/ቤት ቀርቦ ከአመልካች ወንበዳዎች የወሰደትን ብር 94,000 እና በገንዘቡ የተገዙትን ቁሳቁሶች በኢግዚቢትነት መያዙን አምኖ መልስ ሰጥቶ እያለ በማስረጃ አመልካች አላስረዲም መባለና ክሱ ውድቅ መደረጉ ያለ አግባብ ነው የሚል ነው።
ተጠሪው ለሰበር አቤቱታ መልሱን ያቀረበ ሲሆን በመልሱ ግን በስር ፍ/ቤት ከሰጠው መልስ የተለየ ነገር አላቀረበም።
የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ፍርድ ከዚህ በላይ የተገለጸ ሲሆን እኛም የስር ፍ/ቤቶች በኢግዚቢትነት የተያዘ ገንዘብና ንብረቶች የብዙ የግል ተበዲዮች ስለመሆኑና ከሣሽ የራሱ ገንዘብና ንብረት ነው የሚለውን ለይቶ በማስረጃ ስላላስረዲ ክሱ ውድቅ ነው ያለት በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የፋዳራል ዐ/ሕግ በ12-7-1993 ዓ.ም በተጻፈ ክስ 14 የወንጀል ክሶችን የውንብድና ወንጀል ፈጽመዋል በተባለ ተጠሪዎች ላይ አቅርቦ የነበረ ሲሆን የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል ከተባለት የግል ተበዲዮችም አንደ በ2ኛ ክስ ስሙ የተጠቀሰው ያሁኑ አመልካች ነው። በክሱም ወንበዳዎቹ ከአሁኑ አመልካች ብር 250,000 ዘርፈው መውሰዲቸው ተገጿል። ከዚህ በተጨማሪ ከክሱ ጋር በተያያዘው የኢግዚቢት ዝርዝር በተራ ቁጥር 3 በወንጀል ክሱ ሶስተኛ ተከሣሸ በ2ኛ እና በ5ኛ ክስ በፈጸመው ዘረፊና የማታለል ወንጀል የገዛው ጃኬት ጫማ ሸሚዝ እና ደብቆ የተገኘው ገንዘብ ብር 48,740 እንዱሁም ስድስተኛ ተከሣሽ በ2ኛ እና በ5ኛ ክስ ላይ በፈጸመው የማታለል እና የዘረፊ ወንጀል ካገኘው ገንዘብ ውስጥ ብር 40,610 እና ከዘረፊው ባገኘው ገንዘብ የተገዛ ሙለ ሶፊ ፣ ፍሪጅ ፣ ፓርሙስ የመሳሰለት ንብረት መያዛቸውን ተጠሪው ገልጿል።
ከዚህ በላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠንና ንብረቶች የተያዙት በ2ኛ ክስ በግል ተበዲይነት ከተጠቀሰው ከአሁኑ አመልካች እና በ5ኛ ክስ ከተጠቀሰው የግል ተበዲይ አቶ ገብረማርያም አሰፊ ከተባለ ግለሰብ ነው። ይህ እስከሆነ ድረስ ደግሞ በኢግዚቢት በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተጠቀሰው ገንዘብና ንብረቶች ከሁለቱ የግል ተበዲዮች መካከል በሚደርሳቸውን የገንዘብ መጠንና የንብረት ዓይነት በማጣራት ከመወሰን በቀር በክሱ ውስጥ ያለ የግል ተበዲዮች ሁለ ንብረት እና ገንዘብ ነው በማለትና አመልካች ክሱን በማስረጃ አላስረዲም በሚል ውድቅ ማድረግ ስለማይገባ የስር ፍ/ቤቶች ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።
No topics extracted.
በመሆኑም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት በመዝ. በቀን 06-7-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት በመዝ. በቀን 26-12-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የስር የመ/ደ/ፍ/ቤት በ5ኛ ክስ የግል ተበዲይ የሆነውን አቶ ገብረማርያም አሰፊ የተባለውን ግለሰብ ወደ ክሱ እንዱገባ በማድረግ እንዱሁም በጊዜው በወንበዳዎቹ ላይ የተጣራውን የፕሉስ ምርመራ መዝገብ አስቀርቦ በመመልከት ማስረጃዎችን በመመዘን የበኩለን ፍርድ በጉዲዩ ላይ እንዱሰጥበት ክርክሩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት እንደገና መልሰናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሣቸውን ይቻለ።