No summary available.
የሰ/መ/.
ታህሳስ 04 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
ተወልደ ብስራት
ሃይላይ ገ/መድህን ከጠበቃ ገብረ እግዚብሓር ተስፊዬ ጋር ቀረቡ።
ገላን ሰቦቃ ተጠሪ፡- የለም።
መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በ1997 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 448(1 እና 3) መሰረት አንድን ሰው ለፍትህ እርዲታ ለመስጠት እንቢተኛ ሁኖአል በማለት ወዱያውኑ ለመቅጣት መሟላት ስላለባቸው ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚመለከት ነው።
የጉዲዩ መነሻ በከሳሽ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አቃቤ ሕግና በተከሳሾች እነ ተካበ ገ/ስላሴ ስድስት ሰዎች መካከል በነበረው የወንጀል ክስ ጉዲይ ነው። የወንጀል ክሱ በዐቃቤ ሕግ በኩል በተከሳሾች ላይ ከተመሰረተና በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ከቀረበ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ወደ አዱስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዱሄደ ትዕዛዝ ሰጥቶ የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን ምርመራ ክፍል ኃላፉዎች ተከሳሾችን ወደ ማረሚያ ቤት ሳይወስደ ወይም ሳይልኩ በራሳቸው ማረፉያ ቤት ለረዥም ጊዜና ወራት አቆይተዋቸዋል፣ የፍርድ ቤቱንም ትእዛዝ ሳያከብሩ ቀርተዋል በማለት የስር ፍርድ ቤት አመልካቾችን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 448(1) እና (3) መሰረት ጥፊተኛ በማድረግ እያንዲንዲቸውን በሁለት ወር ቀላል እስራት እንዱቀጡ ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ጉዲዩ ከተመረመረ በሁዋላ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በስር ፍርድ ቤት አመልካቾች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 448(1 እና 3) ስር ጥፊተኛ መባላቸውና ቅጣት መተላለፈን አግባብነት ተቀብል የቅጣቱን አፈጻጸም ብቻ በገደብ እንዱሆን በማድረግ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ለጉዲዩ አመልካቾች ተጠያቂ መደረጋቸው የድንጋጌውን ይዘት እና በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን ባላገናዘበ መልኩ መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍርድ ቤቶች የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካቾችን ቅሬታ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በጭብጥነት ላታይ የሚገባው አመልካቾች የፍርድ ቤቱ ዋራንት በአግባቡ እንደደረሳቸው ሳይረጋገጥ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 448(1(ሀ)) እና (3) ድንጋጌዎች ስር ጥፊተኛ መባላቸው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች ከላይ በተገለጸው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ ሉባለ የቻለት የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን በአቶ ተካበ ገ/ስላሴ ላይ በመሰረተው የኮንትሮባንድ የወንጀል ክስ በመ/ ፊይል ተከፍቶላቸው ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤቱም ጥር 03 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የተከሳሹን የዋስትና መብት ጠብቆላቸው ተከሳሹ የተፈቀደላቸውን የዋስትና መብት ካላሟለ በአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው እንዱቆዩ ሲል የእስር ዋራንት እንዱፃፍ በማለት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ተከሳሹ ወዱያውኑ ማረሚያ ቤት ሳይገቡ በባለስልጣን መስሪያ ቤት ደረቅ ፕሉስ ጣቢያ ከአስር ወራት በላይ ታስረው የተገኙ መሆኑን፣ ይኸው ግለሰብ በአጠቃላይ ከአንድ አመት ሁለት ወራት በላይ የታሰሩ መሆኑን፣ መስፍን ካሳሁን የተባለት ተከሳሽም በተከሰሱበት ወንጀል በወንጀል መዝገብ ፊይል ተከፍቶባቸው በፍርድ ቤቱ ቀርበው ፍርድ ቤቱ ግንቦት 24 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት በተመሳሳይ መልኩ በመዝገቡ ላይ የዋስትና መብታቸውን ጠብቆላቸው ሲያበቃ የተፈቀደላቸው የዋስትና ግዳታ ተከሳሹ መፈፀም ካልቻለ በአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው እንዱቆዩ ሲል ትእዛዝ ሰጥቶ ተከሳሹ ወዱያውኑ ማረሚያ ቤት ሳይላኩ የእስር ዋራንቱ በመዝገቡ ላይ ከተሰጠ በሁዋላ በባለስልጣኑ ፕሉስ ጣቢያ ከስድስት ወራት በላይ መታሰራቸውን፣ ሃይለ ወርቁ እና ሉዊዛ ፊርቤታ የተባለት ሁለት ግለሰቦች ደግሞ በተከሰሱበት የጉምሩክ ማጭበርበር የወንጀል ድርጊት በመ/ በሆነው ፊይል ተከፍቶላቸው ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስትና መብት ላይ ትዕዛዝ ከተሰጠ በሁዋላ የዋስትና ግዳታቸውን በትዕዛዙ አግባብ መፈፀም ካልቻለ በአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው እንዱቆዩ ሲል ፍርድ ቤቱ የእስር ዋራንት እንዱፃፍ ሰኔ 18 ቀን 2002 ዓ/ም በዋለው ችልት ትዕዛዝ ሰጥቶ በትእዛዙ መሰረት ወደ አዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ሳይላኩ እያንዲንዲቸው እጃቸው በፕሉስ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት ጊዜ ያለውን ሳይጨምር በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከስምንት ወራት በላይ ታስረው መቆየታቸው መረጋገጡን፣ መንግስቱ አብርሃምና አህመድ መሐመድ በተከሰሱበት የኮንትሮባንድ ወንጀል ደግሞ በመ/ እና ባምላክ ይስማው የተባለት ተከሳሽ ደግሞ በመ/ ፊይል ተከፍቶላቸው ፍርድ ቤት ቀርበው በአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው እንዱቆዩ የእስር ዋራንት እንዱጻፍ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ወደ ማረሚያ ቤት ሳይላኩ እያንዲንዲቸው ቢያንስ ሶስት ወራትን ያህል በፕሉስ ጣቢያ መታሰራቸውን የስር ፍርድ ቤት መገንዘቡን ነው።
የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩ በቀጥታ ይመለከተቸዋል ያላቸውን የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት የወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪ ኃላፉዎችን ችልት ቀርበው እንዱያስረደና ሕጋዊ መግለጫ እንዱሰጡበት በማለት በሶስት የወንጀል መዛግብት ላይ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን የአሁኑ አመልካቾችም ወደ ፍርድ ቤቱ ቀርበው አለኝ ያለትን ምክንያት ያቀረቡ ሲሆን የአሁኑ ሁለተኛው አመልካች የባለስልጣኑ መሰሪያ ቤት ፕሉስ ጣቢያ የእስረኞች ሰነድች ክትትል ኃላፉ መሆናቸውን ገልፀው የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሳይከበር የቀረው ከፍርድ ቤቱ ለአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት የተላኩት የእስር ዋራንቶች የስም ስህተት ስለተከሰተባቸውና ማረሚያ ቤቱም አልቀበልም ስለአለ ነው፣ የሥም ስህተቱ በዋራንቱ እንዱስተካከልም በተደጋጋሚ ጊዜያት ወደ ፍርድ ቤቱ በመምጣት አቤት ብያለሁ፣ ከፍርድ ቤቱ ግን የተሰጠኝ አፊጣኝ ምላሽ የለም፣ ከዚህ ላላም ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፉዎች ጋር ደጋግሜ ተነጋግሬበታለሁ፣ ግን መፍትሓ ሉገኝ ባለመቻለ ተከሳሾች ለበርካታ ወራት ሉታሰሩ ችለዋል በማለት የዘረዘሩ ሲሆን የአሁኑ 1ኛ አመልካችም ከቦታው ላይ በኃላፉነት ከመመደባቸው ከመጋቢት 2002 በፉት ተከሳሾች በፕሉስ ጣቢያው ታስረው ነው ያገኟቸው መሆኑን፣ በፕሉስ ጣቢያ ለበርካታ ወራት መታሰራቸው ኃላፉነትን እንደሚያስከትል በመገንዘብም ወደ አዱስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዱገቡ የበኩላቸውን ጥረት እንደአደረጉ፣ በመዝገብ ላይ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ከሆነም ተገልብጦ እንዱመጣላቸው ዐቃቤ ሕጎችን ሳይቀር በተደጋጋሚ ጊዜያት መላካቸውን፣ ሆኖም ግን ከመስሪያ ቤቱ አቃቤ ሕጎች አንደ የሆኑት አቶ ወንድወሰን ደሳለኝ ተከሳሾች ወደ አዱስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዱገቡ የተሰጠ ትዕዛዝ የለም ብለው ሉገልፁላቸው የቻለ መሆኑንና ከዚያም ተከሳሾች ወደ ማረሚያ ቤት ሳይገቡ በእድገት ምክንያት ከወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪነታቸው መነሳታቸውን በምክንያትነት ያቀረቡ መሆኑን ነው። የአሁኑ ሶስተኛ አመልካች ደግሞ የወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪ ኃላፉ መሆናቸውን ጠቅሰው የወንጀል ምርምራ አጣርተው ከጨረሱ በኋላ ምርመራውን ያጣሩበትን ተከሳሽ በዋስ ሉወጣ/ሉለቀቅ የቻለ መሆኑን፣ ከዚያ በሁዋላ በተጠረጠረበት ወንጀል የወንጀል ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ስለሆነው ነገር እንደማያውቁ፣ ተከሳሽ መስፍን ካሳሁን ወይም ላልች ተከሳሾች በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ፕሉስ ጣቢያ ለበርካታ ወራት መታሰራቸውን ያወቁት ቀርበህ አስረዲ ተብል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲደርሳቸው መሆኑን፣ የወንጀል ምርመራውን ያጣሩት እርሳቸው ስለሆኑ ጉዲዩን እስከመጨረሻው የመከታተል ኃላፉነት እንደነበረባቸውና ላልች ኃላፉዎችም ተከሳሾች ለበርካታ ወራት መታሰራቸውን እንደሚያውቁ ዘርዝረው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንግዱህ ከላይ የተመለከተው አመልካቾች እያንዲንዲቸው ያቀረቡት ምክንያት ሲሆን የሁለም አመልካቾች የጋራ ምክንያታቸው በጥቅለ ሲታይ ግን ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ የእስር ዋራንት ትእዛዝ መሰረት በአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ታስረው መቆየት ሲገባቸው በፕሉስ ጣቢያ ለበርካታ ወራት መታሰራቸው ስህተትም ጥፊትም መሆኑን አምነው ጥፊቱ ግን የእነርሱ ያለመሆኑን፣ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ያልተከበረው በራሳቸው ምክንያት ያለመሆኑን ጠቅሰው መከራከራቸውን ነው።
ከላይ ከተመለከቱት ፍሬ ነገሮች የሚያሳዩት ለአመልካቾች ለወንጀለ ተጠያቂነት ምክንያት የሆነው በጉምሩክ ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት የቀረቡት ተከሳሾች ማረሚያ ቤት እንዱታሰሩ የፍርድ ቤት ማሰሪያ ዋራንት ተሰጥቶ እያለ በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ፕሉስ ጣቢያ ለበርካታ ወራት እንዱታሰሩ መደረጉ ለፍትህ እርዲታ ለመስጠት እንቢተኛ መሆንን ነው ተብል በስር ፍርድ ቤቶች መደምደሚያ ላይ መደረሱን ነው። ይህ ችልትም ከላይ ለተያዘው ጭብጥ ምላሽ ለመስጠት ይቻል ዘንድ የስር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገውን ድንጋጌ ይዘት መመልከቱ ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 448(1) ስር አንድ ሰው ጥፊተኛ ልባል የሚችለው ፍርድ ቤት ወይም የዲኝነት ስልጣን ያለው አካል በያዘው ጉዲይ ላይ በተከሳሽነት፣ በምስክርነት ወይም በልዩ አዋቂ ምስክርነት ወይም በአስተርጓሚነት፣ በነባሪነት ወይም በተቺነት እንዱረዲ በሕግ መሰረት የተጠራ ወይም ተከሳሽን ወይም ማስረጃን እንዱያቀርብ ወይም እንዱልክ የታዘዘ ማንም ሰው በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሳይቀርብ የቀረ ወይም ለመቅረብ እንቢተኛ የሆነ እንደሆነ፣ ተከሳሽን ወይም ማስረጃን ያላቀረበ ወይም ያልላከ እንደሆነ፣ ወይም ቀርቦ ሕግን በሚቃረን አኳኋን ለተጠየቀው መልስ ለመስጠት ወይም እንደታዘዘው ለመፈፀም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ ሲሆን ይህ አድራጎት ወንጀል ሁኖ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ሳይሰጥ ወዱያውኑ ቅጣት የሚወስን ስለመሆኑም የአንቀፁ ንዐስ ቁጥር ሶስት ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። ከድንጋጌው መንፈስ የምንገነዘበው አንድን ሰው ለፍትሕ እርዲታ ለመስጠት እንቢተኛ ሆኖአል በማለት በወንጀል ጥፊተኛ አድርጎ ለመቅጣት በፍርድ ቤት ወይም የዲኝነት ነክ ስልጣን ባለው አካል በተከሳሽነት፣ በምስክርነት፣ በልዩ አዋቂ ምስክርነት፣ በአስተርጓሚነት፣ በነባሪነት በተቺነት የተጠራ ወይም ተከሳሽን ወይም ማስረጃን እንዱያቀርብ ወይም እንዱልክ የታዘዘ መሆኑ በቅድሚያ ሉረጋገጥ የሚገባ የወንጀለ መሰረታዊ የማቋቋሚያ ባህሪ ስለመሆኑ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(2) እና 58 ጋር ተዲምሮ ሲነበብ የምንገነዘበው ጉዲይ ስለመሆኑ ነው። ያለመቅረቡና የታዘዘውን ነገር ያለመፈፀሙን ምክንያት ማስረዲት ጉዲይ ደግሞ ከላይ የተመለከቱት የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች ተሟልተው መገኘት ከተረጋገጠ በሁዋላ የሚፈፀም ተከታይ ተግባር መሆኑን የተጠቃሹ አንቀፅ አቀራረፅና ይዘት እንዱሁም ዓላማው የሚያስገነዝበን ነጥብ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለት የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ባለማክበር በወንጀል የተከሰሱትን ሰዎች ማረሚያ ቤት መውስድ ሲገባቸው በባለስልጣኑ ፕሉስ ጣቢያ በማሰር ለበርካታ ወራት አቆይተዋል በሚል ነው። ይሁን እንጂ አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት ተከሳሾች ለበርካታ ወራት በፕሉስ ጣቢያ ያላግባብ መታሰራቸውን አናውቅም በማለት ሳይሆን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ለማረሚያ ቤቱ ለማስረከብ ሲሞከር በስም ስህተት የተነሳ ማረሚያ ቤቱ ሉረከብ ያለመቻለንና ፍርድ ቤቱም በማሰሪያ ዋራንቱ ላይ የተከሰተውን የስም ስህተት እንዱያስተካክል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት ሉያስተካክል ያለመቻለን፣ እንዱሁም በፍርድ ቤቱ የተሰጠ ማሰሪያ ዋራትን የላለ መሆኑን የሚመለከታቸው የአቃቤ ሕግ ባለሙያዎች ሲገልፁላቸው የነበረ መሆኑን በመጥቀስ ነው። በስር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋጋጠው ደግሞ ተከሳሾቹ በአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዱታሰሩ በመዝገብ ላይ የማሰሪያ ዋራንት እንዱፃፍ ትእዛዝ መሰጠቱ እንጂ በትክክል የተፃፈ የማሰሪያ ዋራንቱ ለአመልካቾች ደርሷቸው አመልካቾች ይህንኑ እያወቁ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበር ተከሳሾቹን ያሰሩ ስለመሆኑ ካለመሆኑም በላይ የስም ስህተት ተከስቷል፣ ይህም ይስተካከልልን በማለት በባለስልጣኑ መሰሪያ ቤት በኩል የቀረበው ጥያቄ በፍርድ ቤቱ በተገቢው ጊዜ ምላሽ የተሰጠበት ስለመሆኑም በፍሬ ነገር ደረጃ አልተረጋገጠም። በመሆኑም ከላይ የተመለከተው ድንጋጌ ከተያዘው ጉዲይ ጋር ተያይዞ ሲታይ አመልካቾች የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበር ለፍትሕ እርዲታ መስጠትን እንቢ ማለት ወንጀል ፈፅመዋል ብል በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ አመልካቾች ከላይ በምክንያትነት የገለጿቸው ፍሬ ነገሮች እውነት መሆን ያለመሆናቸው በተገቢው ማስረጃ ሉጣራ የሚገባው እንጂ ወንጀለ የተፈጸመው በፍርድ ቤት ነው፣ ተከሳሾቹ ለበርካታ ወራት ተገቢ ባልሆነ ቦታ ታስረዋል በሚል ምክንያት ቀጠሮ ሳይደረግ ወዱያውኑ ቅጣት ለማስተላለፍ የሚያስችል አይደለም።
ስለሆነም አመልካቾች ፈጸሙ የተባለውን አድራጎት በተመለከተ በማስረጃ ሳያጣራና ድርጊቱም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 448(1(ሀ)) ስር የሚወድቅ ስለመሆኑ በተገቢው ሁኔታ ሳያረጋግጥ የስር ፍርድ ቤት አመልካቾችን ወዱያውኑ ጥፊተኛ በማድረግ መቅጣቱም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በመቀበል የቅጣቱን አፈፃጸም በገደብ እንዱሆን መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እና በዚሁ ፍርድ ቤት በተጠቀሰው መዝገብ ጥር 05 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ እንዱሁም በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/
No topics extracted.