No summary available.
ታህሳስ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አደነ ንጉሴ አመልካች፡- .1. አቶ ታረቀኝ ተክለ ገመዲ 2. ወ/ሮ እማዋይሽ ገብረመስቀል 3. አቶ አብይ ታመነ ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ባለቤት ሆኖ የመገኘት የወንጀል ተግባርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች ላይ በሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት ግንቦት 24 ቀን 2001 ዓ/ም በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።ተጠሪ በአመልካቾች ላይ የመሰረተው ክስ ይዘት በ1997 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ለ))፣33 እና 419(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ አመልካቾች በግብረአብርነትና በልዩ ተካፊይነት ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ወይም ገንዘብ ለማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው።ዝርዝር ይዘቱም፡-1ኛ አመልካች ከሰኔ 01 ቀን 1986 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2000 ዓ/ም ድረስ በሀዋሳ ዙሪያ እና በወንድገነት ወረዲዎች ታክስ አስተዲደር ጽ/ቤት በእለት ገቢ ሰብሳቢነት ሲሰሩ መነሻ ደመወዛቸው ብር 182.00(አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር) ሁኖ በየጊዜው በተደረገላቸው የእርከን ጭማሪ እና የደረጃ እድገት ስራቸውን እስከለቀቁበት መጋቢት 2000 ዓ/ም ድረስ ደመወዙ ብር 928.00(ዘጠኝ መቶ ሃያ ስምንት ብር) የደረሰ መሆኑንና የደመወዙ ከፍተኛ መጠን ሲሰላም ጠቅላላ ገቢያቸው ከብር 70,000.00(ሰባ ሺኅ ብር) እንደማይበልጥ፣2ኛ አመልካች ደግሞ የ1ኛ አመልካች ባለቤት ሁነው ከባለቤታቸው ደመወዝ ውጪ በግላቸው የሚያገኙት ሕጋዊ የሆነ የገቢ ምንጭ የላላቸው የቤት እመቤት ሁነው እያለ በስማቸው የከተማ ቦታና እና የይስሙላ ንግድ ፈቃድ(የማይሰራበት ንግድ ፈቃድ) በመውሰድ በዚሁ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ በመውሰድ በሕገ ወጥ ንብረትና እና ገንዘብ ከ1ኛ አመልካች ጋር ግብረ አበር ወይም ልዩ ተካፊይ በመሆን ንብረቱን እንዲፈሩ፣3ኛ አመልካችም የ2ኛ አመልካች ወንድም ሁነው በስማቸው ቋሚ እና ሕጋዊ የገቢ ምንጭ የላላቸው ተማሪ ሁነው እያለ ከ1ኛ እና ከ2ኛ አመልካቾች ጋር ያለውን ዝምድና ምክንያት በማድረግ 1ኛ አመልካች በስማቸው የሉዝ ቦታ ጠይቀው ከሉዝ ደንብና መመሪያ ውጪ G+1(Ground Plus One) የመኖሪያ ቤት ሰርተው ከ2ኛ አመልካች ጋር የሚኖሩበትን ቤት ለ3ኛ አመልካች በሕግ የተረጋገጠ ወይም የተፈጸመ ወራሽነት ሳይኖረው ከወላጅ አባቱ ከውርስ ባገኘው ገንዘብ ቤቱን እንደሰራ በማስመሰል በስሙ ባወጣው የሐሰት ባለቤትነት ማረጋገጫ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ሕገ ወጥ ንብረት እንዱያፈሩ በማድረግ በግብረአብረት ወይም በልዩ ተካፊይነት ወንጀል መፈጸማቸውን የሚጠቅስና በጠቅላላው አመልካቾች ክስ እስከ ቀረበባቸው ድረስ ብር 3,602,000.84(ሶስት ሚሉዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺኅ ከሰማኒያ አራት ሳንቲም) የሚሆን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት ማፍራታቸውንና ይህም ንብረት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ የማፍራት የሙስና ወንጀል ነው በማለት አመልካቾች እንዱጠየቁ ክስ ማቅረቡን የሚያሳይ ነው።ክሱን ለማስረዲትም የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ዘርዝሯል።አመልካቾች ክሱን ክደው በመከራከራቸውም ተጠሪ አለኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን አቅርቦ አስምቷል።ከዚህም በሁዋላ አመልካቾች እንዱከላከለ ተደርጎ የመከላከያ ማስረጃዎቻቸውን አሰምተዋል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም አመልካቾች በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ማስተባበላቸውን በመግለጽ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 149(2) መሰረት በነፃ አሰናብቷቸዋል።በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ አመልካቾች በተከሰሱት የሕግ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ ተብለው 1ኛ አመልካች በልላ ጉዲይ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የተቀጡ መሆናቸው በመረጋገጡ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት፣2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ደግሞ እያንዲንዲቸው በአንድ አመት ቀላል እስራት እንዱቀጡ የተወሰነ ሲሆን በሕገ ወጥ መገንድ መገኘቱ የተረጋገጠውን ንብረት ደግሞ አይነቱና መጠኑን ይኸው ይግባኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት ከለየው በሁዋላ ለመንግሰት እንዱወረስ በማለት ወስኗል።በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸው ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ሚያዚያ 04 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ዘርዝረው አቅርበዋል።ይዘቱም ባጭሩ፡-አመልካቾች በወንጀል ድርጊት እንዱጠየቁ የተደረገው የሀብት ምዝገባና ማሳወቂያ ሥርዓት ባልተዘረጋበት ሁኔታና የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈማቸው በተገቢው መንገድ ከሳሽ ሳያስረዲ መሆኑንና የአመልካቾች የመከላከያ ማስረጃዎች ቃልም ውድቅ የተደረገው ያላግባብ መሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው እንዱሻር መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ የምዝገባ ስርዓት ባልተዘረጋበት ሁኔታ አመልካቾች ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አፍርተዋል ተብል የመቀጣታቸውንና ንብረታቸውም እንዱወረስ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት የሚያስቀርብ ነው በመባለ ማመልከቻው ለተጠሪው ተልኮ ተጠሪ ቀርቦ መልሱን በጽሐፍ እንዱሰጥበት ተደርጓል።ተጠሪ ሰኔ 27 ቀን 2003 ዓ/ም ጽፍ ባቀረበው መልስ የሀብት ምዝገባና ማሳወቂያ ስርኣት ያለመዘርጋት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 419 ስር በተመለከተው ድንጋጌ ከመጠየቅ የማይከለክል መሆኑን፣አመልካቾች ለሰበር ችልቱ ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ በሥር ፍ/ቤት የህግ ስህተት ተፈጽሟል ብለው የገለጿቸው ምክንያቶች ስለማስረጃ ምዘና የሚመለከቱ እንጅ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለመኖሩ የሚያስረደ አለመሆኑን፣የፍደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት እንዱህ አይነት የማስረጃ እና የፍሬ ነገር ክርክሮችን በሕጉ የማየት ስልጣን የላለው መሆኑን፣አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለት በበቂና አሳማኝ ማስረጃ የወንጀል ድርጊቱን መፈፃማቸው ተነግሮባቸው በመከላከያ ማስረጃዎቻቸውም የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ባለማስተባበላቸው ምክንያት መሆኑን ዘርዝሮ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ሆኖ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል እንዱፀና ጠይቋል።የአመልካቾች ጠበቃም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሱን በጽሐፍ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ የምዝገባ ሥርዓት ባልተዘረጋበት ሁኔታ አመልካቾች ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አፍርተዋል ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የመቀጣታቸውንና ንብረታቸውም እንዱወረስ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል ነው።ይሁን እንጂ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419 መሰረት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ የመገኘት የወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት ለማስከተል የሚችለው የምዝገባ ሥርዓት ሲዘረጋ ስለመሆኑ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ የላለ በመሆኑ በአመልካቾች ጠበቃ በኩል የቀረበው ክርክርም ሆነ በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ላላው አመልካቾች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 419(1) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ በእጃቸው ገብቶ ተገኝቷል ተብለው በወንጀል የተከሰሱባቸውን ጉዲዮች በሚመለከት ይግባኙን በተመለከተው የክልለ ጠቅለይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት የሰጠው የጥፊተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን ሲታይም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለም።ምክንያቱም ይኸው ፍርድ ቤት አመልካቾችን ለወንጀል ድርጊቱ ተጠያቂ ናቸው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው ለጉዲዩ የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ ሲሆን የማስረጃ ምዘና ጉዲይ ደግሞ በዚህ ሰበር ችልት ላታይ የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነውና።ይህ ችልት ሉመለከተው የሚችለው የሕግ ጥያቄን ብቻ ሲሆን ከዚህ አንፃር በስር ፍርድ ቤት ማስረጃዎቹ ተመዝነው የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ተይዞ በሕግ ረገድ ያለው ነጥብ ሲታይ አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለበትን የወንጀል ድርጊት ያቋቁማል?
ወይስ አያቋቁምም? የሚለውን ጉዲይ ስንመለከተው የአሁኑ 1ኛ አመልካች በመንግሥት ሥራ ላይ ሆነው ከብር 182.00 የወር ደመወዝ ተነስተው በጭማሪና በዕድገት ብር 928.00 የወር ደመወዝ ላይ ደርሰው በዚህ መጠነኛ ደመወዝ ራሣቸውን ሲያስተዲድሩ እንደቆዩና ባለቤታቸውም ላላ ህጋዊ ገቢ እንዲልነበራቸው፣3ኛ አመልካችም ሕጋዊ ገቢ ያልነበራቸው ሁኖ ከ1ኛ እና 2ኛ አመልካች ጋር በመመሳጠር ሕጋዊ ያልሆነ ንብረት 1ኛ እና 2ኛ አመልካች እንዱይዙና በሕጋዊ መንገድ የተገኘ ለማስመስል በመፈለግ በወንጀል ተግባሩ መካፈላቸው ተረጋግጦ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ምንጩ ያልታወቀ በሚሉዮን የሚቆጠር ንብረትና ገንዘብ በእጃቸው ገብቶ መገኘቱና ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረት ባለቤት ሆነው መገኘታቸው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ለ))፣33 እና 419(1) የወንጀል ተጠየቂነትን የሚያስከትል ተግባር ሁኖ አግኝተነዋል።በመሆኑም አመልካቾች ጥፊተኛ መባላቸውም ሆነ የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ተጠይቆ ስለቅጣት በወንጀል ሕጉ የተመለከቱት የቅጣት አጣጣል መርሆች መሰረት ተደርገው እያንዲንዲቸው ላይ ተገቢ የእስራት ቅጣቱ መጣለ እንዱሁም ንብረቱ እንዱወረስ መወሰኑ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።ሲጠቃለልም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት በመ/ ተሰጥቶ በክልለ የሰበር ችልት በመ/ ጥር 17 ቀን 2003 ዓ/ም የፀናው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 195 ((2(ለ-2)) መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.