No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣሥ 03 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሃይለ ተስፊኡ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ብርሃነ መብራቱ - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ገንዘብን ለማስመለስ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪና በወ/ሪት መብርሂት ቅደስ ላይ በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመስረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም የአሁኑ ተጠሪ ዘበኛ፣ ወ/ሪት መብርሂት ቅደስ ደግሞ የሽያጭና መዛኝ ሰራተኛ ሁነው በአመልካች የወፍጮ ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ በወፍጮ ድርጅቱ ውስጥ ባለው መጋዝን ካዝና አመልካች ያስቀመጡትን ብር 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ) መጋዝኑ ተከፍቶ ካዝናው ተሰብሮ ስለተሰረቀባቸው የተሰረቀው ይኸው ገንዘብ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የድርጅቱ ሰራተኛ መሆናቸውን ሳይክደ ድርጅቱ ተሰረቀ በተባለበት ጊዜ በፈቃድ ለጠበል ሂደው ላላ ቦታ ያደሩ መሆናቸውን ገልጸው ለክሱ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀሪያ ደረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የስር 2ኛ ተከሳሽ የነበሩትን ከክሱ ነጻ፣ ተጠሪን ደግሞ ኃላፉ በማድረግ ብር 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ) ለዲኝነት የተከፈለበት ብር 662.00 ኪሳራና ላላ ወጪ እንዱሁም የድካም ዋጋ በቁርጥ ብር 300.00 ለአመልካች እንዱከፍለ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የተጠሪ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ የደርጅቱ ዘበኛ ሁነው ተቀጥረው እየሰሩ ቢኖሩም ካዝናው ተሰብሮ ገንዘቡ በጠፊበት በ30/05/2000 ዓ/ም በአመልካች ፍቃድ ወደ ጠበል ሂደው ስለነበር አልነበሩም፣ አመልካች ራሱ የፍርድ ቤት መጥሪያ ለተጠሪ በሚሰጡበት ጊዜ ገንዘቡ አልጠፊም ከእህቴ ጋር አግኝቼዋለሁ ብለው ሲናገሩ ሰምተናል ብለው ስለመሰከሩ እንዱሁም ብር 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ) ያክል በመጋዘን ውስጥ በካዝና ያስቀምጣል ተብል አይገመትም የሚለትን ምክንቶችን በመያዝ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪን ለገንዘቡ ኃላፉ ሉሆኑ አይችለም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀረቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በወንጀለ ጉዲይ ጥፊተኛ ተብለው ተቀጥተው እያለ ለፍትሐብሕር ክስ ኃላፉነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 2149 ድንጋጌን ያላገናዘበ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ በወንጀለ ጉዲይ ጥፊተኛ ተብለው ተቀጥተው እያለ ለፍትሐብሓሩ ክስ ኃላፉነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር፣ የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህ ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አብይ ነጥብ ተጠሪ ተጠያቂነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሁኖ ተገኝቷል።
አመልካች ክሱን ሉመሰርቱ የቻለት ተጠሪን በድርጅታቸው በጥበቃ ስራ ቀጥረው በማስራት እያለ በድርጅቱ መጋዝን ውስጥ በሚገኘው ካዝና የተውት ገንዘብ ካዝናው ተሰብሮ እንዱሰረቅባቸው አድርገዋል በማለት ገንዘቡን እንዱተኩላቸው ሲሆን የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተሰምቶ የበታች ፍርድ ቤቶቹ ተገቢ ነው ያለትን ውሳኔ ሰጥተዋል። አመልካች እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አጥብቀው የሚከራከሩትና በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ነጥብ ነው ተብል የተያዘውም ተጠሪ በወንጀል ተከስሰው ጥፊተኛ ተብለው ተቀጥተው እያለ በፍትሐብሓሩ ክስ ኃላፉነት የለባቸውም ተብል መወሰኑ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ ነው።
የሥር ፍ/ቤት ከቀረቡት የአመልካች ማስረጃዎች መካከል ተጠሪ በጉዲዩ በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ የተባለበትና የተቀጡበትን የፍ/ቤት ውሣኔ ለጉዲዩ ያለውን አግባብነት ወይም ብቁነት ሳይገልጽ ስለማለፈ የውሣኔ ግልባጭ ያሳያል። የተቆጠረው ወይም የቀረበው ማስረጃ ለክርክሩ መነሻ ከሆኑት ፍሬ ነገሮች ጋር ግንኙነት እያለው እና ፍሬ ነገሮችን ለማረጋገጥ በሕጉ ክልከላ ያልተደረገበት የማስረጃ ዓይነት እስከሆነ ድረስ በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ሁለም ማስረጃዎች መመዘን አለባቸው። በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ሁለን ማስረጃዎች በአንድነት ሳይመዘኑ የተወሰኑትን ብቻ ነጥል በመወሰድ የሚሰራ ምዘናም ሆነ ውጤት ሕጋዊነት አይኖረውም።
No topics extracted.
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪ በጉዲዩ ላይ በወንጀል ተከሰው ፍ/ቤቱ ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡ መሆኑንና በበላይ ፍ/ቤትም አለመለወጡ ተረጋግጦ እያለ ይህ የአመልካች ማስረጃ በሰበር ፍ/ቤት በዝምታ ታልፎል። ይህም የማስረጃ አቀባበል ሥርዓትን ያልተከተለ ነው። የዚህን ማስረጃ አግባብነት እና ብቁነት ስንመለከተውም ለጉዲዩ በማስረጃነት ላቀርብ የሚችል ነው።
በወንጀል ጉዲይ የተሰጠ ውሣኔ በዚያው ጉዲይ በፍትሐብሕር በማስረጃነት አግባብነት እና ብቃት የሚኖረው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2149 ተቃራኒው ንባብ ያስገነዝባልና። በዚህ ድንጋጌ መሰረት በወንጀል የተሰጠ ውሣኔ በፍትሐብሕር ለቀረበው ክስ በማስረጃነት አግባብነት የሚኖረው በወንጀል ክሱ በወንጀል ፍ/ቤት ተከሣሹ ጥፊተኛ ተብል ከተወሰነ ስለመሆኑ እና ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት የወንጀል ክስ ማስረጃ አመዛዘን መርህ ከፍትሐብሓሩ የበለጠ ጠንካራና የማያሻማ ማስረጃ የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ አያዲግትም የሚል ነው። ወደዚህ ድምዲሜ ለመድረስም በወንጀለ ጉዲይ የተሰሙት ማስረጃዎችም በፍትሐብሓሩ ጉዲይም የቀረቡና የተሰሙ ሉሆኑ ይገባል። በወንጀለና በፍትሐብሕር ጉዲይ የተሰሙት ማስረጃዎች የተለያዩ ከሆነ እና በወንጀል ጉዲይ ክስ የቀረበበት ነጥብም ከፍትሐብሓሩ ክስ ጋር ግንኙነት የላለው ከሆነ በወንጀል ክስ ተጠያቂ መሆን ሁል ጊዜ በፍትሐብሓሩ ክስ ኃላፉነትን የማያስከትል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2149 ድንጋጌ ይዘት፣ መንፈስና አላማ ያስገነዝበናል። የሥር ፍ/ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን የፍትሐብሕር ጉዲይ የተመለከተው የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን ክብደት በመመዘን ነው፡፤ በወንጀለ ጉዲይ ተጠሪ ጥፊተኛ የተባለት በሰራተኝነት የጥበቃ ስራ ግዳታቸውን አልተወጡም በሚል ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ የፍትሐብሕር ክስ ሉመሰርቱ የቻለት ካዝና ላይ የተቀመጠው ጥሬ ገንዘብ ስለተሰረቀብኝ ተጠሪ ይመልሱልኝ በሚል ነው። ይህም በግልጽ የሚያሳየው አመልካች ተጠሪ ሰርቀው የወሰደትን ገንዘብ እንዱመልሱ ክስ የቀረበባቸው መሆኑን እንጂ በንዝህላልነት የተሰጠውን የስራ አመራር ግዳታ ያለመወጣትንና በወንጀል ሕጉ 702(2) ስር የሚያስጠይቀውን የወንጀል ድርጊት ፈጸመው ገንዘቡ ላይ ጉዲት ማድረሳቸውን የሚያሳይ አይደለም።
ሲጠቃለልም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ገንዘብ ተጠሪ በወንጀል ተከስሰው ጥፊተኛ ከተባለት የወንጀል ድርጊት ጋር ሙለ በሙለ ተመሳሳይነት የላለው በመሆኑ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2149 መሰረት ኃላፉ የሚሆኑበት አግባብ የለም በማለት በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ በውጤት ደረጃ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 27225 መጋቢት 17 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሚያዚያ 13 ቀን 2001 ዓ/ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መ/ቤት ይመለስ።