No summary available.
ህዲር 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሣጅን ታዬ ተክለኋይማኖት - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ መርማሪ ከሣሽ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ ሲሆን የተጀመረው በደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ነው።
በተከሣሽ ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ ሶስት ሲሆን ይዘቱ 1ኛው ክስ ተከሣሽ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁ. 670 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በሀዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ ጨርቃ ጨርቅ አካባቢ በስራው አካባቢ በእጁ በሚገኙት የሀዋሳ ከተማ የፕሉስ ተሽከርካሪ የሆኑትን 1ኛ ከላይ ክፈት ላንድ ኪሩዘር የሰላዲ ቁጥር ፕሉስ ደ.ህ 0007 2ኛ ሽፍን ልንግ ቤዝ መኪና የሰላዲ ቁጥሩ 4-11529 በማሽከርከር ዘወትር ማክሰኞና አርብ ከንግድ ስራቸው የሚመለሱትን የተለያዩ ስምንት ሰዎችን በተለያዩ ጊዜያት ያስጫናችሁት ዕቃ ይወረሳል ካልሆነ ገንዘብ አምጡ በማለት በማስፈራራት 10,700 ብር የተቀበለ በመሆኑ በፈጸመው የውንብድና ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፤ ሁለተኛ ክስ ደግሞ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁ.
407/ሐ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከላይ በክስ አንድ ስር በተገለጹት ቀናት ወር ዓመተ ምህረት እና ቦታ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 ድረስ ስማቸው በተገለጹት የግል ተበዲዮች የፕሉስ አባል መሆኑንና የፕሉስ መኪና ማሽከርከሩን መከታ በማድረግ ይህ የያዛችሁት የንግድ ዕቃ “ቡና” ይወረሳል አልያም ገንዘብ አምጡ እያለ ገንዘቡን እየተቀበለ እንዱያልፈ በማድረግ በስልጣን አለ አግባብ መገልገል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው 3ኛው ክስ ደግሞ በክስ አንድ ስር የተጠቀሱትን የመንግስት ተሽከርካሪዎች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 677/1ሀ/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ያለአግባብ በመገልገል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተከሣሹን የእምነት ክህደት ቃል በመቀበል የግራቀኙን ማስረጃ በመስማት ውሣኔ የሰጠ ሲሆን የውሣኔው ይዘት ተከሣሽ በአንደኛው ክስ ስር የውንብድና ወንጀል ሰርቷል በተባለበት ወቅት በእረፍት ላይ የነበረ ስለመሆኑ ከዐቃቤ ህግ ምስክር በተሻለ ያስመሰከረ በመሆኑ ከክሱ በነጻ ሉሰናበት ይገባል 3ኛ ክስ በተመለከተም በተመሳሳይ ተከሣሽ በእረፍት የነበረ ስለመሆኑ እና በወቅቱም የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች ለላላ ተረኛ ሹፋር ያስረከበ እና በእጁ የላለ ስለመሆኑ ከመስሪያ ቤቱ የቀረቡት የተሽከርካሪ መረካከቢያ ቅጾች የሚያስገነዝቡ በመሆኑ የወንጀል ኋላፉነት የለበትም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በሁለተኛ ክስ ስር ግን ፍ/ቤቱ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 407/ሐ/ ስር ጥፊተኛ ነው በማለት በአምስት /5/ ዓመት ጽኑ እስራትና በ2000 ብር /ሁለት ሺህ ብር/ የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመቀጠል ደግሞ ለክልለ የሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታውን ያቀረበ ሲሆን የቀረበላቸውን ቅሬታ ባለመቀበል አያስቀርብም በማለት ቅሬታውን ሰርዘውለታል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር በጽሁፍ ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች በሁለተኛ ክስ ስር ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ በአግባቡ ስለመሆኑ ተመርምሮ እልባት ማግኘት ያለበት ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት ሁለተኛውን የዐቃቤ ህግ ክስ እና አመልካች ጥፊተኛ ተብል የተቀጣበትን ድርጊት ስንመለከት ራሱን ችል የቆመ ሳይሆን በአንደኛው ክስ ውስጥ በተጠቀሰው ሰዓት ቀን ወር ዓመተ ምህረት ቦታ እና የግል ተበዲዮች ላይ ስለመሆኑ ከክሱ ይዞታ መረዲት ይቻላል። በዚህ በአንደኛ ክስ ላይ በተመለከተው የውንብድና ወንጀል ክስ ስር ተከሣሽ በወቅቱ በእረፍት ላይ የነበረ ስለመሆኑ ተረጋግጧል በማለት ከቀረበበት ክስ በነጻ እንዱሰናበት ውሣኔ ተሰጥቶበታል።
ይሄ ከሆነ በተመሣሣይ ጊዜ ቦታ እና የግል ተበዲዮች ላይ ተፈጸመ ለተባለው የስልጣን አለአግባብ የመገልገል ወንጀል ጥፊተኛ የሚባልበት አግባብ አይኖርም። በተመሣሣይ ሁለተኛውን ወንጀል ሲፈጽም የፕሉስ መምሪያ መኪና ተጠቅሟል ተብል በክሱ የተመለከተ ቢሆንም በአመልካች ላይ የቀረበው የመንግስትን ንብረት ያለአግባብ የመገልገል ወንጀል በተመሣሣይ ጊዜ ቦታ እና የግል ተበዲዮች ላይ ተፈጸመ ተብል በሶስተኛ ክስ ከቀረበበት ክስ በነጻ የተሰናበተ መሆኑን ተገንዝበናል።
No topics extracted.
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች የወንጀል ድርጊቱን ያለመፈጸሙን እና ወንጀለ ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ በእረፍት ላይ የነበረ ስለመሆኑ ወንጀለንም ሲፈጽም የፕሉስ መምሪያውን ተሽከርካሪ ተጠቅሟል የተባለውም በወቅቱ የተባለት ተሽከርካሪዎች በእጁ ያልነበሩና ለላላ ተረኛ ሹፋር ያስረከበ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ስለመረጋገጡ በአንደኛውና በሶስተኛው ክስ ላይ መደምደሚያ ላይ ደርሶ እያለ በሁለተኛው ክስ ስር በተመሣሣይ ጊዜና ቦታ እንደዚሁም የግል ተበዲዮች ላይ ተፈጸመ ለተባለው ወንጀል ጥፊተኛ የሚሆንበት አግባብ የለም። አንድ ተከሣሽ ጥፊተኛ ልባል የሚችለው ወንጀለን ሉያቋቁሙ የሚችለ ተግባራት ስለመፈጸማቸው በፍሬ ነገር ረገድ ለማጣራት ስልጣኑ ባላቸው ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በይግባኝ ያየው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የወ/መቀጫ ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 141,142 እና 149/1/ ዓላማ ፣ ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበን ነው። በዚህ ጉዲይ ግን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ እና ቦታ የላለ መሆኑን ወይም በእረፍት ላይ የነበረ ስለመሆኑ እና ወንጀለን ለመፈጸም ተጠቀመበት በማለት የተጠቀሱትንም ተሽከርካሪዎች በወቅቱ ያልያዘና ለላላ ሰው አሳልፍ አስረክቦ በነበረበት ወቅት በመሆኑ አልተረጋገጠም ወደሚለው የፍሬ-ነገር መደምደሚያ ላይ ደርሷል። በመሆኑም ባልተረጋገጠ ፍሬ ነገር ፍርድ ቤቱ መልሶ በሁለተኛ ክስ ስር ጥፊተኛ ነው በማለት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሣኔ መስጠቱ አግባብነት የላለውና ውሣኔውም እርስ በራሱ የሚጋጭ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከቱትን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝቦች ብሓ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ. 51055 በቀን 12-4-2003 ዓ.ም ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 50973 በቀን 23-3-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት በመዝ.ቁ. 08979 በቀን 16-3-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁ. 195/2/ /ለ/ /1/ መሰረት ተሽሯል።
በአመልካች ላይ የተላለፈው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሣኔ አግባብነት የላለው በመሆኑ ተሰርዞ በነጻ እንዱሰናበት ብለናል። የወንጀል ኋላፉነቱን ሉያቋቁሙ የሚችለት ተግባራት በበታች ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች ጥፊተኛ ተብል የሚቀጣበት አግባብ የለም ብለናል።
አመልካች በልላ ወንጀል የሚፈለግ ካልሆነ ከማረሚያ ቤት እንዱለቀቅ መፍቻ ለሚመለከተው ይጻፍ ብለናል።