No summary available.
ሕዲር 07 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐ/ሕግ- ገ/እግዚአብሓር ሙናቸው ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በመሰረተው የወንጀል ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው።1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች የ3ኛ ተጠሪ ድርጅት እንደቅደም ተከተላቸው ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆች ሲሆኑ፣ አራት ክሶች ቀርበውባቸዋል።
የመጀመሪያው ክስ፡- በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1)፣ በማዕድን አዋጅ ቁጥር 52/85 አንቀጽ 53(1)፣(5) እና በወንጀል ሕግ አንቀጽ 347 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች እንደዚሁም በአዋጅ ቁጥር 52/85 አንቀጽ 26(4) በተመለከተው መሰረት ለስራ ተፈጻሚነት ባላቸው ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት ማካሄድ ሲገባቸው በተጠቃሹ የማዕድን አዋጅ አንቀጽ 29(2) የተመለከተውን መረጃ የማኖር ወይም የመያዝ ግዳታን በመተላለፍ እንዱሁም በማእድን ስራዎች ደንብ ቁጥር 182/86 አንቀፅ 30(1ሀ(3))፣((ለ)) እና((4(ሐ)) ስር እንደተመለከተው የማዕድን ማምረት ፈቃድ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ የተመረቱትን፣የተከማቹትን፣የተዘጋጁትን ወይም ለሽያጭ የቀረቡትን ማእድናትን አስመልክቶ መረጃ መያዝ እንዲለበት የተቀመጠውን ግዳታ በመጣስ እንዱሁም በተጠቃሹ ደንብ አንቀጽ 38 እና 39 ላይ እንደተመለከተው የተሟለና ትክክለኛ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያሳይ ሪፕርቶችን፣ላልች ሰነድችን በወቅቱ ካላቀረቡ ወይም ተፈላጊ ማስታወቂያዎችን በወቅቱ ካልሰጡ ጥፊት ነው ተብል የተደነገገውን በመተላለፍ ግንቦት 02 ቀን 2001 ዓ/ም .18 ግራም ፣ዋጋው ብር 5,065,005.12(አምስት ሚሉዮን ስልሳ አምስት ሺህ አምስት ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም) የሆነውን የሐገር ውስጥ ጥፍጥፍ ወርቅ ትክክለኛና ሕጋዊ መረጃ ሳይኖራቸው ወይም ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልፅ ሰነድ ሳይዙ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 2-39968 አ.አ በሆነ ቪታራ መኪና በሮቹን በመፍታት መደበቂያ አዘጋጅተው ምንም አይነት ፈቃድ ሳይዙ በህገወጥ መንገድ ወርቅ ሲያዘዋዉሩ የተያዙ በመሆኑ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው።
ሁለተኛው ክስ ደግሞ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ የቀረበ ሆኖ ይዘቱም የወ/ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና አንቀጽ 346 እንዱሁም ብሓራዊ ባንክ ባወጣቸው መመሪያዎች መሰረት ለገበያ የሚቀርበውን ወርቅ ያገኙበትን መንገድ ወይም ቦታ ለማሳወቅ ወቅታዊ መረጃ ይዘው እንዱዘዋወሩ እና ያመረቱትን ወይም የገዙትን ወርቅ ለብሓራዊ ባንክ አቅርበው እንዱሸጡ የተጣለባቸውን ግዳታ በመተላለፍ መጠኑ በ1ኛው ክስ የተገለጸውን ወርቅ ወደ አዱስ አበባ በማጓጓዝ ሕጋዊ ወደአልሆነ ገበያ ለማቅረብ ሲለ ተይዘዋል የሚል ነው።
ሶስተኛው ክስም በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ የቀረበ ሆኖ ይዘቱም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.591/2ዐዐዐ አንቀጽ 26(1)(ለ) እንዱሁም በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና አንቀጽ 378 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ በስር 3ኛ ተከሳሽ በሀሰት የተዘጋጀውን ማስረጃ እያወቁ ተጠቅመዋል የሚል ነው።
የመጨረሻው ክስ በ3ኛ ተጠሪ ላይ የቀረበ ሆኖ ይዘቱም፡- በወርቅና ታንታለም ማእድናት ማምረት የግብይት ስራ መስክ የሕግ ሰውነት ተሰጥቶት ሲንቀሳቀስ የወርቅ ምርትን ከማጓጓዝና ለግብይት ከማቅረብ ጋር በተያያዘ አሰፈላጊውን ሕጋዊ ሰነድ መያዝ እና ማህበሩ ስላለው፣ ስላመረተው፣ ስላጓጓዘው እና ለግብይትም ስላቀረበው ወርቅ ሁኔታ የሚገልፅ መረጃ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ማቅረብ እንዲለበት የማእድን ሃብትን ለማስፊፊት በወጣው አዋጅ ቁጥር 52/85 እና በማእድን ስራዎች ደንብ ቁጥር 182/86 ላይ የተመለከቱትን ግዳታዎች በመጣስ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ፣የማእድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጂኦልጂካል ሰርቨይ በወርቅ ግዥና አቀራረብ ሂደት ስለሚከተለት የጋራ አሰራር የወጣውን መመሪያ ቁጥር 01/2000 በመተላለፍ ያለምንም ሕጋዊ ፈቃድ .18 ግራም የሆነ ወርቅ ሕጋዊ ላልሆነ ገበያ ለማቅረብ ሲንቀሳቀስ ተይዟል ተብል በ1997 ዓ/ም የወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 353(1(ለ))፣((ረ)) እንደሁም አንቀጽ 354(1 እና 2)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፎል በሚል ነው።
ክሱ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የአቃቤ ሕግ ክስ ለተጠሪዎች እንዱደርስ አድርጎና በግልፅ ችልትም ተነቦላቸው እንዱረደት ካደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠይቅ ተጠሪዎች በክሱ ላይ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ገልጸው፣ የድርጊቱን አፈጻጸም ግን ክደው ተከራክረዋል። አቃቤ ሕግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን አቅርቦ አስምቷል። ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ህግን ማስረጃዎች ሰምቶ ተጠሪዎች የወንጀል ድርጊቶችን መፈጸማቸው በአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ መረጋገጡን በማመን የተጠሪዎችን የመከላከያ ማስረጃዎችን የማሰማት መብት ጠብቆላቸው መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን ሰምቷል። ቀጥልም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የተጠሪዎች መከላከያ ማስረጃዎች ይዘት በአቃቤ ማስረጃዎች ይዘት ላይ ምክንያታዊ ጥርጣሬ የፈጠረ ሆኖ ተገኝቷል የሚል ምክንያት በመስጠትና ተጠሪዎች የአቃቤ ሕጉን ማስረጃዎች ማስተባበላቸውን በመግለጽ ተጠሪዎችን ከክሱ በነፃ አሰናብቷቸዋል።በስር 3ኛ ተከሳሽ የሆነውን ግለሰብ ግን በወ/መ/ሕ/ቁጥር 375(1(ሀ))እና ((መ)) ስር ሐሰተኛ ሰነድ የመስጠት ወንጀል መፈፀማቸው ተረጋግጧል በማለት ጥፊተኛ አድርጎ ተገቢ ነው ያለውን ቅጣት አስተላልፍበታል። የአሁኑ ተጠሪዎችን ከክሱ ነፃ ከማድረግ በተጨማሪም በኤግዚቢትነት የተያዘው የሀገር ውስጥ ወርቅም በጊዜው ባለው የወርቅ ተመን መሰረት የወርቁን ዋጋ አመልካች ለተጠሪዎች እንዱከፍል ትዕዛዝ ሰጥቶአል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበትን ውሳኔ አጽንቶአል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪዎች የተከሰሱት ሕጋዊ ፈቃድ የላቸውም በሚል ሳይሆን የወርቅ ግብይቱን ለሚመለከተው አካል ሳያቀርቡ በሕገ ወጥ መንገድ ለላላ አካል ለመሸጥ ሲለ ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል፣1ኛ ተጠሪም ማስረጃው በጥቅም አሰርቶ ያመጣው ከመሆኑም በላይ ለራሱና ለ2ኛ ተጠሪ ጥቅም ላይ ሉያውል ሲል መያዙ ተረጋግጧል የሚል ሆኖ እያለ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ስለመሆኑ በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው አረጋግጠዋል በማለት በነጻ የተሰናበቱት ያላግባብ በመሆኑ ውሳኔው ተሽሮ ተጠሪዎች ጥፊተኛ ተብለው ቅጣት እንዱጣል እና ኢግዚቢትነት የተያዘው ወርቅ ለመንግስት ውርስ እንዱሆን ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪዎች ከክሱ በነጻ የተነሰናበቱት ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው የተጠሪዎች ጠበቃ ባቀረቡት የፅሐፍ መልስ ተጠሪዎች በነፃ የተሰናበቱት ባግባቡ ተከላክለው በመገኘታቸው በመሆኑና አድራጎታቸውም የወንጀል ተጠያቂነትን የማያስከትል መሆኑ በመረጋገጡ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም ተጠሪዎች ከክሱ በነጻ እንዱሰናበቱ በስር ፍርድ ቤቶች መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።ይህንኑ ጭብጥ ለመመለስም በስር ፍርድ ቤት በአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች እንዱሁም የተጠሪዎች መካላከያ ማስረጃዎች ያስረደትን ፍሬ ነገር ይዘት ባጭሩ በሚከተለው መልኩ አይተነዋል።
በአቃቤ ሕግ በኩል በ1ኛ ምስክርነት የተጠቀሱት ግለሰብ እውነት ለመመስከር ምለው በሰጡት የምስክርነት ቃል፡-ግንቦት 02 ቀን 2001 ዓ/ም ከጥዋቱ 2፡30 አከባቢ 1ኛ ተጠሪ ደውለውላቸው ወርቅ አምጣልኝ፣ከአዋሳ 2ኛ ተጠሪ ይጠብቅሃል ሲሎቸው ወደ 2ኛ ተጠሪ ደውለው 1ኛ ተጠሪ አዝዞኛል ሲሎቸው 2ኛ ተጠሪ "ና!" ብሎቸው ከቀኑ 11፡30 አከባቢ አዋሳ ገብርኤል አካባቢ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ተገናኝተው በጥቁር ሻንጣ ወርቁን እንዲመጣላቸው፣ከመንገድ ወጣ ብለው በመኪናው ሻግ ውስጥ በማድረግ ስድስቱን እሽግ ወርቅ በመደበቅ በእለቱ አዱስ አበባ መንቀሳቀስ እንደጀመሩ፣ወደ አዱስ አበባ እየመጡ ሳለም ከምሽቱ 4፡00 አከባቢ ወደ አቃቂ ቃሉቲ የጉምሩክ ፍተሻ አከባቢ ሲደርሱ በጉምሩክ ኦፉሰሮችና በጸጥታ ኃይልች መያዛቸውንና ወዱያውኑ ወደ ጉምሩክ ጣቢያ እንዱገቡ መደረጋቸውን፣በጉዞ ወቅት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች አፍሪካ ወርቅ ድርጅት ከተባለው ጋር በስልክ ይነጋገሩ እንደነበር፣በበነጋው ወርቁን የት እንዲስቀመጡት ሲጠየቁም ሻጉን ከፍተው እንደሳዩ፣ወርቁን በተመለከተ ቀኑ 30/08/2001 ዓ/ም የሚል ተሰርቶ ማስረጃ እየመጣላቸው መሆኑን 2ኛ ተጠሪ ሲነግራቸው እንደነበር፣በወቅቱም ምስክር አትሁን ሲሎቸው እንደነበር፣ከዚያ በፉትም ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ወርቅ ሲያመጡ እንደነበር፣በሻግ ውስጥ የሚያስቀምጡትም የይለፍ ወረቀት ስለማይዙና በወቅቱም ያለመያዛቸውን፣ወርቁ ወደ ጅቡቱ እንደሚወጣም በስልክ 2ኛ ተጠሪ ሲናገር መስማታቸውን ዘርዝረው መስክረዋል።
ሁለተኛ የአቃቤ ሕግ ምስክር ደግሞ የአቃቤ ሕግ 1ኛ ምስክር የሆኑት ግለሰብ በእለቱ ከምሽቱ 5፡00 አካበቢ ሲሆን ጉምሩክ ታስሬአለሁ ጠዋት "ና!" እንደአሎቸውና ጥዋት 1፡00 አከባቢ ጉምሩክ ሲደርሱም የታሰሩበት ምክንያት ወርቅ ጭነው እንደሆነ የተነገራቸው መሆኑን፣2ኛ ተጠሪ አብሮት እንደነበር፣ይኸው ተጠሪ ወዱያውኑ ለ1ኛ ተጠሪ ደውልለት ብሎቸው ለምስከሩ ሲነግሩትም ምስክሩ ለ1ኛ ተጠሪ ደውለውለት 2ኛ ተጠሪና ወርቁ መያዙን የነገሩት መሆኑን፣ከዚያም ቀን ላይ 1ኛ ተጠሪ መልሶ ደውለውለት እመጣለሁ ጠብቀኝ እንዲለት፣ከቀኑ 8፡00 አከባቢም 1ኛ ተጠሪ ወረቀትም አስርቼ እያመጣሁ ነው ብለው ሲሎቸው ከኢትዮጵያ ሆቴል አከባቢ ሲገናኙ 1ኛ ተጠሪ ወርቁን ለማስለቀቅ ቀኑ በ30/08/2001 ዓ/ም ተብል ወደኋላ ተደርጎ የተጻፈ ወረቀት መያዛቸውን ለምስክሩ ገልፀው ወረቀቱን ለ2ኛ ተጠሪ ምስክሩ እንዱሰጥላቸው ነግሯዋቸው ምስክሩ "እኔ አልሰጥም፣ራስህ ስጥ ሲለት" 1ኛ ተጠሪ ወረቀቱን ለመስጠት በሄደበት መያዛቸውን እንደሚያውቁ መስክረዋል።
3ኛ እና 5ኛ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች በበኩላቸው 2ኛ ተከሳሽን በአቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት ወርቅ ጭነው ሲመጡ በደረሳቸው መረጃ መሰረት ሃና ማሪያም ቀለበት መንገድ አከባቢ መያዛቸውን፣ወርቁም በመኪናዋ በሮች መደበቂያ ተሰርቶለት በአንድ በኩል ሶስት፣በልላ በኩል ሶስት እሽግ ሆኖ ሲጓዝ እንደነበርና በወቅቱም ማስረጃ ተጠይቀው የለንም በማለት መልስ የሰጧቸው መሆናቸውን መስክረዋል። 4ኛው የአቃቤ ህግ ምስክር ደግሞ 2ኛ ተጠሪን ወርቅ ከደቡብ ጭነው ሲመጡ ከሃና ማሪያም አከባቢ የያዟቸው መሆኑን፣ 1ኛ ተጠሪ ግንቦት 04 ቀን 2001 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 አከባቢ የይለፍ ወረቀት አጣጥፍ ለ2ኛ ተጠሪ በአጥር ሲያቀብለ እንደያዙት መስክረዋል።ከዚህም በተጨማሪ አቃቤ ሕግ 3ኛ ተጠሪ የወርቅና የታንታለም ማእድናት አምራችና ግብይት ኃ.የተ.የግል ማህበር ስለመሆኑ ከክልለ የማዕድን ቢሮ ፈቃድ አግኝቶ ማዕድን በማምረት ስራ ላይ የተሰማራ መሆኑን፣1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ደግሞ የዚሁ ማህበር አመራሮች መሆናቸውን፣በአድ ሻኪሶ የሚገኘው የገቢዎች ጽ/ቤትም 3ኛ ተጠሪ የመረጃ አያያዙ ችግር ያለበት መሆኑን የገለፀበት መግለጫ፣2ኛ ተጠሪ ከአፍሪካ ወርቅ ቤት ጋር በስልክ ሲገናኙ የነበሩ መሆኑን የሚያሳዩ ከቴላኮሙኒኬሽን ኮርፕሬሽን የተገኘና ላልች የወርቁን ዋጋና 2ኛ ተጠሪ ወርቁ ከተደበቀበት የመኪና ክፍል መርተው ሲያስወጡ የተነሱትን ፍቶ ግራፍ በሰነድ ማስረጃነት ማቅረቡን የሥር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ያሳያል።1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው የሰነድ ማስረጃዎችን በመከላከያ ማስረጃነት ያቀረቡ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎቻቸው ይዘትም ከአንድ አመት በፉት ማዕድን ለማምረት ተደራጅተው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የማእድንና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ፈቃድ ማግኘታቸውን፣ፈቃደም የታደሰ መሆኑን፣ከብሓራዊ ባንክ ጋር ወርቅ የማቅረብ ግንኙነት እንዲላቸው፣ሮያሉቲ ታክስም እንደሚከፍለ ከተደራጁበት ጊዜ ጀምሮ የከፈለትን የሮያሉቲ መጠን፣ለብሓራዊ ባንክ ከአስራ ሁለት ጊዜ በላይ ወርቅ አቅርበው የሸጡ መሆኑን የሚያሳዩ መሆናቸውን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል።
እንግዱህ በግራ ቀኙ ማስረጃዎች የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ከላይ የተገለጹት ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎችን ከክሱ ነፃ ያደረጋቸው ተጠሪዎች ሕጋዊ የወርቅ ማምረት ፍቃድ ያላቸው መሆኑ ተረጋግጧል፣በአዋጅ ቁጥር 52/865 አንቀጽ 2 መሰረት ማምረት ማለት መሸጥን እንደሚጨምር መደንገጉን፣ማዕድኑ ሲሸጥ ለማን እንደሚሸጥ ይህ ድንጋጌ በግልጽ ያላመለከተ መሆኑና በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ቁጥር 182/86 ደግሞ ማእድንን ለማምረት ፈቃድ የተሰጠው ማህበር ያመረተውን ማእድን በተመለከተ ያመረተውን፣ያጓጓዘውን፣ያከማቸውን እንዱሁም የሸጠውን መዝግቦ መያዝ እንዲለበት፣ሲጠይቅም ማሳየት እንዲለበት ከሚደነግግ ውጪ ማዕድኑን ለዚህ አካል መሸጥ ወይም ማስረከብ አለበት ብል የደነገገው ድንጋጌ ያለመኖሩን፣የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጂኦልጂካል ስርቬይ በጋራ ባወጡት መመሪያ ላይም ማንኛውም ሕጋዊ ወርቅ አምራች ያመረተውን ወርቅ ለባንኩ ማቅረብ ይችላል ከሚል በስተቀር የማቅረብ ግዳታ እንዲለበትና ከባንኩ ውጪ ለላላ ሲያቀርብ ቢገኝ በዚህ ሕግ መሰረት ይቀጣል ተብል ያለመደንገጉን፣በደንብ ቁጥር 182/86 አንቀጽ 38 እና 39 ስር ጥፊት ተብለው የተቀመጡት ድርጊቶች ሪኮርድ ያለመያዝ፣ስለአመረቱት ፣ስለአጓጓዙት፣ስለአከማቹት እና ስለሚሸጡት ማእድን ተገቢውንና ወቅታዊውን መረጃ ባለመያዛቸው የሚወሰድባቸው ቅጣት አስተዲደራዊ እንጂ የወንጀል ቅጣት ያለመሆኑን የደንቡ አንቀጽ 40 ድንጋጌ የሚያሳይ መሆኑን በምክንያትነት በመያዝ ነው።ተጠሪዎች እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚከራከሩትም ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆኑና በተለያዩ ጊዜያት ለብሓራዊ ባንክ ወርቁን በማቅረብ ሲሸጡ የነበሩ መሆኑ መረጋገጡን መሰረት በማድረግ ሲሆን አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ደግሞ ተጠሪዎች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ሳይክድ የወርቅ ሽያጩን በሕገ ወጥ መንገድ ለመፈፀም ሲሯሯጡ ተይዘዋል፣ተገቢውን መረጃም በወቅቱ አልያዙም በማለት ነው።እኛም ጉዲዩን አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ ተመልክተነዋል።
በመሰረቱ የወርቅ ማዕድን ዝውውርን ለመቆጣጠር ስልጣን የተሰጠው ብሓራዊ ባንክ መሆኑን ብሓራዊ ባንክን ከአቋቋሙት ሕጎች መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው።የወንጀል ድርጊቱ ተፈፀመ በተባለበት ጊዜ በስራ ላይ ያለው አዋጅ ቁጥር 591/2000 ሲሆን ይህ አዋጅ በአንቀፅ 27(2) እና በአንቀጽ 5 ድንጋጌዎች ስር ብሓራዊ ባንክ የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካትና አዋጁን በሚገባ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ለማውጣት የሚያስችል ስልጣን ሰጥቶታል።ይኸው አዋጅ በአንቀጽ 28 ስር ደግሞ አዋጁን የሚቃረን ማናቸውም ሕግ፣ደንብ ወይም መመሪያ በአዋጁ ውስጥ የተመለከቱትን ጉዲዮች በሚመለከት ተፈጻሚነት እንደማይኖረው ይገልፃል።ከዚህ ድንጋጌ ተቃራኒ ንባብ ይዘት መገንዘብ የሚቻለውም አዋጁን የማይቃረን ሕግ፣ደንብ እና መመሪያ በአዋጁ ውስጥ ለተመለከቱት ጉዲዮች ተፈጻሚነት ያለው መሆኑን ነው።በአዋጁ አንቀጽ 27/2/ እና አንቀፅ 5(9) ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎች በተለይ ሲታዩም ስለወርቅና ስለውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ባንኩ መመሪያ የማውጣት ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ያስገነዝባለ። ከዚህ ድንጋጌ እና ከአዋጁ አጠቃላይ መንፈስ መረዲት የሚቻለው የገንዘብ እና የወርቅ ሥራ እንቅስቃሴ በሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን አለታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት በመመልከት በተለየ ሁኔታ ሥርዓት እንዱበጅለት እና ቁጥጥር እንዱደረግበት ማድረጉ የሕግ አውጪው ፍላጎት መሆኑን ነው።ይህንንም በእውን ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ደግሞ በአዋጁ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች በተጨማሪ ባንኩ በዝርዝር መመሪያ መሰረት ጉዲዮችን ለማስተዲደር እንዱችል ሥልጣን የተሰጠው መሆኑን አዋጁ ያስረዲል።ስለሆነም ተጠሪዎች የተከሰሱበት ድርጊት ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ በስራ ላይ የነበረው መመሪያው ቁጥር ወን/001/1997 በአንቀጽ 1 እና 2 ስለወርቅ ንግድና ዝውውር፣መያዝ ወይም ማኖር የባንኩን ፈቃድ አስፈላጊነትና የመጠኑም ገደብ አስመልክቶ ድንጋጌ ይዟል።ይህ መመሪያ ከአዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 27(2) እና 5(9) እንዱሁም አንቀጽ 28 ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘት ሲታይ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ሲሆን አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀጽ 26(1) ድንጋጌ ሲታይ ደግሞ አዋጁን ወይም አዋጁን ተከትል የወጡ ደንቦችንና መመሪያዎችን የተላለፈ ሰው የሚቀጣበትን አግባብ አስቀምጧል።ስለሆነም የወንጀል ተጠያቂነትን አስመልክቶ የተደነገገው በአዋጁ መሰረት መሆኑን እንረዲለን። በአዋጅ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት የሚወጣ መመሪያ ሕጋዊ ተፈጻሚነት ያለው መሆኑን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።በመሆኑም ባንኩ በግልጽ በአዋጁ ስለወርቅ መመሪያ ማውጣት ስልጣን አለው ተብል ስልጣን በሕግ አግባብ ከተሰጠው መመሪያው ተፈጻሚነት ሉኖረው ይገባል።ከዚህ አንፃር በመመሪያው የተመለከተውን ገደብ በመተላለፍ ለተፈፀመ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት በአዋጁ እና በወንጀል ሕጉ በተመለከተው አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ በተያዘው ጉዲይ ላይም መመሪያው ተፈጻሚነት አለው ብለናል።መመሪያ ቁጥር ወን/001/1997 ከግንቦት 10 ቀን 1997 ዓ/ም ጀምሮ በስራ ላይ ያለ ሲሆን በዚህ መመሪያ መሰረት የወርቅ አሻሻጥ ስርዓትን በብቸነት የመቆጣጥር ስልጣን ያለው አካል ብሓራዊ ባንኩ ነው።በዚህ መመሪያ መሰረት ወርቅ የሚሸጥ ግለሰብ ወይም ሰው በቅድሚያ መሸጥ ያለበት ለባንኩ በማቅረብ ነው።መመሪያው ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ግለሰቦች ከባንክ ብቻ በሕጋዊ መንገድ ጥፍጥፍ ወርቅ መግዛት እንደሚችለም ይደነግጋል።የመመሪያው አጠቃላይ ይዘት ሲታይም የወርቅ ግዥና ሽያጭ የሚከናወነው በብሓራዊ ባንክ ብቻ መሆኑን በግልፅ ያሳያል።በመመሪያው መሰረት ጥፍጥፍ ወርቅ የማምረት ፍቃድ ካላቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በቀጥታ የመግዛት ስልጣን ያለው ብቸኛ አካል ብሓራዊ ባንኩ ነዉ።ባንኩ ጥፍጥፍ ወርቁን ለመግዛት የሚችለው ደግሞ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ወርቁን ለባንኩ በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት ገቢ ሲያድርጉ ነው።በዚህ በመመሪያው መሰረት በተዘረጋው የወርቅ ግብይት ስርዓት መሰረት የማይከናወን ማንኛውም የወርቅ ግብይት ሕገ ወጥ ድርጊት ነው ተብል የሚፈረጅ መሆኑን የመመሪያው አጠቃላይ ይዘት፣መንፈስና ዓላማ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 346 ድንጋጌዎች ይዘት ጋር ተጣምሮ ሲነበብ ያስረዲል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመጣ ተጠሪዎች የወርቅ ማምረት ፍቃድ አለን በማለት ያቀረቡትን ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች እንዲለ ሲቀበለ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠውንና ሕገ ወጥ ነው የተባለውን ድርጊት ሳይለዩ አልፈዋል።ይኸውም አቃቤ ሕግ ለክሱ መሰረት ያደረገው የተጠሪዎችን ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው መሆን ያለመሆኑን ሳይሆን የወርቅ ግብይቱን በሕጉ ከተዘረጋው ስርዓት ውጪ ለመሽጥ ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል በሚል ነው።ለጉዲዩ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ደግሞ ወርቁ ለብሓራዊ ባንክ ሳይሆን ለአፍሪካ ወርቅ ቤት ቀርቦ ወደ ጅቡቲ በመላክ ለመሸጥ በማሰብ ወርቁ ሲጓጓዝ የነበረ፣በወቅቱም መያዝ የሚገባቸው መረጃዎች ሁለ በተገቢው ሁኔታ ያልተያዙ መሆኑን አረጋግጠዋል።ለጉዲዩ ቀጥተኛ ምስክር የነበረው የአቃቤ ሕግ 1ኛ ምስክርና ከኢትዮጵያ ቴላኮሙኒኬሽን ኮርፕሬሽን የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ይህንኑ የሚያስረደ መሆናቸውን የሥር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ በግልጽ የሚያሳይ ሆኖ አግኝተናል።
ወደሕጉ ስንመጣ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ በአቃቤ ሕግ የተጠቀሰው 1ኛው ክስ በዋናነት መሰረት ያደረገው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1)፣ በማዕድን አዋጅ ቁጥር 52/85 አንቀጽ 53(1)፣(5)፣26(4) ፣29 እና በወንጀል ሕግ አንቀጽ 347 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች እንደዚሁም በማእድን ስራዎች ደንብ ቁጥር 182/86 አንቀፅ 30(1ሀ(3))፣((ለ)) እና((4(ሐ)) ስር እንደተመለከተው የማዕድን ማምረት ፈቃድ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ የተመረቱትን፣የተከማቹትን፣የተዘጋጁትን ወይም ለሽያጭ የቀረቡትን ማእድናትን አስመልክቶ መረጃ መያዝ እንዲለበት የተቀመጠውን ግዳታ በመጣስ እንዱሁም በተጠቃሹ ደንብ አንቀጽ 38 እና 39 ላይ እንደተመለከተው የተሟለና ትክክለኛ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያሳይ ሪፕርቶችን፣ላልች ሰነድችን በወቅቱ ካላቀረቡ ወይም ተፈላጊ ማስታወቂያዎችን በወቅቱ ያለማቅረባቸው የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል በማለት ነው።ይህ ችልትም ጉዲዩን በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጡት ነጥቦች አንፃር ሲመለከት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 347 ስር የወንጀል ተጠያቂነት ሉከተል የሚችለው በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 346 በተመለከተው አኳኋን ማንም ሰው ሕገወጥ በሆነ መንገድ የከበሩ ማእድናት እንደወርቅ፣ፔላቲኒም፣ዩራኒየም እና ላልችንም እነዚህን የመሳሰለ ማእድናት እንዱሁም የከበሩ ድንጋዮችን ለመጠበቅ ወይም ሕገ ወጥ ዝውውሩን ለመቆጣጠር የወጣውን ሕግ በመጣስ ወንጀል የተሰራ መሆኑ ሲረጋገጥ ሲሆን ቅጣቱም ወንጀለን የፈፀመበት ሀብት የመውረስ ደንብ የሚጸናበት መሆኑ ሳይቀር ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና ከሀምሳ ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚሆን ሕጉ ያሳያል።በደንብ ቁጥር 182/1986 አንቀጽ 38 እና 39 ላይ እንደተመለከተው የተሟለና ትክክለኛ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያሳይ ሪፕርቶችን፣ላልች ሰነድችን በወቅቱ ካላቀረቡ ወይም ተፈላጊ ማስታወቂያዎችን በወቅቱ ያለማቅረባቸው የአስተዲደራዊ ጥፊቶች ሉባለ እንደሚችለ በደንቡ የተመለከተ ሲሆን የጥፊቱን ደረጃና ተደጋጋሚነት መሰረት በማድረግም የሚመለከተው አካል አስተዲደራዊ ቅጣት ሉጥል የሚችልበት አግባብ የደንቡ አንቀፅ 39 እና 40 ድንጋጌዎች በግልፅ ያሳያለ።ደንቡ የወንጀል ተጠያቂነትን እንደሚያስከትለ የሚገለፀው ከደንቡ አንቀጽ 38 እና 39 ውጪ ያለትን ድንጋጌዎችን በመጣስ የሚፈፀመውን ተግባር ስለመሆኑ በአንቀጽ 40(5) ስር በግልጽ አስቀምጧል።በመሆኑም በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ በአቃቤ ሕግ በኩል የተጠቀሰባቸው የደንብ ቁጥር 38 እና 39 ድንጋጌዎች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 347 መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት ሉያስከትለ የማይችለ መሆኑን ከደንቡ አንቀፅ 40(5) ስለተገነዘብን 1ኛ ክስን በተመለከተ 1ኛና 2ኛ ተጠሪዎች ኃላፉ የሚሆኑበትን አግባብ ስላላገኘን በዚህ ረገድ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም።
ላላው 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች የተጠቀሰባቸው የወ/ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና አንቀጽ 346 እንዱሁም ብሓራዊ ባንክ ባወጣቸው መመሪያዎች መሰረት ለገበያ የሚቀርበውን ወርቅ ያገኙበትን መንገድ ወይም ቦታ ለማሳወቅ ወቅታዊ መረጃ ይዘው እንዱዘዋወሩ እና ያመረቱትን ወይም የገዙትን ወርቅ ለብሓራዊ ባንክ አቅርበው እንዱሸጡ የተጣለባቸውን ግዳታ በመተላለፍ መጠኑ በ1ኛው ክስ የተገለጸውን ወርቅ ወደ አዱስ አበባ በማጓጓዝ ሕጋዊ ወደአልሆነ ገበያ ለማቅረብ ሲለ ተይዘዋል የሚል ነው።ከላይ በፍሬ ነገር ደረጃ እንደተገለጸው 1ኛ ተጠሪ የአቃቤ ሕጉን 1ኛ ምስክር ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ተገናኝቶ ወርቁን ወደአዱስ አበባ እንዱያጓጉዝ ማድረጉ፣2ኛ ተጠሪ ወርቁን ሲያጓጉዙ ወደ ብሓራዊ ባንክ ሳይሆን አፍሪካ ወርቅ ቤት ለተባለው የንግድ ድርጅት በማቅረብ ወደ ጅቡቱ በመላክ ለመሽጥ በማቀድ ወርቁ ሲጓጓዝ በጉምሩክ አፉሰሮችና በጸጥታ ኃይልች አማካኝነት በመንገድ ላይ የተያዘ መሆኑ በሚገባ በአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ተረጋግጧል።ስለሆነም ወርቁ በሕጉ አግባብ ከተዘረጋው ሥርዓት ውጪ ለገበያ ላቀርብ ሲል የተያዘ መሆኑ ተረጋግጧል።ይህም ተጠሪዎች ወርቁን በሕገ ወጥ መንገድ ለማዘዋወር በማሰብ ወንጀለን በማድረግ፣የወንጀለን ድርጊት እስከ መጨረሻው ያልተከታተለት ወይም ለመከታተል ያልቻለት ወይም የወንጀለን ድርጊት እንዱፈፀም እስከ መጨረሻው ተከታትለው አስፈላጊ የሆነውን ውጤት ያላገኙ ቢሆንም ተጠሪዎች ወንጀለን ለመፈፀም ከማይመለሱበት ደረጃ /Point of no return/ ደርሰው የነበረ መሆኑ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የሚያረጋግጥ በመሆኑ ወርቅን በሕገ ወጥ መንገድ መሸጥ በወ/መ/ሕ/ቁጥር 27(1)፣32(1(ሀ))((ለ)) እና 346 መሰረት ወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል ድርጊት መፈፀማቸውን የሚያስገነዝብ ሆኖ አግኘተነዋል።ተጠሪዎች ያቀረቡት የመከላከያ ሰነድም ተጠሪዎች ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ እንጂ ለክሱ መሰረት የሆነው ድርጊት ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ ወርቁን ለብሓራዊ ባንክ ሉያቀርቡ የነበረ መሆኑን የማያሳይ በመሆኑ ክብደት ሉሰጠው የሚገባው አይደለም።በመሆኑም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በ2ኛው ክስ ነፃ ሉባለ የሚችለበት ማንኛውም አግባብ ስለላለና ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው ደግሞ በአቃቤ ሕግ ክስ በተመለከተው መልኩ ሳይሆን ወርቁን በሕገ ወጥ መንገድ ለመሸጥ በመሞከር የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በወ/መ/ሕ/ቁጥር 27(1)፣32(1(ሀ))((ለ)) እና 346 ስር በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት ሆኖ አግኝተናል።ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የአቃቤ ሕግ ክስ ይዘትን ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር ጋር በማዛመድ ጉዲዩን መመልከት ሲገባቸው ለክሱ መሰረት ያልሆነውን የተጠሪዎች ሕጋዊ ነጋዳ የመሆን ጉዲይ በምክንያትነት በመያዝ 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪን ከ2ኛው ክስ ሙለ በሙለ ነፃ በማድረግ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶችን የነፃ መልቀቅ ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2((ሀ)) መሰረት በመሻር 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በወ/ህግ አንቀጽ 27(1)፣32(1(ሀ))(ለ)) እና 346 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የተላለፈ ጥፊተኞች ናቸው ብለናል።
ላላው 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ የተከሰሱበት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.591/2ዐዐዐ አንቀጽ 26(1)(ለ) እንዱሁም በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና አንቀጽ 378 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ በስር 3ኛ ተከሳሽ በሀሰት የተዘጋጀውን ማስረጃ እያወቁ ተጠቅመዋል የሚል ነው።ተጠሪዎች ማስረጃውን በጥቅም ላይ አውለው የተገኙ መሆኑ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ሐሰተኛ ማስረጃውን ያዘጋጀው የስር 3ኛ ተከሳሽም በበታች ፍርድ ቤቶች ጥፊተኛ ተብል ተገቢው ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል።1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎችም ሕጋዊ የወርቅ አምራችና አቅራቢ ድርጅት የስራ ኃላፉ ከመሆናቸው ውጪ ግንቦት 02 ቀን 2001 ዓ/ም ሲያጓጉዙትና በሕገ ወጥ መንገድ ሉሸጡት ለነበረው ወርቅ ቀድመው ትክክለኛውን ማስረጃ የያዙ መሆኑን ሉያረጋገጥላቸው የሚችል የመከላከያ ማስረጃ አላቀረቡም።ይልቁንም ተገቢውን ማስረጃ የያዙ ለማስመሰል ቀኑ ወደኋላ ሆኖ የተጻፈ ሐሰተኛ ሰነድ ለተገቢው አካል አቅርበው ጥቅም ላይ ለማዋል ሲለ ተይዘዋል።በመሆኑም 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በ3ኛ ክስም ነፃ የሚወጡበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ስለሆነ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2((ሀ)) መሰረት በመሻር 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና (ለ))) እና አንቀጽ 378 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የተላለፈ ጥፊተኞች ናቸው ተብለው ሉቀጡ የሚገባ ሆነው ተገኝተዋል።
በመጨረሻም 3ኛ ተጠሪን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ ተገቢነት ተመልክተናል።ይህ ተጠሪ ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው አካል ሲሆን የተከሰሰውም በ1997 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 353(1(ለ))፣((ረ)) እንዱሁም አንቀጽ 354(1 እና 2)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፎል በሚል ነው።ከላይ እንደተለገፀው 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች የ3ኛ ተጠሪ ድርጅት የስራ ኃላፉዎች ሆነው በሚሰሩበት ጊዜ በሕገ ወጥ መንገድ ወርቁን ለመሸጥ ሲሞክሩ በመገኘታቸው ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባ ሆነው ተገኝተዋል።እንዱህ ከሆነ ደግሞ የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወ/ሕ/አንቀጽ 34 እና በወንጀል ሕግ አንቀጽ 353(1(ለ))፣((ረ)) እንዱሁም አንቀጽ 354(1 እና 2)) ስር በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት በወንጀል ሉጠየቅ የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።በዚህም መሰረት 3ኛ ተጠሪ ነጻ የተባለበትን ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2)(ሀ))መሰረት በመሻር በ1997 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 27(1)፣353(1(ለ))፣((ረ)) እንዱሁም አንቀጽ 354(1 እና 2)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የተላለፈ ጥፊተኛ ነው ልባል የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።
ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪዎችን ሙለ በሙለ ነጻ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ሕጋዊ ባለመሆኑ ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።በዚህም መሰረት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በ2ኛው ክስ የወ/ሕግ አንቀጽ 27(1)፣32(1)(ሀ)(ለ) እና አንቀጽ 346 እንዱሁም ብሓራዊ ባንክ ባወጣቸው መመሪያዎች መሰረት ለገበያ የሚቀርበውን ወርቅ ያገኙበትን መንገድ ወይም ቦታ ለማሳወቅ ወቅታዊ መረጃ ይዘው እንዱዘዋወሩ እና ያመረቱትን ወይም የገዘቱትን ወርቅ ለብሓራዊ ባንክ አቅርበው እንዱሸጡ የተጣለባቸውን ግዳታ በመተላለፍ በሕገ ወጥ መንገድ ወርቅ ለመሸጥ ሲሞክሩ የተገኙ ጥፊተኞች ናቸው፣እንደሁም ሁለቱም ተጠሪዎች በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና አንቀጽ 378 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ በስር 3ኛ ተከሳሽ በሀሰት የተዘጋጀውን ማስረጃ እያወቁ የተጠቀሙ ጥፊተኞች ናቸው፣ 3ኛ ተጠሪ ደግሞ ያለምንም ሕጋዊ ፈቃድ .18 ግራም የሆነ ወርቅ ሕጋዊ ላልሆነ ገበያ ለማቅረብ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች አማካኝነት ሲንቀሳቀስ የተገኘ በመሆኑ በ1997 ዓ/ም የወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 34፣27(1)፣353(1(ለ))፣((ረ)) እንዱሁም አንቀጽ 354(1 እና 2)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የተላለፈ ጥፊተኛ ነው ብለናል።
No topics extracted.