No summary available.
ጥቅምት 23 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡ ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉምሩክ ወንጀል ድርጊት ተፈጽሟል በሚል የቀረበውን ክስ ተከትል የተነሳውን የዋስትና ጥያቄ የሚመለከት ነው። በጉዲዩ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆነው የተጠሪው ባለስልጣን አቃቤ ሕግ በአመልካቾችና በላልች በርካታ ሰዎች ላይ ክስ መስርቷል። በአመልካቾች ላይ የቀረበው ክስ አንድ ሁኖ አመልካቾች የጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 60/1989 በአዋጅ ቁጥር 368/1995 እንደተሻሻለ በአንቀጽ 67 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ 1ኛ አመልካች በስር ፍርድ ቤት 5ኛ ተከሳሽ የሆነውንና በጉምሩክ አስተላላፉነት ስራ ላይ የተሰማራ ዩኒቨርሳል ልጂስቲክ ሰርቪስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የተባለውን ድርጅት በስራ አስኪያጅነት ሲያስተዲድሩ ፣ 2ኛ አመልካች ደግሞ የዚሁ ድርጅት በሰነድ ምርመራ (ኦፉሰር) ሰራተኛነት የስራ ኃላፉነት ሲያከናውኑ በመላው ሃሳባቸውና አድራጎታቸው ድርጊቱ የሚያስከትለውን ውጤት በመቀበል ለመንግስት በጠቅላላ ሉከፍል የሚገባ ብር 21,602,608.64(ሃያ አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺኅ ስድስት መቶ ስምንት ብር ከስልሳ አራት ሳንቲም) ሳይከፈል ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ሲሚንቶ በሕገ ወጥ ጥቅም ላይ እንዱውል አድርገዋል በሚል አንድ ክስ መመስረቱን የአቃቤ ክስ ይገለፃል። አመልካቾች የዋስትና ጥያቄ ያቀረቡት በክሱ የተመለከተው የወንጀል ድርጊት የዋስትና መብት የሚያስነፍግ አይደለም በማለት ሲሆን አቃቤ ሕግ ደግሞ ይህንኑ የአመልካቾችን ጥያቄ የተቃወመው በአመልካቾች ላይ የተመሰረተው ክስ ከበድ ያለ ቅጣት የሚያስከትል በመሆኑ ምስክሮችን በማባበል ማስረጃ ሉያጠፈ ስለሚችለና ላላ ወንጀል ሉፈጽሙ ይችላለ የሚለ ምክንያቶችን በማንሳት የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67(ሀ)፣(ለ) እና (ሐ) ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ነው። ከዚህም በኋላ የስር ፍርድ ቤት ከሁለቱም ወገኖች የቀረበውን ክርክር መርምሮ እና በዚህ ሰበር ችልት በመ/ የተሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት በማድረግ በዚህ ውሳኔ መሰረት የስር ፍርድ ቤት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67 መሰረት ብይን ሲሰጥ በሕጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ግምት ወስድ የሚያስተናግዲቸው ስለመሆኑ መተርጎሙን ግንዛቤ ወስድ አመልካቾች የተከሰሱት የወንጀል ክስ እስከ ሃያ አምስት አመት በሚደርስ እስራትና ከሃያ አንድ ሚሉዮን ብር በላይ መቀጮ ሉያስቀጣ የሚችል ነው ፣ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ቀላል አይደለም ፣ ምስክሮችንም አያባብለም ፣ የዋስትና ግዳታቸውንም አክብረው ችልት ይቀርባለ ብል ፍርድ ቤቱ ሉገምት አይችልም የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ የአመልካቾችን የዋስትና መብት በመንፈግ ማረሚያ ቤት ሁነው ጉዲያቸውን እንዱከታተለ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
እኛም የአመልካቾች ጠበቃ ሚያዚያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ጽፈው ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን በፁሐፍ እንዱያደርጉ አድርገናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የአመልካቾች አኮኖሚያዊ አቅም ቀላል የሚባል አይደለም ፣ በዋስ ቢለቀቁ ምስክሮችን አያባብለም ፣ የዋስትና ግዳታቸውን አክብረው ችልት ይቀርባለ ተብል ፍርድ ቤቱ አይገምትም የሚለ ምክንያቶች ተይዘውና የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67(ሀ) እና (ሐ)) ድንጋጌዎች ተጠቅሰው የዋስትና ጥያቄው ተቀባይነት የለውም በሚል ውድቅ መደረጉ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ የአመልካቾች ጠበቃ እና አቃቤ ሕግ ያቀረቡትን የጹሐፍ ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
የስር ፍርድ ቤቶች በአመልካቾች ላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ በራሱ ዋስትና የሚከለክል አለመሆኑን የተቀበለት ጉዲይ ነው። ፍርድ ቤቶቹ ለዋስትናው መንፈግ መሰረት ያደረጉት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 67 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ፍርድ ቤት ተግባራዊ ሲያደርግ ግምትን መነሻ ለማድረግ የሚችለው ሕጋዊ ስልጣን ያለው መሆኑንና የድንጋጌው አጠቃላይ ትርጉምም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) መሰረት አስገዲጅነት ባለው የሰበር መ/ ላይ መሰጠቱን መሰረት በማድረግ ነው።
በመሰረቱ የዋስትና መብት በሕገ መንግስት ጥበቃ ከተደረጉት የተያዙ ሰዎች መሰረታዊ መብቶች አንደ ነው። የኢ.ፋ.ዱ.ረፏብሉክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 19(6) ስር የተያዙ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት ያላቸው መሆኑን በመርህ ደረጃ ያስቀመጠ ሲሆን ይህ በህገ መንግስቱ የተከበረው መብት ሉነፈግ ፣ ሉገደብ ወይም በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዱቀርብ ላደረግ የሚችለውም አግባብነት ባላቸው ላልች ዝርዝር ሕጎች መሰረት በልዩ ሁኔታ ስለመሆኑ ይኸው የሕገ መንግስቱ ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። በመሆኑም የዋስትና መብት መሰረታዊ የሆነ ሕገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም ፍፁም መብት ሳይሆን በሕጉ አግባብ ሉነፈግ ወይም ሉገደብ የሚችል ነው። ስለሆነም የዋስትናው ጥያቄ ተቀባይነት አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ላይ ውሳኔ የሚሰጠው ፍርድ ቤት እንደመሆኑ መጠን በዚህ ረገድ አግባብነት ያለውን ልዩ ሕግ መሰረት አድርጎ ጉዲዩን ሉመዝነውና ተገቢውን ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው ጉዲይ መሆኑ እሙን ነው።
የስር ፍርድ ቤት የአመልካቾችን የዋስትና ጥያቄ ያልተቀበለው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67(ሀ) እና((ሐ)) መሰረት ነው። ይህ ድንጋጌ በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ማመልከቻ ለመቀበል የማይቻልባቸው ሁኔታዎችን አስቀምጧል። የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 67(ሀ)) ድንጋጌ ሲታይ በዋስትናው ወረቀት የተመለከቱትን ግዳታዎች አመልካቹ የሚፈጽም የማይመስል የሆነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ በዋስትና ወረቀት የመለቀቅ ማመልከቻውን መቀበል እንደማይችል ሲደነግግ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 67(ሐ)) ስር የተመለከተውና የዋስትና ወረቀቱን ላለመቀበል ምክንያት የሚሆነው ነገር ደግሞ አመልካቹ ምስክሮችን በመግዛት (በማባበል) ወይም አስረጂ የሚሆኑበትን ያጠፊ ይሆናል ተብል የሚገመትበት ሁኔታ መኖሩ ነው። እነዚህ ድንጋጌዎች ይዘታቸው ሲታይ ፍርድ ቤቱ ግምት ለመውሰድ በሕጉ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ያስገነዝባለ። የስር ፍርድ ቤትም ድንጋጌዎቹን በዚህ መንገድ መገንዘቡን በውሳኔው ላይ ጠቅሷል። በእርግጥም ድንጋጌዎቹ በዋስትና ወረቀት የተመለከቱትን ግዳታዎች አመልካቾች የሚፈፅሙ የማይመስለ እንደሆነና ማስረጃዎችን የመግዛት(የማባበል) ወይም አስረጂ የሚሆኑበትን ያጠፈ ይሆናል ተብል የሚገመትባቸው ሁኔታዎች መኖራቸው ጥያቄውን ውድቅ ለማድረግ እንደሚቻል ያሳያለ።
እዚህ ላይ ሉስተዋል የሚገባው ዋናው ጉዲይ ግን ድንጋጌውን በመተግበር ረገድ ፍርድ ቤቱ ግንዛቤ/ግምት/ ውስጥ ሉያስገባው የሚገባው ምክንያት ምንድነው? የሚለው ነው። ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከልከል ግምቱን መነሻ የሚያደርግባቸው ሁኔታዎች በተጠቀሰው ድንጋጌ በግልፅ አልተመለከቱም። እንዱህ ከሆነ አንድ ተከሳሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዳታውን የሚፈፅም የማይመስል ነው ፣ ማስረጃም ሉያጠፊ ይችላል ተብል ግምት የሚወስደው በቂና እና ሕጋዊ ሉባለ በሚችለ ምክንያቶች ሉሆኑ ይገባል ተብል የሚታመን ሲሆን ምክንያቶች በቂና ሕጋዊ ናቸው የሚለው ጉዲይ ከተለያዩ ከባቢያዊ ሁኔታዎችና ከጉዲዩ ልዩ ባህርይ አንፃር እየታየ በፍርድ ቤቱ ግንዛቤ ሉወሰድባቸው የሚችላቸው ነጥቦች ናቸው ተብል የሚታሰብ እንጂ ቁርጥ ያለ ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች አለ ለማለት የማይቻልበት ጉዲይ ነው።
ስለሆነም የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 67 በጠቅላላው ሲታይ ፍርድ ቤት የዋስትና መብትን የሚነፍግባቸውን ሁኔታዎች የሚያሳይ ሲሆን ምክንያቶችን ፍርድ ቤቱ ከተለያዩ ሁኔታዎች በመመልከት ሉመዝናቸው የሚገባቸው ሲሆን የድንጋጌው ቅርጽ ፣ ይዘትና መንፈስ ሲታይ በሁኔታዎቹ ግምት የመወሰድ ያለመውሰድ ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት ስልጣን(Discretion) መሆኑን ያሳያል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት በዋስትና ቢወጡ የዋስትናውን ግዳታ አክብረው ይገኛለ ለማለት የሚቻል አይደለም በሚል ምክንያት ነው። ይህ ግምት መሰረቱ በአመልካቾች ላይ የተመሰረተባቸው ክስ ሉያስክትል ከሚችለው የእስራት ቅጣትና የገንዘብ መቀጮ የከበደ መሆኑ ፣ ምስክሮችን የማባበልና የማጥፊት እድልም አመልካቾች ሉሰሩ የሚችለባቸውን ሁኔታዎች መኖራቸውን መገመቱንም ፍርድ ቤቱ በትዕዛዙ ላይ ገልጿል። ፍርድ ቤቱ በእነዚህ ምክንያቶች ላይ በመመስረት ዋስትናውን ነፍጎአል። እነዚህን ምክንያቶች ለግምቱ መነሻ እንዱያደርግ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸው በሕጉ የተከለከለ ካለመሆኑም በላይ ግምት የመወሰድ ጉዲይ በሕጉ ለፍርድ ቤቱ የተሰጠው ስልጣን ነው። ግምቱ በቂ ነው ወይም አይደለም የሚለው ክርክር ደግሞ የጠቅላላ ሁኔታዎች ምዘና ጉዲይ ነው። ይህ ሰበር ችልት ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት የተሰጠው ሥልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ የማስረጃና የላልች ከባቢያዊ ነገሮችን ምዘና ጉዲይ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ማረም አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 19(6) እና የወ/መ//ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 67(ሀ)(ሐ) መሰረት የሰጡት ውሳኔ ሕጉ የሰጣቸውን ሥልጣን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር በሕጉ አተረጓጎምና አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 14 ቀን 2003 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 08 ቀን 2003 ዓ/ም በውሳኔ የጸናው ትእዛዝ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 75(2) መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.