No summary available.
ጥቅምት 15 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የጉዲዩ መነሻ ተጠሪ ዐ/ሕግ አመልካቾች በ1949 ዓ/ም በወጣው የወ/መ/ሕግ ቁጥር 36(1)(ለ) ፣ 27(1) እና 523 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ አመልካቾች በአሶሳ ከተማ ክልል ውስጥ ልዩ ስፍራው ግሪን ሆቴል ተብል በሚጠራው ቦታ ሐምል 09 ቀን 1993 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡15 በሚሆንበት ጊዜ በወንጀለ ስራና በሚሰጠው ውጤት ሙለ ተካፊዮች ሁነው ባልታወቀ ምክንያት ተነሳስተው የግል ተበዲይ አብደል መሀሙድ ኢብራሂም የተባለውን ለመግደል አስበው፤ 1ኛ አመልካች ይዞት በነበረው ሽጉጥ ሁለት ጥይት ተኩሶ የግል ተበዲይን ቀኝ እጅ በመምታት እንዱሁም 2ኛ አመልካች ከወንጀለ ድርጊት በፉትና በሂደቱ ወሬ በማቀበል፣ ዘዳ በመፍጠርና አንድ ጥይት በመተኮስ ሰውን የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ክስ በማቅረቡ ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም የአቃቤ ሕጉን ክስ ለአመልካቾች በግልጽ ችልት አንብቦላቸው እንዱረደ ከአደረገ በሁዋላ በክሱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በመጠየቅ ሁለተኛው አመልካች ክሱን እቃወማለሁ በማለት ምክንያታቸውን ገልፀው ተቃውሞ ያስመዘገቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተቃውሞውን ውድቅ አድርጎ ስለድርጊቱ አፈጻጸም አመልካቾችን የእምነት ክህደት ቃል ጠይቆ የድርጊቱን አፈፃፀም በመካዲቸው ምክንያት አቃቤ ሕጉ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አሰምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች እንዱከላከለ ተደርጎ የመከላከል መብታቸው ተጠብቆላቸው መከላከያ ምስክሮቻቸውን ከአሰሙ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የአመልካቾችን መከላከያ ማስረጃ የአቃቤ ሕጉን ማስረጃ ለማስተባበል ብቃት የላለው መሆኑን ዘርዝሮ ውድቅ ከአደረገ በሁዋላ አመልካቾችን በአቃቤ ሕጉ ተጠቅሶ በቀረበባቸው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ በማድረግ እያንዲንዲቸውን በ 5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ወሰነ። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይኸው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ላይ የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔ በማፅናት ቅጣቱን በተመለከተ ግን 1ኛ አመልካችን በአራት ዓመት ፅኑ እስራት፣ 2ኛ አመልካችን ደግሞ በሶስት ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ በማለት በማሻሻል ወሰኗል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ቢያቀርቡም ሰበር ችልቱ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አቃቤ ሕግ ከሰባት አመት በፉት ጉዲዩ አያስከስስም በማለት መዝገቡን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 42(1(ሀ)) ከዘጋው በሁዋላ እንደገና ክስ መመስረቱ ሕጋዊ ያለመሆኑንና የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችም የአመልካቾችን የወንጀል ተሳትፍ በበቂ ሁኔታ ባላስረደበት እንዱሁም የአመልካቾች የመከላከል መብት ባግባቡ ባልተጠበቀበት አመልካቾች ለወንጀለ ተጠያቂ መደረጋቸው ያላግባብ በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች ጥፊተኛ የተባለት በ1993 ዓ/ም በተፈጸመ ድርጊት ሆኖ ዐቃቤ ሕግ በ1994 ዓ/ም አያስከስስም በማለት ክሱን ከዘጋው ከሰባት አመት በሁዋላ በዚያው ድርጊት ጥፊተኛ ተብለው የመቀጣታቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ተጠሪን ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምሮታል።
አመልካቾች በጉዲዩ ላይ ድጋሚ ክስ ቀርቧል የሚለበት ምክንያት የስር የዞኑ አቃቤ ሕግ በመጀመሪያ በጉዲዩ ላይ የተከናወነውን ምርመራ ተመልክቶ የተሰበሰበው ማስረጃ ክስ ለማቅረብ የማያስችል ነው በማለት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 42(1(ሀ)) ዘግቶት ከቆየ በሁዋላ ከሰባት አመታት በሁዋላ ክሱን ማቅረቡ ተገቢነት የለውም በማለት ነው። ከዚህ የአመልካቾች ክርክር መገንዘብ የሚቻለው አመልካቾች በአንድ ጉዲይ ሁለት ጊዜ ልንከሰስ አይገባም በማለት በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የሚከለክለውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 23 ድንጋጌንና በዚህ ረገድ ተቀባይነት ያለውን የወንጀል ሕግ ፅንሰ ሀሳብ መሰረት በማድረግ የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ችልቱም የዚህን የወንጀል ሕግ ጽንሰ ሀሳብ ለጉዲዩ ያለውን አግባብነት ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነ ሥርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፊተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና የማይከሰስ ወይም የማይቀጣ መሆኑን ጽንሰ ሃሳቡ እንደሚያስገነዝብና የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስትም ይህንኑ በግልፅ የሚያስቀምጥ መሆኑን ተመልክተናል። በመሆኑንም በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የተከለከለው የመጨረሻ ውሳኔ በሆነ ጥፊተኝነቱ በተረጋጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል ሲሆን ነው።
በዚህም መሰረት በወንጀል ሥነ ሥርዓቱ ለአቃቤ ሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ጉዲዩ ክስ ለመመስረት የሚያስችል አይደለም በማለት ተጠርጣሪውን በነፃ የመልቀቅ የውሳኔ ሃሳብ በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከልን ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም። በአንድ ወንጀል ድጋሚ ቅጣት የመከልከለ ጥያቄ በፍርድ ቤት ጉዲዩ ታይቶ ተገቢ ነው የተባለ ውሳኔ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ነው።
በመሆኑም አመልካቾች በዚህ ረገድ ያነሱት የሕግ ክርክር ስለድጋሚ ቅጣት ክልከላ መርህ (principle of double jeopardy) የተቀመጡትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
ላላው ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን የሕግ ማስረጃዎች ክብደት እንዱሁም በክርክሩ አመራር የስር ፍርድ ቤት የተከተለውን ሥነ ሥርዓት የሕግ ግድፈት ያለበት መሆኑን አጥብቀው የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ይህ ችልትም ይህንኑ የአመልካቾችን የክርክር ነጥብ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዲዩን ከሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት የስር ፍርድ ቤት አመልካቾችን ለድርጊቱ ኃላፉ ያደረጋቸው የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን በመስማትና ቃላቸው ለጉዲዩ አግባብነት፣ ክብደት ያለው መሆኑን በማመን አመልካቾች በመካላከያ ማስረጃዎቻቸው እንዱያስተባብለ የመከላከል መብታቸውን በመጠበቅ የአመልካቾችን የመከላከያ ማስረጃዎችን ከሰማ በሁዋላ የመከላከያ ማስረጃዎቹ የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ለማስተባበል የማይችለ መሆኑን ዘርዝሮ ቃላቸውን ውድቅ በማድረግ መሆኑን ከውሳኔው ግልባጭ ተገንዝበናል። በመሆኑም አመልካቾች በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው አቀራረብ የስር ፍርድ ቤት ተገቢውን ሥነ ሥርዓት አልተከተለም ይበለ እንጂ የአመልካቾች የመካላከል መብት ተጠብቆ ውሳኔ መሰጠቱን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ የሚያሳይ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተነሳው የአመልካቾች ክርክር ተቀባይነት የላለው ሆኖ አግኝተናል። የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ክብደትን በተመለከተ ያቀረቡትን ቅሬታ ስንመለከተውም ጉዲዩ የማስረጃ ምዝና ጉዲይ በመሆኑና ይህ ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት ለዚህ ሰበር ችልት ከተሰጠው የመሰረታዊ ሕግ ስህተት ማረም ስልጣን ስር የማይወድቅ ወይም የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የማያሟላ በመሆኑ የምንቀበለው ሆኖ አላገኘነውም። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 2717 ሚያዚያ 25 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 16 ቀን 2002 ዓ/ም ተሻሽል በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 29 ቀን 2002 ዓ/ም የፀናው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2)) መሰረት ጸንቷል።
ውሳኔው የጸና መሆኑን እንዱያውቀው ለማረ/ቤቱ ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.