No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አደም የሱፍ ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ አብደሰላም መሐመድ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤተታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የክርክሩ መነሻ የአሁን ተጠሪ ያቀረበው ክስ ነው። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርቦ ያደራ መቻሬ መንገድ በንብረቴ ላይ በመውጣቱ ምክንያት መስከረም 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. ብር 86,44ዐ /ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ ብር/ ካሣ ተሰጥቶኝ ተከሣሽ /አመልካች/ የባለቤቴ ዘመድ ስለሆነ ይህንን ገንዘብ ገጠር ይዘህ አትሂድ ይገድለሀል ገንዘቡን እኔ በአደራ ላስቀምጥልህ ብልኝ መስከረም 13 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰው ማስረጃ ባለበት ብር 7ዐ,ዐዐዐ /ሰባ ሺህ ብር/ እንደታሰረ ሰጥቸዋለሁ።
ተከሣሽ በአደራ የሰጠሁትን ገንዘብ እንዱሰጠኝ ብጠይቀው ሉሰጠኝ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ገንዘቤን እንዱከፍል ይወስንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ከከሣሽ በአደራ የተቀበልኩት ገንዘብ የለም። ከብር 5ዐዐ /አምስት መቶ ብር/ በላይ ብድር ወይም የአደራ ገንዘብ በሰው ማስረጃ ለማስረዲት አይቻልም የሚል ክርክር አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተከሣሽ /አመልካች/ ከከሳሽ /ተጠሪ/ በአደራ ገንዘብ የተቀበለ መሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ሉመልስ ይገባዋል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርቦ የነበረ ቢሆንም አቤቱታው ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች ጥር 3ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ምንም አይነት የሰነድ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ብር 7ዐ,ዐዐዐ እንዱከፍል በህግ ተቀባይነት የላለውን የሰው ምስክር በመስማት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ እንደ እኔ ካሣ ተቀብለው ገንዘቡን ገጠር የወሰደ አርሶ አደሮች በመዘረፊቸው ገንዘቡን ይኸው ገጠር ብሄድ የዘረፊ ወንጀል ሉፈፀምብኝ ይችላል በሚል ፍርሃት የሰው ምስክሮች ባለበት የሰጡት አደራ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች በመተርጎም የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መጋቢት 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርቧል አመልካች መጋቢት 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ከተጠሪ በአደራ የተቀበለውን ገንዘብ እንዱከፍል በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መመርመር አስፈላጊ ነው።
ከላይ ይዞታቸው ከተገለፀው የህግ ድንጋጌዎች አንፃር በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጠውን የፍሬ ጉዲይ ስናገናዝበው ተጠሪ በካሣ መልክ የተቀበለውን ገንዘብ ወደሚኖርበት ገጠራማ ቦታ ቢወስደው ደህንነቱን ጠብቆ ለማቆየትና ገንዘቡን ለማስቀመጥ የማይችል በአንፃሩ ገንዘቡን ለመዝረፍ ሲለ ሰዎች ሉገድለት የሚችለ መሆኑን በግልፅ ለአሁን አመልካች በማስረዲት ብር 7ዐ,ዐዐዐ እንዱያስቀምጥለት የፈፀመው ተግባር በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2782 የተገለፀው አላቂ ዕቃ በአደራ የመስጠት ተግባር ሣይሆን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 28ዐዐ ልዩ ትርጉም ህጋዊ ዕውቅናና ጥበቃ የተሰጠው አስፈላጊ የሆነ አደራ የመስጠት ተግባር ነው። ተጠሪ የፈፀመው አስፈላጊ የሆነ አደራ የመስጠት ተግባር ማናቸውንም አይነት ማስረጃ በማቅረብ ለማስረዲት እንደሚችል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 28ዐ2 ንዐስ አንቀፅ 2 የተደነገገ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአመልካች ብር 7ዐ,ዐዐዐ አስፈላጊ የሆነ አደራ ሲሰጥ ያዩትን ምስክሮች ቃል በመስማትና በመመዘን የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2782 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2472 ድንጋጌዎች በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን የህግ ግንኙነት ለመወሰን ተፈፃሚነት የላላቸው ድንጋጌዎች ናቸው።
ድንጋጌዎቹ ስለሚያልቅ ነገር አደራ አቀማመጥና የሚያልቅ ነገር በአደራ የተሰጠ ስለመሆኑ ማስረዲት ስለሚቻልበት ሁኔታ የሚደነግጉ ጠቅላላ ድንጋጌዎች ሲሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 28ዐ2 በልዩ ሁኔታ ስለአስፈላጊ አደራ አቀማመጥና አስፈላጊ አደራን ስለማስረዲት የሚደነግግ ልዩ ድንጋጌ ነው። በመሆኑም አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የሰው ምስክር በመስማት የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2782 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2472 ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 28ዐዐ እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 28ዐ2 ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ አመልካች ከተጠሪ የተቀበለውን የአስፈላጊ አደራ ብር 7ዐ,ዐዐዐ እንዱከፍል የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የካቲት 2 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.