No summary available.
ሕዲር 18 ቀን 2001 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አልጋነሽ አበበ ቀርበዋል ተጠሪዎች፡-
አቤቱታው የቀረበው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በጠ/ፍ/የፍ/ይ/መ/ቁ.
1051/99 የካቲት 05 ቀን 2000 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አመልካቾች መጋቢት 29 ቀን 2000 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ በመጠየቃቸው ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በደቡብ ወል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት የአሁኗ አመልካች ከሳሽ፣የአሁኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች የነበሩ ሲሆን በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር ደግሞ የአሁኑ ተጠሪዎች ይግባኝ ባይ እንዱሁም የአሁኑ አመልካች መልስ ሰጭ በመሆን ተከራክረዋል።
የስር ከሳሽ ጥቅምት 28 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ያቀረቡት ክስ መሰረታዊ ይዘቱ ተከሳሾች በኩታበር ከተማ፣ቀበላ 01 የሚገኘውን በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውን ሁለት ክፍል የቆርቆሮ ቤት በመስከረም 13 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ የሽያጭ ውል በብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) ሸጠውልኝ ገንዘቡንም ሙለ በሙለ ተቀብለው እያለ ቤቱን እንዱያስረክቡና ስመ ንብረትነቱም ስላላዞሩልኝ ተገደው እንዱያስረክቡኝና ስመ ንብረቱም በስሜ እንዱያዞሩልኝ ውሳኔ ይስጠኝ የሚል ነው፤ውለ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮም የቤቱን ኪራይ በወር ብር 60 (ስድሳ ብር) ሂሳብ የ26 ወራት ይክፈለኝ ብለዋል።
ተከሳሾችም በሰጡት መልስ ስልጣኑ የወረዲ ፍ/ቤት በመሆኑ ከፍተኛ ፍ/ቤቱ በጉዲዩ የማከራከር ስልጣን እንደላለው እንደተቃወሙና ውለን ፈጽመን ገንዘቡን ከተቀበልን በኋላ ውለ እንዲፈረስንና ገንዘቡን እንዱወሰደ ለከሳሹ ቢያሳውቋቸውም ገንዘባቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም፤ በመሆኑም የውለ ይፈፀምልኝ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም ብለዋል።
የስር ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን እንደሚያይና በከሳሽና ተከሳሽ መካከል ከመጀመሪያውኑ ጀምሮ ውል መኖሩ የታመነ በመሆኑና እንደውለ ላለመፈፀም ያቀረቡት ምክንያት ተቀባይነት ስለላለው ተከሳሾች ውለን ተገደው እንዱፈጽሙ፣ስመ ንብረቱንም በከሳሽ ስም እንዱያዞሩ እንዱሁም የቤቱን ኪራይ ብር 1500 ለከሳሽ እንዱከፍለ ወስኗል።
የስር ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍርድ ቅሬታ በማሳደር የስር ተከሳሾቹ ወደ አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን አቅርበው ከተከራከሩ በኋላ ፍ/ቤቱ በፍ/ይ/መ/ቁ.1051/99 የካቲት 05 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ በግራ ቀኙ ወገኖች ተደረገ የተባለው የቤት ሽያጭ ውል ወደ ደቡብ ወል አስ/ፍ/መምሪያ የውልና ማስረጃ አካል ቀርቦ በመጣራት ላይ እያለ የቆመ በመሆኑና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ መሰረት ያልተፈፀመ በመሆኑ በመካከላቸው የሚጸና ውል እንደላለና ተዋዋዮቹ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1815 መሰረት ወደ ነበሩበት ይመለሱ፣ ስለሆነም ይ/ባዮች የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) ለመልስ ሰጪ የነበሩት የአሁኗ አመልካች እንዱመልሱ ወስኗል።
ይህ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አመልካች መጋቢት 29 ቀን 2000 ዓ.ም. የተፃፈ አቤቱታ ለሰበር ችልት ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም ውለ በጽሁፍና በምስክሮች ፉት የተፈፀመና ለምዝገባም ወደሚመለከተው አካል ቀርቦ እያለና ተጠሪዎች ውለን ማድረጋቸውና ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) ወስደው እንደነበር አምነው እያለ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1723/1/ን መሰረት በማድረግ ውለ በአዋዋይ ፉት አልተመዘገበም በሚል አተረጓጏም ውል የለም ማለቱ ተገቢ አይደለም፣ በመካከላቻው ውል መኖሩን አምነው ባለመመዝገቡ ብቻ ውል የለም ብለው ለመከራከር ለሚቃጡ ተከራካሪዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ አያገለግልም የሚል ሆኖ ተጠሪዎች በሰጡት መልስም ውለ በሚመለከተው አካል ያልተመዘገበና በእንጥልጥል የቀረ በመሆኑ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለላለ እንዱጸድቅላቸው ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ በአጭሩ እንደተመለከተው ሲሆን ይህ የሰበር ችልትም፣በመካከላቸው ውል አድርገው እንደነበር እያመኑ የቤት ሽያጩ በውልና ማስረጃ ባለመመዝገቡ ብቻ ምክንያት በማድረግ ውላቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ን መሰረት በማድረግ ተቀባይነት የለውም ሉለ ይችላለ ወይስ አይችለም? የሚል መሰረታዊ ጭብጥ በማስቀመጥ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
No topics extracted.
የአሁኑ አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በመካከላቸው የቤት ሸያጭ ውል እንዲካሄደና ተጠሪዎች የሽያጩ ጠቅላላ ገንዘብ ብር ለተጠሪዎቹ እንደሰጡ ሲገለጽ በስር ተከሳሾች የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎችም ውል አድርገው የነበረ ቢሆንም በውልና ማስረጃ የተመዘገበ ባለመሆኑ የሰጧቸው ገንዘብ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) እንዱወስደ ቢጠይቋቸውም ለመውሰድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ቤቱን እንደሚያስረክባቸው ገልጸዋል፤ በዚህም የተጠሪዎች መልስ ከአመልካች ጋር የቤቱን ሽያጭ ውል አድርገው እንደነበር እንጅ ውለ በመካከላቸው እንዲልነበረ ፈጽሞ የሚክደ አይደለም። የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በ
ሚያዝያ 30 ቀን 1999 ዓ.ም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ እና 2878 አስመልክቶ የሰጠው ትርጉም በመካከላቸው የቤት ሽያጭ ውል እንደነበር አምነው በውልና ማስረጃ አካል ባለ መመዝገቡ ብቻ ውል የለም፤ ብለው የሚቃወሙ ተከራካሪዎችን የሚያጠቃልል አይደለም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723/1/ መሰረት የሚከናወነው የምዝገባ ዋና አላማ በተዋዋይ ወገኖች የቤት ሽያጭ ውል ለመኖሩ በማስረጃነት እንዱያገለግል ሆኖ ውል ማድረጉና ገንዘብም ተቀብል እንደነበር አምኖ ውለ አልተመዘገበም በሚል ምክንያት ብቻ መቃወሙ ከላይ ከተቀመጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1723 ዓላማ ጋር የሚሄድ አይደለም። ስለሆነም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል፤ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል በሕግ የሚጸና የቤት ሽያጭ ውል አለ ብለናል።