No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቶች፡ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ነ/ፈጅ እንግዲወርቅ ጌታቸው ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1ኛ- አቶ ተመስገን ማጉላ አልቀረቡም 2ኛ- ዶ/ር ብዙአየሁ ተስፊዬ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው ከዋስትና ውል የመነጨ ግዳታ የሚጠየቅበትን አግባብ በሚመለከት በክልለ ፍ/ቤቶች የተሰጠውን የህግ ትርጉም ግራ ቀኙ በሰበር ደረጃ ካደረጉት ክርክር ጋር በማገናዘብ ተገቢውን የህግ ትርጉም ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩም መነሻ 1ኛ ተጠሪ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ አገር ለመማርና ተምሮ ሲጨርስ አገልግልት ለመስጠት አመልካችም የሚጠበቅበትን ተነፃፃሪ የገንዘብ ክፍያ ለመፈፀም ጥቅምት ዐ3 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ውል አድርገው በውለም መሰረት 2ኛ ተጠሪ ወደ ውጭ ሀገር ሄድ 23 ወራት ያህል ከተማረ በኋላ ከስምምነቱ ውጭ ወደ ላላ / ጣሉያን / ሀገር ስለሄደ ግዳታውን ጥሷል። ስለሆነም እንደውለ ባለመፈፀሙ በጠቅላላው ብር 195,796 ብር ሉከፍል ይገባል 2ኛ ተጠሪም ከዋናው ባለዕዲ ጋር ከዋስትና ግዳታ የመነጨ የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት ስላለባቸው ይክፈለ ሲል የአሁን አመልካች በሥር በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ያቀረበው ክስ ሲሆን ተጠሪዎችም በየግላቸው መልስ ሰጥተዋል። ዋናው ባለዕዲ የተባለው 1ኛ ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ከመድረሱ በፉት እንደግዳታው እንዱፈፅሙ ሉጠየቁ እንደማይገባ ገልፀው ከክሱ በነፃ እንዱሰናበቱ የጠየቁ ሲሆን፤ 2ኛ ተጠሪም በበኩላቸው የ1ኛ ተከሣሽ እምቢተኛ መሆኑ ሳይረጋገጥ መከሰሴ አግባብ አይደለም የግዳታውም ዓይነት ተራ ዋስትና በመሆኑ ከሣሽ ለግዳታው አፈፃፀም የዋናውን ባለዕዲ ንብረት ከመከተል ያለፈ ኃላፉነት ስለማይጥል የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ተከራክረዋል።
የሥር ከፍተኛው ፍ/ቤትም ይህንኑ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ተመልክቶ ሚያዚያ 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት ክሱ የቀረበው የግዳታው መፈፀሚያ ጊዜ ከመድረሱ በፉት ስለሆነ የግዳታው መፈፀሚያ ጊዜ ከደረሰ በኋላ ከሚጠይቅ በቀር በዚህ ደረጃ ላይ ተከሣሾችን ለመክሰስ አይችልም በማለት ዲኝነት የሰጠ ሲሆን ይግባኙን የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይሄው የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ለይግባኝ ሙለ ክርክር የሚያበቃ ሆኖ አልተገኘም በማለት የውሣኔውን አግባብነት ተቀብልታል ።
በዚህ የሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ ያቀረቡትም ክርክር በይዘቱ በሥር ፍ/ቤት ከቀረቡት የተለየ ሆኖ ባለመገኘቱ በድጋሚ ማስፈሩ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘነውም።
እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
ግራ ቀኙ በፍሬ ነገር ክርክር ደረጃ ካቀረቡት ክርክር አንፃር ሁለቱንም ወገኖች ያለያያቸውን ነጥብ ለይቶ በዚሁ ላይ ማስረጃ ሰምቶ ተገቢውን ዲኝነት በመስጠት ረገድ በጭብጥነት ሉያዝ የሚገባው 1ኛ ተጠሪ የውለ ግዳታ መፈፀሚያ ጊዜ ከመድረሱም በፉት ቢሆን በእራሱ ተግባር የተነሣ እንደ ውለ ግዳታውን ለመፈፀም በማይችልበት ደረጃ ተገኝቷል ወይስ አልተገኘም?
የሚለው እንጂ የግዳታ መፈፀሚያው ጊዜ ደርሷል ወይስ አልደረሰም የሚለው ጭብጥ አልነበረም።
በዚህም ረገድ አመልካች እንደሚለው ተዋዋዩ ሃያ ሶስት ወራት በውለ በተጠቀሰው አገር ከተማረ በኋላ ከተዋዋዩ ፈቃድ ውጪ በእራሱ አነሳሽነት ወደ ላላ አገር መዛወሩ ከተረጋገጠ የተዛወረበት ምክንያትም በዋናው ውል ከተጠቀሰው ተግባር ጋር የተያያዘም አይደለም ከተባለ እና ይህ በማስረጃ የሚረጋገጥ ከሆነ 1ኛው ተከሣሽ እንደውለ የመፈፀሚያው ጊዜ ከመድረሱ በፉት ውለ ውጤት እንዲይኖረው በማድረግ እንደውለ ግዳታውን ለመፈፀም የተሣነው በመሆኑ የውለ መፈፀሚያ ጊዜ ከመድረሱም በፉት መረጋገጡን ስለሚያሳይ ከሣሹ የግድ የውለ መፈፀሚያ ከደረሰ በኋላ እንጂ ከዚያ በፉት ከውል የመነጨ መብትህን ማረጋገጥ አትችልም ልባል አይገባም። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ያቀረቡትን ክርክር ተመልክቶ ተገቢውን ጭብጥ በመለየት ጉዲዩን ከመምራት አንፃር የተከተለው የጉዲይ አመራር ሥነሥርዓታዊ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል 2ኛ ተከሣሽ እንደ 1ኛ ተከሣሽ ሆኖ ለመፈፀም የገባው የዋስትና ዓይነት ተራ ዋስትና ነው ወይስ የአንድነትና የነጠላ? 1ኛው ተከሣሽ ግዳታውን ለመፈፀም እንዲልቻለ ተረጋግጧል ቢባል ሉከፈል የሚገባው ገንዘብ ምን ያህል ነው? የሚለውን አስመልክቶ ግራ ቀኙ በሥር ፍ/ቤትም ሆነ በዚህ ሰበር ደረጃ አንስተው የተከራከሩበት ቢሆንም በእነዚህ ነጥቦች ላይ የሥር ፍ/ቤት ዲኝነት ያላሳረፈበት በመሆኑ በዚህ ደረጃ የምንመለከተው አይደለም። ከዚህ በላይ በፍርደ በተመለከተው ሐተታ ምክንያት የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት በፍ/ብ/ መ/ ሚያዚያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ፤ የሰጠው ውሣኔ ፤ እንዱሁም የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በ16/9/2003 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በፍርደ ሐተታ በተመለከተው ጭብጥ መሰረትም ሆነ በክርክር ምክንያት ከባከነው ጊዜ አንፃር በመካከለ የተከሰቱትን ሁኔታዎች ሁለ አገናዝቦ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን ዲኝነት ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት ወደ ሥር ፍ/ቤት መልሰናል። ግልባጭ ይድረሳቸው። ግልባጩ ይተላለፍ።
የዚህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ማናቸውም ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።