No summary available.
ሐምል 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ጌታቸው በየነ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የቤትና የቦታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች ሞግዚት ባሁኑ አመልካች ላይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የተጠሪዎች ክስ ይዘትም ከሴት አያታቸው ከወ/ሮ ጌጤ ለገሰ አባታቸውን አቶ በቀለ በየነን በመተካት የሚወርሱትን በባህርዲር ከተማ ቀበላ 01 ክልል ውስጥ የሚገኘውንና ቁጥሩ ኤ-49 በሚል የሚታወቀውን መኖሪያ ቤት የአሁኑ አመልካች ያላግባብ ይዘው እንደሚገኙና ሉለቁላቸውም ፈቃደኛ ያለመሆናቸውን ገልጸው ቤቱን ለቀው እንዱያስረክቧቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርበዋል።አመልካች ተጠሪዎች ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም የላላቸው መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሱ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃም ቤቱና ቦታው የሟች ወ/ሮ ጌጤ ለገሰ ስለመሆኑ ሳይክደ ቤቱና ቦታውን ሟች ለአመልካች በስጦታ ያስተላለፈላቸው መሆኑን፣ስጦታው ላደረግላቸው የቻለውም ሟችን ሲጦራቸው ስለነበርና ለሟች በ1988 ዓ.ም ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) አበድረው እስከ 1993 ዓ/ም ድረስ ሉከፍል ይችል የነበረው የጥሬ ገንዘብ ብድር ባለመመለሱ ምክንያት ቤቱን ሟች ብድሩን ግንዛቤ ውስጥ አስገብተው የሰጧቸውና በስጦታ ውለ መሰረትም ስመ ሀብቱ ለአመልካች እንዱዞር ሟች ወደ ሚመለከተው አካል ቀርበው በማመልከቻ ጠይቀው ጉዲዩ በሂደት ላይ እንዲለ የካቲት 11 ቀን 2000 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፣ቤቱን ይዘው ግብር እየገበሩበት እንደሚኖሩና በ1997 ዓ/ም በደረሰው የጎርፍ አዲጋ ምክንያትም ቤቱ በመፍረሱ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ወስደው ብር 56,347.00 ወጪ አድርገው ቤቱን የሰሩት መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የአመልካችን ክርክሮች ሕጋዊ ያለመሆናቸውን ያሳያለ ያላቸውን ምክንያቶችንና ለጉዲዩ አግባብነት አላቸው ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን፣አስገዲጅ የሕግ ትርጉሞችን ሁለ በዋቢነት ከጠቀሰ በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ቤቱን ሉያስረክቡ ይገባል በማለት ወስኗል።በዚኅ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።ከዚህም በኋላ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የበታች ፍርድ ቤቶች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436 እና 1723 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ያላግባብ መተርጎማቸውንና በፍሬ ነገር ደረጃ ተዛማጅነት የላላቸውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉሞችን በመጥቀስ ውሳኔ መስጠታቸውን በመግለጽ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቹ በስጦታ ውለ ሳይፈርም መቅረቱ ውለን ፈራሽ ያደርገዋል የመባለን አግባብነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436 ድንጋጌ አንፃር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተድርጎላቸውም ሞግዚታቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሁፍ ባቀረቡት ክርክር በይዘቱ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ክርክር በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎቸ በአመልካች ላይ ክስ ሉመሰርቱ የቻለት ሴት አያታቸውን ሟች ወ/ሮ ጌጤ ለገሰን የእኚሁ ሴት ልጅ የሆነውንና ሴትዩዋን ቀድሞ የሞተውን አቶ በቀለ በየነን በመተካት በውርስ የሚያገኙትን ቤት የአሁኑ አመልካች ያላግባብ ይዞ ይገኛል በሚል ምክንያት መሆኑን፣አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ደግሞ በስጦታ ውለ ላይ ስጦታ ተቀባይ የሆኑት አመልካች ባይፈርሙም ሟች ወ/ሮ ጌጤ ለገሰ በ24/03/1996 ዓ/ም ስጦታ አድርገውላቸው የቤቱ ስመ ሀብት እንዱዞር ለሚመለከተው አካል ማመልከቻ አስገብተው ጉዲዩ በመጣራት ላይ እንዲለ ወ/ሮ ጌጤ ለገሰ ከዚህ አለም በሞት የካቲት 11 ቀን 2000 ዓ/ም የተለዩ መሆናቸውን ገልፀው ስጦታውን በተግባር የተቀበለ መሆኑን ያሳያል በሚል መሆኑን ነው።
አመልካች ስጦታ በሟች ወ/ሮ ጌጤ ለገሰ ተደረጎልኛል የሚለት ሕዲር 24 ቀን 1996 ዓ/ም ሲሆን ሟች ከዚኅ አለም በሞት የተለዩት የካቲት 11 ቀን 2000 ዓ/ም መሆኑንና እስከዚህ ጊዜ ድረስ የስመ ሀብት ዝውውር ማመልከቻ ቀርቦ ነበር ከማለት ውጪ አመልካች ቤቱን በይዞታቸው ስለማድረጋቸው ያለመረጋገጡንም ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል።በመሆኑም ሟች አደረጉ የተባለት የስጦታ ውል ከሟቹ ህልፈተ ሕይወት በኋላ ተፈፃሚ የሚሆነው ነው።
በእንደዚህ አይነት የስጦታ ውል ስለኑዛዜ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2428 ድንጋጌ በኃይለ ቃል ያስቀምጣል።በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2443 ስር ደግሞ በማይንቀሳቀስ ንብረት የሚደረግ ሥጦታ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር አይነት ካልተደረገ ፈራሽ ስለመሆኑ ተደንግጓል።በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ አሰራር በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 ስር ተመልክቷል።እንዱህ ከሆነ የሟች ሕጋዊ እና የኑዛዜ ወራሾች የስጦታው አሰራር በሕጉ የተቀመጠውን አሰራር የተከተለ መሆን ያለመሆኑን መሰረት አድርገው ክርክር ሲያቀርቡ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችን በመመልከት ለጉዲዩ እልባት መስጠት ተገቢ ይሆናል።
በተያዘው ጉዲይ የስጦታ ውለ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑን በግራ ቀኙ ክርክር የቀረበበት ሲሆን የተጠሪዎች ሞግዚት አጥብቀው የሚከራከሩት የስጦታ ሰነደ በሕጉ አግባብ ያልፀደቀና አመልካችም ያልፈረሙበት ነው በሚል ነው።የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436(1) ድንጋጌ ሲታይም የስጦታ ውል ፍጹም የሚሆነው ስጦታ ተቀባዩ ለእርሱ የተደረገውን ልግስና እቀበላለሁ ብል አሳቡን የገለጸ እንደሆነ ስለመሆኑ ያስቀመጠ ሲሆን በተጠቃሹ ቁጥር ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ስር ደግሞ ሰጪው ከሞተ ወይም ችልታ ከአጣ በኋላ ስጦታውን እቀበላለሁ የማለት ቃል ዋጋ የለውም የሚል ሃይለ ቃል በያዘ መንገድ ተቀምጧል።ሁለቱ ድንጋጌዎች አንድ ላይ ሲታዩም የመቀበለ አሳብ በፅሐፍ ይሁን በድርጊት ለይተው ያስቀመጡት ነገር የላለ ሲሆን ከድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ በዚህ ረገድ መገንዘብ የሚቻለው የስጦታው መቀበለ ሀሳብ በፅሐፍ(ፊርማ) ወይም በድርጊት መቀበል የሚቻል መሆኑን ነው።ስለሆነም ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን ስለመቀበለ የሚያስረዲ የጽሁፍ ማስረጃ ወይም ስለመቀበለ ጠቋሚ የሆነ ድርጊት ስለመኖሩ ሉያረጋግጥ ይገባል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ስጦታ ውለ ላይ ያልፈረሙ ስለመሆኑ የሚክደት ፍሬ ነገር ሳይሆን ስጦታውን መቀበላቸውን ያሳያል በማለት የሚከራከሩት በቤቱ ላይ ግብር መገበራቸውን፣ቤቱ ላይ እድሳት ማድረጋቸውንና ሟች በወቅቱ የስጦታ ውለን ይዘው ወደሚመለከተው አካል ቀርበው ስመ ሃብቱ ለአመልካች እንዱዞር አቤቱታ አቅርበው የነበረ ስለመሆኑ መረጋገጡን ነው።ይሁን እንጂ ከላይ እንደተገለጸው የስጦታ መቀበል ተግባር መኖር ያለመኖሩ በጽሐፍ ማስረጃ ወይም በድርጊት ወይም በልላ አግባብነት ባላቸው መንገድች የሚረጋገጥ ሁኖ እነዚህ ፍሬ ነገሮች መኖር ያለመኖራቸውን ፍሬ ነገሩን ለማረጋገጥ እና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች የሚያረጋገጡት ጉዲይ ሲሆን በዚህ አግባብም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች የስጦታ ተቀባዩ እቀባለለሁ ስለማለቱ ሉያሳዩ የሚችለ አይደለም፣ሉታመኑም የሚችለ አይደለም በማለት ደምድሞ ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ሙለ በሙለ ተቀብልታል።
በመሆኑም አመልካች ስጦታውን አልተቀበለም ተብል ድምዲሜ የተደረሰው ፍሬ ነገሩ ተጣርቶና ማስረጃው ተመዝኖ በመሆኑ ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አንቀጽ 25/1988 አንቀጽ 10 ተለይቶ ከተሰጠው ስልጣን አንጻር አመልካች ስጦታውን ስለመቀበላቸው ያሳያለ በማለት የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ታዓማኒነት እና ክብደት በዚህ የክርክር ደረጃ የሚታዩ ሁኖ አላገኘንም። አመልካች ሟች ከመሞታቸው በፉት ስጦታውን መቀበላቸው አልተረጋገጠም ከተባለ ደግሞ ከስጦታ ሰጪው መሞት በኋላ የስጦታ ውለን እቀበላለሁ ቢለ በሕጉ ዋጋ የሚሰጠው ተግባር ያለመሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436(2) ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436(2) ድንጋጌን በመተርጎም ረገድ የፈጸሙት ስህተት የላለ በመሆኑ በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የላለው ነው።
የስር ፍርድ ቤት የስጦታ ውለ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1723 ድንጋጌን ያላሟላ ነው በማለት የያዘው ምክንያት ሲታይ ግን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1723 ለስጦታ ውል ተፈፃሚነት የላለው መሆኑን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ሐምል 02 ቀን 2001 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያላገናዘበ በመሆኑ ምክንያቱ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው።እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት የብድር ጉዲዩን በተመለከተ ለውሳኔው አሰጣጥ በምክንያትነት መያዙም ሆነ ብድሩ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) መሰረት እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው በማለት መደምደሙ ለክርክሩ አግባብነት የላለው ሲሆን የክፍያ ግምት በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም በፍርድ ቤት ሉነሳ ይችላል ተብል በሰ/መ/ ሐምል 29 ቀን 1997 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በሰ/መ/ እና በላልች በርካታ መዛግብት የተለወጠ ስለመሆኑ ያላገናዘበ በመሆኑ ምክንያቱ ተቀባይነት የላለው ነው።በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1723 እና ስለብድሩ የቀረበውን ክርክር በተጨማሪ ምክንያትነት በመያዝ የስጦታ ውለ ፈራሽ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱበት አግባብ ተገቢ ባይሆንም የስጦታ ውለ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436(2) መሰረት ዋጋ የለውም በሚል የያዙት አብይ ምክንያትና ቤቱን አመልካች ለተጠሪዎች እንዱያስረክቡ ሲለ የሰጡት የውሳኔ ክፍል ግን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 14 ቀን 2002 ዓ.ም፣በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 23 ቀን 2002 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
አመልካች የሥጦታ ውለን ስጦታ አድራጊዋ ከመሞታቸው በፉት የተቀበለ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም ተብል በ24/03/1996 ዓ.ም ተደረገ የተባለው የስጦታ ውል በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2436 መሰረት ዋጋ የለውም፣ቤቱን ለተጠሪ ሕፃናት እንዱያስረክቡ ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
አመልካች በቤቱ ላይ ያወጡትን ወጪ በሕጉ አግባብ ከመጠየቅ ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት በ25/02/2003 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል።ለሚመከታቸው አካላት ይፃፍ።
No topics extracted.