No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንክ አ.ማ - ነ/ፈጅ ነጋ አበበ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ ደበበ ተሉላ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ከማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል ጋር በተያያዘ ሁኔታ የተነሣውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአፈፃፀም ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን የአፈፃፀም ተከሳሾች ደግሞ እነ ስንደ ሹሜ /ሶስት ሰዎች/ ነበሩ። ተጠሪው በአፈፃፀም ተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተው ብር 148,985.05 /አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ብር ከዜሮ አምስት ሳንቲም/ በፍርድ የተወሰነለት መሆኑን በመግለጽ ከወጪና ኪሣራ ጋር በድምሩ ብር 153,293.05 /አንድ መቶ ሃምሳ ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ብር ከዜሮ አምስት ሳንቲም/ በአንድነት እንዱከፍለ፣ ይህንን ባይፈፅሙ የካርታ ቁጥሩ MR.497052 የሆነ ቤትና ለብድሩ 2ኛ የፍርድ ባለእዲ የሆኑት አቶ ሹሜ ሮቢ በመያዣ ቁጥሩ 355 የሆነ በሁሩታ ከተማ ቀበላ 01 ክልል ውስጥ የሚገኝ ቤት ያስያዙ መሆኑን ገልፆ አፈፃፀሙ በዚህ አግባብ እንዱመራለት ዲኝነት ጠይቋል። በዚህ መሰረት ባለእዲዎች የተባለውን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላቸው ተጠሪ የጠቀሰው ንብረት በሐራጅ እንዱሸጥ ትእዛዝ ላሰጥ ንብረቱ ተገምቶ እንዱቀርብ የሚመለከተው አካል ሲታዘዝ ቁጥሩ 355 የሆነ ቤት ፈርሶ በቦታው ላይ አዱስ ሆቴል ቤት የተሰራ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ የገለጸ ሲሆን የአሁኑ አመልካችም ይህንኑ የሆቴል ንብረት በብር 536,822.00 /አምስት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ብር/ ብድር በካርታ ቁጥር 8205/ሹ/71/88 ይዞ ለስር 2ኛ እና 3ኛ የአፈፃፀም ተከሳሾች ብድር ያበደረ መሆኑን ጠቅሶ በንብረቱ ላይ የቀደምትነት መብት ያለው መሆኑን ዘርዝሮ ሐራጁ በንብረቱ ላይ ሉቀጥል አይገባም ሲል ተቃውሞውን አቅርቦ የአሁኑ ተጠሪም ቤቱ ላይ የቀዲሚነት መብት ያለው ራሱ መሆኑን ያሳያለ ያላቸውን ምክንያቶችን አንስቶ ተከራክሯል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣ አመልካች ንብረቱን የያዘው ከተጠሪ በተለየ ካርታና የቤት ቁጥር ስለመሆኑ መረጋገጡን ገልፆ የተጠሪ አፈፃፀም በሆቴል ቤቱ ሉቀጥል አይገባም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠ/ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ በቦታው ላይ የነበረውን ቤት ቀድሞ በመያዣነት የያዘው የአሁኑ ተጠሪ መሆኑን፣ አመልካች ያዝኩ የሚለው የሆቴል ቤት በቦታው ላይ እንደ አዱስ የተሰራ እንጂ የተለያየ ቤት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም የሚለ ምክንያቶችን ይዞ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽሮታል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል። ያሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች በመያዣነት የያዘው ንብረት በካርታ ቁጥሩም ሆነ በንብረቱ አይነት ተጠሪ በመያዣነት ያዝኩ ከሚለው ንብረት የካርታ ቁጥርና የንብረት አይነት የተለየ ሁኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የመያዣ ቀዲሚ መብት ያለው ተጠሪ ነው በማለት መወሰናቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3066 ድንጋጌንና ላልች የመያዣ ሕግ ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ባግባቡ ያላገናዘበ ነው የሚል ሲሆን ጉዲዩ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ መታየት ያለበት መሆኑ ታምኖ እንዱቀርብ ከተደረገ በኋላ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርበው በፅሐፍ በሰጠው መልስ አመልካች ያዝኩ የሚለው የሆቴል ድርጅት ተጠሪ ቀድሞ በመያዣነት የያዘው ንብረት በነበረበት ቦታ ላይ የተሰራ በመሆኑ ይኸው ንብረት ተጠሪ ቀድሞ የያዘው ንብረት አካል ተደርጎ ከሚቆጠር በስተቀር የተጠሪን የመያዣ መብቱን ሉያሳጣ የሚችል አይደለም በማለት ተከራክሯል። የአሁኑ አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪ በመያዣ ይዞት የነበረው ንብረት መኖሪያ ቤት ሲሆን አመልካች ደግሞ የሆቴል ድርጅቱን መሆኑን፣ የሁለቱም ቤቶች ካርታ ቁጥር የተለያዩ መሆናቸው የሚታወቅ ከሆነ አመልካች በልላ አዱስ ካርታ ቁጥር በመያዣ የያዘው የሆቴል ድርጅት ተጠሪ ቀደም ብል በመያዣነት ይዞት በነበረው መኖሪያ ቤት የፈረሰበት ቦታ ላይ የተሰራ በመሆኑ ብቻ ተጠሪ በመያዣ በተያዘው የሆቴል ድርጅት ላይ የቅድሚያ መብት አለው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዘበን መርምረናል።
No topics extracted.
በመሰረቱ አከራካሪው ነጥብ የሚወሰነው ስለማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መያዣ እና አፈፃፀሙን በሚመለከት በፍትሐብሕር ሕጉ በተቀመጡት ድንጋጌዎች መሰረት ነው። ከሥር ጀምሮ በተደረገው ክርክር በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው ተጠሪ በመያዣ ይዞት የነበረው ንብረት መኖሪያ ቤት ሲሆን አመልካች ደግሞ የሆቴል ድርጅቱን መሆኑን፣ የሁለቱም ቤቶች ካርታ ቁጥር የተለያዩ መሆናቸውን፣ አመልካች በልላ አዱስ ካርታ ቁጥር በመያዣ የያዘው የሆቴል ድርጅት ተጠሪ ቀደም ብል በመያዣነት ይዞት በነበረው መኖሪያ ቤት የፈረሰበት ቦታ ላይ የተሰራ መሆኑን፣ አመልካች ብድሩን የሰጠው ጥቅምት 18 ቀን 1989 ዓ/ም እና መስከረም 20 ቀን 1990 ዓ/ም በተፈረመ የብድር ውል ሁኖ የገንዘቡ መጠንም ብር 536,822.00 /አምስት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ብር/ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ብድሩን የሰጠው ሰኔ 05 ቀን 1985 ዓ/ም ሁኖ የገንዘቡ መጠንም ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ/ ነው። ይህም ማለት አመልካች ብድሩን ከተጠሪ በኋላ የሰጠ ሁኖ ለብድሩ በመያዣነት የተያዙት ንብረቶች የሚታወቁበት ካርታ ቁጥር፣ የንብረቶቹ አይነት የተለያየ ሁኖ አንድ የሚያድርጋቸው ቦታው ብቻ መሆኑን ያስገነዝባል።
በመሰረቱ የማይንቀሳቀው ንብረት በመያዣነት ከተሰጠ በኋላ አዱስ ሥራ ቢሰራ ወይም ማሻሻል ቢደረግ የመያዣ ውለን አፈፃፀም በተመለከተ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ የፍ/ብ/ሕግ ቁ.3066 ግልጽ የሆነ መልስ ሰጥቶአል። የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት የመያዣው መብት በሚመለከተው የማይንቀሣቀስ ንብረትና በዚሁ ንብረት ላይ የሚሰሩትን አዲዱስ ሥራዎች እንደሚያጠቃልል ያመለክታል። ይህን ድንጋጌ ከያዝነው ክርክር ጋር አገናዝበን ስንመለከተው ተጠሪ ቤቱን በመያዣነት ከተበዲሪዎች ከያዘ በኋላ ተሰራ የሚባለው አዱስ ሆቴል ድርጅት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ንብረቱ የሚታወቅበት የካርታ ቁጥርና የንብረቱ መለያ ቁጥር ተጠሪ ከያዘው ንብረት በአይነትም ሆነ በመለያ ቁጥሩ ፈፅሞ የማይገናኝ ከሆነ ስራው አዱስ ቢሆንም ቀድሞ ከነበረው ንብረት ስር የሚጠቃለል ነው ልባል የሚችል አለመሆኑን ያሳያል። በተለይ የዚህን ድንጋጌ መንፈስ እና አላማ ስንመለከት መያዣ ሰጪው ንብረቱ በመያዣ የተሰጠ መሆኑን እያወቀ በንብረቱ ላይ አዲዱስ ስራዎችን ቢሰራ መያዣ ያዡ አዲዱስ ስራዎችን ሁለ በመያዣ እንደያዘ የሚያስቆጥረው እና መያዣ ሰጪው እያወቀ ለሰራቸው ሥራዎች መያዣ ያዡን ለመጠበቅ ተብል የተቀረፀ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም ይህንን ድንጋጌ ተፈፃሚ ለማድረግ የንብረቱ መለያ የሆነው ካርታ ቁጥር ተለያይቶና ንብረቱ ሙለ በሙለ በአይነቱ ተለይቶ መሰራቱ ግንዛቤ ካልተወሰደና ይህንኑ መሰረት በማድረግ በንብረቱ ላይ እግድና እዲ የላለ መሆኑን በመገንዘብ መያዣ የሚወስደ ቅን ልቦና መያዣ ሰጪዎችን መብት ስንመለከት በሕግ ጥበቃ የማያገኙበት ምክንያት የለም። የፍ/ብ/ቁጥር 3052/1/ የአስተዲደር ክፍለ የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት መሆኑን አውቆለት የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት ከሰጠው ሰው ጋራ የተደረገ የንብረት መያዣ ውል የሚፀና ነው በሚል የተቀመጠው ድንጋጌ በሕግ አግባብ የተሰጠውን ካርታ ይዞ የሚያበድረው አበዲሪ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባ መሆኑን የሚያስገነዝበን ነው። በመሆኑም አመልካች በመያዣነት የያዘው ንብረት ካርታ ቁጥሩም ሆነ አይነቱ ከተጠሪ የተለየ ሁኖ እያለ ቦታው አንድ በመሆኑ ብቻ አመልካች የያዘው ንብረት ተጠሪ በያዘው ንብረት ስር የሚጠቃለል ነው ተብል ሉወሰን የማይገባውና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3066፣ 3052 እና ላልች ድንጋጌዎችን ዓላማና መንፈስ የሚጥስ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
አቤቱታ የቀረበባቸው የኦሮሚያ ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 106039 ጥር 21 ቀን 2003 ዓ/ም የሰጠው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 66122 ጥቅምት 06 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
አንድ ቀድሞ በመያዣ የተሰጠ ንብረት ካርታ ቁጥሩና የቤት ቁጥሩ ተለውጦ እንዱሁም ንብረቱ ፈርሶ በቦታው ላይ አዱስ ንብረት ተሰርቶና አዱስ ካርታና የቤት ቁጥር ተሰጥቶ በተገኘ ጊዜ ይህንኑ አዱሱን ንብረት በመያዣ የያዘ አበዲሪ ቀድሞ የነበረውን ንብረት ከያዘው አበዲሪ የቅድሚያ መብት አለው ብለናል።
በካርታ ቁጥር 8205/ሹ/71/88 በሚታወቀው የሆቴል ቤት የቀዲሚነት መብት ያለው አመልካች ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።