No summary available.
ሰኔ 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሽመልስ አበራ - ጠበቃ አቶ ማሩ ባዘዘው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ጌታቸው አያልቄ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በኀዲር 8 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በመጋቢት 14 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። ጉዲዩ የፉልም ሥራ ውል አፈፃፀም ክርክርን የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርቦ ከተከሳሽ ጋር ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ ታሪክ ወደ ፉልም ለመቀየር ጥቅምት 16 ቀን 1997 ዓ.ም ውል ተዋውለናል። በውለ ከሳሽ ለፉልም ሥራ ወጭ መሸፈን ግዳታ ያለብኝ ሲሆን ተከሳሽ ፉልሙን ለመሥራት የወጣው ወጭ ከተሸፈነ በኋላ ትርፍ እኩል ለመካፈል ተስማምተናል። ከሳሽ በውለ መሰረት ፉልሙ ተጠናቆ ለእይታ እስከበቃ ጥር 24 ቀን 1999 ዓ.ም ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ አውጥቻለሁ። ተከሳሽ ፉልሙ ለእይታ ከበቃ በኋላ በውለ መሰረት በፉልሙ የተገኘውን ገቢ አላሳወቀኝም፣ ለፉልሙ ሥራ ያወጣሁትን ወጭ አልከፈለኝም። ከስፕንሰር የተገኘውን ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ አልከፈለኝም። ከሣሽ ለፉልሙ ሥራ ከእንግሉዝ አገር ስመላለስ ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ አውጥቻለሁ። ስለሆነም ከሳሽ ከእንግሉዝ አገር ስመላለስ ያወጣሁትን ወጭ ተከሳሹ እንዱሸፍን፣ ፉልሙ ለእይታ እንዲይቀርብና የፉልሙ ማስተር እንዱቃጠልና ለገበያ የተሰራጨው እንዱሰበሰብ፣ በፉልሙ የተገኘው ገቢ ታስቦ ድርሻዬን እንዱያካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ክስና ከሳሽ በአማራጭ ሂሳቡ ተጣርቶ ለፉልም ሥራው ያወጣሁት ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ ተከሳሽ እንዱከፍል፣ ፉልም የሚያስተዲድር ባለሙያ ተሹሞ ፉልሙን ተረክቦ በማሳየትና በማስተዲደር ገቢውን እንዱያካፍለን፣ ከስፕንሰር ከተገኘው ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ድርሻዬን ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ተከሳሽ እንዱከፍልና ተከሳሽ የፉልሙን ፔሮዱውሰር ሪሽ ማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅት በሚል ስያሜ ከከሳሽ ስምምነት ውጭ ያሳተመ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 4 መሰረት የኢኮኖሚና ሞራል ጉዲት ካሳ ከውለ መቀጫ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ ነው።
አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው ከሳሽ በውለ መሰረት ያወጡት ወጭ ብር 232,000 /ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ብር/ ብቻ ነው። ከከሳሽ ጋር ውል የፈጸመው ወጋየሁና አበራ የቴአትር ኢንተርፔራይዝ ስያሜው ሪሽ የማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅት በሚል ስም በሕጋዊ መንገድ የተቀየረ በመሆኑ ክሱ የሕግ መሰረት የለውም። ሪሽ የማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅት ለፉልሙ ሥራ የከሳሽ ወኪል እያጸደቀው ብር 307,338.73 /ሦስት መቶ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰባ ሦስት ሣንቲም/ ያወጣ በመሆኑ ከሳሽ ይህንን ገንዘብ ሉተካ ወይም ሉያቻቻል ይገባል። ከሳሽ ለፉልም ሥራ የሚሆነውን የድርሰት ሥራ በማቅረባቸው ብቻ የተከሳሽን የፔሮዱውሰርነት መብት ለመጋፊት አይችልም። ከስፕንሰር የተገኘው ገንዘብ ፉልሙን ለማስመረቅ ለወጣው ወጭ የዋለ ስለሆነ ከሳሽ ያቀረበው ጥያቄ ተገቢ አይደለም።
ፉልሙን የማስተዲደር መብት ያለው ተከሣሽ በመሆኑ ክሱ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማና ከመረመረ በኋላ በከሳሽና በተከሳሽ መካከል የተደረገው ውል ሉፈረስ ይገባል ወይስ አይገባም? ከሳሸ ለፉልሙ ማሰሪያ ያወጣውና ለተከሳሽ የሚከፍለው ተጨማሪ ገንዘብ አለ ወይም የለም? ተከሳሽ ለከሳሽ ካሳ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለትን ጭብጦች ከመሰረተ በኋላ ውለ በተከሳሽ ጥፊት ሉፈረስ ይገባዋል ተከሳሽ ለፉልሙ ማሰሪያ አውጥቻለሁ በማለት ያቀረበው የተጨማሪ ገንዘብ ጥያቄ ሚዛን በሚደፊ ማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። ከሳሽ ፉልሙን በካሳ ክፍያነት ይረከቡት በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ከመረመረ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ይህንን ውሣኔ በመቃወም መጋቢት 21 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት።
በመጀመሪያ ደረጃ ተጠሪ ውል የተዋዋለው በመጀመሪያ ወጋየሁና አበራ የቴአትር ኢንተርፔራይዝ ከሚባለውና በኋላ ስያሜው ሪሽ ማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅት በሚል ስም በሕጋዊ መንገድ ከተቀየረው ድርጅት ጋር ነው። ስለዚህ ተጠሪ አመልካችን በስሙ መክሰሱ የሕግ መሰረት የለውም። የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የውል ግዳታውን በመተላለፍ የተጠሪን የስራ አመንጭነትና የኢኮኖሚ መብት አሳጥቷል በማለት ውለ እንዱፈርስ የሰጡት ውሣኔ አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 1፣ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2፣ አንቀጽ 30፣ አንቀጽ 21 ንዐስ አንቀጽ 5/ሐ/ እና ላልች አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች የሚተላለፍና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ውለ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሣኔ የሕግ መሰረት የላለው ሲሆን አመልካች የተጠሪ ወኪል በመሆን ያጸደቀው ወጭ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ ከሃያ አመት በፉት የደረስኩትና ተወዲጅ የሆነው የድርሰት ሥራዬን ወደ ፉልም ለመቀየር ከአመልካች ጋር ውል በመዋዋል በውለ መሰረት ግዳታዬን ተወጥቻለሁ። አመልካች ውለ ሲደረግ የነበረውን ድርጅት ስያሜ በመቀየር ከኃላፉነት ለማምለጥ የሞከሩ በመሆኑ ክሱ በስሙ መቅረቡ ተገቢ ነው። ለኦድቪዥዋል ሥራው ሙለ ግብአት የሆነው የእኔ ድርሰት በመሆኑና ለፉልም ስራው የወጣውን ወጭ ተጠሪ የሸፈንኩ በመሆኑ የፉልሙ ፔሮዱውሰር ተደርጌ መወሰድ ያለብኝ እኔ እንጂ አመልካች አይደለም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች ውለን ያላከበረ መሆኑን በማረጋገጥ ፉልሙን እኔ እንድረከብ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ሰኔ 13 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ተከራክረዋል። አመልካች በሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ የመልስ መልስ በሰበር አቤቱታው ያነሳቸውን ነጥቦች በማጠናከር ክርክር አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካችና ተጠሪ ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ ታሪክ ወደ ፉልም ለመቀየር ጥቅምት 16 ቀን 1997 ዓ.ም ያደረጉት ውል እንዱፈርስና ተጠሪ ፉልሙን እንዱረከብ የሰጡት ውሣኔ የሕግ መሰረት አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
በውለ ተጠሪ ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም ለመለወጥ የሚያስፈልገውን ወጭ ለመሸፈን፣ አመልካች ደግሞ የፉልም ሥራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉትን ተግባራት ሁለ በመፈጸም የፉልም ሥራውን በማጠናቀቅ ለዕይታ ለማብቃት ግዳታ የገቡ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ተጠሪ ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም ለመለወጥ የወጣውን ወጭ ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ በውለ መሰረት ሸፍኛለሁ በማለት የተከራከረ ሲሆን አመልካች ተጠሪ በውለ መሰረት ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም ለመለወጥ ከወጣው ወጭ ብር 539,338 /አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር/ ውስጥ ብር 232,000 ብቻ የከፈለ በመሆኑ በውል የገባውን መሰረታዊ ግዳታ አልተወጣም የሚል ክርክር አቅርቧል።
ለፉልሙ ሥራ የወጣው ወጭና ተጠሪ ለአመልካች የከፈለው የገንዘብ መጠን ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት መሰረታዊ ጭብጥ ነው። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ነጥብ በጭብጥነት በመያዝ የግራ ቀኙን ማስረጃ የሰማውና የመረመረው የፉልሙን ሥራ ለማጠናቀቅ የወጣው ወጭ ብር 539,338 /አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር/ ነው በማለት አመልካች ተጠሪ ብር 307,338.73 /ሦስት መቶ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰባ ሦስት ሳንቲም/ ያወጣ በመሆኑ ለአመልካች ሉተካ ወይም ሉቻቻል ይገባል በማለት ታዓሚነት ባለውና ሚዛን በሚደፊ ማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት ውድቅ አድርጎታል። ይህንን የሥር ፍርድ ቤት መደምደሚያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተቀብልታል። በልላ በኩል ተጠሪ ለፉልሙ ሥራ ማጠናቀቂያ ያወጣው አመልካች እንደሚለው ብር 232,000 /ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ/ ብር ሣይሆን ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። በአጠቃላይ ተጠሪ በውለ መሰረት የፉልሙን ሥራ ለማጠናቀቅ የወጣውን ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ በመሸፈን በውለ የገባውን ግዳታ ሙለ በሙለ የተወጣ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። በልላ በኩል አመልካች ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም በመለወጥ የፉልም ሥራው የተጠናቀቀና ፉልሙ ለዕይታ ከበቃ በኋላ በዚህ ክርክር ምክንያት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታገደ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል።
አመልካች ፉልሙ ለዕይታ ከበቃ በኋላ በውለ መሰረት ገቢውን ለተጠሪ አለማሳወቁ፣ ተጠሪ ያወጣው ወጭ በመጀመሪያ አለመተካቱና፣ ከተጠሪ ጋር በመጀመሪያ ውል የተዋዋለውን ወጋየሁና አበራ የቴአትር ኢንተርፔራይዝ የሚባለውን ድርጅት ሪሽ ማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅት በሚል ስም እንዱመዘገብ በማድረግ የውል ግዳታውን በመፈጸም በኩል ጉድለት ያሳየ መሆኑን የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።
የቅጅ መብት ባለቤቱ ኢኮኖሚያዊ መብቱን በሙለ ወይም በከፉል በስምምነት ለማስተላለፍ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 23 ተደንግጓል። ስለሆነም ተጠሪ ከአመልካች ጋር በውል ከተስማማ በኋላ የድርሰቱ ባለቤት እኔ ስለሆንኩ የኢኮኖሚ መብት ያለኝ እኔ ብቻ ነኝ በማለት የሚያቀርበው ክርክርና አመልካች የፉልሙ ፔሮዱውሰር በመሆኔ መብቱ የእኔ ብቻ ነው በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1711፣ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1731 ንኡስ አንቀጽ 1 እና የአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 23 ድንጋጌዎች ያላገናዘበና የሕግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በአመልካችና ተጠሪ ጥቅምት 16 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው ውል መሰረታዊ ይዘት የተጠሪ ድርሰት ሥራ የሆነውን ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም በመለወጥ ወጭው ከተተካ በኋላ የሚገኘውን ገቢ በመካፈል የፉልሙ የጋራ የሞራልና ኢኮኖሚ መብት ተጠቃሚ መሆን ነው። ተጠሪ በውለ መሰረት የፉልሙን ሥራ ለማጠናቀቅ የወጣውን ወጭ ሙለ በሙለ በመሸፈን በውለ የገባውን ግዳታ ሙለ በሙለ የተወጣ መሆኑን ፍሬ-ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። በልላ በኩል አመልካች ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም በመለወጥ የፉልም ሥራው የተጠናቀቀና ፉልሙ የተመረቀና ለዕይታ የበቃ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። ተጠሪ ውለ እንዱፈርስ የጠየቀው አመልካች ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም ለመለወጥና የፉልም ስራውን ለማጠናቀቅ የገባውን መሰረታዊ ግዳታ አልተወጣም በሚል ምክንያት አይደለም። ተጠሪ ውለ እንዱፈርስ የጠየቀው ፉልሙ ከተመረቀና ለዕይታ ከበቃ በኋላ አመልካች ፉልሙን በውለ መሰረት በማስተዲደር የተገኘውን ገቢ የማሳወቅና የተጠሪን የጋራ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ግዳታውን በአግባቡና በውለ መሰረት አልተወጣም በማለት ነው።
አንድ የጸና የውል ግዳታ የገባ ሰው ውለ በፍርድ እንዱሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለው ላላኛው ተዋዋይ ወገን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ግዳታዎቹን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም የፈጸማቸው ሙለ ወይም ፍጹም ባልሆነ አኳኋን እንደሆነ መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1784 ተደግንጓል። ከዚህ በተጨማሪ በውለ አይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ካልተደረገ በስተቀር ዳኞች ውለ እንዱፈርስ እንደማይወስኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገ ሲሆን ዳኞች ውሣኔ ለመስጠት የተዋዋዮቹን ጥቅምና ለቅን ልቦና የሚያስፈልገውን ነገር መሰረት ማድረግ እንዲለባቸው በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። አመልካችና ተጠሪ የተጠሪ ድርሰት ሥራ የሆነውን ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም በመለወጥ ወጭው ከተተካ በኋላ የሚገኘውን ገቢ በመካፈል የፉልሙ የጋራ የሞራልና ኢኮኖሚ መብት ተጠቃሚ ለመሆን ያደረጉትን አይነተኛ የውል ግዳታ ፈጽመው አሁን ሚከራከሩት በፉልም አስተዲደር ሥራ አመራርና ገቢ ክፍፍል በተለይም ተጠሪ ለፉልም ሥራው ያወጣውን ወጭ ፉልሙ ለዕይታ ከቀረበ በኋላ በቀዲሚነት ሉሸፈን ይገባው ነበር፤ ይህንን ባለመፈጸሙ አመልካች የውል ግዳታውን ጥሷል በማለት ነው።
ውለን ማፍረስ አመልካችና ተጠሪ፣ የተጠሪ ድርሰት ሥራ የሆነውን ቃልኪዲን የተባለውን ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ፉልም በመለወጥ የሚገኘውን ገቢ በመካፈል የፉልሙ የጋራ የሞራልና ኢኮኖሚ መብት ተጠቃሚ መሆን ለማረጋገጥ የሚያስችል አይደለም። በያዝነው ጉዲይ ፉልሙ ከተመረቀና ለእይታ ከበቃ በኋላ የፉልሙን አስተዲደርና የገቢ ክፍፍል በማስመልከት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተነሳውን አለመግባባት መነሻ በማድረግ ውለ እንዱፈርስ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ በውለ ዓይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ካልተደረገ በስተቀር ዳኞች ውለ እንዱፈርስ እንደማይወስኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም። እንደዚሁም ተጠሪ ከወጋየሁና አበራ የቴአትር ኢንተርፔራይዝ ከሚባለው አመልካች ሥራ አስኪያጅ ከሆነበት ድርጅት ጋር ውል ከተዋዋለ በኋላ የድርጅቱ ስያሜ ሪሽ ማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅት በሚል ስም በሕጋዊ መንገድ መቀየሩ ተጠሪ በፉልሙ ላይ ያለውን የሞራልና የኢኮኖሚ የጋራ ባለመብትነት የሚጋፊ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ አግባብነት ያላቸውንና ከላይ የጠቀስናቸውን ድንጋጌዎች ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም። ዳኞች ውሣኔ ለመስጠት የተዋዋዮቹን ጥቅምና ለቅን ልቦና የሚያስፈልገውን ነገር መሰረት በማድረግ እንዲለበትና የውለ መሰረታዊ ነገሮች ባልተነካበት ሁኔታ ውለ እንዱፈርስና ተጠሪ ፉልሙን እንዱረከብ የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1784 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀጽ 1፣ ንዐስ አንቀጽ 2 እና ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማን ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ ፉልሙን እንዱረከቡ የሰጡት ውሣኔ ተጠሪ በአማራጭ ባቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ፉልሙ ገለልተኛ በሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዱተዲደር ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም መነሻ ፉልሙ ከተመረቀና ለእይታ ከበቃ በኋላ የፉልሙን አስተዲደርና የገቢ ክፍፍል በማስመልከት አመልካች በውለ መሰረት ግዳታውን ያልተወጣ መሆኑን መነሻ በማድረግ ውለ እንዱፈርስ ከመወሰን ይልቅ ተጠሪ በአማራጭ ባቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ መሰረት ፉልሙ ገለልተኛ በሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዱተዲደር በማድረግ ተጠሪ ለፉልሙ ሥራ ያወጣው ወጭ ከተተካ በኋላ አመልካች ሪሽ ማስታወቂያና የፉልም ሥራ ድርጅትና ተጠሪ ትርፈን እኩል እንዱካፈለ ማድረግ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1731 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎችን ይዘት መንፈስና ዓላማ የሚያሳካ ሆኖ አግኝተነዋል። ከላይ በዝርዝር በጠቀስናቸው ምክንያቶች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውለ እንዱፈርስና ተጠሪ ፉልሙን እንዱረከብ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በኀዲር 8 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በመጋቢት 14 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሻሸሎል።
አመልካችና ተጠሪ ጥቅምት 16 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው ውል መሰረት አይነተኛ ግዳታቸውን ተወጥተው የፉልም ሥራው ተጠናቆ የተመረቀና ለዕይታ የበቃ በመሆኑ ውለ አይፈርስም በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ለፉልም ሥራው ያወጣሁት ተጨማሪ ወጭ አለ በማለት የጠየቀውን ብር 307,338.73 /ሦስት መቶ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰባ ሦስት ሳንቲም/ የመቻቻል ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው በአግባቡ ነው በማለት አጽንተነዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለፉልም ሥራው የወጣውን ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ ሙለ በሙለ የሸፈነው ተጠሪ ነው በማለት የሰጡት የውሣኔ ክፍል ጸንቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ፉልሙ ከተመረቀና ለእይታ ከበቃ በኋላ የፉልሙን አስተዲደርና የገቢ ክፍፍል በማስመልከት አመልካች በውለ መሰረት ግዳታውን አልተወጣም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ በአግባቡ ነው በማለት ወስነናል።
ተጠሪ በአማራጭ ባቀረበው የዲኝነት ጥያቄ መሰረት ፉልሙ ገለልተኛ በሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዱተዲደር እንዱታይ በማድረግና ከዚህ በፉት ፉልሙ ከተመረቀና ለእይታ ከቀረበ በኋላ ፉልሙን በማሳየት የተገኘው ገቢ ፉልሙን ለማሳየት የወጣው ወጭ ሂሳብ ተሰርቶ በመጀመሪያ ተጠሪ ለፉልም ሥራው ያወጣውን ወጪ ብር 304,000 /ሶስት መቶ አራት ሺህ ብር/ እንዱተካ ከተደረገ በኋላ ትርፈን አመልካችና ተጠሪ በውለ መሰረት እኩል እንዱካፈለ በማድረግ በፉልሙ ላይ ያላቸው የጋራ የሞራልና የኢኮኖሚ መብት ተጠቃሚነት መብት ለማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ በዚሁ መንገድ የውለ ተግባራዊነት ሉቀጥል ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚህ ችልት ሚያዝያ 6 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ በማለት ወስነናል።
No topics extracted.