No summary available.
ሚያዝያ 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ቄስ አብርሃ በርሄ - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ብርነሽ ሕለፍ - አልቀረቡም።
ጉዲዩን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በመቀላ ወረዲ ፍርድ ቤት በቀዲማዊ ወያኔ ምድብ ችልት ነው። በወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የብድር ገንዘብን የሚመለከት ነው።
አመልካች ግንቦት 7 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ተጠሪ ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ እስከ የካቲት 1994 ዓ.ም ልትመልስ፣ በዚህ ጊዜ ባትከፍል መቀጫ 8,000 /ስምስት ሺህ ብር/ በድምሩ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለመክፈል ተስማምታ በብድር ወስዲለች። ገንዘቡን ያልከፈለችኝ በመሆኑ በውለ መሰረት ብር 20,000 ከነወለደ እንድትከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ለወረዲው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ በከሳሽነት ቀርበው ገንዘብ በብድር አልወሰድኩም ፊርማውም የእኔ አይደለም በማለት ክደው ተከራክረዋል። የተጠሪ ነው የተባለው ፊርማ እንዱመረመር ትዕዛዝ ተሰጥቷል። በምርመራው ፊርማው የማን እንደሆነ መለየት እንዲልተቻለ ተገልጿል። የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ገንዘብ ሉከፍለ አይገባም በማለት ወስኖ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውለ ላይ የነበሩት ምስክሮች ሰምተህ ወስን በማለት በይግባኝ ሽሮ መልሶታል። በዚህ መሰረት የወረዲው ፍርድ ቤት የምስክሮችን ቃል ከሰማ በኋላ ምስክሮች ተጠሪ ስትበድር አይተናል፣ በውለ ላይ ፈርመናል ብለው መመስከራቸውን በመጥቀስ ተጠሪ በብድር የወሰደችውን ብር 12,000 እና መቀጫ ብር 8,000 በድምሩ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ዕዲው ተከፍል እስከሚያልቅ የባንክ ወለድ ታስቦ ይክፈለ በማለት ወስኗል። ተጠሪ ይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ በባንክ ወለድ እንድትከፍል የሰጠውን ውሣኔ ብቻ በማሻሻል ላላውን የወረዲውን ፍርድ ቤት ውሣኔ አፅንቶታል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የወረዲው ፍርድ ቤት የሰው ምስክሮችን ቃል መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2472 ድንጋጌን የሚጥስ ነው በማለት የወረዲውንና የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ በመሻር ተጠሪ ለአመልካች ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቤቱታ አቅርቦ የሰበር ችልት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቷል።
አመልካች ነሐሴ 9 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በብድር ገንዘብ የወሰደች መሆኑን ለማስረዲት ያቀረብኩት የሰነድ ማስረጃ ነው። ተጠሪ በሰነድ ላይ ያለውን ፊርማ ስለካደና ፊርማውን በቴክኒክ ምርመራ ለማረጋገጥ ስላልተቻለ ውለ ሲፈረም የነበሩ ምስክሮች ተጠሪ በሰነደ ላይ የፈረሙ መሆኑን ለማረጋገጥ የሰጡትን ምስክርነት መሰረት በማድረግ የተሰጠውን ውሣኔ አላግባብ መሻሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ኀዲር 4 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪ ግንቦት 7 ቀን 1993 ዓ.ም ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ተበድራ የወሰደች መሆኑን ለማስረዲት የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ማለትም ግንቦት 7 ቀን 1993 ዓ.ም በተፃፈና በተዋዋይ ወገኖች የተፈረመ የብድር ውል መሆኑን ከበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ተገንዝበናል። ይህም አመልካች የብድር ውለን ለማስረዲት ያቀረበው ማስረጃ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2472 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን መስፈርት የሚያሟላና ተቀባይነት ያለው ማስረጃ መሆኑን ያሣያል።
ተጠሪ በብድር ውለ ላይ ያለው ፊርማ የእኔ ፊርማ አይደለም በማለት በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2008 መሰረት ክዲ ተከራክራለች። በውለ ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪ መሆኑን ለማረጋገጥ የቴክኒክ ምርመራ የተደረገ ቢሆንም ፊርማው የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ እንዲተልቻለ፣ የፕሉስ ፍረንሲክ ላብራቶሪ በመግለፁ፣ ፊርማው የተጠሪ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለማረጋገጥ /Authenticate/ ለማድረግ በውለ ላይ ስማቸው የተገለፁት ሰዎች ተጠሪ በውለ ላይ ስትፈርም ያዩ መሆኑን እንዱያረጋግጡ ተደርጓል። እዚህ ላይ ተበዲሪው በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2472 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት የብድር ውለን ለማስረዲት በቀረበው የሰነድ ማስረጃ ላይ ያለው ፊርማ ተበዲሪው የእኔ አይደለም በማለት የካደ በሆነ ጊዜ ፊርማው የተበዲሪው መሆኑን ለማረጋገጥ ምን ዓይነት ማስረጃ ተቀባይነት አለው የሚለው በሰነድ ላይ ያለ ፊርማዎችን ለማረጋገጥ /Authenticate/ ተቀባይነት ያላቸውን ማስረጃዎች መመልከት አስፈላጊ ነው።
በሰነድ ላይ ያለ ፊርማ በተካደ ጊዜ ፊርማውን የማረጋገጫው የመጀመሪያው መንገድ የቴክኒክ ምርመራ እንዱደረግ ማድረግ ነው። ሆኖም ፊርማውን በቴክኒክ ምርመራ የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ባልተቻለ ጊዜ ፊርማው ሲፈረም የነበሩ ምስክሮችን ቃል በመስማትና በላልች ማስረጃዎች ፊርማው የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ /Authenticate/ ለማድረግ የሚቻል መሆኑ ከማስረጃ ሕግ ጠቅላላ መርሆች ለመረዲት ይቻላል። በአገራችን ፊርማ በምስክሮች ቃልና በልላ ማስረጃ እንዲይረጋገጥ /Authenticate/ እንዲይደረግ የሚከለክል ግልፅ የሕግ ድንጋጌ የለም።
በአንፃሩ ፊርማ በተካደ ጊዜና ፊርማውን በፍረንሲክ ምርመራ ለመለየት የማይቻል በሆነ ጊዜ በምስክሮች ቃልና በላልች ማስረጃዎች ማረጋገጥ እንደሚቻል በፍርድ ቤቶች ለረዥም ጊዜ የዲበረው የአሰራር ልምድ ያሳያል። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የብድር ውልን በሰነድ ማስረዲት በአስገዲጅነት የሚደነግገውን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2472 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ በማስረጃነት በቀረበ ሰነድ ላይ ያለ ፊርማ ሲካድ ፊርማው ከሚረጋገጥበት ሁኔታ /Authentication/ ጋር ያላቸውን ልዩነት ሳያገናዝቡ አመልካች በውለ ላይ ያለውን ፊርማ ከማረጋገጥ /Authentication/ ጋር አንድና ተመሣሣይ አድርጎ በመውሰድ የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2472 ንዐስ አንቀጽ 1ን ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል በብድር ውል ላይ ያለው ፊርማ የተጠሪ ፊርማ መሆኑን በማስረጃ ያረጋገጡት የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በብድር የወሰደችው ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ በተጨማሪ 8,000 /ስምስት ሺህ ብር/ ጨምራ እንድትከፍል የሰጡት ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2472 ንዐስ አንቀጽ 3 የሚቃረንና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ሙለ በሙለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። እንደዚሁም የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የቀዲማዊ ወያኔ ወረዲ ፍርድ ቤትና የመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪ ብር 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ በዚህ ጉዲይ ለወረዲ ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ታስቦ ለአመልካች የመክፈል ኃላፉነት አለባት በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.