No summary available.
ሚያዚያ 25 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፉሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሻምበል ይኩኖ ለገሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መሐመድ በሽርና ቤተሰቦቹ ጨው አምራች ኃ/የተ/የግል ማህበር አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ እንደ ውለ ያልተፈፀመለት ወገን በውለ መሰረት ባለመፈፀሙ ምክንያት ለደረሰበት ጉዲት ኪሣራ በመጠየቅ ረገድ የሚኖረው መብትና ተነፃፃሪ ግዳታን የሚመለከት ነው።
ግራ ቀኙ ግንቦት 02 ቀን 1996 ዓ.ም በተደረገ የፅሐፍ ውል የአሁን ተጠሪዎች በውል ሰጪነት/፤ አመልካች ደግሞ በውል ተቀባይነት ተሰይመው የውል ሰጭዎች የጨው ማምረቻ ቦታ ውል ተቀባይ ተረክቦ ለመጀመሪያ ሰባት አመታት በራሱ ወጪ እና ማቴሪያል ለሚያመርተው ምርት 70% ለእራሱ አስቀርቶ 30% ለውል ሰጭዎች ለማካፈል በቀሪው ሶስት አመታት ግን በግራ ቀኙ ውጭ ለሚመረተው ምርት እኩል በእኩል ለመካፈል ተስማምተዋል።
እንደ ውለ ያልፈፀመ ወገንም ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ውል ላልተፈፀመለት ወገን ከፍል ቀጣዩ በውለ መሰረት እንዱፈጽም እንደሚደረግም አክለው ተስማምተዋል።
ይህ ውል ከተደረገ ከአምስት ዓመት በኃላ የአሁን ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በተዋዋይነው ጨው የማምረት ሥራ መሰረት ውል ተቀባይነት ሥራውን መሰረት ባለመቻለ፣ እንደውል ባለመፈፀሙ የቀረብን የ30% ጥቅም ብር 3,548,666.00 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ አርባ ስምነት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) እና የገደብ መቀጮ ሉከፍለን ይገባል በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁን አመልካች በተከሣሽነት እንደውለ ያልተፈፀመው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በማለት እና ምክንያቱን በመጥቀስ የተቋረጠ ጥቅም ሉጠየቅ እንደማይገባ እንደውል አልተፈፀመም ከተባለም በውለ መሰረት ሉጠይቁ የሚችለት የ5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የገደብ መቀጮ እና እንደውለ በቀጣይ እንዱፈፀም ብቻ ነው በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በላይ በግራ ቀኙ ከተነሣው ክርክር አንፃር የአሁን አመልካች እንደውለ ሉፈጽም ያልቻለው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ስለመሆኑ በማስረጃ አልተረጋገጠም፣ እንደውለ ለመፈፀም አልቻለም። ስለሆነም ውለ ፈርሶ ሁለቱም ወገኖች ወደ ነበሩበት ቦታ ይመለሱ፤ ውለ በመፍረሱ ምክንያት ከሣሽ ይክፈለኝ የሚለትን ገንዘብ በልላ ክስ ይጠይቁ በማለት የአፊር ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲወስን፤ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በበኩለ ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ የአሁን አመልካች እንደውለ ያልፈፀመው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ባለመሆኑ ለውለ አለመፈፀም ኃላፉ ነው።
ውለ ባለመፈፀሙ በአሁን ተጠሪዎች ላይ ለደረሰው ጉዲት ማስጠንቀቂያ ከተሰጠበት ከሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ይህ ውሣኔ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በዓመት በውል በተሰጠው መሬት ምን ያህል የጨው ምርት ማምረት እንደሚቻል የክልለ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ እንደተመነና በተጠቀሰው ምርትም የጨው ዋጋ በስንት ሲሸጥ እንደነበር ለግብይት ማህበሩ በማጣራት አስተሳስቦ የደረሰባቸው ኪሣራ ይከፈል፤ እንዱሁም እንደውለ ሉቀጥለ የሚችለ ወገኖች ባለመሆናቸው በውለ መሰረት ገደቡን ብር 5,000 ይክፈል በማለት አሻሽል ወስኗል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭር የተጠቀሰው ሲሆን፤ የአመልካች የሰበር ቅሬታ ነጥብ ከሥር ፍ/ቤቶች ጀምሮ ባቀረበችው የመከራከሪያ ነጥቦች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከተጠሪዎች የተሰጠ የተለየ ክርክር አልቀረበም።
እኛም ጉዲዩን እንደሚከተው ተመልክተናል። የአሁን አመልካች እንደውለ ሉፈፀም ያልቻለው ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ስላጋጠመው ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ የሥር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ረገድ የቀረበውን ምክንያት በማስረጃ አጣርተው እና ማስረጃውን መዝነው የአሁን አመልካች ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አላጋጠመም የሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሱ በመሆኑ ጉዲዩ የህግ ትርጉምን የሚጋብዝ ሆኖ አላገኘነውም። አመልካች አጠንክሮ የተከራከረበት ላላው ነጥብ እንደ ውለ አልተፈፀመም እንኳ ቢባል እደውለ ሳይፈፀም በቀረ ጊዜ ምን ውጤት እንደሚከተል አስቀድመን በውላችን እንዱገዛ አድርገናል። በውለም እንደተገለፀው ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ/ ለተጠሪዎች ከፍል እንደ ውለ እንድፈጽም ነው ግዳታዬ የሚለው ነው።
በእርግጥ የውለ ይዘት አመልካቹ እንደሚለው መሆኑን በፍርደ መግቢያ ላይ እንደተገለፀው ቃል በቃል ሰፍሮ ተገኝቷል። ይሁን እንጂ እንደ ውለ ያልተፈፀመ ከሆነ እንደ ውለ ያልፈፀመው ወገን ብር 5,000.00 ለላላው ወገን ከፍል ቀጣይ የውል ግዳታውን ይወጣል የሚለውን የውለ አገላለጽ ከተያዘው ጉዲይ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ ተዋዋይ ወገኖች ባላቸው የመዋዋል ነፃነት ተጠቅመው ለአምስት ዓመት ያህል እንደውለ ሥራ ቢጀምሩም ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ከፍል ቀጣይ ሥራውን ይጀምራል የሚለውንም ሁለ ለማጠቃለል በማሰብ ያስገቡት የውል ቃል ነው ብል ለመተርጎም የሚቻል አይደለም። ይልቁንም የውለ አገላለጽ መለስተኛ የጊዜ ብክነትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተደረገ ለመሆኑ የገንዘቡ መጠን እና ያጋጠመው መስተጓጉል የግራ ቀኙን የውል መሰረታዊ ግንኙነት የሚያውከው መሆኑን በመገንዘብ ቀጣይ ሥራውን ያከናውናል የሚለው ውጤት አስረጂ ናቸው።
ስለሆነም የአሁን አመልካች ለአምስት ዓመታት ያህል እንደውለ አለማከናወኑ ቢታወቅም ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ከፍዬ ውለን መቀጠል ብቻ ነው ግዳታዬ የሚለው ስለ ውል አተረጓጏም የተቀመጡትን ደንቦች መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
በልላ በኩል የአሁን ተጠሪዎች ውለ ከተደረገበት ከግንቦት 1996 ዓ.ም ጀምሮ ባለት ተከታታይ ዓመታት እንደ ውለ አለመፈፀሙን እያወቁ ከውል የመነጨውን መብት ለማስጠበቅ ክስ ያቀረበችው በሰኔ 2001 ዓ.ም እንደሆነ ውሣኔው ያስረዲል።
እንደውለ ያልተፈፀመለት ወገን እንደ ውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት ለደረሰበት ጉዲት በጥቅም መቋረጥ ስላትም ሆነ በልላ ኪሣራ የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ በመርህ ደረጃ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1771 የተደነገገ ቢሆንም፤ ከውል አለመፈፀም የተነሣ ሉደርስ የሚችለውን የጉዲት መጠንን በመቀነስ ረገድ በእርሱም ላይ በተነፃፃሪ ግዳታ የተጣለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1802 ተደንግጓል።
ከዚህም አንፃር ተጠሪዎች ውለ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት ዘግይተው በአምስተኛ ዓመቱ መገባደጃ ላይ የብር 3,548,666 /የሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ስላሳ ስድስት ብር/ ኪሣራ ዓመታትን መነሻ በማድረግ አስልተው ከማቅረብ ይልቅ እንደ ውለ ያለመፈፀሙን፤ እንደውለ ሉፈጽም የሚችልበትን ሁኔታ በመረዲት ሉደረስ የሚችለውን ኪሣራ ለመቀነስ ቀደም ብለው ክስ የማቅረብ ግዳታቸውን ያልተወጡ መሆኑን የሚያመላክት ነው።
ስለሆነም ይህ በኪሣራ ጠያቂው በኩል በህግ የተጣለው ተነፃፃሪ ግዳታ የኪሣራ መጠንን ለማስላት ግምት ውስጥ ሉገባ የማይገባ ላላው ጉዲይ ሆኖ ተገኝቷል። በልላ በኩል የተቋረጠ የሚባለውን ጥቅም ለማስላት ፍ/ቤቶች የባለሙያን ድጋፍ የሚጠይቁ መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ የሚቀርበውን ሙያዊው አስተየያት በማስረጃነቱ በመያዝ ስለኪሣራው መጠን እራሳቸው የሚወስኑትና የፍ/ቤቱን ዲኝነት የሚጠይቅ ተግባር ሆኖ እያለ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እንደገለፀው የክልለ ማእድንና ኢነርጂ መሬት በየዓመቱ ምን ያህል የጨው ምርት እንደሚያገኝ ዋጋውም ስንት እንደሆነ ከግብይት ማህበራት በኩል ተጣርቶ ድርሻቸውን ይከፈላቸው በማለት የሰጠው ውሣኔ ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት አማካኝነት ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ያስከበረ ተግባር አይደለም።
በዚህ ሁለ ምክንያት የአሁን አመልካች እንደውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት በተጠሪዎች ላይ ለደረሰው ጉዲት የመካስ ኃላፉነት አለበት በሚል የተሰጠው ውሣኔ አግባብ መሆኑ እንዲለ ሆኖ ሉከፈል የሚገባውን የኪሣራ መጠን በመወሰን ረገድ የተጠሪዎች ተነፃፃሪ ግዳታ ሳይያዝ፣ ይህ በተቻለ መጠን የጉዲት ኪሣራን በመቀነስ በኩል በተጠሪዎች በኩል መፈፀም የሚገባውን ግዳታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደውለ ያልፈፀመው ወገን ሉከፍል የሚገባውን የጉዲት ኪሣራ ልክ ባባከነው ጊዜ አንፃር መሬቱ በሚያስገኘው የምርት መጠን እና በየጊዜው በነበረው የዋጋ ተመን መሰረት ይሆናል የሚለው ከተያዘ በዚህ መሰረት አስልቶ ለመወሰን የባለሙያ እገዛን ፍ/ቤቱ ከሚጠይቅ በቀር የኪሣራ አወሳሰኑን ዲኝነት ሰጭ አካል ላልሆነ አሳልፍ በመስጠት የተሰጠው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና በዝርዝር ህጉን ባካተተው በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት ይህንኑ ስህተት በማረም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ የአፊር ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዲዩን በይግባኝ ተመልክቶ በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ.
2108 መጋቢት 17 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
348(1) መሰረት በማሻሻል፣ የአሁን አመልካች እንደውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት በተጠሪዎች ላይ ለደረሰው ጉዲት ኪሣራ የመክፈል ኃላፉነት አለበት የሚለው የውሣኔው ክፍል እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ውለ ከተደረገበት ጊዜ ግንቦት /1996/ ጀምሮ ተጠሪዎች ክስ እስካቀረቡበት ሰኔ 2001 ዓ.ም. ድረስ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1802 እንደተደነገገው ኪሣራ በመቀነስ ረገድ ተጠሪዎችም የሚጠበቅባቸውን ተነፃፃሪ ግዳታ አለመወጣታቸው የኪሳራውን መጠን በማናር አስተዋጽኦ ያደረጉ መሆኑን ከግምት ውስጥ ሉገባ የሚገባውን ጉዲይ መሆኑን መነሻ በማድረግ ለኪሣራው ስላት መሰረት ሆኖ የሚያዘውን የጊዜ ርዝመት ፍ/ቤቱ ባለው የማመዛዘን ሥልጣን ተጠቅሞ እንዱቆረጥና የጊዜው ርዝመት ምን ያህል እንደሆነ ከተቆረጠ በኃላ በዚህ ጊዜ ውስጥ መሬቱ ምን ያህል የጨው ምርት ማስገኘት ይችል የነበረ መሆኑና በትይዩ ጊዜውም የጨው ዋጋ ስንት እንደነበር ፍ/ቤቱ በጠቀሳቸው አካላት ተተምኖ እና ተጣርቶ እንዱቀርብ ካደረገ በኃላ ይህንኑ ውጤት በማስረጃነት ይዞ የጉዲት ኪሣራውን ልክ መወሰን ይችል ዘንድ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት እንዱመለስ ወስነናል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ስላስከተለው ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.