No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የፉንፉኔ ዙሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት አመልካቾች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በወልመራ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው።
በወረዲው ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሣሽ ተጠሪዎች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል ጉዲዩ ወለድ አገድ ውልን የሚመለከት ነው። አመልካቾች ከተጠሪዎች ጋር መስከረም 28 ቀን 03 ዓ.ም ያደረጉት የወለድ አገድ ስምምነት ቁጥሩ 777 የሆነውን ቤትና ላልች ሁለት ክፍል ቤቶች ተጠሪዎች በወለድ አገድ በመያዝ እንዱጠቀሙበት አስረክበው ለአንድ አመት የሚቆይ 2500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ መበደራቸውን ገልፀው፣ ተጠሪዎች ገንዘቡን ወስደው ቤቱን እንዱለቁ ቢጠይቋቸው ፈቃደኛ ስላልሆኑ ገንዘቡን ወስደው ቤቱን እንዱለቁ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪዎች ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። የወረዲው ፍርድ ቤት ክሱ በይርጋ አይታገድም ተከሣሾች /ተጠሪዎች/ ገንዘቡን ወስደው ቤቱን ለከሣሾች /አመልካቾች/ ያስረክቡ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። የፉንፉኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ብድሩን ለመመለስ የተስማሙት መስከረም 28 ቀን 1984 ዓ.ም በመሆኑ ውለ በይርጋ ይታገዲል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርበው አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ የውለን ልዩ ባህሪ ያላገናዘበና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3128 ንዐስ አንቀጽ 2 የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያመለከቱ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው አመልካቾች በአንድ ዓመት ውስጥ ለመመለስ የገቡትን የብድር ውል ሣይፈጽሙ ከአስራ ስድስት ዓመት በኃላ በመጠየቃቸው ክሱ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1845 በይርጋ ይታገዲል በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የአመልካቾች ክስ በይርጋ ቀሪ ነው ተብል የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። “ወለድ አገድ” ማለት አንድ ባለእዲ ግዳታውን ለመፈፀም ማረጋገጫ በማድረግ ለገንዘብ ጠያቂው የማይንቀሣቀስ ንብረት ለማስረከብ የሚገደድበት ውል መሆኑ በፍታብሓር ህገ ቁጥር 3117 ተደንግጓል። የወለድ አገድ፣ ውል የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3124 የተደነገገ ሲሆን ማንም ሰው በወለድ አገድ የማይንቀሣቀስ ንብረት ካስያዘ ወለድ አገድ የተቋቋመበትን ግዳታ በመፈፀም በማናቸውም ጊዜ ወለድ አገድ እንዱቀር ማድረግ እንደሚችል በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3128 ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 3128 ንዐስ አንቀጽ 2 “እንዱሁም ተቃራኒ የውል ቃል ከላለ በቀር የተባለው ወለድ አገድ የተቋቋመበትን ግዳታ በመፈፀም ባለእዲው በማናቸውም ጊዜ ወለድ አገደ እንዱቀር ለማድረግ ይችላል” በሚል ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ “ተቃራኒ የውል ቃል ከላለ በቀር” የሚለውን ሀረግ ሲተረጉም የልዩ ዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድንጋጌውን መንፈስ አላማና ይዘት መሰረት ባደረገ ሁኔታ መተርጎም ሲገባው ይህንን አላደረገም። በዚህ ድንጋጌ “ተቃራኒ የውል ቃል ከላለ በቀር” የሚለው አመልካቾች እስከ መስከረም 28 ቀን 1984 ቤቱ ተጠሪዎች በወለድ አገድ እንዱያዝ የተስማሙ ስለሆነ ከመስከረም 28 ቀን 1984 ዓ.ም በፉት ገንዘቡን በመክፈል ተጠሪዎች በወለድ አገድ የያዙትን ቤት ለማስለቀቅ የማይችለ መሆኑን የሚደነግግ ነው። ይህ ማለት ግን በወለድ አገድ ውለ የተገለፀው ጊዜ ካለፈ በኃላ አመልካቾች በማናቸውም ጊዜ እዲቸውን በመክፈል ቤታቸውን ማስመለስ የሚችለ ስለመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3128 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት መጠየቅ አይችለም ማለት አይደለም። ተጠሪዎች በወለድ አገድ የያዙት ቤት ባለሀብት ሆነው የሚቀሩበት የህግ መሰረት የለም። በቤቱ እየተጠቀሙና አላባ እየሰበሰቡ መኖር ካልተስማማቸው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 3128 አንቀጽ 1 የወለድ አገድ መብቱን ለመተው የሚችልበት አጋጣሚ እንዲለ ተደንግጓል።
በአጠቃላይ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 3117 እስከ ፍታብሓር ህግ ቁጥር 1130 የወለድ አገድ የውል መሰረታዊ ባህሪ፣ ውጤትና የወለድ አገድ ውል እንዱቋረጥ ለመጠየቅ ስለሚቻልበት ሁኔታ የሚደነግጉ ልዩ ድንጋጌዎች ናቸው። በዚህ ጉዲይ ስለጠቅላላ ውል ህግ የተደነገገው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1845 ተፈፃሚነት የለውም። ስለሆነም የልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካቾች ክስ በአስር ዓመት ይርጋ ይቋረጣል በማለት የሰጠውን ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፉንፉኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የአመልካቾች ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በማለት ወስነናል።
የውልመራ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካቾች ብር 2500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለተጠሪዎች በመክፈል በወለድ አገድ ያስያዙትን ቤት የመረከብ መብት አላቸው በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.