No summary available.
መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገብረስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- ወ/ሮ ንፁህ በላይ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ምንትዋብ አዲነ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደብረ ማርቆስ ወረዲ ፍርድ ቤት ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የቤት ሽያጭ ውል የጠፊ መሆኑን በምስክር ለማስረዲት የቀረበ ጥያቄን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በደብረማርቆስ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። ወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ ፣ በዚህ ክርክር ተሣታፉ ያልሆነው አቶ እንዲወቅ አያላው ተከሣሽ አመልካች ጣልቃ ገብ ተከራካሪ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ አቶ እንዲወቅ በማላውቀው ሁኔታ እቤቴ ውስጥ ገብቶ እየኖረ ስለሆነ ቤቱን እንዱለቅና የኪራይ ገንዘብ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርባለች።
አቶ እንዲወቅ ቤቱን ያከራዩት አመልካች መሆኑን ገልፆ በክርክሩ ጣልቃ እንድትገባ ጠይቋል።
አመልካች በክርክሩ ጣልቃ ገብታ ቤቱን አሁን በህይወት ከላለው ባለቤቷ አቶ አየነው ድርሻ በ2ዐዐዐ ዓ.ም ከተጠሪ ገዝተው ፣ ለሥር ተከሣሽ በውል ያከራዩት መሆኑን በመግለፅ የተከራከረች ሲሆን የሽያጭ ውለ የጠፊ ቢሆንም ፣ ለቤቱ መብራትና ውሀ አስገብቻለሁ በማለት ተከራክረዋል። የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1723/1/ መሰረት የሽያጭ ውል አላቀረቡም በማለት አመልካች ለተጠሪ ቤቱን ለቅቀው እንዱያስረክቡ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና የተጠሪን ቃለመሃላ ከሰማ በኋላ እንደዚሁም የሰነድ ማስረጃው ይገኝባቸዋል ከተባለ መስሪያ ቤቶች የተሰጠውን ምላሽ በማገናዘብ የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም።
አመልካች ግንቦት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ክስ ያቀረበችበትን ቤት በሟች ባለቤቴ አየነው ድረስ ስም ብር 38,ዐዐዐ /ሰላሣ ስምንት ሺህ ብር/ ተጠሪ ሸጣልን ፣ ገንዘቡን ከፍለን ቤቱን ተረክበን ኖረናል። ቤቱን ከተረከብን በኋላ በብር 3ዐ,ዐዐዐ ወጭ በማድረግ አድሰናል። መብራትና ውሀ በሟች ባለቤቴ አቶ አየነው ድረስ ስም አስገብተናል። የሽያጭ ውለ ባለቤቴ አቶ አየነው ድረስ በመሞቱ ምክንያት የጠፊ በመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ3 እንዲስረዲ ያቀረብኩት ጥያቄ ውድቅ መደረጉና የቤት ኪራይ ብር 285ዐ /ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሣ ብር/ እንዱከፍል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክታለች።
ተጠሪ ነሐሴ 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ቤቱን ለአመልካችም ሆነ ለሟች ባለቤቷ የቤቱ ባለሃብት የሆንኩት ተጠሪ አልሸጥኩላቸውም። አመልካች ቤቱ የተሸጠላቸው መሆኑን ያቀረቡት የፅሁፍ ማስረጃ የለም። አመልካች ቤት አድሻለሁ በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተጠሪን የማይመለከትና በማስረጃ ያልተደገፈ ነው። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች መስከረም 15 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ ማለትም አመልካች ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ የተዋዋለችበት ሰነድ የጠፊ መሆኑን በምስክር ለማስረዲት ያቀረበችው ጥያቄ መታለፊ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሣሽነት ሣይሆን ቤቱን ከእሷ ተከራይቶ ይዞት ለነበረው አቶ እንዲወቅ አያላው መድን በመሆን ጣልቃ ገብተው በክርክሩ የተሣተፈ መሆኑን ተረድተናል። አመልካች ተጠሪ ክስ ያቀረበችበትን ቤት በ2000 ዓ.ም ሟች ባለቤቷ አየነው ድረስ በውል የገዛ መሆኑና የሽያጭ ውለ ሟች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የጠፊ መሆኑን በመጥቀስ ሰነደ የጠፊ መሆኑንና ቤቱን በውል የገዛች መሆኑን ለማስረዲት ያቀረበችውን ጥያቄ የወረዲው ፍርድ ቤትም ሆነ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አልተቀበለትም።
ውል መኖሩን በማንሣት የሚከራከር ሰው የውል ግዳታው መኖሩን የማስረዲት ግዳታ እንዲለበት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ1 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገ በመሆኑ ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ቤቱን ከተጠሪ በውል የገዛችው መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለባት በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው። የቤት ሽያጭ ውል በፅሐፍ ላደረግ የሚገባው መሆኑን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1723/1/ እና ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2877 ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል።
No topics extracted.
በመርህ ደረጃ በፅሐፍ መደረግ ያለባቸውን ውልች ለማስረዲት የሚቻለው በፅሐፍ የተደረገውን ውል በማቅረብ መሆኑን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ8 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ከተከታይ ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል። ይህ አጠቃላይ መርህ እንዲለ ሆኖ በልዩ ሁኔታ በፅሁፍ የተደረገን ውል በምስክሮች ወይም በህሉና ግምት ለማስረዲት የሚችልበት ሁኔታ ያለ መሆኑን “ውለ በፅሐፍ እንዱሆን ሕግ ባዘዘ ጊዜ ይህ ፅሐፍ የተቀደደ ፣ የተሰረቀ ፣ የጠፊ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ውለን በምስክሮች ወይም በህሉና ግምት ለማስረዲት አይችልም ” በማለት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ3 ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ አቀራረፅና ይዘት አንድ ሰው በመጀመሪያ በፅሐፍ የተደረገው ውል የተቀደደበት የተሰረቀበት ወይም የጠፊበት መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ በማቅረብ ውለ የተሰረቀ፣ የጠፊ ወይም የተቀደደ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለፍርድ ቤቱ ካስረዲ በፅሐፍ የተደረገውን ውል በምስክሮች ቃል ወይም በህሉና ግምት እንዱያስረዲ የሚፈቀድለት መሆኑን የሚደነግግ ነው።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ሟች ባለቤቷ አየነው ድረስ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ፣ ሟች ባለቤቷ አየነው ድረስ ከተጠሪ ቤቱን ለመግዛት ተዋውልት የነበረው የቤት ሸያጭ ውል የጠፊበት ስለመሆኑ በምስክሮች ለማስረዲት ያቀረበችው ጥያቄ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ3 ድንጋጌን መሰረት ያደረገና የህግ መሰረት ያለው ነው። የወረዲው ፍርድ ቤት በመጀመሪያ አመልካች ሟች ባለቤቷ አከራካሪውን ቤት ከተጠሪ ለመግዛት የተዋዋለው የፅሐፍ ውል የጠፊበት ስለመሆኑ የምታቀርባቸውን ምስክሮች በመስማት የፅሐፍ ውለ የጠፊ መሆኑን አስረድታለች ወይስ አላስረዲችም? የሚለውን ጭብጥ መወሰንና ውለ የጠፊ መሆኑን አመልካች በበቂ ሁኔታ አስረድታለች የሚል መደምደሚያ ላይ ከደረሰ አመልካች በሟች ባለቤቷ አየነው ድረስና በተጠሪ መካከል የተደረገውን የቤት ሽያጭ ውል በምስክሮች ቃልና በህሉና ግምት እንድታስረዲ በመፍቀድ ማስረጃውን በመሰማትና በመመርመርና በመመዘን መወሰን ሲገባው ፣ አመልካች የሽያጭ ውል አላቀረበችም በማለት ቤቱን ለተጠሪ እንድታስረክብ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። የዞኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች ያቀረበችውን ጥያቄ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ3 መሰረት በማድረግ መመርመርና መወሰን ሲገባው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ2 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ የተጠሪን ቃለመሃላ ሰምቶ ውሣኔ መስጠቱ የአመልካችን መብት ያጣበበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ከላይ የዘረዘርናቸው የህግ ስህተቶች ሣያርም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የወረዲው ፍርድ ቤት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2ዐዐ3 ድንጋጌ አመልካች ያላትን መብት የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደብረ ማርቆስ ወረዲ ፍርድ ቤትና ፣ የምስራቅ ጎጃም ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የደብረ ማርቆስ ወረዲ ፍርድ ቤት ፣ በመጀመሪያ አመልካች ሟች ባለቤቷ አቶ አየነው ድረስና ተጠሪ በፅሐፍ ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል የጠፊባት መሆኑን ለማስረዲት የምታቀርባቸውን ማስረጃዎች በመስማት፣ በመመርመርና በመመዘን አመልካች ውለ የጠፊ መሆኑን በበቂ ሁኔታ አስረድታለች ብል ካመነ አመልካች የሽያጭ ውለን በምስክሮች ቃልና በህሉና ግምት እንድታስረዲ በማድረግና የተጠሪን የመከላከያ ማስረጃ በመስማት ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።