No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 16 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዲሽን የህትመትና የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ነ/ፈጅ አቶ ትዕዛዙ ዓለማሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ፍስሐ ይሁን - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ የሰበር አመልካች በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሳሽ ሲሆን ተጠሪው ደግሞ ተከሳሽ ነበር። ክሱም ከተከሳሽ ጋር ባደረግነው ውል ከሳሽ ለተከሳሽ ፍስሐና ስራው የሚል መፅሐፍ 300 ቅጂ ለማዘጋጀትና ተከሳሽም ለከሳሽ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ለመክፈል የተስማማን ሲሆን በስምምነታችን መሰረት ተከሳሽ ቅድመ ክፍያ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ከፍል መጽሐፍቹን ከሳሽ አዘጋጅቼ ባጠናቅቅም ቀሪውን ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሳይከፍለኝ ከአንድ ዓመት በላይ ስለቆየ ገንዘቡ ተከፍል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለኝ ይወሰንበት የሚል ነው።
ተከሳሽም ሞቷል በመባለ ወራሾች ካለ ቀርበው ለክሱ መልስ እንዱሰጡ መጥሪያ በተከሳሽ ቤት ተለጥፍ ወራሾች ባለመቅረባቸው ክርክሩ በላለበት ቀጥል የመ/ደ/ፍ/ቤቱ መዝገቡን በመመርመር በሰጠው ፍርድ ከሳሽ ክሱን ለማስረዲት ያቀረባቸው ማስረጃዎች ሁለም በከሳሽ የተጻፈ ናቸው።
እነዚህ ማስረጃዎች ደግሞ እንደ ማስረጃ ሆነው የሚቀርቡት በራሱ በከሳሽ እንጂ በተከሳሽ ላይ አይደለም። ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ግዳታ ስለመኖሩ በማንኛውም ማስረጃ በበቂ ሁኔታ ማስረዲት ይጠበቅበታል። በመሆኑም ከሳሽ በመካከላቸው አስገዲጅ ውል መኖሩን ባላስረዲበት እንደውለ እንዱፈጸምለት ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም ብሎል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋ/ከ/ፍ/ቤት በበኩለ መልስ ሰጪን መጥራት ሳያስፈልግ የይግባኝ ባይን የይግባኝ መዝገብ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/337 መሰረት በመዝጋት ይግባኝ ባዩን አሰናብቷል።
የአሁኑ የሰበር አመልካችም በመ/ደ/ፍ/ቤት ፍርድም ሆነ በከ/ፍ/ቤት ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሰው ቅሬታ የህትመት ስራ ውል በቃል ጭምር ማድረግ የሚቻል ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤቶች በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሉያስገድዲቸው የሚችል የጽሁፍ ውል የለም ሲለ ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው ያለአግባብ ነው የሚል ነው።
በሰበር ደረጃም የተጠሪው ወራሾች ቀርበው መልስ እንዱሰጡ የፍ/ቤቱ መጥሪያ የደረሳቸው ቢሆንም ቀርበው መልስ ባለመስጠታቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
አመልካች ያቀረበው ክርክርና በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ፍርድ ከዚህ በላይ የተገለጸ ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶች በአመልካችና በስር ተከሳሽ መካከል አስገዲጅ ውል ስለመኖሩ አመልካች ያቀረበው ማስረጃ የለም ሲለ ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች ለስር የመ/ደ/ፍ/ቤት ውለ ስለመኖሩ በማስረጃነት ያቀረባቸው የጽሁፍ ሰነድች ቅድመ ክፍያና ተጨማሪ ክፍያ ከተከሳሽ የተቀበላቸውን ደረሰኞችና አመልካች ለተከሳሽ የጻፈውን የዋጋ ማቅረቢያ ነው። ከእነዚህ ሰነድች በስተቀር ውለ በጽሁፍ የተደረገ ስለመሆኑ ያቀረበው የጽሁፍ ማስረጃ የለም። በፅሁፍ የተደረገውን ውል አለማቅረብ ደግሞ በውል ሰጪና ውል ተቀባይ መካከል ውል የለም ወደሚለው ድምዲሜ የሚያደርስ አይሆንም። ምክንያቱም በፍ/ህ/ቁ/1681(1) እንደተደነገገው ውል በቃል ወይም በጽሁፍ ወይም በተለመደ ጠቅላላ ምልክቶች ወይም ለውለ መነሻ ከሆነው ምክንያት የተነሳ ግዳታ መግባት መፍቀድን በማያጠራጥር አሰራር በማስታወቅ ጭምር መግባት ስለሚቻል ነው። ይህ ሲባል ግን ሁለም የውል ዓይነቶች በቃል ወይም በተለመደ ጠቅላላ ምልክቶች ወይም ግዳታ ለመግባት መፍቀድን በማያጠራጥር አሰራር በማስታወቅ ይደረጋለ ማለት አይደለም። ለዚህም የ/ፍ/ህ/ቁ/1725ን መመልከት ተገቢነት አለው።
በዚህ በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት ለብዙ ጊዜ የሚቆዩ ውልች፤ እንዱሁም የዋስትና ውልች፤
የኢንሹራንስ ውልች እና ህጉ በግልጽ በጽሁፍ እንዱደረጉ የሚያስገድዲቸው የውል ዓይነቶች ሁለ በጽሁፍ መደረግ አለባቸው።
ይህንኑ የህግ አነጋገር ይዘን ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ከስር ተከሳሽ ጋር ገብተናል በሚለው የህትመት ስራ ውል ውለ በፅሁፍ እንዱሆን የሚያስገድድ የህግ ድንጋጌ የለም።
አመልካች ከስር ተከሳሽ ጋር ገብተናል የሚለው ውልም በገቡት ውል መሰረት 300 ቅጂ መጽሀፍችን አባዝቶ ከመስጠት ያለፈና ለረጅም ጊዜ ይቆያል ተብል የማይገመት በመሆኑ የውለ በጽሁፍ መሆን የግድ የሚያስፈልግ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ የስር ፍ/ቤቶች አመልካች ያቀረባቸውን አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በመመርመር እንዱሁም በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/264(2) እንደተደነገገው ውለ ከዚህ በላይ በተጠቀሱ መንገድች የተደረገ መሆን ስላለመሆኑ፣ በውል ሰጪና ውል ተቀባይ መካከል አለ ስለተባለው የውል ግንኙነት አመልካች ባቆይቆጠራቸውም እንኳን ምስክሮችን መስማት ጠቃሚ መስል ከታየ አስቀርቦ መስማት በጉዲዩ ላይ ፍርድ ለመስጠት የሚያስችለ ፍሬ ነገሮችን በአግባቡ አጣርተው ተገቢውን ፍርድ መስጠት ሲገባቸው ይሄንኑ በማለፍ አመልካች አስገዲጅ ውል መኖሩን አላስረዲም በሚል ክሱን ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ባለመሆኑ የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመዝገብ በቀን 26/08/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ እንዱሁም የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመዝገብ በቀን 23/10/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 348(1) መሰረት ሽረናል።
አመልካች ከስር ተከሳሽ ጋር አድርገናል በሚለው የህትመት ውል መሰረት ፍስሐና ስራው የሚል 300 ቅጂ መጽሐፍችን ማዘጋጀቱንና አለማዘጋጀቱን የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 272 መሰረት ምትክ ዲኛ እስከ ቦታው ድረስ በመላክ ምትክ ዲኛው ተገቢውን ምርመራ አድርገው በሚያቀርቡት የምርመራ ውጤት መሰረት የበኩለን ፍርድ በጉዲዩ ላይ እንዱሰጥ ክርክሩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/343 (1) መሰረት መልሰናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ አመልካች የራሱን ይቻል ብለናል።