No summary available.
ጥር 01 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አንዲርጌ እምሩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ቴላቭዥን ከነሲዱው ተጠሪ እገዛልሃለሁ በማለት ተቀብላኝ ዕቃውም ተገዝቶ ያልቀረበ ከመሆኑም በላይ ገንዘቡም አልተከፈለኝም በሚል የቀረበ ክስ ሲሆን የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበላ 10/11/12 ማህበራዊ ፍርድ ቤት በአሁኑ አመልካች ከሳሽነት ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ ተከሳሽ መስከረም 17 ቀን 2001 ዓ.ም. በከሳሽ ቤት መጥተው አንድ ባለ 21 ኢንች ሶኒ ቴላቪዥን ከነሲዱው ቀረጡን ጨምሮ በብር 4750(አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ) ገዝቼ አመጣልሃለሁ ብለውኝ በምስክሮች ፉት ገንዘቡን ቆጥሬ ሰጥቼያቸው ቴላቪዥኑን ያላስረከቡኝ ሲሆን ገንዘቡም እንዱሰጠኝ ብጠይቃቸው ወይም ዕቃውን እንዱያስረክቡኝ ብጠይቃቸው ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ዕቃውን እንዱያስረክቡኝ ወይም ገንዘቡን እንዱመልሱልኝ እንደዚሁም በክሱ ምክንያት የወጣውን ወጪና ኪሳራ ጭምር እንዱከፍለኝ እንዱወሰንልኝ የሚል ነው። በቀረበው ክስ ላይ ተከሳሽ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዙት መሰረት መጥሪያ ተልኮላቸው ለመቀበል ፍቃደኛ ያለመሆናቸውን ከሳሽ በቃለ መሒላ ማረጋገጣቸውን በማመልከቱ ጉዲዩ ተከሳሽ በላለበት እንዱታይ ትእዛዝ ተሰጥቶ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በመመርመር ፍርድ ሰጥቷል። የሰጠውም የፍርድ ይዘት ተከሳሽ በቀረበው ክስ ላይ ቀርበው መልስ ያለመስጠታቸው የቀረበውን ክስ እንዲመኑ ስለሚቆጠር ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከወጪና ኪሳራ ጭምር እንዱከፍለ በማለት በአሁኑ ተጠሪ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በቀጥታ ይግባኛቸውን ለከተማው አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የቀረበውን ቅሬታ ከመረመረ በኋላ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 337 መሰረት አጽንቷል። በዚህ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ቅሬታቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የሰበር ሰሚ ችልት የአሁን ተጠሪ ያቀረቡ ሲሆን ችልቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በፍትሐ ብሓር ህግ ቁ. 2472(1)(2) መሰረት ከብር 500 (ብር አምስት መቶ) በላይ የሆነ ብድር በጽሐፍ፣ በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም ቃለ-መሒላ ካልሆነ በስተቀር በሰው ምስክር ማስረዲት እንደማይቻል፤ በተመሳሳይም ከብር 500 በላይ ከፍያለሁ በማለት የሚቀርበው ክርክር ይሄው ድንጋጌ ተፈጻሚነት ያለው መሆኑን በማመላከት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪን ከቀረበባቸው ክስ በነጻ በማሰናበት በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩም ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር በጽሐፍ ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ አመልካች ቴላቪዥን እና ሲዱ ገዝተው እንዱያመጡላቸው ለተጠሪ የሰጡትን ብር 4750 (አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር) በሰነድ እንጂ በሰው ማስረጃ ማረጋገጥ አይቻልም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል የነበረ በመሆኑ ጉዲዩን ከዚሁ አኳያ ተመርምሮ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት ጉዲዩን ስንመረምር የአሁን ተጠሪ በክሱ እንደተመለከተው ገንዘቡን የተቀበለት ቴላቪዢን እና ሲዱ ገዝቼ አመጣልሃለሁ በማለት እንጂ በብድር ምክንያት ያለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተመሳሳይም ተፈጻሚነት ያለው ከዚሁ ብድር ጋር በተያያዘ መልሼ ከፍያለው የሚል ተከራካሪን የሚመለከት እንጂ በዚህ ጉዲይ ላይ በግራ ቀኙ መካከል ብድርን መሰረት ያደረገ ክርክር በላለበት ሁኔታ የፍትሐብሕር ህግ ቁ.2472 ን በመጥቀስ ከብር 500 በላይ የሆነን የገንዘብ መጠን በሰው ምስክር ማስረዲት አይቻልም ወደ ሚለው መደምደሚያ መድረሱ አግባብነት የላለው እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በዚህ ነጥብ ላይ በአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት አነስተኛ ድምጽ አስቀምጦት የነበረው ሃሳብ አግባብነት የነበረው ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት ተጠሪ መጥሪያ ለመቀበል ፍቃደኛ ያለመሆናቸው ተገልጾ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ በመስጠቱ የቀረበውን ክስ ከሳሽ በቆጠረው ምስክር ተከሳሽ ባይቀርቡም በመስማት እና ጉዲዩን በማጣራት ውሳኔ መሰጠት ሲገባው የተጠሪ ያለመቅረብ ጉዲዩን እንዲመኑ የሚያስቆጥር ባለመሆኑ ክሱን እንዲመኑት ይቆጠራል በማለት ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የላለው እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
ባጠቃላይ በግራ ቀኙ መካከል አከራካሪ የሆነው ጉዲይ ቴላቪዢን እና ሲዱ ለመግዛት ተጠሪ 500 ብር የተቀበለ መሆኑን እንጂ የብድር ገንዘብ ስለመሆኑ ባልተነሳበት ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የላለውን የብድር ውል እና ክፍያ የተመለከተን ድንጋጌ በመጥቀስ ከብር 500 (ብር አምስት መቶ) በላይ በሰው ምስክር ማስረዲት አይቻልም በማለት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የሰበር ሰሚው ችልት በአብላጫ ድምጽ የደረሰበት መደምደሚያ እንደዚሁም ጉዲዩን በመጀመሪያ ተመልክተው የቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ተጠሪ ቀርበው መልስ ያለመስጠታቸው ወይም ጉዲዩ በላለበት በመታየት ክሱን እንደማመን ይቆጠራል በማለት የሰጠውም ውሳኔ በተመሳሳይ አግባብነት የላለው እና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የሰበር ሰሚ ችልት በመዝ.ቁ.14696 በቀን 07-04-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት፣የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ በፍርድ ቤት በመዝ.ቁ.04417 ህዲር 07 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የአዱስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበላ 10/11/12 ማህበራዊ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ.016/03 መስከረም 27 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽሯል።
የተከሳሽ በአንድ ክስ ላይ ቀርቦ ያለመከራከር ወይም የጉዲዩ ተከሳሽ በላለበት መታየት የቀረበው ክስ ክሱን ሉያስረደልኝ ይችላለ በማለት ከሳሽ በክሳቸው በመዘርዘር ያቀረቡትን ምስክሮች ብቻ በመስማት እና ተገቢዉን ማጣራት በማድረግ ውሳኔ ከሚሰጥ ውጪ የተከሳሽ ያለመቅረብ ጉዲዩን እንዲመኑት ይቆጠራል በማለት በክሱ መሰረት ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ የለም ብለናል። በመሆኑም አመልካች በክሱ ላይ የቆጠራቸው ምስክሮች ተሰምተው እና ለፍትህ አሰጣጡ አስፈላጊ ናቸው ብል የማህበራዊ ፍርድ ቤቱ ያመነባቸውን ማስረጃዎች በመቀበል ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።