No summary available.
ጥር 3 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ መጋቢት 12 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልካቾች በጋራ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የሆቴል ንግድ ድርጅትና የሕንፃ ሽያጭ ውልን የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ አመልካቾች ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. የሴንትራል ቬንዩ ሆቴልን ከነመገልገያ ዕቃዎቹና ህንፃው ልንሸጥላቸው በፅሐፍ ውል ተዋውለናል። አንደኛ ተጠሪ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ቀብድ ከከፈለ በኋላ ቀሪውን ግዳታውን እንዱወጣ በሰጠነው ማስጠንቀቂያ መሰረት ግዳታውን ባለመወጣቱ ውለን ሰርዘነዋል። ስለዚህ ሆቴለን ከነመገልገያ ዕቃዎቹ እንዱያስረክበን፣ በውለ መሰረት ብር 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ መቀጫ እንዱከፍለን፣ የሆቴለን ስም በመቀየር ላደረሰው ጉዲት ክስ የማቅረብ መብታችን እንዱጠበቅልን በማለት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው።
በክርክሩ አራተኛ አመልካችና ሁለተኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ተከራካሪዎች ሆነው ገብተዋል። ተከሳሽ /አንደኛ ተጠሪ/ እና ሁለተኛ ተጠሪ የሽያጭ ውለ አለመፈፀም በኃላፉነት የሚጠየቁት ከሳሾች ናቸው። እኛ በውለ በገባነው ግዳታ መሰረት ብር 6,450,000 /ስድስት ሚሉዮን አራት መቶ ሀምሣ ሺህ ብር/ ዕዲ ከፍለናል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ውለ ፈራሽ ነው በማለት ወስኖ ተጠሪዎች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶቷል። ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የተጠሪዎችና የአመልካቾችን ክርክር በሰበር መዝገብ ከሰማ በኋላ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ ሐምል 26 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ይግባኝ ሰሚው ችልት፣
የሥር ከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ ሸዋወንድም ተስፊዬ /ሁለተኛ አመልካች/ እና አቶ ዲዊት ከበደ /ሶስተኛው አመልካች/ ውለን በተናጠል ሰርዘነዋል በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም?
የውለ መሰረዝ በፍርድ ቤት ሉወሰን የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
የሥር ጣልቃ ገብ የነበረችው ወ/ሮ ነጠረች ከበደ /አራተኛ አመልካች/ ውለ እንዱፈረስ ለመጠየቅ ይችላለ ወይስ አይችለም? ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ መብት አላቸው ወይስ የላቸውም? መብት አላቸው ከተባለ መብታቸው በምን ሁኔታ መከበር አለበት የሚለትንና ላልች ከውል መሰረዝ ጥያቄ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ተጨማሪ ነጥቦች በመመልከት ውሣኔ ይሰጥበት በማለት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መልሶታል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰበር ችልቱ በሰበር መዝገብ ጥር 7 ቀን 2001 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ በመሰረታቸው ጭብጦችና ላልች ተያያዥነት ባላቸው ነጥቦች ላይ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን እንዱያቀርቡ ካደረገ በኋላ የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካቾች ውለን በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለበት ሁኔታ የለም በማለት ወስኗል።
በሁለተኛው ጭብጥ አመልካቾች ውለን በፍርድ ቤት ውሣኔ ለማሰረዝ የሚያስችል ምክንያት ያለ ስለመሆኑ በፍሬ ጉዲዩ ደረጃ አላስረደም ውለ ያልተፈፀመው በአመልካቾች ቀሪ ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው ባለመሆኑ ሻጮች /አመልካቾች/ ውለን በፍርድ ለማስረከብ የሚያስችል የሕግም ሆነ የፍሬ ጉዲይ መሰረት የላቸውም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። ሶስተኛውን ጭብጥ በተመለከተ አራተኛ አመልካች የሟች ወራሽ መሆናቸው የተረጋገጠው ንብረቱ በውል ከተላለፈ በኋላ በመሆኑ ድርሻዋን ከሻጮች ከምትጠይቅ በቀር ውለ እንዱፈርስ ለመጠየቅ አትችልም ውለ እንዱፈርስ የመጠየቅ መብት አላት ቢባል እንኳን ተዋዋዮቹን ወደ ነበሩበት መመለስ አይቻልም በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 26 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ ሙለ በሙለ ሽሮታል።
አመልካቾች በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት መጋቢት 17 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ነው። አመልካቾች ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች አንደኛው ተጠሪ በውለ መሰረት ግዳታውን እንዱወጣና ቀሪውን ክፍያ እንዱከፍለ መስከረም 27 ቀን 1998 ማስጠንቀቂያ የሰጡት ቢሆንም ተጠሪ ግዳታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ውለን በተናጠል ሰርዘውታል። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካቾች ውለን በተናጠል ለመሰረዝ የሚያስችላቸው ሁኔታ የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። አንደኛ ተጠሪ የሆቴል ድርጅቱን ህንፃውን በሆቴለ ላይ ካለው ዕዲና የሰራተኛ ዕዲ ጭምር ገዝቷል። ገዥ ለሻጮች ብር 1,000,000 /አንድ ሚሉዮን ብር/ ለመክፈል ከተስማማ በኋላ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ቀብድ ከፍል ቀሪውን ሰማኒያ ፏርሰንት ክፍያ ያልፈፀመና ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑና በእኛ በኩል ይግባኝ ሰሚው ችልት ውለን በፍርድ ቤት ውሣኔ ለመሰረዝ የሚያበቃ ሁኔታ የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1983/1/ ድንጋጌዎችን ያላገናዘበና በሰበር ሉታረም የሚገባው ነው።
አራተኛ አመልካችን በተመለከተ አከራካሪው ንብረት ያልተከፊፈለ የውርስ ንብረት ባለበት ሁኔታ ያለ አራተኛ አመልካች ፈቃድና ስምምነት ንብረቱን ለላላ ሰው ለማስተላለፍ እንደማይችል በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1060 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1266 ተደንግጎ እያለና፣ አራተኛ አመልካች የሟች ወራሽ ናቸው ተብለው የሚያዙት ሟች ህይወት ካለፈበት ቀን ጀምሮ መሆን ሲገባው የሽያጭ ውለ እንዱፈርስ መጠየቅ አትችልም ተብል መወሰኑ የሕግ ስህተት አለበት።
ከዚህ በተጨማሪ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውለን አፍርሶ ተዋዋዮቹን ወደ ነበሩበት ለመመለስ አይቻልም በማለት የሰጠው የሕግ ትርጉምና ምክንያት ስህተት ያለበት ነው። በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ኀዲር 30 ቀን 2003 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። አመልካቾች ውለን በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለ ስለመሆኑ በሸያጭ ውለ በግልፅ አልተመለከተም። ገዥ ቀሪውን ብር 800,000 /ስምንት መቶ ሺህ ብር/ ለመክፈል የውል ግዳታ የገባው የንብረቱ ስመ ሀብት ወደ ገዥ ሲዛወር መሆኑ በውለ ተመልክቷል። ስለሆነም አመልካቾች በጠየቅነው ጊዜ ቀሪውን ዋጋ ስላልከፈለን ውለን ሰርዘናል በማለት ያቀረቡት ክርክር የሕግ መሰረት የለውም።
አመልካቾች ኀዲር 23 ቀን 1998 ዓ.ም ለሰጡት ማስጠንቀቂያ ተጠሪዎች ኀዲር 26 ቀን 1998 ዓ.ም በፅሐፍ መልስ ሰጥተዋል። ስለዚህ አመልካቾች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሕግ መሰረት የለውም ይባልልን። የሆቴል ድርጅቱ ሽያጭ ውል በፍርድ ቤት ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባዋል በማለት አመልካቾች የሚከራከሩት ተጠሪዎች መሰረታዊ የሆነ የውል መጣስ ተግባር ፈፅመዋል በማለት ነው። አመልካቾች ገዥ የሽያጩን ሰማኒያ ፏርሰንት ዋጋ አልከፈለም በማለት የሚከራከሩት ገዥ በሁለት ባንኮች ይፈለግ የነበረውን ስምንት ሚሉዮን ብር /ብር 8,000,000/ ዕዲ የከፈለ መሆኑንና ላልች የውሀ፣ የመብራት፣ የስልክና የመሳሰለት ውዝፍ ዕዲዎች በመክፈል በውለ የገባውን ኃላፉነት የተወጣ መሆኑን ወደ ጎን በመተው ነው። ተጠሪዎች የውል ግዳታቸውን ከዘጠና ፏርሰንት በላይ የተወጡ ሲሆን አመልካቾች የሰጡትን ውክልና በመሻር የንብረቱ ስመ-ሀብት ወደ ገዥ እንዲይዘወር እንቅፊት በመፍጠር ኃላፉዎች ናቸው።
ሟች አቶ ከበደ ጠቅላላ ንብረታቸውን ለሁለተኛ አመልካችና ለሶስተኛ አመልካች በኑዛዜ ሰጥተው የሁለተኛ አመልካችና ሶስተኛው አመልካች የሟች የኑዛዜ ወራሾች መሆናቸው በመዝገብ ቁጥር 1262/90 ኀዲር 2 ቀን 1999 ዓ.ም በፍርድ ቤት ተወስኗል። አራተኛ አመልካች የፍርድ መቃወሚያ በማቅረብ የሁለተኛና የሶስተኛ አመልካቾች የኑዛዜ ወራሽነት አላሰረዙም። ተጠሪዎች የግዥ ውል የፈፀሙት ሁለተኛ አመልካችና ሶስተኛ አመልካች የሟች ወራሽ መሆናቸውን በማረጋገጥ በፍርድ ቤት የተሰጠውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው። አራተኛ አመልካች የሟች ወራሽ መሆናቸውን አረጋግጠው ያቀረቡት ሟች ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ከስምንት ዓመት በኋላ ሲሆን በክርክሩ ሂደት ንብረቱ ላይ የሰጡት የእግድ ትእዛዝ የለም። ስለዚህ አራተኛ አመልካች ቀደም ብል በፍርድ ቤት በተሰጣቸው ማስረጃ መሰረት ሁለተኛ አመልካችና ሶስተኛ አመልካች የፈፀሙትን የሽያጭ ውል እንዱሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለበት የሕግ መሰረት የለም።
ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በማፅናት እንዱያሰናብተን በማለት ተከራክረዋል። አመልካቾች ታህሳስ 26 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል። የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው፡-
ተጠሪዎች ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው ውል መሰረት ግዳታቸውን እንዱፈፅሙ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናቸው ግዳታቸውን ያልፈፀሙ በመሆኑ ውለን በተናጠል ሰርዘነዋል በማለት አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር ይግባኝ ሰሚው ችልት ውድቅ ያደረገው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የመጀመሪያው ጭብጥ የሚታላለፍ ቢሆን፣
ተጠሪዎች መሰረታዊ የውል መጣስ ተግባር የፈፀሙ በመሆኑ ውለ በፍርድ ቤት ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባዋል በማለት አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሕግ ድጋፍ የለውም በማለት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
አራተኛ አመልካች ሟች ወ/ሪት ነጠረች ከበደን በመተካት በሰበር ተከራካሪ የሆኑት ወ/ሮ አሰገደች አበበ ከተጠሪዎች ጋር ሰኔ 13 ቀን 2003 ዓ.ም ያደረጉት የዕርቅ ስምምነት ተመዝግቦ ሕጋዊ ውጤት ሉሰጠው ይገባል ወይስ አይገባም?
አራተኛ አመልካች የነበሩት ወ/ሪት አበራች ከበደ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የእኔ የጋራ ሀብት የሆነውን የንግድ ድርጅትና ህንፃውን ለአንደኛ ተጠሪ ለመሸጥ የተዋዋለት ውል እኔ ያልተስማማሁበት በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል በማለት ያቀረበችውን ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ሳይቀበለው መቅረቱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለትን ጭብጦች ይግባኝ ሰሚው ችልት ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ካረጋገጣቸው ፍሬ ጉዲዮችና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በመመርመር ውሣኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የመጀመሪያው ጭብጥ ይህ የሰበር ችልት ጉዲዩን ለይግባኝ ሰሚው ችልት በሰበር መዝገብ ሲመልስ ይግባኝ ሰሚው ችልት አጣርቶ ውሣኔ እንዱሰጥባቸው ከመሰረታቸው ጭብጦች አንደኛውና የመጀመሪያው ነው። ይግባኝ ሰሚው ችልት ይህንን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር ውሣኔ ሰጥቶበታል። አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ አመልካቾች ተጠሪዎች ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገው የንግድ ድርጅትና የሕንፃ ሸያጭ ውል በገቡት ግዳታ መሰረት ቀሪውን ክፍያ ብር 800,000 /ስምንት መቶ ሺህ ብር/ በአእምሮ ግምት በቂ ነው ባልነው በአስር ቀን ውስጥ እንዱፈፅሙ መስከረም 27 ቀን 1998 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ ሰጥተናቸዋል። ተጠሪዎች በውለ መሰረት ክፍያ ያልፈፀሙ በመሆኑ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ውለን በተናጠል የሰረዝነው መሆኑንና ይህንም በፍታብሓር ህግ የተደነገገ መሆኑን በማንሣት ያቀረበውን ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገው አላግባብ ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል። ተጠሪዎች በበኩላቸው አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች በውል በገቡት ግዳታ መሰረት የሸጡትን የንግድ ድርጅትና ህንፃ ስመ ሃብት ወደ ገዥዎች እንዱዛወር ተገቢውን ተግባር አልፈፀሙም። ለውለ አለመፈፀም በኃላፉነት የሚጠየቁት አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች በመሆናቸው ውለን በተናጠል የመሰረዝ መብት የላቸውም በማለት ተከራክረዋል።
በመርህ ደረጃ በሕግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ በመሆናቸው ተዋዋይ ወገኖች በውል የገቡትን ግዳታ የመፈፀም ግዳታ አለባቸው። ተዋዋይ ወገኖች በሕግ አግባብ ያቋቋሟቸው ውልች ተገዥ የመሆንና ግዳታቸውን በታማኝነት የመፈፀም ኃላፉነት ያለባቸው በመሆኑ ህጉ ተዋዋይ ወገኖች በህግ መሰረት ያደረጉትን ውል አንደኛው ወገን በፈለገው ጊዜ የፈለገውን ምክንያት እየሰጠ ውለታውን እንዱሰረዝ የሚፈቅድ አይደለም። ይህም በመሆኑ በህግ አግባብነት የተቋቋመን ውል አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በሕግ በግልፅ ከተመለከቱ ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ አንድ ውልን ለመሰረዝ የሚያስችል ልዩ ሁኔታ መሟላቱን በማረጋገጥ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በህግ የተደነገገው ውልን ለመሰረዝ በሚያስችል ልዩ ምክንያት ውለን የሰረዘ መሆኑን የማስረዲት ግዳታ ያለበት ውለን በተናጠል ሰርዠዋለሁ የሚለው ተዋዋይ ወገን ነው።
በአገራችን አንደኛው ተዋዋይ ወገን ውለን በተናጠል ሉሰርዝ የሚችልባቸው ሁኔታዎች በፍታብሓር ሕግ ውልን ስላለመፈፀም በሚደነግገው ክፍል ተዘርዝረዋል። ስለሆነም በአገራችን አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውል ሉሰርዝ የሚችለው ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1786 እስከ ፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1789 ከተዘረዘሩት ምክንያቶች አንደኛው ተሟልቶ ሲገኝ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1786 እስከ ፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1789 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተከታታይነትና ተያያዥነት ያላቸውና አንደኛው ተዋዋይ በተናጠል ውልን ሉሰርዝ ስለሚችልባቸው ሁኔታዎች የሚደነግጉ መሆኑን የድንጋጌዎቹን አቀራረፅና ህግ አውጭው ለድንጋጌዎቹ የሰጠውን ተከታታይነት ያላቸው ተራ ቁጥሮች በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። በመጀመሪያ “በአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ የውል ማፍረስ” የሚል ጠቅላላ ርዕስ የተሰጠው
“ቁርጠኛ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ” የሚል ርዕስ ያለው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1787 ዝርዝር ይዘት ስንመለከተው “በውለ ላይ አንድ ግዳታ መፈፀሚያ ሆኖ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ፤
ወይም ማስጠንቀቂያ በተሰጠበት ጊዜ በአእምሮ ግምት ይበቃል ተበል በተሰጠው ቀን ወይም በዲኛ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ከተዋዋይ አንደኛው ወገን የገባው ግዳታ ሳይፈፀም የቀረ እንደሆነ ውለ ይፍረስልኝ የሚለው ወገን ይህ ከዚህ በላይ የተነገረው የማፍረስ መብት አለው” የሚል ይዘት ያለው ነው። የዚህ ድንጋጌ የእንግሉዘኛው ቅጅ “A party may cancel the contract where the other party has failed to perform his obligation with in the period of time fixed in accordance with art 1770, 1774 or 1775 (b) “ በሚል መንገድ ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ የአማርኛና የእንግሉዝኛ ቅጅ ለመረዲት እንደሚቻለው አንደኛው ተዋዋይ ወገን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ውልን በተናጠል ለመሰረዝ የሚቻለው ከሚከተለት ሶስት ሁኔታዎች አንደኛው የተሟላ መሆኑን ለማስረዲት ሲችል ነው።
የመጀመሪያ ባለዕዲው በውለ ላይ በተመለከተው መሰረት የውለን ግዳታ የሚፈፀምበት ቁርጠኛ ጊዜ በውለ ላይ በግልፅ ተመልክቶ እንደሆነና በውለ ላይ የተገለፀው ቁርጥ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው። በዚህ ሁኔታ አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውለን ለመሰረዝ የሚችል መሆኑን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1775(ለ) ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። ሁለተኛው ምክንያት ባለዕዲው ውለን ያልፈፀመበትን ምክንያትና ላልች የአካባቢ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዳኞች ባለዕዲው ውለን የሚፈፅምበት የችሮታ ጊዜ ከሰጡት በኋላ ባለእዲው በዲኛ ወሣኔ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዳታውን ሣይፈጽም የቀረ እንደሆነ መሆኑን ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 እና ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1770 ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል።
ሶስተኛውና አመልካቾች መከራከሪያ ያደረጉት ባለገንዘቡ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1774 በተደነገገው መሰረት ላላኛው ተዋዋይ (ባለዕዲው) በውል የገባውን ግዳታ የሚፈፅምበትን ጊዜ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆንና በማስጠንቀቂያው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈፅም ሲቀር መሆኑን ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1774 እና ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አንደኛው ተዋዋይ ላላው ወገን በውል የገባውን ግዳታ እንዱፈፅም በአእምሮ ግምት በቂ ነው የሚለውን የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ ለመስጠትና በማስጠንቀቂያው የተገለፀው የውል መፈፀሚያ ሲያልፍ ውለን በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው እሱ በበኩለ ምን ምን ተግባራትን ፈፅሞ ነው? የሚለው ነው።
አንደኛው ተዋዋይ ወገን ላላኛው ተዋዋይ ወገን በውለ መሰረት እንዱፈፅም ለመጠየቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የሚችለው በመጀመሪያ እሱ የበኩለን ግዳታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የተዘጋጀ ሲሆን እንደሆነ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1857 በግልፅ ይደነግጋል። ስለሆነም ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ መሰረታዊ ዓላማና ግብ እንደዚሁም የድንጋጌው የተፈፃሚነት ወሰን ለመረዲት የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1771 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር መመርመር ያስፈልጋል። ከዚህ አንፃር ስንመዝነው አንደኛው ተዋዋይ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1771 ንዐስ አንቀጽ 1 ላላኛው ተዋዋይ ውለን እንዱፈፅምለት ለመጠየቅ፤ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1774 ድንጋጌዎች መሰረት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና በፍታብሓር ቁጥር 1787፣ በተደነገገው መሰረት ውለን በተናጠል ለመሰረዝ በመጀመሪያ በእሱ በኩል በውል የተጣለበትን ግዳታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ በማስረጃ ለማረጋገጥ የቻለ መሆን እንዲለበት የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎችን ይዘትና መሰረታዊ ግብ በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። ሕግ አውጭው በውል ለገባው ግዳታ ተገዥ በመሆን በእሱ በኩል ያለውን ግዳታ ያልፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያልቻለ አንድ ተዋዋይ ወገን ላላኛውን ተዋዋይ ወገን ቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለን በተናጠል እንዱሰርዝ በማሰብ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን አውጇል ተብል አይገመትም። አንድ ተዋዋይ የውለን መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ በመግለጽ ለላላኛው ወገን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውል በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በመጀመሪያ እሱ በውለ የገባውን ግዳታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው። በያዝነው ጉዲይ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ከተጠሪዎች ጋር ባደረጉት የንግድ ድርጅትና የህንፃ ሽያጭ ውል መሰረት የበኩላቸውን ግዳታ አሟልተው ያልፈፀሙ መሆኑንና በተቃራኒው ውለ እንዲይፈፀም የተለያየ ችግሮችን የፈጠሩ መሆኑን ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያለው ይግባኝ ሰሚው ችልት በማረጋገጥ በውሣኔው አስፍሯል።
በመሆኑም አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች በውለ የገቡትን ግዳታ አሟልተው ያልፈፀሙና ውለ በአግባቡ እንዲይፈፀም የተለያዩ ችግሮችን የፈጠሩ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ፣ ተጠሪዎች በአስር ቀን ውስጥ በውለ መሰረት ግዳታቸውን እንዱፈፀሙ ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ግዳታቸውን ያልተወጡ በመሆኑ ውለን በተናጠል ሰርዘነዋል በማለት ያቀረቡት ክርክር የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያልተከተለና የህግ መሰረት የላለው ነው። ስለዚህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ውለን በተናጠል የሚሰርዘበት የሕግና የፍሬ ጉዲይ ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1784 በይዘቱ ፈቃጅ የሆነ የህግ ድንጋጌ በመሆኑ ዳኞች ውለ እንዱፈርስ ሣይወስኑ ሉያልፈ የሚችለ መሆኑንም የሚያመለክት ድንጋጌ ነው።
በአንፃሩ ዳኞች በአንደኛው ወገን ጠያቂነት ውል እንዱሰረዝ ውሣኔ ከመስጠታቸው በፉት የተዋዋዩቹን ጥቅምና ለቅን ልቦና የሚያስፈልገውን ነገር መሰረት ማድረግ እንደሚገባቸው በውለ ላይ አይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ካልተደረገ በስተቀር ዳኞች ውለ እንዱሰረዝ ውሣኔ መስጠት እንደላለባቸው የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 አስገዲጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋለ። አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካች ውለ በፍርድ ቤት ውሣኔ ሉሰረዝ ይገባዋል በማለት የሚከራከሩት ተጠሪዎች መሰረታዊ የሆነ የውል መጣስ ተግባር ፈፅመዋል በማለት ምክንያት በመሆኑ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ከአንደኛ ተጠሪ ጋር በተዋዋለት ውል የተጠሪዎች ግዳታና ኃላፉነት ምንድን ነው? ተጠሪዎች በውለ የገቡት ግዳታ ምን ያህል ፏርሰንቱን ፈፅመው ምን ያህል ፏርሰንት ይቀራቸዋል? ተጠሪዎች ቀሪውን ግዳታቸውን ያልፈፀሙበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚለት ነጥቦች ይግባኝ ሰሚው ችልት ከደረሰበት መደምደሚያና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝበናል።
በመርህ ደረጃ ተዋዋዮች ውል የመዋዋል ነፃነት አላቸው። ሕግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች በስተቀር ተዋዋዮች ሁለ የሚዋዋለበትን ጉዲይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት አላቸው በማለት የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1711 በግልፅ ይደነግጋል። ከዚህ በተጨማሪ ተዋዋዮች ለሚዋዋለት ሰው በአንድ ነገር ላይ ያላቸውን መብት ለመስጠት ወይም አንድ ነገር ለማድረግ ወይም ላለማድረግ ሉዋዋለ እንደሚችለና ውልች አስገዲጅነታቸው በውለ በተነገረው ጉዲይ ብቻ ሣይሆን ልማድ፤ ፍትሕ፣ ቅን ልቦና የውለታው ዓይነት የሚያስከትሎቸውን ነገሮች ጭምር እንደሆነ ከፍታብሓር ቁጥር 1712 እና ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1713 ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል። አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾችና ተጠሪዎች ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም.በተደረገው ውል ያለባቸውን ግዳታና ኃላፉነት ከላይ የተጠቀሱን የህግ ድንጌጋዎች መሰረት በማድረግ መመርመር ተገቢ ነው።
በውለ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የሆቴል ንግድ ድርጅት ህንፃውንና በድርጅቱ ውስጥ ያለትን የመገልገያ እቃዎች ላይ የነበራቸው የባለሀብትነት መብት ለአንደኛ ተጠሪ ለማስተላለፍ የተስማሙ መሆኑና አንደኛ ተጠሪ በበኩለ በንግድ ድርጅቱና በህንፃው ላይ ያለውን ዕዲ ለባለመብቶች ለመክፈልና ለሻጮች ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ /አንድ ሚሉዮን ብር/ ለመክፈል የተስማማ መሆኑን ግራ ቀኙ ያልተካካደበትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በውሣኔው ያረጋገጠው ነጥብ ነው። ተጠሪዎች በውለ ሁለት መሰረታዊ ግዳታዎች ተጥልባቸዋል። የመጀመሪያው በንግድ ድርጅቱና በህንፃው ላይ ያለ የባንክ ዕዲ እና ላልች ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዲዎችን መክፈል ሲሆን ሁለተኛው ለሻጮች ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ /አንድ ሚሉዮን ብር/ መክፈል ነው። ተጠሪዎች ለሁለተኛና ሶስተኛ አመልካች ብር 2ዐዐ,ዐዐዐ /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የከፈለ መሆኑ ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪዎች የዕዲው መጠን በውለ ላይ ያልተገለፀ ቢሆንም ከብር 6,45ዐ,ዐዐዐ /ስድስት ሚሉዮን አራት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ በላይ የንግድ ድርጅቱንና የህንፃውን የባንክ ዕዲ፣ ላልች የውሃ፣ የመብራት የስልክና ላልች ውዝፍ ዕዲዎች የከፈለ መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ችልት ፍሬ ጉዲይ ማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣኑን መሰረት በማድረግ አረጋግጦ በውሣኔው በግልፅ አስፍሮታል።
ይህም ተጠሪዎች በውል ከገቡት ግዳታ ከሰማኒያ አምስት ፏርሰንት በላይ የፈፀሙ መሆኑን የሚያሣይ ነው። ተጠሪዎች በውለ ከተጣለባቸው ግዳታቸው አብዛኛውን ክፍል የፈፀሙ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባለው ይግባኝ ሰሚው ችልት አረጋግጧል።
ተጠሪዎች አይነተኛ የሆነ የውል ግዳታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለው ነጥብ የሚመዘነው ተጠሪዎች በውል መሰረት ለመፈፀም ከተስማሙባቸው ሁለት መሰረታዊ ግዳታዎች ምን ያህለን ፈፅመው ምን ያህል ይቀራቸው የሚለውን በመመዘን ነው። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በማውጣት በውለ በገቡት ግዳታ መሰረት የገዙት የንግድ ድርጅት ከነበረበት ዕዲ የከፈለት ተጠሪዎች ለእኛ ሉከፍለ ከተስማሙት ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ /አንድ ሚሉዮን ብር/ ውስጥ የከፈለት ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ በመሆኑ መሰረታዊ የውል መጣስ ተግባር ፈፅመዋል በማለት አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ያቀረቡት ክርክር የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎችን ይዘት መንፈስና ዓላማ መሰረት ያላደረገና ከቅን ልቦና ውጭ የቀረበ ነው በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪዎች በሽያጭ ውለ የገቡትን አይነተኛ ግዳታቸውን የተወጡና ቀሪውን ግዳታቸውን እንዲይወጡ ችግር የፈጠሩት አንደኛ፣ ሁለተኛ ሶስተኛ አመልካቾች መሆናቸውን በማስረጃ በማረጋገጥ ውለ በፍርድ ቤት ውሣኔ የሚሰረዝበት ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1784 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1785 ድንጋጌዎች ላይ የጠቀስናቸውን ላልች የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው በማለት ወስነናል።
እኛም ሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የተደረገውን የዕርቅ ስምምነት ይዘት መርምረናል። በዕርቅ ስምምነቱ ወ/ሮ አሰገደች አበበ ከወ/ሪት ነጠረች ከበደ በውርስ የሚተላለፍላቸውን መብት ወይም በራሳቸው የሚደርሳቸውን መብትና ጥቅም ለተጠሪዎች ለማስተላለፍና ተጠሪዎችም ለወ/ሮ አሰገደች አበበ ብር 550,000 /አምስት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ ለመክፈል ያደረጉት የዕርቅ ስምምነት የሟች ወ/ሪት ነጠረች ከበደ ወራሽነትን አረጋግጠው የሚመጡ ላልች መብት የማይመለከትና ወ/ሮ አሰገደች አበበ የሟች ነጠረች ከበደ ወራሽ መሆናቸው በራሳቸው ያላቸውን መብትና ጥቅም ለተጠሪዎች ለማስተላለፍ የተደረገ በመሆኑ ሶስተኛ አመልካች የዕርቅ ስምምነቱ የእኔን ጥቅም ይነካል በማለት ያቀረበውን ተቃውሞ አልተቀበልነውም። ወ/ሮ አሰገደች አበበ ከተጠሪዎች ጋር ያደረጉት የዕርቅ ስምምነት እንዱመዘግብላቸው ለችልቱ ሰኔ 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም፣ ሰኔ 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም እና ሰኔ 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በአካል እየቀረቡ ካመለከቱ በኋላ የዕርቅ ስምምነቱን ትቸዋለሁ በማለት በፅሐፍና በቃል ያቀረቡት አስተያየት የዕርቅ ስምምነቱን ውድቅ ለማድረግ በቂ ምክንያት ባለመሆኑና የዕርቅ ስምምነቱ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ ስላላገኘነው የአራተኛ አመልካች ወራሽ ወ/ሮ አሰገደች አበበ ከተጠሪዎች ጋር ሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ያደረጉትን የዕርቅ ስምምነት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 277/ሰ/ መሰረት በመመዝገብ የዕርቅ ስምምነቱ በወ/ሮ አሰገደች አበበና በተጠሪዎች መካከል አስገዲጅና ህጋዊ ውጤት ያለው ነው በማለት ወስነናል።
ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች ወ/ሪት ነጠረች ከበደ የሟች አቶ ከበደ ዘለቀ ልጅና ወራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ የወራሽነት የምስክርነት ወረቀት ከማግኘቷ በፉት በፍታብሐር ሕግ ቁጥር 996 መሰረት የሟች አቶ ከበደ ዘለቀ የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን በፍርድ ቤት ውሣኔ ያረጋገጡት ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የንግድ ድርጅቱን እና ህንፃውን ለአንደኛ ተጠሪ የሰጡ መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ችልት በማረጋገጥ በውሣኔው አስፍሮታል። ይህም የሚያሣየው የፀና የወራሽነት ማስረጃ ያላቸው ሁለተኛ አመልካችና ሶስተኛ አመልካች የሟች ከበደ ዘለቀ የውርስ ንብረት ክፍል የሆነውን የንግድ ድርጅትና ህንፃ ለአንደኛ ተጠሪ ከሸጡት በኋላ ወ/ሪት ነጠረች ከበደ የሟች ከበደ ዘለቀ ወራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ የወራሽነት የምስክር ወረቀት ያገኙት መሆኑን ነው።
ይግባኝ ሰሚው ችልት ያረጋገጡትን ይህንን ፍሬ ጉዲይ ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 997 ድንጋጌዎች አንፃር የሚኖረው ውጤት ምንድን ነው የሚለውን ተመልክተናል። ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 996 ጋር ተያያዥነት ያለውና የዚሁ ድንጋጌ ተከታይ የሆነው የፍታበሓር ሕግ ቁጥር 997 “ውጤቶች” በሚል ርዕስ የወራሽነት ሰርተፉኬት መያዝ የሚያስከትላቸውን ህጋዊ ውጤቶች ይደነግጋል። የወራሽነት ወረቀቱ እስካልተሰረዘ ድረስ ወራሽ በተባለው የምስክር ወረቀት እንደተገለፀው ወራሽ እንደሆነ የሚገመት መሆኑን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 997 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደግጋል። ከዚህ አንፃር ስናየው ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካች የሟች ከበደ ዘለቀ የኑዛዜ ወራሽ ናቸው የሚለውን የፍርድ ቤት የወራሽነት ማረጋገጫ እስከያዙና ይኸው የወራሽነት ማስረጃቸው እስካልተሰረዘ ድረስ የሟች ከበደ ዘለቀ ወራሾች ናቸው ብል ህጉ ግምት የሚወስድበት መሆኑን ነው።
ከዚህ በተጨማሪ “ በወራሽነት ስም በወራሹ የተፈፀሙ ተግባሮች ያለ እንደሆነ ተግባሮቹ በተፈፀሙበት ጊዜ የተባለው ወራሽ የወራሽነት መብት እንዲልነበረው በግልፅ ማወቁ ካልተረጋገጠ በቀር እነዚህን ተግባሮች ለመቃወም የማይቻል” መሆኑን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 997 ንዐስ አንቀፅ 2 አስገዲጅነት ባለው መንገድ ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ የምንረዲው ሟች ወ/ሪት ነጠረች ከበደ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የሟች ከበደ ዘለቀ ወራሽ ስለመሆናቸው የፀና የወራሽነት የምስክር ወረቀት አግኝተዋል። ይህንን የፀና የወራሽነት ማስረጃ በመያዝ የንግድ ድርጅቱንና ህንፃውን አንደኛ ተጠሪ ለመሸጥ የተዋዋለትን ውል እንዱፈርስ ወ/ሪት ነጠረች ከበደ ለመጠየቅ የምትችለው ተጠሪዎች ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የሟች አቶ ከበደ ዘለቀ ወራሾች አለመሆናቸውን እያወቁ ውል የተዋዋለ መሆኑን በማስረጃ በማስረዲት ብቻ እንደሆነ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 997 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ ይዘት ለመገንዘብ ይቻላል።
ወ/ሪት ነጠረች ከበደ እኔ የሟች ከበደ ዘለቀ ልጅና ወራሽ ነኝ የሚል ክርክር ከሚያቀርቡ በስተቀር ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የሟች ከበደ ዘለቀ የኑዛዜ ወራሾች አይደለም። አንደኛ ተጠሪ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች የሟች ከበደ ዘለቀ ወራሽ አለመሆናቸውን እያወቀ የንግድና የህንፃ ሽያጭ ውል ተዋውሎል የሚል ክርክር አላቀረቡም። ይህንንም የሚያስረዲ ማስረጃ እንዲላቀረቡ ይግባኝ ሰሚው ችልት ከሰጠው ውሣኔ ተገንዝበናል። ይህም በመሆኑ ሟች ወ/ሪት ነጠረች ከበደ የሟች ከበደ ዘለቀ ልጅና ወራሽ መሆኑ በፍርድ ቤት ከመረጋገጡ በፉት የፀና የወራሽነት ማስረጃ በመያዝ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ከአንደኛው ተጠሪ ጋር ያደረጉት የንግድ ድርጅትና የህንፃ ሽያጭ ውል እንዱፈርስ የመጠየቅ መብት የላትም። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ችልት አራተኛ አመልካች ወ/ሪት ነጠረች ከበደ ሁለተኛና ሶስተኛ አመልካቾች ከአንደኛው ተጠሪ ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል እንዱፈርስ የመጠየቅ መብት የላትም በማለት የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 996 እና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 997ን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም አራተኛ አመልካች የነበረችው ወ/ሪት ነጠረች ከበደ በዚህ መዝገብ በክርክር በተያዘው ጉዲይ ያላት መብት የሟች ከበደ ዘለቀ የውርስ ንብረት ክፍል የሆነውን የንግድ ድርጅትና ህንፃ የሸጡት ሁለተኛ አመልካችና ሶስተኛ አመልካች ንብረቱን ሸጠው ካገኙትና ወደ ፉትም በውለ መሰረት ከሚያገኙት የንብረቱ ዋጋ ከሆነው ገንዘብ ውስጥ በድርሻ መጠን እንዱያካፍሎት መጠየቅ ነው በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው የሆቴል ንግድ ድርጅትና የህንፃ ሽያጭ ውል የሚሰርዝበትም ሆነ የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
የአራተኛ አመልካች ወራሸ የሆኑት ወ/ሮ አሰገደች አበበና ተጠሪዎች ሰኔ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ያደረጉት የዕርቅ ስምምነት ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ባለመሆኑ ፀድቋል።
ተጠሪዎች ለወ/ሮ አሰገደች አበበ በዕርቅ ውለ በገቡት ግዳታ መሰረት ብር 550,000 /አምስት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ ይክፈለ።
የአራተኛ አመልካች ወ/ሪት ነጠረች ከበደ ወራሽ የሆኑት የወ/ሮ አሰገደች አበበ በዚህ መዝገብና ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጠው ውሣኔ ያላቸው መብትና ጥቅም በዕርቅ ውለ መሰረት ወደ ተጠሪዎች ተላልፎል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.