No summary available.
የሰ/መ/ ሕዲር 21 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፣ መትከል ልምዓት ሁለገብ መ/ህ/ስ ማህበር ተጠሪዎች፣ ቄስ ካላዩ ኪሮስ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በብድር የተሰጠን ገንዘብ ይመለስ በሚል የቀረበውን ክስ የሚመለከት ነው። ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ ያስተናገደው የስሃርቲሳምሬ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው አመልካች ነው። አመልካች ተጠሪን የከሰሰው ታህሳስ 15 ቀን 1997 ዓ.ም. የውሃ ሞተር ዋጋው 4900.00(አራት ሺኅ ዘጠኝ መቶ ብር) በ9% ወለድ ስላት ለአራት አመት ጊዜ ከፍለው እንዱጨርሱ ፣ጊዜው ካለፈ ግን በ18% ወለድ ስላት እንዱከፍል በአይነት በብድር ውል የሰጣቸው መሆኑን፣ተጠሪ በጊዜው ሉከፍለው ያለመቻለን ገልጾ ተጠሪ ዋናውን ገንዘብ ብር 4900.00 በ9% ብር 1764.00፣ጊዜው በማለፈ ደግሞ በ18% ወለድ ብር 1499 በጠቅላላው ብር 8163.00(ስምንት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሶስት ብር) እንዱከፍለው ይወሰን ዘንድ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ውለ ስለመኖሩና የመክፍያ ጊዜው ስለማለፈ አመነው ወለደን በተመለከተ ግን አስተያየት እንዱደረግላቸው ጠይቀዋል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዲ ፍርድ ቤትም ተጠሪን ለገንዘቡ ያለመመለስ ኃላፉ አድርጎ የኃላፉነታቸውን መጠን ግን ዋናው ገንዘብ በ9% ወለድ ታስቦ እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚኅ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታውን ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የወለድ መጠኑ 18% መሆን ሲገባው የበታች ፍርድ ቤቶች 9% ብቻ በማለት የወሰኑት የፋዳራለን አዋጅ ቁጥር 147/1991፣402/1996 እና በክልለን አዋጅ ቁጥር 145/2000 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ ዋናውን የብድር ገንዘብ ከ9% ወለድ ጋር ብቻ እንዱከፍለ በበታች ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀፅ 34(2) እና አዋጅ ቁጥር 402/1996 አንቀጽ 5 አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ገንዘብ ከአመልካች በውል የተበደሩት ገንዘቡ በአራት አመታት ውስጥ የሚመለስ ሁኖ በዚህ ጊዜ የሚታሰብ የወለድ መጠን 9%፣ጊዜው ካለፈ ደግሞ ወለደ 18% እንደሚሆን መስማማታቸውን የብድር ውለ የሚያረጋግጠው ጉዲይ ሲሆን ተጠሪም ይህንኑ ስምምነት የሚክደት ጉዲይ አይደለም። የበታች ፍርድ ቤቶች የወለድ መጠኑ 9% እንዱሆን የወሰኑት አመልካች አግባብነት ያላቸውን የማህበራት ሕጎችን መሰረት አድርጎ ክርክሩን አቅርቦ እያለ በማለፍ ነው።
በመሰረቱ በሕግ የተቋቋሙ ውልች በተዋዋይ ወገኖች መካከል የሕግን ያህል አስገዲጅነት ያላቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል።አንድ ውል ሕጋዊ ነው ለማለት ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1678 ስር የተመለከቱትን የውል አቋሞችን ማሟላት ይገባዋል። በዚህም መሰረት የሚፀና ውል ነው ለማለት የሚቻለው ውል ለመዋዋል ችልታ ባላቸው ሰዎች መካከል ጉድለት የላለው ስምምነት መኖር፣በቂ የሆነ እግጠኛነት ያለው የሚቻልና ሕጋዊ የሆነ ጉዲይ እና በሕጉ የሚፈለገው የውለ አፃጻፍ ፍርም መሟላት አለባቸው።
በተያዘው ጉዲይ አከራካሪው ነጥብ የወለድ መጠኑ 18% ላሆን ይገባል ተብል በአመልካች የተጠየቀው ዲኝነት ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑን ነው።አመልካች ይህንኑ የዲኝነት ጥያቄ ሕጋዊ ነው በማለት በዋቢነት የሚጠቀሰው የማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀጽ 34(2) እና አዋጅ ቁጥር 402/1996 አንቀጽ 5 እንዱሁም የክልለን የማህበራት አዋጅ ቁጥር 145/2000ን ነው።
በበኩላችን እንደአየነው በአዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀጽ 34(2) ስር አንድ ማህበር ላበደረው ገንዘብ የሚያገኘው ወለድ ከባንክ የማበደሪያ ወለድ ሉበልጥ አይችልም በሚል በሃይለ ቃል የተቀመጠ የነበረ ሲሆን ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 402/1996 ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀጽ 34(2) ስር ተቀምጦ የነበረው ድንጋጌ ሙለ በሙለ መሻሩን በአንቀጽ 5 ስር አስፍሯል። እንዱሁም የአዋጅ ቁጥር 147/1991ን ለማስፀፈም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 106/1996 በአንቀጽ 11 እና 14 ድንጋጌዎች ስር ከአስቀመጣቸው ሁኔታዎች የብድር አሰጣጥ ስርኣት በማህበሩ መተዲደሪደያ ደንብ ሉወሰን እንደሚችል መገንዘብ የሚቻል ነው። ከዚህም በተጨማሪ የክልለ የማህበራት አዋጅ ቁጥር 145/2000ም ተመሳሳይ ይዘት ያለው መሆኑን ተገንዝበናል። በሕጉ ረገድ ያለው ማዕቀፍ ይህን የሚመሰል ከሆነ አመልካች ከተጠሪ የ18% ወልድ ጥያቄ ያቀረበው በሕጉ አግባብ የተመሰረተው መተዲደሪያ ደንብ የሚፈቅድ መሆኑንና ይህንኑም ተጠሪ አውቀው ግዳታ የገቡ መሆኑን በመግለጽ ነው።እንዱህ ከሆነ አመልካች ከተጠሪ 18% ወለድ የማይጠይቅበት እና ተጠሪም በገቡት ግዳታ መሰረት የማይወጡበት ወይም 18% ወለድ የማይከፍለበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ በዋናው ገንዘብ 9% ወለድ ብቻ ነው ሉከፍለ የሚገባው በማለት የሰጡት ውሳኔ ከላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስናል።
ው ሣ ኔ
እንዱሁም በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/
No topics extracted.