No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 7 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ፀሐይ ፍቃደ - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1- አቶ ብቻዬ ተስፊዬ - አልቀረቡም 2- አቶ መሰለ አዲነ ወኪል ታደሰ አዲነ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ በጋብቻ ወቅት የተፈራ የጋራ ሃብትን አንደኛው ተጋቢ ለላላ ሶስተኛ ወገን የፈፀመውን የሽያጭ ውል የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ሲሆን በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሣሽ ተጠሪዎች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ከአንደኛው ተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሣሥረው ሲኖሩ ጋብቻቸው ሀምላ 11 ቀን 2000 ዓ.ም የፈረሰ መሆኑን ገልፀው በጋብቻ ወቅት ያፈራነውን በኦሮሚያ ክልል በባቱ ከተማ ያፈራነውን ቤት አንደኛ ተከሣሽ /አንደኛ ተጠሪ/ ለሁለተኛ ተከሣሽ /ሁለተኛ ተጠሪ/ ያለእኔ ፈቃድና ስምምነት ሸጧል። ቤቱ መሸጡን ያወቅሁት ነሐሴ 12 ቀን 2000 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ያለፈቃድና ስምምነቴ አንደኛ ተጠሪ ለሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ ያደረገው ውል ፈራሽ ነው ተብል ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል። አንደኛ ተጠሪ በተከሣሽነት ቀርቦ ቤቱን 1994 ዓ.ም ለአቶ መስፍን ዝንቱ አስተላልፋዋለሁ። ይህንንም ያደረግሁት በከሣሽ ፈቃድና ስምምነት ነው።
ቤቱን እኔ ለሁለተኛው ተከሣሽ /ለሁለተኛው ተጠሪ/ አልሸጥኩም ቤቱ በሁለተኛ ተከሣሽ ስም ስለተዛወረ ውለ እንዱፈርስ መጠየቅ አይችልም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ሁለተኛው ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ቀርቦ መልስ ባለመስጠቱ ጉዲዩ በላለበት ታይቷል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካችና አንደኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አንደኛ ተከሣሽ ለሁለተኛው ተከሣሽ ቤቱን መስከረም 8 ቀን 2000 ዓ.ም. በተደረገ የቤት ሽያጭ ውል በመሸጡ የቤቱ ስመሀብት ወደ ሁለተኛው ተከሣሽ የተዛወረ መሆኑ ተረጋግጧል። ስለዚህ አንደኛ ተከሣሽ ቤቱን ለሁለተኛ ተከሣሽ አልሸጥኩም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል ቤቱ በገዥው በሁለተኛው ተከሣሽ ስም የተዛወረ በመሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1806 ውለ ቀሪ ስለሆነ ከሣሽ ውለ እንዱፈርስ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርባለች። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችንና የአንደኛ ተጠሪን ክርክር ከሰማ በኋላ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የበታች ፍርድ ቤቶች ቤቱን ያለ እኔ ፈቃድና ስምምነት አንደኛው ተጠሪ ለሁለተኛው ተጠሪ የሸጠ በመሆኑን አረጋግጠዋል።
ንብረቱ በጋብቻ ወቅት የተፈራ የጋራ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህንን ካጣሩና ካረጋገጡ በኋላ ውለ ተፈፅሞ የቤቱ ስመሀብት በሁለተኛ ተጠሪ ስም የተዛወረ በመሆኑ ውለ ቀሪ ስለሆነ እንዱፈርስ መጠየቅ አይችልም በማለት የሰጡት የህግ ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክታለች። ተጠሪ በበኩለ ቤቱ የተሸጠው 1994 ዓ.ም ለአቶ መስፍን ዝንቱ ነው። ከእጃችን ከወጣ ስምንት ዓመት ሆኖታል። ስለዚህ የአመልካች መቃወሚያ ተገቢነት የለውም። አመልካች ገንዘብ ይገባኛል በማለት አላቀረበችም። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። ሁለተኛው ተጠሪ በበኩለ ሀምላ 25 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን መጥሪያ በአግባቡ አላደረሰችልንም።
ቤቱን አንደኛ ተጠሪ 1994 ዓ.ም ለአቶ መስፍን ዝንቱ በሽያጭ አስተላልፈዋል። ከዚያ በኋላ ለአቶ መስፍን ዝንቱ ባልቻ አንደኛ ተጠሪ ቤቱን ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችለው ውክልና መስከረም 9 ቀን 2000 ዓ.ም. ከአንደኛ ተጠሪ ተሰጥቶታል። ከዚህ በኋላ እኔ ከአቶ ዝንቱ ባልቻ ቤቱን የገዛሁት በመሆኑ አመልካች ውለ እንዱፈርስ ያቀረቡት ክርክር ተገቢነት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር ክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን አኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች በጋብቻ ወቅት የተፈራው የጋራ ንብረት አንደኛ ተጠሪ ለሁለተኛ ተጠሪ ለመሸጥ የተዋዋለው ውል ሙለ በሙለ ተፈፅሞ ቤቱ በሁለተኛው ተጠሪ ስም ተመዝግቦ ቀሪ ስለሆነ ውል ይፍረስልኝ ብል ለመጠየቅ አይችልም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አንደኛው ተጠሪ ቤቱ የተሸጠው 1994 ዓ.ም አመልካች አውቃና ፈቅዲ ነው።
ቤቱን ለሁለተኛ ተጠሪ የሸጥኩት እኔ ሳልሆን አቶ ዝንቱ ባልቻ ነው በማለት ያቀረበው የፍሬ ጉዲይ ክርክር ዕውነትነት የላለው መሆኑንና አንደኛ ተጠሪ በወኪለ አቶ ዝንቱ ባልቻ በኩል ለሁለተኛው ተጠሪ ቤቱን መስከረም 8 ቀን 2000 ዓ.ም የሸጠ መሆኑን ከባቱ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተላከለትን ማረጋገጫና በላልች ማስረጃዎች የተረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ቤቱን ለሁለተኛው ተጠሪ የሸጠለት አንደኛ ተጠሪ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ሁለተኛው ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተከራከረበትንና ሁለተኛው ተጠሪ በላለበት ፍርድ ቤቱ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የደረሰበትን መደምደሚያ ትክክል እንዲልሆነ በመዘርዘር ለሰበር ችልት የሰጠው መልስ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329/1/ የሚጥስና ለዚህ ፍርድ ቤት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ 3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 10 የተሰጠውን ሥልጣን ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ሁለተኛው ተጠሪ ሀምላ 23 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ፅፍ ባቀረበው መልስ በመጀመሪያው ገፅ ሁለተኛው ፕራግራፍ ቤቱን የገዛው አንደኛ ተጠሪ ቁጥሩ 4039/1/2000 በሆነና መስከረም 9 ቀን 2000 ቤቱን ለመሸጥ ለመለወጥ የሚያስችለው ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሰጠው ከአቶ ዝንቱ ባልቻ መሆኑን ግልፅ አድርጎታል። አንድ ተወካይ ከወኪልነቱ ሥልጣን ወሰን ሣያልፍ በልላ ሰው ስም የመዋዋል ተግባሮች የፈፀመ እንደሆነ በእሱ የተፈፀሙት ተግባሮች በቀጥታ በሿሚው እንደተፈፀመ እንደሚቆጠሩ በፍትብሓር ህግ ቁጥር 2189 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገ በመሆኑ አቶ ዝንቱ ባልቻ ከሁለተኛው ተጠሪ ጋር ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል በአንደኛው ተጠሪ እንደተፈፀመ የሚቆጠር ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች በጋብቻ ወቅት የተፈራውን የጋራ ንብረት ያለአመልካች ፈቃድ ለሁለተኛው ተጠሪ የሸጠው አንደኛው ተጠሪ ነው በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ስህተት የላለውና ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የቤት ሽያጭ ውለ እንዱፈርስ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው የቤቱ ስመሀብት በሁለተኛው ተጠሪ ስም የተዛወረ መሆኑን የባቱ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ነሐሴ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ደብዲቤ አረጋግጧል። የአንድ ውል መፈፀም ውለን ቀሪ የሚያደርገው በመሆኑ አመልካች ውለ በሙለ በመፈፀሙ ምክንያት ቀሪ የሆነ ውል ፈራሽ እንዱባል ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም በማለትና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1806 ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1806 ተዋዋይ ወገኖች በውል የገቡት ግዳታ ቀሪ የሚሆንበትን መሰረታዊ ምክንያት የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። ተዋዋይ ወገኖች በህግ አግባብ ያቋቋሙት ውል በመካከላቸው ሕግ እንደሆነ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1731/1/ ይደነግጋል።
ስለሆነም ተዋዋይ ወገኖች አንዲቸው ለላላው በዉል የገቡት ግዳታ ሙለ በሙለ ከፈፀሙ ውለ እንደ ህግ ሆኖ ተዋዋዮቹን ማስገደደ ቀሪ የሚሆን መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 18ዐ6 ይደነግጋል። ድንጋጌው ተዋዋዮች በውለ የገቡት ግዳታ ቀሪ የሚሆንበትን /Extinction of contract ” ምክንያት ከሚሆኑት ነገሮች አንደኛውን የሚደነግግ ነው። የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1806 ተዋዋይ ወገኖች የተዋዋለትና ሙለ በሙለ ግዳታቸውን የፈፀሙበት ውል የእኔን መብትና ጥቅም የሚነካና ህጋዊ ዉጤት ሉሰጠው የሚገባ ውል አይደለም። ስለዚህ ውለ ፈራሽ እንዱሆን ይወሰንልኝ የሚል ጥያቄ የሚያቀርቡ ሶስተኛ ወገኖች የውለን ህጋዊነት በመቃወም ውለ እንዱፈርስ ከመጠየቅ የሚገድብ የህግ ድንጋጌ አይደለም። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች አንደኛው ተጠሪ የጋራ ሀብቴ የሆነውን ቤት ያለእኔ ስምምነት ለሁለተኛው ተጠሪ ሸጧል።
ስለዚህ ውለ ፈራሽ ነው ተብል ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበችው ክስ አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ የተዋዋለት የቤት ሽያጭ ውል ሙለ በሙለ ተፈፅሞ ቤቱ በገዥው በሁለተኛው ተጠሪ ስም መመዝገቡ የማያግዲት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በፍታብሓር ህጉ ስለውለ ታውቆ መቅረት ለተደነገገው ክፍልና የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 18ዐ6 የተዛባ ትርጉም በመስጠት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም አመልካች አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ የፈፀሙት የቤት ሽያጭ ውል በፍርድ ፈራሽ እንዱሆን ክስ ያቀረበችው ታህሣሥ 4 ቀን 2001 ዓ.ም. በመሆኑ ይኸም አመልካች ውለ መፈፀሙን ካወቀችበት ከነሐሴ 12 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከአራት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ያሣያል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የቤት ሽያጭ ውለ ከተፈፀመበት መስከረም 8 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ዐመት ከሶስት ወራት ውለ እንዱፈርስ ክስ ያቀረበች መሆኑን ያሣያል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አንደኛ ተጠሪ አመልካች ውለ እንዱፈርስ ያቀረበችው ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት ከሥር ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ሰበር ችልት ያቀረበው ክርክር የተሻሻለውን የቤተሰብ ህግ አንቅፅ 69 ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገና ተገቢነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በባቱ ከተማ ዐ1 ቀበላ በአንደኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ የነበረው ቤት አመልካችና አንደኛ ተጠሪ በጋብቻ ሲኖሩ ያፈሩት የጋራ ሀብት መሆኑ ተረጋግጧል። አንደኛ ተጠሪ ይህንን የጋራ ሃብት ያለአመልካች ስምምነት ለሁለተኛው ተጠሪ መስከረም 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ውል የሸጠው የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 69 ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው። ስለሆነም አንደኛ ተጠሪ የጋራ የሆነውን የንብረት ያለአመልካች ፈቃድ ለሁለተኛ ተጠሪ ለመሸጥ የፈፀመው ውል ፈራሽና አመልካች ላይ ህጋዊ አስገዲጅነት የላለው ነው ብለው መወሰን ሲገባቸው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1806 ድንጋጌ በመጥቀስ የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አንደኛ ተጠሪ የአመልካች የጋራ ሃብት የሆነውን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ ቀበላ 01 የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ለሁለተኛው ተጠሪ ለመሸጥ አመልካች ሣታወቅና ሳትስማማ መስከረም 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በወኪለ አማካኝነት የተዋዋለው ውል ፈራሽ ነው በማለት ወስነናል።
አንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ በመሆኑ አመልካች በቤቱ ላይ ያላትን የጋራ ባለሀብትነት መብትና ድርሻ የመጠየቅ መብት አላት በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.