No summary available.
ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- ወ/ሮ እታለማሁ መስፍን - አልቀረበችም ተጠሪ፡- አጋ አንዳ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የቤት ሽያጭ ውል አፈፃፀምን መሰረት በማድረግ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ሲሆን፣ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በውል የሸጠችልኝን ቤት ስም በስሜ ለማዛወር እንድችል በውለ መሰረት እንድትፈፅምልኝ ብጠይቃት ፈቃደኛ አልሆነችም።ፍርድ ቤት ያስገድድልኝ በማለት ነው። አመልካች በበኩልዋ ለክሱ በሰጠችው መልስ በአንድ በኩል ውል አልተደረገም የሚል ክርክር ስታቀርብ፤ በልላ በኩል ደግሞ ውለ በፍ/ብ/ሕግ 1723 የተመለከተውን መስፈርት ስለማያሟላ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክራለች። ክሱ የቀረበለት የሃላባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሁለቱ ወገኖች የቀረበለትን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ፣ የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ የቤቱን ሰነድ እና ማናቸውም ማስረጃ ሁለ ለተጠሪ ትሰጥ በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሣኔውን በመቃመም ይግባኝ በማቅረብዋ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውለ የሕጉን ፍርም አያሟላም የሚል ምክንያት በመስጠት ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ ሽሮአል። በመጨረሻም በተጠሪ አቤቱታ አቅራቢነት ጉዲዩ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ክርክሩ የተሰማ ሲሆን፣ ችልቱም ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በመሻር የሃላባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ አቤቱታ ባቀረበችበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የምትልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምላት ዘንድ ጠይቃለች። እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው የአመልካች ክርክር ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው ወይ? የሚለው ጭብጥ ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የቤት ሸያጭ ውል በጽሐፍ ስለመደረጉ እና በዚህ ውል መሰረትም ተጠሪ ቤቱን ተረክቦ በይዞታው ሥር አድርጎት እንደሚገኝ ክሱን በሰማው ፍ/ቤት በማስረጃ ተረጋግጦአል። አመልካችም ብትሆን በአንድ በኩል የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል የለም፤
ቢኖርም የሕጉን ፍርም አያሟላም በማለት ስትከራከር፣ በልላ በኩል ደግሞ ቤቱ ተጠሪ ተረክቦት በይዞታው ሥር መገኘቱን አልካደችም። በእርግጥ ተጠሪ ቤቱን ሉይዝ የቻለው በኪራይ ነው የሚል መከራከሪያ ወደ መጨረሻው አካባቢ አቅርባ እንደነበር፣ ነገር ግን በዚህ መሰረትም ማስረጃ ማቅረብ እንዲልቻለች በፍ/ቤቱ ውሣኔ ተመልክቶአል። ክሱን የሰማው ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ እንደውለ እንድትፈፅም የወሰነውም እነዚህን በማስረጃ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መሰረት በማድረግ ነው።
እንደምናየው አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገችው የቤት ሸያጭ ውል እንዱፈርስ የበኩልዋን ክስ ወይም የተከሣሽ ከሳሽነት ክስ አላቀረበችም /የፍ/ብ/ሕግ. 1808/2/። ውለን መሰረት በማድረግ ቤቱን ለተጠሪ እንዲስረከበችም ፍሬ ነገርን በማስረጃ የማረጋገጥ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ተረጋግጦአል። ተጠሪ ክስ ሉመሰርት የቻለው ለውለ አፈፃፀም አስፈላጊ የሆኑትን ሁኔታዎች እንዱሟለለት ነው። እነዚህም ቤቱን የሚመለከቱ ሰነድች ሲሆኑ፣ በፍ/ቤቶቹ የተወሰነውም አመልካች እነዚህን ሰነድች እንድትሰጠው ነው። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ የአንድ ነገርን ባለሃብትነት ማስተላለፍን ስለሚመለከቱ ውልች በተደነገገው አንቀጽ 15 /የፍትሐብሕር ሕጉ/ በተመለከተው ደንብ መሰረት እንደሚመራ በፍ/ብ/ሕግ ቁ. 2875 ተመልክቶአል። በአንቀጽ 15 ሥር ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ውስጥ ለያዝነው ጉዲይ ተገቢነት ካላቸው አንደ በቁ. 2281 የተመለከተው ሲሆን፣ ይህም ሻጩ የሸጠውን ነገር ባለሃብትነት ለገዢው የማስተላለፍ ግዳታ ያለበት መሆኑን ያመለክታል። ሻጩ የሸጠውን ነገር የማያስነካ መብት ለገዢው ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ለመፈጸም እንዲለበትም ደንጏአል። በያዝነው ጉዲይ አመልካች በሥር ፍ/ቤቶች የተወሰነበት በሕጉ የተጣለበትን ግዳታ እንዱፈጽም ነው። በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻልበት አግባብ የለም። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
39512 ነሐሴ 28 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቶአል።
አመልካች ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።