No summary available.
ጥቅምት 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቴላ-ኮሙኒኬሽን ኮርፕሬሽን-ነገረ ፈጅ በፍቃደ መኯንን ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ሚ/ር ጀርመን ግናሆ - በላለበት የሚታይ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የስልክ አገልግልት ሂሳብ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአመልካች ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪ ጋር ጥር 10 ቀን 1998 ዓ.ም. በተፈረመ የጽሐፍ ውል ስምምነት ስልክ አመልካች አስገብቶላቸው ተጠሪ ሲገለገለበት ከቆዩ በኋላ ያልከፈለትን ገንዘብ ብር 5,873.20 እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአመልካችን ክስ መርምሮ የአመልካች ጥያቄ የአገልግልት ሂሳብ በየወሩ የሚመጣ እዲን የሚመለከት ነው፣ እንደዚህ አይነት ጥያቄ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት አመት ሳይከፈል ከቀረ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚል ምክንያት ይዞ የስልክ አገልግልት ክፍያ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) መሰረት ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኖታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ጥቅምት 10 ቀን 2003 በጻፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ግንኙነቱ ውልን መሰረት ያደረገ ሁኖ እያለ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 ድንጋጌ መጠቀሱ አግባብነት የላለው መሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው እንዱሻር እና አመልካች የስልክ አገልግልት ሂሳቡን እንዱከፍል ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ዋናውና የህግ ትርጉም የሚያስፈልገው ጉዲይ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌ ለስልክ አገልግልት ሂሳብ (ገንዘብ) አግባብነት አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ነው። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌን በሚገባ መረዲት ያስፈልጋል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 በጠቅላላው ሲታይ በሕግ የሕሉና ግምት የሚሸፈን የፍሬ ነገር ነጥብን (Legal Presumptions) የሚመለከት ሲሆን ዓይነቱም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 እና 2026 ድንጋጌዎቸ ጋር ተዛምድ ሲታይ ውስን የሆነ የማስተባበያ ማስረጃ የሚቀርብበት (not freely rebuttable or rebuttable but in a limited way) የሕግ የህሉና ግምት ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 የተለያዩ የክፍያ አይነቶች የሚዘረዝር ሆኖ 2024 በጠቅላላው ሲታይ ግን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎች (እዲዎች) በዚሁ የሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ሳይጠየቁ የቀሩ እንደሆኑ ክፍያውን (እዲውን) የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ወገን የተባለውን ክፍያ (እዲ) እንደከፈለ የሕግ ግምት እንደሚወሰድበት ያስገነዝባል። ድንጋጌው የስልክ አግልግልት ሂሳብን ለይቶ አላስቀመጠም።
ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነትና ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌ ተብል በተጠሪ የሚጠቀሰውን በስር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ሆነ ሰበር ሰሚ ችልት ተቀባይነት ያገኘው በፍ/ሕ/ቁጥር 2024 ድንጋጌ በፉደል (ረ) ስር የተመለከተው የክፍያ ግምት ሲሆን ሙለ ይዘቱም በሚከተለው መልኩ የተቀመጠ ነው።
ቁ. 2024 በሁለት አመት የተወሰነ ጊዜ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቆጠረው ፡- (ረ)በብድር ለተሰጠ፤ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ወሰን ውስጥ ሉከፈል የሚገባው ዕዲ የሆነ እንደሆነ ነው። የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዝኛው ቅጂም፡- Art. 2024 presumption of payment after two Years The following debts shall be deemed to have been paid where two years have elapsed since they fell due: (f) interest on loans and generally any sum payable annually or at shorter periodical intervals. በሚል ተቀምጧል።
ከላይ ከተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የድንጋጌው መጀመሪያ ፒራግራፍ የመክፈያ ጊዜያቸው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ ሁለት አመት ያለፊቸው እዲዎች(ክፍያዎች) እንደተከፈለ ይቆጠራለ የሚል ሲሆን በተከታይ የተዘረዘሩት ንዐስ ድንጋጌዎች ደግሞ የሚወሰንባቸውን የክፍያ (እዲ) ዓይነቶችን የሚዘረዝር ነው። በድንጋጌው ፉደል (ረ) ስር የተመለከተው ሲታይ በብድር የተሰጠ ወይም ለማናቸውም የአከፊፈል ሁኔታ በየአመቱ ወይም ከአመት ባነሰ ጊዜ እየተከፈለ እንዱያልቅ ጊዜ ተቆርጦለት የተሰጠ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ ወለድ እዲው ከበሰለበት ወይም በየተወሰነ ጊዜ የሚከፈል ገንዘብ ከሆነ ደግሞ ገንዘቡ ተከፍል ማለቅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ በእነዚህ ክፍያዎች (እዲዎች) ላይ ሉጠየቅ የሚችለው የወለድ ክፍያ እንደተከፈለ የሕግ ግምት የሚወሰድ መሆኑን ያሳያል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው በብድር ለተሰጠ ገንዘብ ወለድ ላይ ሲሆን ዋናውን የብድር ገንዘብ የማይጨምር መሆኑን የድንጋጌው ይዘትና አቀራረፅ ያስገነዝባል። ምክንያቱም ድንጋጌው ዋናውን የብድር ገንዘብ የሚጨምር ቢሆን ኖሮ የብድር ገንዘብንና ወለድ በማለት ያስቀምጠው ነበር እንጂ ለብቻው ነጥል የብድር ገንዘብ ወለድን በማለት አይፅፈውም ነበር። ይህ ስለመሆኑም ይህ ችልት በሰ/መ/ እና የሰ/መ/ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገደድ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌ አግባብነት የሚኖረው ለብድር ገንዘብ ወለድ እንጂ በዋናው የብድር ገንዘብ አይደለም፣ የስልክ ፍጆታ ሂሳብም ብድር ባለመሆኑ ከመነሻውም ድንጋጌው አግባብነት ሉኖረው አይችልም።
ላላው ስለክፍያ ግምት የሚያወሳው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2023 ሲሆን ይህ ድንጋጌ የስድስት ወር ጊዜ ማለፍ ክፍያው እንደተፈፀመ ያስቆጥራል በሚል የተቀመጠ ነው። ይህ ድንጋጌ የስድስት ወር ማለፍ ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥርባቸው ሁኔታዎችን ለይቶ አስቀምጧል። በዚህ ድንጋጌ ስር የወርሃዊ የስልክ አገልግልት ሂሳብ አልተመለከተም።
በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2023 ድንጋጌ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው። እንዱሁም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2022 ድንጋጌ ሲታይም የተከፈለው እዲ ወለድችን ወይም በተወሰነው ጊዜ የሚከፈለትን ላልች የክፍያ ድርሻዎችን የሚመለከት እንደሆነ የተከፊዩን አይነት ለይቶ ሳይገልጽ ለአንደ የክፍያ ደረሰኝ የሰጠ ባለገንዘብ ያለፈውንም ድርሻ እንደተቀበለ ይቆጠራል በማለት በንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። በመሆኑም ጉዲዩ በዚህ ድንጋጌ መሰረትም ላታይ የሚገባው ሁኖ አልተገኘም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም የስልክ አገልግልት ሂሳብ ከመሰረቱ ብድር አይደለም፤ የብድር ባህርይም የለውም። የስልክ አገልግልት ሂሳብ አመልካች ለህብረተሰቡ በሚያቀርበው አገልግልት መሰረት የሚከፈል ሲሆን መሰረቱም ውል ነው። አመልካች ክስ ያቀረበው ተጠሪ በውለ መሰረት ለተጠቀመበት ጊዜ የስልክ አገልግልት ሂሳብ እንዱከፈለው ነው። ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ቀርበው መልስ ስለመስጠታቸው የስር ብይን አያሳይም። በመሆኑም የስልክ አገልግልቱ ተጠሪ በውል አግባብ ስለመጠቀሙ አመልካች ጠቅሶ የተከራከረ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ከውለና በውለ መሰረት ደግሞ ተጠቃሹ የስልክ ቁጥር ሂሳብ መጠን በአመልካች ክስ የተጠቀሰውን መጠን ያህል የቆጠረ መሆን ያለመሆኑን በአመልካች የሚቀርበውን ክርክርና ማስረጃ አግባብነት እና ጥንካሬ በመመርመር ተገቢውን መወሰን ሲገባ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ድንጋጌ ለብይኑ መሰረት ማድረጉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ለስልክ አገልግልት ሂሳብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) እና ድንጋጌን መሰረት ማድረጋቸው ያላግባብ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 22 ቀን 2002 ዓ.ም.
በትእዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሽሯል።
የስልክ አገልግልት ሂሳብ ይከፈለኝ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2022 መሰረት የክፍያ ደረሰኝ ያልቀረበበት ከሆነ በይርጋ ደንብ የሚገዛ እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር በተመለከተው የሕሉና ግምት የሚሸፈን አይደለም ብለናል።
ተጠሪ ብር 5,873.20 (አምስት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ሶስት ብር ከሃያ ሳንቲም) ለአመልካች የሚከፍለ መሆን ያለመሆኑን፣ የሂሳቡን መጠን የአመልካችን ክርክርና ለጉዲዩ የቀረቡትን ማስረጃዎችን አግባብነትና ጥንካሬ የስር ፍርድ ቤት መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰንለታል። ይጻፍ።
No topics extracted.