No summary available.
ሕዲር 06 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- እነ ወ/ሮ አበበች ቡልቻ ተጠሪ፡- የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የኑዛዜ አፃፃፍ ሥርዓትን የሚመለከት ነው። ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካች ሟች አቶ በቀለ በዲኔ ህዲር 28 ቀን 2003 ዓ/ም የተውት ኑዛዜ እንዱፀድቅላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተው ሚስትነታቸውና የህጻን ግርማ በቀለና አይናለም በቀለ የሟቹ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል። የኑዛዜውን ሰነድ በተመለከተ ግን በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፉት ያልተነበበ ነው በሚል ምክንያት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881(2)"ን" በመጥቀስ ውድቅ ነው በማለት ወስኗል። ይህ ውሳኔ በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ሆነ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ተቀባይነት አግኝቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ሟች ያደረጉት ግልፅ ኑዛዜ በውል አዋዋይ ፉት የተደረገ ሁኖ እያለ ኑዛዜው ስለመነበቡ አይገልጽም ተብል ውድቅ መደረጉ ያላግባብ ነው፣ ፍርማሉቲውን ፍርድ ቤቱ በራሱ ማንሳት አይችልም ነበር በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታውም ተመርምሮ በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገ ሲሆን በጉዲዩ ላይ ተጠሪም የላለበት በመሆኑ የአመልካቾችን የቅሬታ ነጥብ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው አመልካቾች የሚከራከሩት ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በውል አዋዋይ ፉት የተደረገ ሁኖ እያለ በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፉት አልተነበበም ተብል ውድቅ መደረጉ ያላግባብ ነው በሚል ነው። ስለሆነም ሟች አቶ በቀለ በዲኔ ያደረጉት ኑዛዜ በሕጉ ላይ የተመለከተውን መስፈርት ያሟላል? ወይስ አያሟላም? የሚለው ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው። ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ግልፅ ኑዛዜ ነው። ግልጽ ኑዛዜ ሉያሟላ የሚገባቸው ስርዓቶች ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881 እስከ 883 ድረስ በተመለከቱት ድንጋጌዎች ሥር ተዘርዝረዋል። ይኸውም 1ኛው ኑዛዜው በአራት ምስክሮች ፉት መነበብ ያለበት መሆኑ፣ ይህም ስርዓት መፈፀሙና በተፃፈበት ጊዜ በኑዛዜው ላይ መመልከቱ፣ ተናዛዥና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዱያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን ማድረጋቸው መረጋገጡ አስፈላጊ ነው።
እንዱሁም በውል አዋዋይ ወይም በዲኛ ፉት የሚደረግ ከሆነ የምስክሮች ብዛት ሁለት በቂ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 882 ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። ከዚህም በተጨማሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 883 ስር የተመለከቱት የምስክሮችን ችልታ የሚመለከቱ ሕጋዊያን ሁኔታዎች ሉሟለ ይገባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም በሟች ተሰጠ የተባለው ኑዛዜም ውል የማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፉት የተደረገ፣ ሶስት ምስክሮች የፈረሙበት፣ ውል የማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ኑዛዜውን አረጋግጦ የፈረመበት፣ ኑዛዜው በምስክሮችና በተናዛዡ ፉት ስለመነበቡ በሰነደ ላይ ስለመገለፁ የማያሳይ እና ተናዛዡ የፈረሙት መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሆኑም ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 881(2) ሥር ከተመለከቱት ስርዓቶች ውስጥ ኑዛዜው በተናዛዡና በምስክሮች ፉት የመነበቡን ሥርዓት ያላሟላ ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች ኑዛዜው የህጉን ሥርዓት አልተከተለም ያለትም ኑዛዜው ስለመነበቡ አይገልጽም በማለት ነው።
በእርግጥ ኑዛዜው በተናዛዡና በምስክሮች ፉት ስለመነበቡ የሚያመላክት ነገር የለውም።
አመልካች የሚከራከሩት ደግሞ ኑዛዜው የተደረገው ሶስቱ ምስክሮች ባለበት ጊዜና ቦታ ከመሆኑም በተጨማሪ ውል የማዋዋል ስልጣን የተሰጠው ሰው ፉት፣ ስራውን በሚያካሂድበት ክፍል ስለሆነ በኑዛዜው ላይ ስለመነበቡ ያለመገለፁ ኑዛዜውን ፈራሽ አያደርገውም በማለት ነው።
ይሁን እንጂ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 882 ድንጋጌ ሲታይ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 ተከታይ ሁኖ ከኑዛዜ አይነቶች አንደ ስለሆነው የግልፅ ኑዛዜን ፍርማሉቲነት የሚያወሳ ድንጋጌ መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ርዕስ፣ ይዘትና ቅርፅ የምንገነዘበው ጉዲይ ሲሆን ይህ ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 ስር ከተመለከቱት የኑዛዜ ፍርማሉቲዎች መካከል ለይቶ ያወጣው የምስክሮችን ቁጥር ብቻ ሁኖ ሁለት ምስክሮች በቂ የሚሆኑበትን አግባብ የሚያሳይ እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881(2) ስር ኑዛዜው በምስክሮችና በተናዛዡ ፉት ስለመነበቡ የሚለው ስርዓት ስለመፈጸሙ በኑዛዜው ላይ ያለመገለፅ ውል አዋዋይ ወይም ዲኛ ፉት ለሚደረግ ግልጽ ኑዛዜ በፍርማሉቲ የማይፈለግ መሆኑን የሚገልፅ አይደለም። ምንም እንኳን ውል አዋዋዩ ሰው ምስክር ተብለው ባይገለፁም የምስክሩን ቁጥር በተመለከተ ኑዛዜው በሕጉ የተመለከተውን ፍርማሉቲ ያሟላ ነው ልባል ከሚችል በስተቀር በሕጉ የሚፈለገውን የኑዛዜውን መነበብ ሥርዓት ግን ይኸው ይተካል ልባል የሚችል አይደለም። ውል አዋዋይ ሟች ኑዛዜውን በነፃ ፈቃዲቸው ሲሰጡና ኑዛዜውም የተናዛዡን መሆኑን አይተውና አረጋግጠው በኑዛዜው ላይ ፈርመዋል፣ የምስክሮች ዋና አስፈላጊነትም ኑዛዜ አድራጊው ኑዛዜውን በነፃ ፍላጎቱ እና በትክክለኛ አእምሮው የሰጠ መሆኑንና የኑዛዜው ቃልም የእርሱ መሆኑን ማረጋገጥ ነው የሚለው ምክንያት ሲታይም በሕጉ በግልጽ የተመለከተውን ፍርማሉቲ ወይም የኑዛዜው መነበብ ስርዓት ያለመፈፀምን አስፈላጊ አይደለም ለማለት የሚያስችል አይሆንም።
No topics extracted.
በመሆኑም ኑዛዜው ለተናዛዡና ለምስክሮች ስለመነበቡ በሰነደ ላይ ያለመገለፁ ብቻ የኑዛዜ ሰነደ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881(2) እና 882 ስር የተመለከተውን ፍርማሉቲ አያሟላም ተብል ፈራሽ እንዱሆን የግድ የሚል ነው። በአጠቃላይ ከውል አዋዋይ በተጨማሪ ላልች ሶሰት ምስክሮች በኑዛዜ ሰነደ ላይ ያለ ከመሆኑም በላይ በውል አዋዋይ ፉት ቃለ መሐላ የተፈጸመበትና የሰነደ ይዘት የተረጋገጠ ስለመሆኑ ሰነደ የሚገልጽ ቢሆንም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 882 ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 ተከታይ በመሆኑና ስለኑዛዜው መነበብ ስርዓት መፈፀም በኑዛዜ ሰነደ ላይ መገለጽ የግድ የሚል ሕጋዊ ፍርማሉቲ ሁኖ ስለአገኘነው ሟች አደረጉ የተባለው ኑዛዜ የሕጉን መስፈርት ያላሟላ ነው። የኑዛዜ ፍርማሉቲ ጥያቄ ደግሞ ሰነደ ለማስረጃነት እስከተጠየቀ ድረስና ከጉዲዩ የክርክር አመራር ሥርዓት አንፃር ሲታይ ፍርድ ቤቱ በራሱ ለማንሳት የሚችለው እንጂ የግድ ከተከራካሪ ወገን ሉነሳ የሚገባው ነው ልባል የሚችል ባለመሆኑ በዚህ ረገድ አመልካቾች ያነሱት ክርክርም ተቀባይነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የሟች አቶ በቀለ በዲኔ ሕዲር 28 ቀን 2003 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ ፈራሽ ነው ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881(2)፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 857 እና 882 ድንጋጌዎችን ያገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ጸንቷል።