No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አሚናት አሉ ጠ/ሙለጌታ ዘመነ ቀረበ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፊጡማ ውበት ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍልን መነሻ ያደረገ ነው። ክርክሩ የተጀመረው ተጠሪ ባቀረበችው ክስ ነው። የጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ከአቶ መሀመድ ሁሴን (የሥር ተከሳሽ) ጋር በ1987 ዓ.ም. በሰርግ ተጋብተው ሲኖሩ ቆይተው በኑሮ ስላልተሰማው ጋብቻው እንዱፈርስና ንብረት እንዱካፈለ እንዱወሰን ሲሆን ተከሳሽ ቀርበው ጋብቻ የለንም አለ ከተባለም ሉፈርስ አይገባም የሚልና የሚፈርስ ከሆነም ከሥር ጣ/ገብ (የአሁን አመልካች) ጋር ሁለተኛ ጋብቻ ስላለ ንብረቱ ለሦስቱ ሉካፈል ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
የአሁን አመልካች ሥር ፍ/ቤት ጣልቃ ገብ ሆና ባቀረበችው አቤቱታ የተከሳሽ ሚስት እሷ ብቻ ስለመሆኗ እና የንብረት ክርክሩ የጋራ ንብረት መብቷን የሚጏዲ ነው በሚል ወደ ክርክሩ እንድትገባ እንዱፈቀድላት አመልክታ ወደ ክርክሩ ገብታ መከራከሪያ አቅርባለች። የባህር ዲር ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ማስረጃ ከሰማ በኋላ ሁለቱም የአቶ መሀመድ ሁሴን ሚስቶች ስለመሆናቸው በበቂ ሁኔታ አስረድተዋል ካለ በኋላ ወ/ሮ ፊጡማ ውበት /ተጠሪ/ ጋብቻ የፈፀመችው በ1987 ዓ.ም መሆኑን በአንፃሩ ወ/ሮ አሚናት አሉ (አመልካች) ጋብቻ የፈፀመችው በ1990 ዓ.ም ስለሆነ የኋለኛው ጋብቻ በጋብቻ ላይ የተፈፀመ ነው በሚል እንዱፈርስ ወስኖ የንብረት ክርክደሩ በተጠሪ እና በተከሳሽ አቶ መሀመድ ሁሴን መካከል እንዱቀጥል ብይን ሰጥቷል።
አመልካች የወረዲውን ፍ/ቤት ውሳኔ በመቃወም ለምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባለች። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ሁለቱም ጋብቻ ያላቸው መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የፉተኛው ጋብቻ በተጠሪ ጥያቄ እንዱፈርስ ከተወሰነ በኋላ የኋለኛውም ጋብቻ ተጠሪ ባቀረቡት ጥያቄ መነሻ ሁለቱም በአንዳ እንዱፈርስ የወረዲው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሯል። በዚሁም መሰረትም የአመልካች ጋብቻ እንዱፀና ሉቀጥል ይገባል ብሎናል።
የንብረት ክርክርን አስመልክቶ የሁለቱንም ጋብቻ ውጤት ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ በቅድሚያ ሦስቱም ወገኖች የግል ሀብት የሚለትን እንዱለዩ ከተደረገ በኋላ ሁለተኛው ጋብቻ ከመፈፀሙ በፉት የተፈራ ንብረት ለመጀመሪያ ተጋቢዎች እንዱሆን ተደርጏ የጋራ ሀብቱ ለሦስት እንዱካፈል ሲል በዚሁ አግባብ የንብረት ማጣራት ሂደት እንዱቀጥል ትእዛዝ ሰጥቷል። የአሁኑ ተጠሪ በበኩላቸው በውሳኔው ቅር ተሰኝተው ለአማራ ብ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ጠቅላይ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሁለቱም ጋብቻ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ሕጉ በጋብቻ ላይ ጋብቻን የማያበረታታ ነው ሲል ለቀደመው ጋብቻ ጥበቃ ሉያደርግ በሚያስችል መልኩ በንብረት ላይ ውሳኔ ላሰጥ እንደሚገባ አመልካች ከሁለተኛው ጋብቻ በኋላ የተፈራው ንብረት ለሦስት ይካፈለ ሲል ከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ የመጀመሪያዋን ተጋቢ ጥቅም የሚጏዲ ነው በማለት በተጠሪ ተዘርዝረው ከቀረቡት ንብረቶች የግል የተባለ ከተለየ በኋላ የተቀረውን ተጠሪና አቶ መሀመድ ሁሴን እኩል ይካፈለ ሲል ወስኗል።
ንብረት የማጣራቱ ሂደትም በዚሁ አግባብ እንዱቀጥል ትእዛዝ ሰጥቷል አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበች ቢሆንም ተቀባይነት አላገኘም።
በዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው። የአመልካች ጠበቃ ሚያዝያ 28 ቀን 2001 ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት አቤቱታ የክርክሩን አመጣጥ በሰፉው በማተት የአመልካች ጋብቻ ፀንቶ ያለ ስለመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ከፍተኛ ፍ/ቤት ካረጋገጡ በኋላ በንብረት ረገድ ግን አመልካች መብት የላትም መባለ የክልለን የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 74 እና 101 ድንጋጌ የሚጥስ ውሳኔ ነው በማለት እንዱታረም አመልክተዋል።
ይህ ሰበር ችልትም የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ አመልካች ከሥር ተከሳሽ ጋር ከጥር ወር 1990 ዓ.ም ጀምሮ ጋብቻ እንደነበራት ተረጋግጦ ሳለ በተጠሪ እና በአመልካች ባለቤት መካከል የነበረው ትዲር በፍቺ ሲፈርስ አመልካች በንብረት ክፍፍለ ምንም ድርሻ የላትም መባለ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመመርመር ተጠሪን አስቀርቧል።
የተጠሪ ጠበቃ ሐምል 28 ቀን 2001 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። ይዘቱም አመልካች ጋብቻ አላት ልባል እንደማይገባ በንብረት ረገድም ሁለተኛው ጋብቻ ህጋዊ ባልሆነበት ሁኔታ ንብረት ለመካፈል የሚያስችል አይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪ ከአቶ መሀመድ ሁሴን ጋር ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ጋብቻ መሥርተው ይኖሩ እንደ ነበር አመልካችም ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ከእኝሁ ሰው ጋር ጋብቻ መሥርተው ይኖሩ እንደነበር በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። የሥር ፍ/ቤቶች በውሳኔያቸው እንዲሰፈሩት የተጠሪ ጋብቻ ከአመልካች የቀደመ ሲሆን የተጠሪ ዲኝነት ጥያቄ የነበረው አመልካች በጋብቻ ላይ ጋብቻ የፈፀመች ስለሆነ ይፍረስ የሚል ሳይሆን ተጠሪና ባለቤቷ በኑሮ ባለመስማማታቸው ጋብቻው እንዱፈርስ እንዱወሰን ነበር።
በዚህ አግባብ የተጠሪ ጋብቻ የፈረሰ እና የአመልካች ጋብቻ ፀንቶ እንዱቀጥል ከተደረገ በዚህ የጋብቻ ሕይወት ውስጥ የተፈራ ንብረት ክፍፍል መርህ ምን ላሆን ይገባል የሚል ጥያቄ ምላሽ የሚያሻው ነው።
ይህ ጥያቄ አወዛጋቢ ሆኖ ላቀርብ የቻለው የአማራ ብ/ክልል መንግስት የቤተሰብ ሕግም ሆነ የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ በጋብቻ ላይ ጋብቻ የማይፈቅድ በመሆኑ በሁለት ተጋቢዎች መካከል የሚፈጥር የንብረት ክፍፍል ጥያቄን አስመልክቶ ሕጉ ግልጽ ምላሽ ስለማይሰጥ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ይህ ጉዲይ አከራካሪ ሆኖ ወደ ፍርድ ቤት ሲቀርብ አጠቃላይ የሕጉን መንፈስና ማህበራዊ ሁኔታዎነችን በማገናዘብ ውሳኔ መስጠት ተገቢ ይሆናል።
ለተያዘው ክርክር መፍትሓ ለመስጠት የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ምክንያት ጋብቻው ሕጋዊ አይደለም ተብል ቢፈርስ እንኳን ጋብቻው ፀንቶ በቀረበት ጊዜ የተፈፀሙ ድርጊቶች ውጤት የሚያጡ አይደለም በሚል ምክንያት ተጋቢዎቹ ያፈሩትን ንብረት እንዱካፈለ ሲወሰን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንን ለመለወጥ የሰጠው ምክንያት ይህ ዓይነት አተረጓጏም ሕጉ ጥበቃ ያደረገለትን የመጀመሪያ ጋብቻ ጥቅም የሚጏዲ ነው የሚል ነው።
በእኛ በኩል እንደተገነዘብነው ሕጉ ጋብቻ ላይ ጋብቻ ባለመፍቀደ ተፈጽሞ ሲገኝ ሕገወጥ ነው ይፍረስ በማለት መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለት ወገኖች የቀደመ ጋብቻ ያለው ተጋቢ ወይም ዐቃቤ ሕግ ስለመሆኑ የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 18(ሐ) እና የአማራ ብ/ክ/መ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 29/ሐ/ በተመሳሳይ ሁኔታ ደንግገው እናገኛለን።
ከፍ ሲል እንደተመለከተው ተጠሪም ሆነች አመልካች ከአቶ መሀመድ ሁሴን ጋር ከአሥር ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ጋብቻ መሥርተው ሲኖሩ የቀረበ መቃወሚያ ስለመኖሩ በዚህ ክርክር አልተጠቀሰም።
ስለሆነም ተጠሪ የቀደመ ጋብቻ የነበራት መሆኑ ቢረጋገጥም የአመልካች ጋብቻ እንዱፈርስ ያቀረበችው መቃወሚያ ሳይኖር ዛሬ በንብረት ክርክር ላይ ወደ ኋላ ተመልሶ ውጤት እንዲይኖር ማድረግ ፍትሀዊ ሆኖ አላገኘንም። ከዚህም ላላ የቤተሰብ ሕጉ አጠቃላይ መንፈስ ሲታይ አንደኛዋ ተጋቢ በልላኛዋ ተጋቢ ጥረት በተፈራ ንብረት ላይ ያለአግባብ እንድትበለጽግ ወይም ላላኛዋ ተጋቢ ያለአግባብ መብቷንና የጥረቷን ውጤት እንድታጣ ለማድረግ ያሰበ አለመሆኑን መረዲት ተገቢ ይሆናል። ለዚህ ማሳያ ላሆን የሚችለው ጋብቻ እንኳን ሳይኖር ከጋብቻ ወጪ እንደባልና ሚስት ከሦስት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ አብረው የኖሩ ሰዎች በዚህ ጊዜ ውስጥ ያፈሩት ንብረት የጋራ ሀብታቸው ስለመሆኑ በፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 102(1) እና በአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 113(1) ተደንግጎ የሚገኝ መሆኑ ነው። ስለሆነም በተሻለ ምክንያታዊ ሁኔታ (for a stronger reason) በጋብቻ ውስጥ በተጋቢዎች መካከል የተፈራ ሀብትን በሚመለከት በግራ ቀኙ ማስረጃ የሚጣራ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከወዱሁ ግን ሁለተኛዋ ተጋቢ በንብረት ረገድ መብት የላትም የሚለው የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ድምዲሜ ተገቢነት የለውም።
ስለሆነም የተጠሪም ሆነ የአመልካች የንብረት ድርሻ ክፍፍል መርህ መሆን የሚገባው በሕጉ በግልጽ እንደተመለከተው አስቀድሞ ሦስቱም የግል ንብረት የሚለትን በማስረዲት የየግላቸውን መውሰድ ይገባቸዋል። የክልለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 97(1) እንዱሁም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 86(1) ይህንኑ ያመለክታል።
ከዚህ ውጪ የሆነው ሀብት እና በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የባልና ሚስቱ ወይም የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ሆኖ የሚገመት ስለመሆኑ የቤተሰብ ሕጉ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ።
የጋራ ሀብት የሚሰኘው በተጋቢዎች የጋራ ጥረት ወይም በአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረትም የተፈራ ላሆን እንደሚችልና በአንደኛው ተጋቢ ስም ተመዝግቦ ቢሆን እንኳ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ መሆኑ ከተረጋገጠ እና በተለያ ሁኔታ ሕጉ ባስቀመጠው አግባብ አንደኛው ተጋቢ የግል መሆኑን ካላስረደ ጭምር መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 62(1) ና 63(1) እንዱሁም የአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 73(1) እና 74(1) ይህንኑ ያስረዲለ።
ከተያዘው ጉዲይ ጋር ስናያይዝ ሁለቱ ሚስቶች ናቸው እስከ ተባለ ድረስ በሕጉ መንፈስና ሃይል (by operation of the law) ከባለቤታቸው ጋር ያፈሩትን ንብረት ከባለቤታቸው ጋር እኩል የመካፈል መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው። በልላ በኩል አንደኛዋ ተጋቢ ከላላኛዋ ተጋቢ በተለየ ሁኔታ ንብረት ለማፍራት በቀጥታ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ማስረዲት ከቻለች ከላላኛዋ ተጋቢ የተሻለ መብት ሉኖራት እንደሚገባ መረዲት ተገቢ ይሆናል።
አሁን በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ከአቶ መሐመድ ሁሴን ጋብቻ ከፈፀመችበት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በራሷ ጥረት ከባለቤቷ ጋር በባህር ዲር ከተማ ስትኖር ያፈራችው ሀብት ላይ ከባለቤቷ ጋር እኩላታ የመካፈል መብት እንዲላት መገንዘብ ይቻላል። አመልካች በባህር ዲር ከተማ በባለቤቷ ስም የተፈራ ንብረት ላይ ሉኖራት የሚችለው መብት በሕጉ አግባብ መሰረት ከባለቤቷ ድርሻ ላይ ብቻ የእኩላታ መብት እንዲላት በማረጋገጥ ይሆናል።
በልላ በኩል አመልካች ከአቶ መሐመድ ሁሴን ጋር ጋብቻ መሥርታ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ አ.አ ከተማ እየኖረች ያለች ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች በተረጋገጠው ፍሬ ነገር መሰረት በአዱስ አበባ ከተማ በአመልካች ጥረት ከባለቤቷ ጋር በጋራ የተፈራ ንብረት አለ ከተባለ በዚህ ንብረት ላይ ግማሽ ድርሻ የአመልካች ይሆናል ማለት ነው።
በአጠቃላይ በጋብቻ ውስጥ የተፈራውን ንብረት የማጣራት እና የማከፊፈል መርህን አስመልክቶ የሥር ፍ/ቤቶች አመልካች ምንም መብት ሉኖራት አይገባም ሲለ የደረሱበት ድምዲሜ የሕጉን መንፈስ ያላገናዘበ እና ፍትሀዊም ሆኖ ስላልተገኘ ሉታረም ይገባል ብለናል። ስለሆነም የአመራ ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች በንብረት ክፍፍል ረገድ ምንም መብት አይኖራትም ሲል የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ በ20/4/ 2001 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ እና የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ01/08/2001 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/መ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪና በአቶ መሐመድ ሁሴን ስም በጋራ በባህርዲር ከተማ ከተፈራው ንብረት ተጠሪ እኩላታ (50%) ድርሻ ያላት ሲሆን አመልካች ደግሞ ለባለቤቷ ከሚደርሰው ድርሻ ብቻ እኩላታ ድርሻ ይኖራታል ብለናል።
በአመልካችና በአቶ መሐመድ ሁሴን ስም በጋራ በአዱስ አበባ ከተማ የተፈራ ንብረት ካለ አመልካች እኩላታ (50%) ድርሻ ያላት ሲሆን ተጠሪ ደግሞ በባለቤቷ ድርሻ ላይ ብቻ የእኩላታ ድርሻ ይኖራታል ብለናል።
በዚሁ መሰረት የንብረት ማጣራትና ክፍፍል እንዱፈጸም ብለናል። ይፃፍ።
በዚህ መዝገብ ግንቦት 5 ቀን 2001 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ ።
No topics extracted.