No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ብዙአየሁ ታደሰ - ጠበቃ ምህረትአብ ልዐልና ወ/ሮ አበባ መንግስቱ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሰልሜ ሻወል - ጠበቃ አቶ ኃይለ ንጋቱ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የፋዳራል የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ አመልካችና ተጠሪ የፍች ውጤትን በተመለከተ ያደረጉት ስምምነት ተፈፃሚነትን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት ተጠሪ (ከሳሻ) አመልካች (ተከሳሽ) በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍች እንዱፈርስና የፍች ውጤት በሆነው የጋራ ንብረት ክፍፍልና የልጆች አስተዲደግ ጉዲይ ከአመልካች ጋር በመስማማት ስምምነቱን በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሀምላ 15 ቀን 2000 ዓ.ም.
ያስፀደቁ መሆኑን ገልፀው በስምምነቱ መሰረት አብዛኛው ሁኔታዎች የተፈፀሙ ቢሆንም በቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 03/05 የሚገኘውና የካርታ ቁጥሩ 2310 የሆነ በተከሳሽ (አመልካች) ስም ያለና በቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 20 የካርታ የሆነና ቁጥሩ 4057 የሆነ ፍቅ ቤት በስምመነታችን መሰረት ከዕዲና እገዲ ነፃ በማድረግ ለከሳሽ (ተጠሪ) አላዛወሩም።
ተከሳሽ በስምምነቱ መሰረት እንዱፈፀም ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም በስምምነቱ መሰረት ያልፈፀመ በመሆኑ ንብረቱን ከዕዲና እገዲ ነፃ አድርገው እንዱያዛውሩ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ ይህ የማይቻል ከሆነ ግምታቸውን እንዱከፍለ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርበው በስምምነቱ መሰረት የቤቶቹን ስመ ንብረት ለከሳሽ (ተጠሪ) ለማዛወር አስፈላጊውን እንዲሟላ ከሳሽ ደግሞ የዳንቨሩን ጋብቻ ሰርተፉኬት አቅርበው የዳንቨሩን ጋብቻ እንድናፈርስ ስምምነት ተደርጓል። ጉዲዩ በሽማግላ ታይቷል። ከሳሽ የዳንቨሩ ጋብቻ ሳይፈርስ ስም እንዱዛወር መጠየቋ ተገቢ አይደለም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የስር ፍ/ቤት ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ስለ ፍችና የፍች ውጤት አቅርበው ባፀደቁት ስምምነት ውስጥ፣ ተከሳሽ (አመልካች) ለከሳሽ (ተጠሪ) የቤቶቹን ስመሀብት የሚያዛውረው በኮልራድ ዳንቨር ያለው ጋብቻ ከፈረሰ በኋላ ነው የሚል ይዘት የለውም። ተከሳሽ በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜው ውስጥ ቤቶቹን ከዕዲና እገዲ ነፃ አድርገው ለከሳሽ ለማዛወር የተስማሙ በመሆኑ አሁን ጊዜ ሲሰላ ሶስት ዓመት የሆነው በመሆኑ በስምምነቱ መሰረት ቤቶቹን ነፃ አድርገው ስመሀብቱን ለከሳሽ ያዛውሩ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ህዲር 11 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልካችና ተጠሪ በሁለት አገር የጋብቻ ሥርዓታቸውን ፈፅመዋል። የስር ፍ/ቤት ስምምነቱን ሲፈፅሙ የአመልካችና ተጠሪ ፍላጎት ምን እንደነበር ስለ ውልች አተረጓጏም የተደነገጉ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ስምምነቱን መተርጏም ሲገባው ይህንን ሳያደርግ ተጠሪ የኮልራድ ዳንቨር ያለውን ጋብቻ ሳታፈርስ የቤቱ ስመ ሀብት እንዱዛወር መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ተጠሪ የበኩለን ግዳታ ባልተወጣበት ሁኔታ አመልካች በስምምነቱ መሰረት እንዱፈጽም ትዕዛዝ ላሰጥ አይገባም። የስር ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ዓለም አቀፍ የግለሰብ የህግ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።
ስለዚህ በሰበር ታይቶ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው አመልካችና ተጠሪ የነበራቸው ጋብቻ በፍች እንዱፈርስና ጋብቻው በፍች ከፈረሰ በኋላ ስለሚኖረው የጋራ ንብረት ክፍፍልና የልጆች አስተዲደግ ሥምምነት ፈፅመው ስምምነቱ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ፀድቋል። ክስ የቀረበባቸው ቤቶች የተጠሪ ድርሻ ስለመሆናቸው በስምምነቱ በግልፅ ተመልክቷል። ተጠሪ የጋራ ንብረት ለመካፈል ባደረገው ስምምነት መሰረት አመልካች እንድፈጽም ያቀረብኩትን ክስ ተቀብል የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ የህግ ስህተት የለበትም። በሰበር የማጣሪያ ችልት የተያዘው ጭብጥም እኔና አመልካች ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ካስመዘገብነው የፍችና የፍች ውጤት ከሚዘረዝረው ስምምነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላለው ነው። አመልካች የኮልራድ ዳንቨር ያለው ጋብቻ ሣይፈርስ ስምምነቱን አልፈፅምም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም። ጉዲዩ የዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም የሚል መከራከሪያ ያቀረቡ ሲሆን አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና አመልካች በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም በታች ፍ/ቤቶች አመልካችና ተጠሪ በመካከላቸው የነበረውን ጋብቻ ለማፍረስ ከፍች በኋላ የጋራ ንብረት ክፍያንና የልጆች አስተዲደግን በተመለከተ ባደረጉት ስምምነቶች ሀምላ 15 ቀን 2000 ዓ.ም ለፋዳራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት አቅርበው ባፀደቁት መሰረት አመልካች ክስ የቀረበባቸውን ሁለት ቤቶች ለተጠሪ ባለሀብትነቱን እንዱያስተላለፍ የሰጡት ትዕዛዝ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካችና ተጠሪ ያደረጉትና የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ሀምላ 15 ቀን 2000 ዓ.ም ያፀደቀው ስምምነት የሚኖረው ውጤት ምንድን ነው የሚለውን ነጥብ ማየት አስፈላጊ ነው። አመልካችና ተጠሪ ሀምላ 10 ቀን 2000 ዓ.ም የፍች የጋራ ሀብት ክፍፍልና የልጆች አስተዲደግ ስምምነት በማድረግ መጋቢት 21 ቀን 1985 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ግዛት ክልል በአዱስ አበባ የፈፀሙትን ብሓራዊ ጋብቻ በፍች እንዱፈርስ፣ ጋብቻው በፍች ሲፈርስ ያሎቸውን የጋራ ሀብቶች የሚከፊፈለበት ሁኔታና የልጆች አስተዲደግ እንዳት እንደሆነ በዝርዝር ፅፈው፣ ፍችውና የፍች ውጤቱን በተመለከተ ያደረጉት ሥምምነት የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት እንዱያጸድቅላቸው በጋራ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ፍችንና የፍች ውጤትን በተመለከተ አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት ስምምነት የአመልካችና የተጠሪ ፈቃዲቸውን የገለጹበት፣ ለልጆች አስተዲደግና ለህግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑን በማረጋገጥ ሀምላ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. የፀደቀው መሆኑን ከሥር ፍ/ቤት ውሳኔና ግራ ቀኙ በሰበር ካቀረቡት የፅሁፍ ክርክር ተረድተናል።
የፍች ስምምነት እንዱያፀድቅ በባልና በሚስቱ ስምምነት ጥያቄ የቀረበለት ፍ/ቤት የፍች ስምምነቱን ከማጽደቁ በፉት የፍች ስምምነቱ የባልና የሚስቱ ትክክለኛ ፍላጎት መሆኑን ባልና ሚስቱ ፈቃዲቸውን በነፃ የሰጡ መሆኑን እንደዚሁም ስምምነቱ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን፣ ባልና ሚስቱ ስለፍች ውጤት ያደረጉት ስምምነት የልጆቻቸውን ደህንነትና ጥቅም በበቂ ሁኔታ የሚያስጠብቅ መሆኑና ስምምነቱ የሁለቱንም ተጋቢዎች ጥቅም ሚያስጠብቅ መሆኑን የማረጋገጥ ግዳታ እንዲለበት በተሸሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 80 ተደንግጓል። እንዱሁም የፍችው ውጤት በስምምነት በሚያልቅበት ጊዜ ስምምነቱ ተፈፃሚነት የሚኖረው ፍ/ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ እንደሆነ የተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 83 ንዐስ አንቀፅ 3 ይደነግጋል። የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት አመልካችና ተጠሪ ሀምላ 10 ቀን 2000 ዓ.ም.
ተፈራርመው በጋራ ማመልከቻ ፍ/ቤቱ እንዱያጸድቅላቸው የጠየቁትን የፍችና የፍች ውጤት ስምምነት ከማጽደቁ በፉት አስገዲጅነት ባለው በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 80 ሉጣሩና ሉረጋገጡ የሚገባቸውን መሰረታዊ ጉዲዮች በማረጋገጥ እንደሆነ ለመገንዘብ ይቻላል። በህግ ስልጣን የተሰጠው ፍ/ቤት የስምምነቱን ይዘት፣ ስምምነቱ በልጆች አስተዲደግ ላይ የሚኖረውን ውጤት፣ የሁለቱንም ተጋቢዎች መብትና ጥቅም የሚያስከብር መሆኑን በማረጋገጥ ካፀደቀው ስምምነቱ ህጋዊ ውጤት ያለውና በባልና ሚስቱ ላይ አስገዲጅነት ያለው ሰነድ እንደሚሆን፣ ከቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 83 ንዐስ አንቀጥ 3 ለመረዲት ይቻላል።
አመልካችና ተጠሪ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘውን የጋራ ሀብታቸውን ለመከፊፈል ባደረጉት ስምምነት መሰረት አመልካች እንዱፈፅም ያቀረበችው ክስ የቤተሰብ ህጉን አንቀጽ 83 ንዐስ አንቀጽ 3 እና የፍትሃብሓር ሥነ ሥርዐት ሕግ ቁጥር 277 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት ያደረገ ነው። አመልካችና ተጠሪ ባደረጉት ስምምነት ተጠሪ ክስ ያቀረበችባቸው ሁለት ቤቶች የተጠሪ ድርሻ መሆናቸው በግልፅ እንደተቀመጠ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው በስር ፍ/ቤትና በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ በጋራ ንብረት ለመካፈል አመልካችና ተጠሪ ባደረጉት ስምምነት የተጠሪ ድርሻ መሆናቸው የተገለጹትና ክስ የቀረበባቸውን ሁለት ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ለማስረከብ የሁለት ዓመት የስድስት ወር የጊዜ ገደብ የተሰጠው ከመሆኑ ውጭ ላላ ቅድመ ሁኔታ ያልተቀመጠ መሆኑንና አመልካች ቤቶቹን የማስረክበው በአሜሪካን አገር የኮልራድ ዳንቨር ግዛት የተፈፀመው ጋብቻ መፍረስ ይገባዋል በማለት የሚያቀርበው ክርክር ግልፅ የሆነውና ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ያፀደቀውን የፍችና የፍች ውጤት ስምምነት የሚጥስ ስለመሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍ/ቤቶች ተረጋግጧል።
አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች ስምምነቱን የአመልካችና የተጠሪን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ትርጉም መስጠት ነበረባቸው በማለት በሰበር ያቀረቡት ክርክርም በመጀመሪያ ደረጃ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካችና ተጠሪ ያቀረቡትን የፍችና የፍች ውጤት ስምምነት ከማጽደቁ በፉት የአመልካችና የተጠሪ ፍላጎት በኢትዮጵያ ውስጥ መጋቢት 21 ቀን 1985 ዓ/ም ያደረጉት ጋብቻ በፍች ማፍረስ፣ እንደዚሁም የልጆቻቸውን አስተዲደግና የጋራ ንብረታቸውን ለመካፈል መሆኑን በማረጋገጥ ያፀደቀው በመሆኑ፣ እንደዚሁም ውልች ግልፅ በሆኑ ጊዜ ግልፅ ሆኖ ከሚሰማው በመራቅ የተዋዋዮች ፈቃድ ምን እንደነበር ዳኞች ለመተርጎም እንደማይችለ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1733 በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ አመልካች ይህንን መሰረታዊ የውል አተረጓጏም መርህ በሚቃረን ሁኔታ ግልጽ የሆነውን የፍችና የፍች ውጤት ስምምነት ፍ/ቤቶች ሉተረጉሙት ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር የህግ ድጋፍ የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
አመልካች ጉዲዩ የዓለም አቀፍ ግለሰብ ህግ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን በአሜሪካን አገር የሚኖር የህግ ባለሙያ የሰጣቸውን አስተያየት በሰበር አቤቱታቸው ውስጥ በመጥቀስ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ሆኖም በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካችና ተጠሪ በኢትዮጵያ ህግ መሰረት መጋቢት 21 ቀን 1985 ዓ.ም. የፈፀሙትን ጋብቻ በፍች ለማፍረስ ያደረጉትን ስምምነትና የፍችውን ውጤት በስምምነት ለመጨረስ ተስማምተው የቀረቡትን የልጆች አስተዲደግና የጋራ ንብረት ክፍያ ውል የተሸሻለውን የቤተሰብ ህግ መሰረት በማድረግ መርምሮ ሀምላ 15 ቀን 2000 ዓ/ም የስር ፍ/ቤት ቀደም ብል በማጽደቅ የሰጠውን ውሳኔ ለማስፈፅም የቀረበ ክርክር ነው። የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ሀምላ 15 ቀን 2000 ዓ.ም.
ባፀደቀው ስምምነት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትንና የተጠሪ ድርሻ የሆኑ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ እንዱያስረክብ ትዕዛዝ መስጠት የዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም።
በአጠቃላይ ተጠሪ አመልካችና ተጠሪ ሀምላ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. ጋብቻቸው በፍች እንዱፈርስና የፍች ውጤትን በተመለከተ ተስማምተው የፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 80 እና አንቀጽ 83 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት መርምሮ ባፀደቀው መሰረት ክስ የቀረበባቸውና የተጠሪ ድርሻ የሆኑት ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ስመ ሀብቱን እንዱያስተላለፍ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ትዕዛዝ ከላይ የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎችና የፍትሃብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 277 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍ/ቤትና የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ትዕዛዝ ፀንቷል።
በዚህ ፍ/ቤት ህዲር 13 ቀን 2004 እና ታህሳስ 05 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍ/ቤት የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.