No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ሶፉያ መሐመድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መሐመድ ይመር - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካችና ተጠሪ ጋብቻቸው ጸንቶ ባለበት ጊዜ በተጠሪ ስም እጣ የደረሰው ቢሆንም ቅድመ ክፍያ ጋብቻው በፍርድ ቤት ውሳኔ መፍረስ በኋላ የተከፈለበት የኮንድሚኒየም ቤት የጋራ ነው ተብል የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተብል ነው። አመልካች ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. በጻፈት የሰበር ማመልከቻ አከራካሪው የኮንደሚኒየም ቤት በጋብቻ ጊዜ በስማቸው የደረሰ ቢሆንም እጣው ሉደርስ የቻለው መንግስት ለሴቶች የተለየ የእጣ እድል ስርዓት በመዘርጋቱ በመሆኑ እና እጣው ከደረሰ በኋላም ጋብቻው በፍርድ ቤት ውሳኔ ፈርሶ ለቤቱ የቅድመ ክፍያ ገንዘብ የተከፈለ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ቤቱ በጋብቻ ጊዜ የተፈራ የጋራ ንብረት ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚለትን የቅሬታ ነጥቦችን ጠቅሰዋል።፡ የጉዲዩ አመጣጥም ሲታይ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ተጠሪ የጋራ ንብረቶች ናቸው የሚሎቸውን አይነታቸውንና ብዛታቸውን በመግለፅ ዲኝነት መጠየቃቸውን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያሳያል። በዚህ ዝርዝር ውስጥም እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚከራክሩበት በሰሚት ሳይት የሚገኝ ሕንፃ ቁጥር 148/11 ባለ ሁለት መኝታ በተጠሪ ስም የተመዘገበ ኮንድሚኒየም ቤት እጣው ጋብቻው ጸንቶ ባለበት ጊዜ የወጣ በመሆኑ በትዲር ጊዜ የተፈራ የጋራ ንብረት ስለሆነ ልንካፈል ይገባል የሚል የዲኝነት ጥያቄ ይገኝበታል። ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረው በነበሩበት ጊዜ በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 10/11 ውስጥ በ350 ካ.ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረና በአመልካች ስም የተመዘገበ መኖሪያ ቤት፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች መኖራቸውን ገልፀው ክፍፍለ እንዱደረግ ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኗ አመልካች ለተጠሪ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ በሰጡት መልስም በአቃቂ ቃሉቲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 10/11 ውስጥ በ350 ካ.ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረና በአመልካች ስም የተመዘገበ መኖሪያ ቤት፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች መኖራቸውን ሳይክደ ክፍፍለ ቢደረግ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን የገለፁ ሲሆን የኮንድሚኒየም ቤቱን በተመለከተ ግን የጋራ ስላልሆነ ተጠሪ ሉጠይቁ አይችለም ሲለ ተከራክረዋል።
የንብረት ክርክሩ በዚሁ መልኩ የቀረበለት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ተገቢውን ማጣራት ከአደረገ በሁዋላ የኮንድሚኒየም ቤቱ የጋራ መሆኑ ማረጋገጡን ገልጾ አመልካች ለቅድመ ክፍያ ከፈልኩ የሚለትን የብር 32,048.40 (ሰላሳ ሁለት ሺህ አርባ ስምንት ብር ከአርባ ሳንቲም) ግማሽ ብር 16,024.20(አስራ ስድስት ሺኅ ሃያ አራት ብር ከሃያ ሳንቲም) ተጠሪ እንዱተኩላቸው ቤቱ ከእነ ቀሪ እዲው ግን የጋራ ነው ፣ በማለትና የታመኑትን ንብረቶች በሕጉ አግባብ ሉከፊፈለ የሚችለበትን መንገድ በመዘርዘር ውሳኔ ሰጥቷል። ኮንድሚኒም ቤቱን በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ አመልካች ቅሬታ አድሮባቸው ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የኮንድሚኒየም ቤቱ የጋራ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሉጣራ የሚገባው ነጥብ ሁኖ በመገኘቱ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መሰረት ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ ጋብቻቸው ጸንቶ ባለበት ጊዜ ሚያዚያ ወር 2002 ላይ አከራካሪው የኮንድሚኒየም ቤት በተጠሪ ስም የደረሳቸው መሆኑን ፣ ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ.ም. ደግሞ ጋብቻው በፍርድ ቤት ውሳኔ መፍረሱን፣ ከዚህም በኋላ የጋብቻ ውጤት የሆነው የንብረት ክርክር ባልተካሄደበት ሁኔታ ነሐሴ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. አመልካች ለኮንዱሚኒየም ቤቱ ቅድመ ክፍያ የከፈለ መሆኑንና ጳጉሜ 04 ቀን 2002 ዓ.ም. ላይ ከሚመለከተው አስተዲደር አካል ጋር የኮንድሚኒየም ቤቱን በተመለከተ ውል የተዋዋለ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጡ ጉዲዮች መሆናቸውን ነው። አመልካች አሁን በዚህ ሰበር ደረጃ አጥብቀው የሚከራከሩት ቤቱ ሴት በመሆናቸው ባገኙት ልዩ ድጋፍ የደረሳቸውና ቅድመ ክፍያውንም ከጋብቻ መፍረስ በኋላ የከፈለት በመሆኑ የጋራ ላሆን አይችልም በሚል ምክንያት ነው። ተጠሪ ደግሞ አመልካች ለእጣው እንዱመዘገቡ የተደረገው ተጠሪ ካላቸው የስራ ባህርይ አንፃር አመልካች በቋሚነት አዱስ አበባ ስለሚኖሩ ጉዲዩን ለመከታተል እንዱቻል ስለመሆኑና እጣውም ሴት በመሆናቸው በተለየ መንገድ ያላገኙት መሆኑን ጠቅሰው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ የቤተሰብ ሕጉን ያገናዘበ በመሆኑ ሉጸና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
No topics extracted.
በመሰረቱ በስር ፍርድ ቤት ያልቀረበ አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር በበላይ ፍርድ ቤት ሉነሳ እንደማይችል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329(1) ድንጋጌ ያሳያል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም የሚመራው በ1958ቱ የፍትሒ ብሓር ስነ ስርዓት ሕጋችን በመሆኑ ከላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ ለዚህ ችልትም ተፈጻሚነት ያለው ነው። በመሆኑም በበታች ፍርድ ቤቶች ያልተነሳ የፍሬ ነገር ክርክር በሰበር ችልት የሚነሳበት አግባብ የለም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች የኮንድሚኒየም ቤት እጣ በጋብቻ ውስጥ የደረሳቸው መሆኑን ሳይክደ እጣው በሴትነታቸው የደረሳቸው መሆኑን ጠቅሰው ተጠሪ በቤቱ ላይ መብት የላቸውም በማለት በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ የቤቱ ዕጣ በጋብቻ ውስጥ ግራ ቀኙ እያለ የደረሰ መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ አመልካች እጣውን በሴትነት ያገኘሁት ነው በማለት እዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚያቀርቡት የፍሬ ነገር ክርክር ስርዓቱን ጠብቆ የቀረበ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329(1) መሰረት ተቀባይነት የላለው ነው። አመልካች እጣው የደረሰው በጋብቻ ውስጥ መሆኑን ሳይክደ ለቤቱ ቅድመ ክፍያ ከጋብቻ መፍረስ በኋላ በስማቸው ወይም ከግል ገንዘባቸው መክፈላቸውና ውለንም ከአስተዲደሩ ጋር ማድረጋቸው በጋብቻ ጊዜ የደረሰውን እጣ ውጤቱን የሚቀየርው ላሆን የሚችልበት ሕጋዊ አግባብ የለም። የኮንድሚኒየም ቤት ለህብረተሰቡ የሚሰጥበትን አግባብ የሚገዙ ሕጎችም ከምዝገባ ጀምሮ የተለያዩ ሂደቶች ያለ ስለመሆኑ የሚሳዩ ሲሆን በትዲር ውስጥ በሚገኙ ባልና ሚስት ለእጣው ሲመዘገቡ ሁለቱም ሉመዘገቡ እንደማይችለ የሚታወቅ ነው። በመሆኑም አንደ ተጋቢ በጋብቻ ጊዜ ስሙ ከተመዘገበና እጣው ጋብቻው ጸንቶ ባለበት ጊዜ ከደረሰ በቤቱ ላይ የሚገኘው መብትና ግዳታ የተጋቢዎች የጋራ ነው ከሚባል በስተቀር የቅድሚያ ክፍያ ጋብቻው ከፈረሰ በሁዋላ በአጭር ጊዜ ወይም ወዱያውኑ በመከፈለና ውለም ጋብቻው ፍርሶ የንብረት ክፍፍል ባልተደረገበት ሁኔታ ከሚመለከተው አካል ጋር እጣው በስሙ የወጣለት ተጋቢ በመፈራረሙ ብቻ ንብረቱ የዚሁ ቅድመ ክፍያውን የከፈለውና ውለን የተዋዋለው ተጋቢ የግል ንብረት ነው የሚባልበት ሕጋዊ አግባብ የለም። በመሆኑም አመልካች የኮንድሚኒየም ቤቱ የግላ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ስርዓቱን ጠብቆ ያልቀረበና ሕጋዊ መሰረት የላለው ሁኖ ስለአገኘነው በጉዲዩ ላይ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ በመ/ቁ. 24526 ሐምል 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 115416 በ12/03/2004 ዓ.ም. የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
የኮንድሚኒየም ቤቱ እጣ የደረሰው ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ስለሆነና አመልካች ለቤቱ ቅድመ ክፍያ በመክፈል ውለን ከአስተዲደር አካለ አደረግሁ የሚለት ጊዜ ጋብቻው በፍርድ ቤት ውሳኔ ከፈረሰ በአጭር ጊዜ ውስጥና የንብረት ክፍፍለ ባልተደረገበት ሁኔታ በመሆኑ ቤቱን የአመልካች የግል ንብረት ነው ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ አግባብ የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።