No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ኃ/ስላሴ ወርቄ - ከጠበቃ ያሲን እድሪስ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ምስራቅ ወርቄ - ከጠበቃ ነሲቡ አልዩ ጋር ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ ኑዛዜን መሰረት በማድረግ የቀረበውን ክርክር መነሻ ያደረገ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ነው። የአቤቱታው ይዘትም የአሁኑ አመልካች እናት ወ/ሮ የሺ ይልማ መስከረም 23 ቀን 1999 ዓ.ም. ያደረጉት ኑዛዜ በፍርድ ቤት ታህሳስ 07 ቀን 2002 ዓ.ም. መጽደቁን ገልፀው ኑዛዜውን ሟች በእርጅና ምክንያት ጃጅተው እያለ ያደረጉት በመሆኑ፣ በኑዛዜው ሰነድ ላይ የተቀመጠው ፊርማም የሟች ባለመሆኑ፣ ኑዛዜው በሐሰት ውንጀላ አመልካችን የነቀለ በመሆኑ፣ የኑዛዜ ቃለ በስጦታ ውለ መተካቱም የኑዛዜ ተጠቃሚነትን ቀሪ የሚያደርግ ነው፣ የህጉን ፍርማሉቲ የጠበቀ ስላልሆነ የተጠሪ የኑዛዜ ተጠቃሚነት ሉሰረዝ ይገባል ሲለ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም ለአመልካች መቃወሚያ አቤቱታ በሰጡት መልስ ሟች በሙለ ጤንነታቸው የሚሰሩትን ተግባር በማወቅና በመገንዘብ ያደረጉት ኑዛዜ መሆኑን፣ አመልካችን ከውርሱ የነቀለትም ይሰድባቸው፣ ያንገላታቸው፣ ያዋርዲቸው፣ ለመደብደብ ሙከራ ያደርግባቸው ስለነበር መሆኑና ይህም በኑዛዜ ሰነደ ተጠቅሶ ከተገኘ እንደ እውነት የሚወሰድና ከውርስ ለመንቀል በቂ እና ሕጋዊ ምክንያት መሆኑን፣ የኑዛዜው ሰነድ በ24/01/2001 ዓ.ም. ስጦታ ውለ መተካቱም እርስ በእርሱ የሚጣጣምና አመልካች ከውርስ እስከተነቀለ ድረስ የስጦታ ውለ ፈራሽ ላሆን ይገባል በማለት መቃወሚያ ሉያነሱ እንደማይችለ በህጉ ክልከላ የተደረገ መሆኑን ገልጸው የአመልካች የመቃወሚያ አቤቱታ ውድቅ ላሆንልኝ ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙ ምስክሮችን በመስማትና ፊርማው በፍረንሲክ ፕሉስ እንዱመረመር አድርጎ ጉዲዩን መርምሮ የሮረንሲክ ምርመራ ውጤቱን በተመለከተ ፊርማውን መለየት አልተቻለም፣ ፊርማውን ማጣራት አልተቻለም የሚለ ሐረጎች በአንድ ላይ የያዘ በመሆኑ ውጤቱ ፊርማው የሟች አይደለም ለማለት የሚያስችል ባለመሆኑ ማለፈን ገልፆ የፊርማውን ክርክር በዚሁ ያለፈው ሲሆን ዋናውን ክርክር በተመለከተ የኑዛዜ ሰነደ በስጦታ ውለ መተካቱን፣ ይህ ሆኖ እያለ ተጠሪ የኑዛዜ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይሰጠኝ ጥያቄ ለፍርድ ቤት ማቅረባቸው አግባብ እንዲልነበር፣ የአመልካች ከውርስ መነቀል ያለመነቀል በኑዛዜ ሰነደ በፀደቀበት ሳይሆን ከስጦታ ውለ ጋር ተያይዞ በሚነሳው ክርክር ላታይ የሚገባው መሆኑን በምክንያትነት ይዞ ለተጠሪ የተሰጠውን የኑዛዜ ወራሽነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 360(2) መሰረት ሰርዞታል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ሟች የውርስ ንብረታቸውን ለአሁኗ ተጠሪ በኑዛዜ መስከረም 23 ቀን 1999 ዓ/ም ከሰጡ በኋላ መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. በተደረገ የስጦታ ውል ደግሞ ለተጠሪ መልሰው ማፅደቃቸው ንብረቱ የተላለፈለት ሰው አንድ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑና ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 900(1) መሰረት ተገቢ መሆኑን ገልጾ የኑዛዜ ሰነደ በስጦታ አልተሻረም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ችልቱ ጉዲዩን መርምሮ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 900(1) ሳይሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 898(2) መሆኑን ገልጾ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በስጦታ ውለ በከፉል ተሽሯል በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ከአሻሻለ በኋላ የስር ፍ/ቤት ያልተሻረውን የኑዛዜ ክፍል በሚመለከት በኑዛዜው ላይ የቀረበውን ክርክር ተመልክቶ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን መልሶ ልኮለታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የከተማው ሰበር ለጉዲዩ አወሳሰን መሰረት አድርገውት የነበረው ኑዛዜ በ24/07/2001 ዓ.ም. በተደረገ የስጦታ ውል በከፉል ተሸሯል ተብል መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ ጉዲዩን ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
No topics extracted.
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የሟች እናታቸውን ንብረት ለመውረስ ሲፈልጉ ተጠሪ በሕጉ አግባብ ባልተደረገ የኑዛዜ ሰነድና የስጦታ ውል መሰረት የውርስ ንብረቱን ይዘው እንደሚገኙ ገልፀው ክስ ሉመሰርቱ የቻለ መሆኑና የስር ፍ/ቤት ክሱን ውድቅ ያደረገው ደግሞ የኑዛዜ ሰነደ በስጦታ ውለ ተተክቷል፣ ላልች መከራከሪያ ነጥቦችን ደግሞ የስጦታ ውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ሲቀርብ የሚታዩ ናቸው በማለት የኑዛዜ ወራሽነትን ብቻ ሰርዞ ሲወስን የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት የኑዛዜ ሰነደ ሙለ በሙለ ሉሰረዝ አይገባም በማለት መወሰኑን ነው። ተጠሪ ስጦታ በሟች የሺ ይልማ ተደርጎልኛል የሚለት መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ/ም ሲሆን ሟች ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ህዲር 10 ቀን 2002 ዓ.ም. መሆኑን እንዱሁም መስከረም 21 ቀን 1999 ዓ.ም. ሟች ኑዛዜ ማድረጋቸውን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል።
በመሆኑም ሟች አደረጉ የተባለት የስጦታ ውል ከሟቹ ህልፈተ ሕይወት በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ነው። እንደዚህ አይነት የስጦታ ውል ላይ ስለኑዛዜ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2428 ድንጋጌ በሐይለ ቃል ያስቀምጣል። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2443 ስር ደግሞ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ስጦታ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ አሰራር አይነት ካልተደረገ ፈራሽ ስለመሆኑ ተደንግጓል። በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ አሰራር በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 ስር ተመልክቷል። እንዱህ ከሆነ የሟች ሕጋዊ እና የኑዛዜ ወራሾች የስጦታው አሰራር በሕጉ የተቀመጠውን አሰራር የተከተለ መሆን ያለመሆኑን መሰረት አድርገው ስጦታው ኑዛዜውን ተክቷል የሚል ክርክር ቢያቀርቡ የሚከለከለበት ሕጋዊ አግባብ የላለ መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 826(2)፣ 842 እስከ 856 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች እንዱሁም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያስገነዝባል።
ከሁለም በላይ ሟች ሲሞት ተፈፃሚነት ያለው ስጦታ ከሆነ ስጦታው መሻር ያለመሻሩን ሉረጋገጥ የሚችለው በውርስ ሕጉ ስለኑዛዜ መሻር በሚደነግጉት ድንጋጌዎች መሰረት ይሆናል።
በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 898 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ለዚህ አይነት ስጦታም ተፈፃሚነት ይኖረዋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት በግልጽ የተደረገ ኑዛዜ በግልጽ አኳኋን በተናዛዡ ሉሻር እንደሚችል ይደነግጋል። የኑዛዜ አንደ አይነተኛ ባህሪይ ተናዛዡ በፈለገው ጊዜ የሚሽረው አይነት መሆኑ እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም በሕጉ አግባብ የመሻሩ ተግባር እስከተከናወነ ድረስ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባው ጉዲይ ነው። በዚህም መሰረት ኑዛዜ ተናዛዡ በፈለገው ጊዜ የሚሽረው ስለመሆኑ ሕጉ የሚያስገነዝበን ከሆነ በዚህ ረገድ የሚሰጠው ትርጉምም የተናዛዡ ኑዛዜውን የመሻር ስልጣን በሚያጣብብ መልኩ ላሆን አይገባም። በመሆኑም የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ለጉዲዩ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 898 ድንጋጌን መሰረት አድርጎ ጉዲዩን በማየት ሟች መስከረም 23 ቀን 1999 ዓ.ም. አደረጉ በተባለት ኑዛዜ ስር የተዘረዘሩትን ንብረቶችን አይነት ብዛት ሟች መጋቢት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. አደረጉ በተባለው የስጦታ ሰነድ ስር ከተጠቀሱት ንብረቶች አይነት እና ብዛት እንዱሁም ከሰነድች ፍርማሉቲ አንፃር ተመልክቶ የኑዛዜ ሰነደ በከፉል የተሻረ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ ሰኔ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
የስጦታው አይነት ስጦታ ሰጪው ከሞቱ በኋላ ተፈፃሚነት እንዱኖረው የተደረገ በመሆኑ ተጠሪ ስጦታው ኑዛዜውን የተካ ነው በማለትና የሥጦታ ውለ በሕጉ የተቀመጠውን ስርዓት ያሟላ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ተቀባይነት አግኝቶ የ23/01/1999 ዓ.ም. የኑዛዜ ሰነድ በ24/07/2001 ዓ.ም. የስጦታ ውል በከፉል ተሽሯል ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።