No summary available.
ሰኔ 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰብስቤ - ወኪል ፍቅርተ እንደሻው ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የባልና ሚስት ክርክር ሆኖ የፍቺ ውጤትን የሚመለከት ሲሆን በዚህ ሂደት በተሸጠው የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ አመልካች የቀደምትነት መብት ይገባኛል ጥያቄን የሚመለከት ሆኖ የተጀመረው በደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝቦች ብሓ/ክል/መንግስት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። ጉዲዩን በቅድሚያ የተመለከተው ይሄው የክልለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀን 28-10-2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት ባልና ሚስት በሚሸጠው የጋራ ቤት ሽያጭ ሂደት ላይ ተጫራች ሆነው እንዱሳተፈ የፈቀደላቸው ስለመሆኑ፣ በጨረታው ሂደት ግን የአሁን 2ኛ ተጠሪ ያሸነፈ ስለመሆኑ፣ ቀደም ሲልም አመልካች ያመለከቱት የቅድሚያ መብት ጥያቄ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግን በጨረታው ሂደት ተጫራች ሆነው እንዱሳተፈ መብት የሰጠ እንጅ የቀደምትነት መብት ባለመሆኑ፣ በዚሁ ቀን ጠዋት የተሰጠው ትዕዛዝ ይሄንን ሳያገናዝብ በስህተት ስለመሆኑ በማመላከት የቀረበውን የቀደምትነት መብት ጥያቄን ውድቅ በማድረግ በጨረታው ሂደት ተሳትፍ አሸናፉ የነበረው 2ኛ ተጠሪ ቤቱን የገዛ ስለመሆኑ የቀረበውን ሪፕርት በማጽደቅ ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበች ሲሆን ፍ/ቤቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራቀኙን ክርክር በመስማት ይሄንኑ የክልለ የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል። የክልለ የሰበር ሰሚ ችልትም የቀረበለትን ቅሬታ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው አቤቱታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች ባቀረበችው የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለቻቸውን ነጥቦች በማንሳት የተከራከረች ሲሆን ፍሬ ሃሳቡ፡- ቀደም ሲል የክልለ የወረዲ ፍ/ቤት ቤቱን ቅድሚያ እንድወስድ የሰጠውን አስገዲጅ ትዕዛዝ በመለወጥ ላላ ትዕዛዝ መስጠቱ ተቀባይነት ያለው አካሄድ ባለመሆኑ፣ ስለጋራ ባለሀብትነት ከሚመለከቱት የፍትሐብሕር ድንጋጌዎች አኳያ በቀደምትነት በግዥ ስለማስቀረት መብት ከሚመለከቱት ድንጋጌዎች አንጻር በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት የላለው በመሆኑ እንዱታረምልኝ የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ታዞ በየራሳቸው ጥቅምት 8 ቀን 2004 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ ባልና ሚስት በሚሸጠው ቤት ጨረታ ላይ እንዱሳተፈ የተደረገ እና በሂደቱ እንደማንኛውም ተሳታፉ ተሳትፈው የተሸነፈ ስለመሆኑ፣ 2ኛ ተጠሪ በሂደቱ አሸናፉ በመሆን ቤቱን የገዛ በመሆኑ እና 1ኛ ተጠሪም ሆነ ለአመልካች የተሰጠው ዕድል በጨረታው ላይ የመሳተፍ እንጂ የተለየ ነገር በላለበት ሁኔታ አመልካች የምታነሳው ቅሬታ አግባብነት የላለው ነው በማለት ተከራክሯል። አመልካች ቅሬታዋን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥታለች።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ክርክር አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ አመልካች ያነሳችው የቀደምትነት መብት ውድቅ መደረግ ስለጋራ ባለሀብት ከተመለከቱት ድንጋጌዎች አኳያ ለመመርመር በሚል በመሆኑ ከዚሁ ቀደም ሲል ተይዞ ከነበረው ጭብጥ አኳያ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች በፍቺ ውጤት አፈጻጸም ወቅት በአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ መካከል የባልና ሚስት የጋራ ሀብት የሆነው ቤት በጨረታ እንዱሸጥ ስለመታዘዙ፣ በዚህን ሂደት ውስጥ ሁለቱም ወገኖች የቀደምትነት መብት መጠየቃቸው፣ ሁኖም ግን ፍርድ ቤቱ በጨረታው ሂደት እንዱሳተፈ እድል በመስጠት እና ለሁለቱም ወገኖች የተለየ መብት ሳይሰጥ የጨረታው ሂደት የተከናወነ ስለመሆኑ፣ በዚህም ሂደት ባልና ሚስት ተሳታፉ የነበሩ ቢሆንም ማንኛቸውም ያላሸነፈ እና በጨረታው ተሳታፉ የነበረው 2ኛ ተጠሪ ያሸነፈ ስለመሆኑ ነው። አመልካችም ብትሆን ቀደም ሲል ጨረታው ከተከናወነ በኋላ በቅድሚያ እንድወስድ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ፍርድ ቤቱ በስህተት ነው በሚል ማስተካከከያ መስጠቱ አግባብነት የለውም ከሚል በስተቀር ከላይ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች በተመለከተ የምታነሳው ክርክር የላለ ከመሆኑም በላይ ከጨረታው መከናወን በፉት የቀደምትነት መብት ከ1ኛ ተጠሪ በተለየ መልኩ ተሰጥቶኛል የሚል ክርክር የላትም።
በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች በመያዝ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ስንመለከት ክርክሩ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት እንደመሆኑ መጠን በቀጥታ ተፈጻሚነት ያለው ህግ የክልለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 75/1996 መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በዚህ የክልለ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 103/1/ መሰረት የፍቺ ውጤትን በተመለከተ በዓይነት ለመከፊፈል አዲጋች የሆነን እና ከተጋቢዎቹ እንደኛው ወገን ለላላኛው ለመተው መስማማት ያልቻለ እንደሆነ ንብረቱ ተሽጦ የተገኘውን ገንዘብ እንዱከፊፈለ የሚደረግ ስለመሆኑ እና በዚሁ ድንጋጌ ስር በአሻሻጡ ሂደት ግራ ቀኙ ያልተስማሙ እንደሆነ ሽያጩ የሚደረገው በጨረታ እንደሆነ ተደንግጓል።
በዚህ ጉዲይ ደግሞ ሁለቱም ባልና ሚስት ሲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ለሁለቱም የፈቀደው እንደማንኛውም ተጫራች በጨረታው እንዱሳተፈ የሚል እስከሆነ ድረስ እና ተሳትፈውም አሸናፉው 2ኛ ተጠሪ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አመልካች በተለየ ሁኔታ የቀደምነት መብት ይገባኛል በማለት የምታቀርበው ክርክር አግባብነት ያለው ሁኖ አልተገኘም። የበታች ፍርድ ቤቶችም በጨረታው ሂደት ያሸነፈውን 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ይረከብ በማለት ውሣኔ መስጠታቸው በአግባቡ እና በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 439 እና ተከታዮቹ ስር መሰረታዊ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሸያጭ መርህን ያገናዘበ ነው ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ የሚያመላክት ነገር አላገኘንም።
ባጠቃለይ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረበችውን የቀደምትነት ግዥ መብት በተመለከተ ውድቅ በማድረግ በጨረታው መሰረት አሸናፉው ወገን /2ኛ ተጠሪ/ ቤቱን እንዱረከብ በማለት ውሣኔ መስጠቱ በአግባቡና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
10567 በቀን 08/11/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የሀዋሳ ከተማ የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝ .ቁ.21347 በቀን 28/10/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካች ያቀረቡት የቀደምትነት ግዥ መብት ወድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ሐምል 14 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.