No summary available.
ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሞላ ንጉሴ - ጠበቃ ሙለጌታ ዘመነ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ንጉሴ ገለታ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአቀረቡት የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ መነሻ ነው።
የአመልካች እህት ወ/ሮ አረጋሽ ሲሳይና የአሁኑ ተጠሪ በጋብቻ አብረው ሲኖሩ በጋራ ያፈሩት ንብረት መኖሩን፣ ወ/ሮ አረጋሽ ሲሳይ ከዚህ አለም በመለየታቸው ምክንያት ጋብቻው በሞት መፍረሱን ገልጸው ውርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብላቸው አመልካች ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ተጠሪን አስቀርቦ ተጠሪ ተገቢ ነው ያለትን ክርክር ከአቀረቡ በኋላ ፍ/ቤቱ የውርስ ንብረቱ ተጣርቶ እንዱቀርብ የውርስ አጣሪዎችን ሹሞ የውርስ አጣሪዎች ሀብቱን አጣርተው ለፍ/ቤቱ ሪፕርቱን ሲያቀርቡ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዱሰጡበት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በመጀመሪያው ዙር የውርስ አጣሪዎች የውርስ ንብረቱን አጣርተው ሲያቀርቡ ሉጣሩ የሚገባቸው ነጥቦች መኖራቸውን ገልፆ እንደገና እንዱያጣሩት አድርጎ ጉዲዩ በድጋሚ ተጣርቶ ቀርቦለት ጉዲዩን መርምሮ ለወ/ሪት ሸዋዬ ንጉሴ እንዱከፈል ተብል በሪፕርቱ በአንድ የውርስ አጣሪ የተካተተውን የብር 21,600.00 (ሃያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ) ክፍያን ያለመቀበለንና የሟች ወ/ሮ አረጋሽ ሲሳይ ወራሾች የአሁኑን አመልካች ጨምሮ አምስት መሆናቸውን ዘርዝሮ በላልች ነጥቦች ላይ ተጣርቶ በ05/03/2002 ዓ.ም. እና በ06/07/2002 ዓ.ም. ተጣርቶ የቀረበውን ሪፕርት ፍ/ቤቱ ተቀብል አፅድቆታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍ/ቤት ተሻሽል የሟችን ድርሻ ወራሾች እኩል እንዱካፈለ ተብል ተወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የሟች ወራሾች በተገቢው መንገድ ተጠርተው ባልቀረቡበት ሁኔታ ተጠሪ የሟች ወራሾች አለ ስላለና ከእድገት ፊና መረዲጃ እድር ውስጥ የተዘረዘሩ ሰዎች የሟች ወራሾች ናቸው ተብል የሟች ድርሻ ንብረት ለአምስት እንዱከፊፈል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ወራሽ ስለመሆናቸው በሕግ አግባብ ያልተረጋገጠና በውርስ አጣሪውም ጥሪ ላልቀረቡ ሰዎች የውርሱ ተካፊዮች ናቸው የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጽሁፍ በሰጡት መልስ የሟች ወራሾች አመልካች ብቻ ሳይሆኑ በበታች ፍ/ቤቶች ስማቸው የተጠቀሱት ሰዎች ሆነው በአማራ ክልል በሰሜን ወል ዞን ወልዱያ አካባቢ በየጂ ቀበላ ማህበር አካባቢ በሕይወት ያለ መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ ተመርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የውርስ አጣሪው ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ሪፕርት የሟች ወ/ሮ አረጋሽ ሲሳይ ወራሾች እንዱቀርቡ ጥሪ ተደርጎላቸው ከአመልካች ውጪ ያለት ያልቀረቡ መሆኑን፣ ሟች ከአመልካች ውጪ ላላ ወራሾች አሎቸው ተብል የሟችን ድርሻ ከአመልካች ጋር እኩል እንዱካፈለ የተወሰነው ከእድገት ፊና መረዲጃ እድር ውስጥ በሟች ወራሽነት ስማቸው ተዘርዝሮ ተገኝቷል በሚል ምክንያት መሆኑን ነው። በመሰረቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 956 እንደተደነገገው የአጣሪው ሥራ ሟቹ አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግና በመጨረሻም ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፣ የውርሱን ሃብት ማስተዲደር፣ መክፈያቸው የደረሰውን የውርስ እዲዎች መክፈል እና ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈልና የኑዛዜውን ቃል ለመፈጸም ማንኛቸውም ላልች አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ማድረግ ነው።
የሟች ወራሾች እነማን እንደሆኑ ለመለየት የሟችን የኑዛዜና ያለኑዛዜ ወራሾችን ማጣራት የውርስ አጣሪው አቢይ ስራ ሲሆን ያለኑዛዜ ወራሾችን የመለየት ስራውን ለመተግበር ደግሞ በፍ/ብ/ሕጉ ከቁጥር 842 እስከ 856 በተደነገጉት ድንጋጌዎች መሰረት ሟች ልጅ ወይም ተወላጆች ያለት መሆኑን ወይም የሟችን ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆችን እንደ የደረጃቸው መኖራቸውን መለየትን የግድ የሚል ነው። የውርስ አጣሪው ይህንኑ ስራ ሲያከናውን ሉከተላቸው ከሚገባቸው መንገድች አንደ የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ ካለ በተገቢው መንገድ ጥሪ ማድረግ ነው። የሟች ወራሾችን ለመለየት ውርስ አጣሪው በመጀመሪያ ደረጃ ማድረግ ያለበት የሟች ኑዛዜን ማፈላለግ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 962(1) ስር የተደነገገ ሲሆን ይህንኑ ግዳታውን ለመወጣትም የሟች የተለያዩ ፅሁፍችን በመፈተሽ ኑዛዜ የተወ መሆን ያለመሆኑን ጥረት ማድረግን፣ ሟች በኖረበት ቦታ በሚገኙት በሕግ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጣቸው ክፍልች ወይም ፍ/ቤት መዝገብ ቤቶች ውስጥ ሟች በሕይወት ዘመኑ ያስቀመጠው ኑዛዜ መኖሩን ማረጋገጥን ሁለ እንደሚያስፈልግ የፍ/ሕ/ቁጥር 891 እና 962/2/ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ያስገነዝባል። እነዚህ ድንጋጌዎች የሟች ጽሐፍችን ውርስ አጣሪው ይመረምራል፣ በሕግ ለማዋዋል ስልጣን ከተሰጣቸው ዘንድና በፍርድ ቤት መዝገብ ቤቶች ተገቢ የሆኑ ፍለጋዎችን እንደሚያደርግ ኃይለ ቃል ባለው አገላለፅ ሲያስቀምጡ የሚያስገነዝቡት ቁም ነገር በየትኛውም ቦታ የሚገኝ ማንኛውም ማስረጃ ቀርቦ የሟች ኑዛዜ ነው ተብል ዋጋ የማይሰጠው መሆኑን ነው። በመሆኑም በሕጉ አግባብ በተመለከቱት ቦታዎች ዘንድ የሚገኙት ሰነድች በጥንቃቄ መፈለግ አለባቸው እንጂ ከየትኛውም ቦታ የሚቀርቡ ማስረጃዎች ሁለ ዋጋ የሚሰጣቸው አይደለም። በዚህም መሰረት በመረዲጃ እድር መዝገብ ይገኛል የተባለው ሰነድ የሟችን ወራሾችን ለጊዜው ለመወሰን ብቃት የላለው ማስረጃ መሆኑን ከፍ/ብ/ቁጥር 962/2/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ሁኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የሟች ወ/ሮ አረጋሽ ሲሳይ ያለኑዛዜ ወራሾች ካለ እንዱቀርቡ በተገቢው መንገድ ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ሲሆን ከአመልካች ውጪ ላልች ሰዎች ያለኑዛዜ ወራሾች አለ ወደሚለው ድምዲሜ የበታች ፍርድ ቤቶች የደረሱት ከእድገት ፊና መረዲጃ እድር መዝገብ ውስጥ ስማቸው ተዘርዝሮ ተገኝቷል በሚል ነው። ይሁን እንጂ በመረዲጃ እድር መዝገብ ውስጥ ስም ተጠቅሶ መገኘት ያለኑዛዜ ወራሽነትን ለማረጋገጥ ብቃት ያለው ማስረጃ አይደለም። ተጠሪ ከአመልካች ውጪ ያለ ላልች የሟች ወራሾች አለ በማለት ይኖሩበታል የሚለትን አድራሻ ሁለ እየጠቀሱ እየተከራከሩ እነዚህ ሰዎች ቀርበው እስካሁን ድረስ የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ ያለማድረጋቸውም ተገቢነት ያለውና የክርክራቸውን እውነትነት የሚያሳይ አይደለም። የሟች ላልች ወራሾች ካለም በሕጉ አግባብ አመልካችን ከሚጠይቁ በስተቀር ከወዱሁ ተጠሪ ከሟች ድርሻ ለመውሰድ ያልቀረቡትን ሰዎች በመወከል ንብረቱን እንዱይዙ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የለም። ተጠሪ ሟች ከአመልካች ውጪ ላልች ወራሾች መኖራቸውን እየገለፁ ከመከራከራቸው በተጨማሪ ለአመልካች የሟች ሁለም ድርሻ አይገባቸውም የሚለበት ላላው ምክንያት ያለኑዛዜ ወራሽ የተባለት ነገር በጥሪው መሰረት ያልቀረቡትን ሰዎች ድርሻ ሉወስድ የሚገባው መንግስት ነው በማለት ነው። ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 852 ስር እንደተመለከተው የሟች ውርስ ለመንግስት ሉተላለፍ የሚችለው በሕጉ አግባብ የተመለከቱት የሟች ወራሽ ሉሆኑ የሚችለ ዘመድች ከላለ ብቻ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው የተጠሪ ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ሲጠቃለልም ወራሽ ስለመሆናቸው በሕግ አግባብ ያልተረጋገጠና በውርስ አጣሪውም ጥሪ ስላልቀረቡ ሰዎች የውርስ ተካፊዮች እንዱሆኑ ተብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 944/ሀ/፣ 962፣ ከቁጥር 842 እስከ 856 እንዱሁም 962 እና ከቁጥር 1097 እስከ 1113 ድረስ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች እና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33/2/ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ውጪ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ በከፉል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኘተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ.ም.
የተሻሻለው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የሟች አረጋሽ ሲሳይ ድርሻ ንብረት አመልካች ለብቻቸው እንዱወስደት ከሚደረግ በስተቀር ከላልች አራት ሰዎች ጋር እኩል ድርሻቸውን እንዱወስደ የሚደረግበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
የሟች አረጋሽ ሲሳይ ወራሽ የሚሆን ሰው ካለ በሕግ አግባብ ድርሻውን ከአመልካች ከመጠየቅ ይህ ውሣኔ አያግድም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።