No summary available.
ሚያዝያ 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ኬሪያት ያህያ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- ሐጂ ጅሀድ ኡመር በላለበት መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የባልና ሚስት የፍቺ ውጤትን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የተጀመረው በጅማ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በአመልካች ከሳሽነት ነው። አመልካች ባቀረበችው ክስ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ በጅማ ዞን የሸሪአ ፍርድ ቤት የፈረሰ መሆኑን፣ ከፍቺ በኋላ የጋብቻ ውጤትን በተመለከተ ግን በመደበኛ ፍርድ ቤት የመጠየቅ መብት ተጠብቆልኝ ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ ድርሻዬን እንዱሰጠኝ በሚል ነው። ተጠሪም መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በሰጠው መልስ ጉዲዩ ከዚህ በፉት ለዚሁ የወረዲ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ውሳኔ መሰጠት ያለበት የፍቺ ውሳኔ የሰጠው ፍርድ ቤት ራሱ ስለመሆኑ በማመልከት ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ድጋሚ ላታይ አይገባውም በሚል የመጀመሪያ ደረጃ ተቃውሞ አቅርቧል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የክልለ የወረዲ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ቀደም ሲል የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ክስ ቀርቦ ማየት ያለበት የፍቺ ውሳኔውን የሰጠው ፍርድ ቤት ነው በማለት ይሄው ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠበት በመሆኑ ድጋሚ ላቀርብ አይገባም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.5 እና 245/2/ መሰረት በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቶታል። ይሄው ውሳኔ በክልለ የከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የሰበር ሰሚ ችልት ጸንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች ነሐሴ 26 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ባቀረበችው አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለቻቸውን ነጥቦች ያነሳች ሲሆን ፍሬ-ሃሳቡ፡- በመካከላችን የነበረው ጋብቻ በጅማ ዞን ሸሪዓ ፍርድ ቤት ከፈረሰ በኋላ የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድርሻዬን እንዱሰጠኝ ክስ አቅርቤ ውሳኔ የሰጠበት ሁኖ ተጠሪ ውሳኔው ላይ ይግባኝ በመጠየቁ የክልለ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልለ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ለመመልከት ስልጣን የለውም በሚል ውሳኔውን በመሻር ክሱን ግን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የማቅረብ መብቴን ጠብቆልኛል። በዚሁ መሰረት ለጅማ ዞን ሸሪዓ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቤ ስከራከር ከቆየሁ በኋላ ጉዲዩን ለማየት አልችልም በማለት ውሳኔ በመስጠቱ ምክንያት ለከተማው የወረዲ ፍርድ ቤት ያቀረብኩት ክስ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ተመልክቶ ውሳኔ ላሰጥበት ሲገባ ከዚህ በፉት የተመለከትኩት ነው በማለት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የቀረበውን የፍቺ ዉጤት ክርክር ውድቅ ማድረጉ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ ፍትሕ የማግኘት መብቴን ያጣበበ ነው በማለት እንዱታረምላት ጠይቃለች። በዚህ ጉዲይ አመልካች ያቀረበችው የፍቺ ውጤት ክስ የሸሪዓም ሆነ የመደበኛ ፍርድ ቤት በመመልከት ውሳኔ መስጠት ሲገባቸው መታለፈ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ-መንግስት አንቀጽ 37 መሰረት ፍትሕ ከማግኘት መብት አኳያ ለመመርመር በሚል ያስቀርባል በመባለ እና ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ መጥሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፍ ጉዲዩ ለውሳኔ አድሮአል።
ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ በሸሪዓ ፍርድ ቤት የተቋጨ ስለመሆኑ አከራካሪ አይደለም። የፍቺ ውሳኔ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ከተሰጠ በኋላ አሁን እያከራከረ ያለውን የፍቺ ውጤት መመልከት ያለበት የትኛው ፍርድ ቤት ነው የሚለው ነጥብ ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል። በእርግጥ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ-መንግስት አንቀጽ 78/5/ መሰረት ለሚቋቋሙት የሐይማኖት ፍርድ ቤቶች እውቅና እንደተሰጠ እና እንደሚደራጁ ተመልክቷል። በዚሁ አግባብ በተቋቋሙት የሐይማኖት ፍርድ ቤቶች የተከራካሪ ወገኖችን ፈቃደኝነት መሰረት በማድረግ ሉዲኙ እንደሚችለ በዚሁ ህገ-መንግስት አንቀጽ 34/5/ ስር ተመልክቷል። በዚህ አግባብ ግራ ቀኙ ጉዲያቸውን ለሸሪዓ ፍርድ ቤት በማቅረብ የፍቺ ውሳኔ ያገኙ ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል። የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ግን አመልካች የሸሪዓ ፍርድ ቤት በመደበኛ ፍርድ ቤት መጠየቅ እንድችል መብቴን ጠብቆልኝ አሰናብቶኛል በሚል ለመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበች ስለመሆኑ ጉዲዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ውሳኔ የፍቺ ውጤትን ተመልክቶ ውሳኔ ላሰጥበት የሚገባው ፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ የሰጠው ነው በማለት ያልተቀበለት መሆኑን፣ ጉዲዩን ለተመለከተው የሸሪዓ ፍርድ ቤት የፍቺ ውጤቱን በተመለከተ ክስ ያቀረበች ስለመሆኑ፣ ሁኖም ግን የፍቺ ውሳኔ የሰጠው የሸሪዓ ፍርድ ቤት አመልካች በመደበኛ ፍርድ ቤት ቀድሞ ክስ ማቅረባቸው በዚህ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዲኘት ፍላጎት የላላቸው መሆኑን ያመላክታል በማለት አናስተናግድም በሚል መዝገቡን የዘጉት ስለመሆኑ መመልከት ይቻላል።
ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው ቀድሞ የፍቺ ውሳኔ የሰጠው የሸሪዓ ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ መካከል ያለውን የፍቺ ውጤት በተመለከተ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ያልፈለገ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት መዝገቡን ስለመዝጋቱ መመልከት ይቻላል። የፍቺውን ውሳኔ የሰጠው የሸሪዓ ፍርድ ቤት የንብረት ክፍፍለንም በተመለከተ እልባት ይሰጣል ተብል ቢገመትም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ይሄንን የክርክር ነጥብ በተመለከተ ለመደበኛ ፍርድ ቤት እንዱያቀርቡ መብት በመጠበቅ መዝገብ ሲዘጉ ወይንም አናስተናግድም በማለት ተከራካሪዎችን ሲያሰናብቱ ዜጎች መብታቸውን ለማስከበር ያላቸው መፍትሓ ምን እንደሆነ መመልከት ተገቢ ይሆናል። በዚሁ መሰረት ከላይ እንደተመለከተው በግራ ቀኙ መካከል ያለውን ክርክር ይዲኛል ተብል የተቋቋመው አካል እና ግራ ቀኙ ፈቃደኝነታቸውን የገለጹለት አካል በተለያየ ምክንያት ጉዲዩን ለመመልከት ያልፈለገ እንደሆነ ዜጎች በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገ-መንግስት አንቀጽ 37/1/ መሰረት ጉዲያቸውን ለመደበኛ ፍርድ ቤት የማቅረብ እና ፍትሕ የማግኘት መብት ሉጠበቅላቸው የሚገባ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል።
መደበኛ ፍርድ ቤቶችም እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ዜጎች ጉዲያቸውን ለመደበኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ ፍትሕ የማግኘት መብታቸው ሉረጋገጥ ስለሚገባ፣ ጉዲዩን እንዱያይ የቀረበለት የሸሪዓ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አልመለከትም በማለት በብይን ተከራካሪዎችን ያሰናበተ ስለመሆኑ እየታወቀ እና ይሄ ሲሆን መደበኛ ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን የማያስተናግደ ከሆነ ደግሞ ዜጎች ያላቸውን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚያጣብብ በመሆኑ አግባብነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ባጠቃላይ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ተከራካሪዎች በፍርድ ቤቱ ለመዲኘት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አላስተናግድም በማለት የዘጋውን ጉዲይ ስልጣን ያለው መደበኛ ፍርድ ቤት አላስተናግድም በማለት ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በመዝ.ቁ.128962 በቀን 21-10-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት፣ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ.18872 በቀን 02-6-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የጅማ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 21069 በቀን 15-4- 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
መደበኛ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበችውን የፍቺ ውጤት ጥያቄ ማስተናገድ አልችልም በማለት ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የላለው ነው ብለናል።
የጅማ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበችውን የፍቺ ውጤት ክስ በተመለከተ የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት እና በማጣራት ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.341/1/መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ችልት በአመልካች ላይ የደረሰውን ወጪና ኪሳራ የራሷን ትቻል ብለናል።
No topics extracted.