No summary available.
መጋቢት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ምንያ ገ/ሥላሴ - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- ወ/ሪት መሰረት ዓለማሁ - አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርምራ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው በጋብቻ ተሳስረው የነበሩ ተጋቢዎች ለረዥም ጊዜ ተለያይተው በመኖራቸው ምክንያት ይህ የትዲር ግንኙነት ተቋርጧል የሚባለው እንዳት ነው? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ አስመልክቶ የአ/አበባ ከተማ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በአብላጫ ድምፅ የሰጠውን ዲኝነት ከዚህ ቀደም በዚህ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ይህንኑ የህግ ጥያቄ አስመልክቶ ከሰጠው ትርጉም ጋር በማገናዘብ አግባብነቱን ለመመልከት በሚል ነው።
የጉዲዩም መነሻ የአሁን አመልካች በአ/አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሚስትነታቸውን የሚያረጋግጥ ውሳኔ ካገኙ በኋላ የአሁን ተጠሪ የሟች ልጅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ይኸው ውሳኔ መብታቸውን እንደሚነካ በማስረዲት የክርክር ተካፊይ ከሆኑ በኋላ አመልካችና ሟች አባቴ በህግ በታወቀ የጋብቻ ሥርዓት ግንኙነት አልመሰረቱም፤ ጋብቻ አለ እንኳ ቢባል አመልካች ከአስር ዓመታት በላይ ኑሯቸውን ውጭ አገር አድርገው ተለያይተው የኖሩ በመሆኑ ጋብቻው ፈራሽ ነው። በመሆኑም የተሰጠው የሚስትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ይሰረዝልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም ጉዲዩን እንደገና አንቀሳቅሶ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በአመልካችና በሟች መካከል የጋብቻ ግንኙነት ስለመኖሩ በሁኔታ ተረጋግጧል። ምንም እንኳ አመልካችና ሟች ጋብቻቸው ባለበት ጊዜ በተለያየ ሀገር ተለያይተው መኖራቸው ቢታወቅም ጋብቻቸውን ቀሪ አያደርገውም። ምክንያቱም በፋዳራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ አንቀጽ 55 እንደተመለከተው ተጋቢዎች በስምምነት ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተለያይተው መኖር እንደሚችለና መብታቸው ስለመሆኑ ተመልክቷል። ስለሆነም የአሁን አመልካች የሟች ሚስት ናቸው በማለት የተሰጠው የሚስትነት ማረጋገጫ ውሳኔ ሉሰረዝ የሚችል አይደለም በማለት ወስኗል። የአ/አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአሁን አመልካችና ሟች የጋብቻ ግንኙነት የነበራቸው ስለመሆኑ በማስረጃ መረጋገጡን ተቀብል፤ ነገር ግን ሁለቱም ለ18 ዓመታት ያህል ተለያይተው በመኖራቸው ምክንያት የቀጠለ የትዲር ግንኙነት እንዲልነበረ መረዲት ይቻላል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 31891 ለረዥም ጊዜ ተለያይተው ከኖሩ፤ በዚህም ጊዜ ውስጥ የባልና ሚስት ዓይነት ግንኙነት ያልነበራቸው ሰዎች ሚስትነት ወይም ባልነት ተረጋግጦ ማስረጃ ሉሰጣቸው እንደማይችል ያመለከተ ሲሆን በላልች የሰበር ሰሚ ችልት መዝገቦችም ተመሳሳይ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ሟችና የአሁን አመልካች ለ18 ዓመት ተለያይተው የኖሩና በዚህም ጊዜ ውስጥ የትዲር ግንኙነታቸው ባቋረጡበት ሁኔታ የአሁን አመልካች ሚስት ናቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብ ሆኖ አልተገኘም በሚለው ትችቱ መነሻ የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። የአ/አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልትም ይኸው የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም በማለት የአሁን ተጠሪን አስቀርቦ ሳያከራክር መዝገቡን ዘግቶታል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ይህንኑ ሲመስል ግራ ቀኙ ከዚህ ቀደም በስር ፍ/ቤቶች በየደረጃው ያቀረቡትን ክርክር በማጠናከር በሰበር ደረጃ የፀሁፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል እንደመረመርነውም የአሁን አመልካችና የተጠሪ አባት ሟች የጋብቻ ግንኙነት የነበራቸው ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤቶች በተሰጡት ዲኝነቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ሲሆን አከራካሪ ነጥብ ሆኖ የተገኘው ይህ የጋብቻ ግንኙነትታቸው ሁለቱም ተለያይተው በመኖራቸው ምክንያት ተቋርጧል ወይስ አልተቋረጠም በሚለው ጭብጥ ስር የተሰጠው የይግባኝ ሰሚው እና የሰበር ሰሚው ችልት ውሳኔዎች ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በዚህ አከራካሪ ነጥብ ስር በላልች ወገኖች ክርክር መነሻ የሰጠውን ትርጉም መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
የአ/አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ምንም እንኳ የአሁን አመልካችና ሟች በተለያየ ሀገር በመኖራቸው በኑሮ የተለያዩ ቢሆኑም የጋብቻ ግንኙነታቸው ግን ሳይቋረጥ የዘለቀ መሆኑ ተረጋግጧል የሚል ውሳኔ የሰጠው በአሁን አመልካች በኩል የቀረቡትን የሰው እና የተለያዩ የሰነድና ገላጭ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ነው። በአኳያው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል የነበረው የጋብቻ ግንኙነት መቋረጡን አረጋግጫለሁ ያለው በአመልካች በኩል በቀረበው የሰነድ እና ገላጭ ማስረጃ ሆኖ የቀረበውን በቪዱዮ የተቀረፀውን ምስል ብቻ ምርኩዝ አድርጏ የማስረዲት ብቃቱን በመመዘን እንደሆነ የውሳኔው ግልባጭ አስረጂ ነው። ይኸውም የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርቦ ከተመለከተውና ለውሳኔው መነሻ አድርጎ ከያዘው ማስረጃ መካከል፤ በአመልካች አማካኝነት የቀረቡት የደብዲቤ ልውውጦችና ፍቶግራፍች ተጠሪዋ የአሁኑ አመልካች በውጭ ሀገር በነበረችበት ጊዜ ከሟች ጋር የነበራት ግንኙነት አለመቋረጡን ያመለክታል፤ የወረዲ 19 መረዲጃ እድር የቀረበው መግለጫ ሟች እና የአሁን አመልካች በባልና ሚስት መመዝገባቸውን አረጋግጦ በመላኩ፤ የቀረበውም የቪዱዮ ፉልም የአሁን አመልካች ከውጭ ሀገር ለሟች በምትልከው ገንዘብ ሟች ቤቱን እየሰሩ መሆኑን በማረጋገጥ የደረሰበትን ውጤት ለባለቤታቸው ለአሁን አመልካች ለመግለፅ መልዕክቱን ለመላክ የተቀረፀ ሲሆን ከዚሁ ምስል ሟች ከአሁን አመልካች ጋር የትዲር ግንኙነታቸው ያልተቋረጠ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሎል በሚል የማስረጃውን አግባብነትና ሚዛን የመረመረበትን ክፍል ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍ/ቤት ከዕድር የመጣው ማስረጃ የዕድሩ ማህተምም ሆነ ቁጥር የላለው በመሆኑ ተአማኒነት ያለው ነው ብል ለመቀበል የሚቻል አይደለም፤ የግል ደብዲቤዎችና ፍ/ቤቱ የተመለከተው የቪዱዮ ማስረጃ የትዲር ግንኙነቱ ስለመቀጠለ የሚያመለክት ነገር የላላቸውና እምነት የሚጣልባቸው ማስረጃዎች አይደለም። ለሟች 40 ቀን መታሰቢያ የታተመው የጥሪ ወረቀትም በማንኛውም ጊዜ ሉታተም የሚችል በመሆኑ ታማኝነት ያለው አይደለም የሚለውን ትችት በመስጠት ከጋብቻ የመነጨው ግንኙነት ስለመቀጠለ በማስረጃ አልተረጋገጠም ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል።
በእርግጥ ይህ በፍሬ ነገርና ፍሬ ነገርን ለማስረዲት የቀረበውን ማስረጃ ታማኝነት የመመርመርና የማስረዲት አቅሙን የመመዘን ሥልጣኑ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንጂ ለዚሁ የሰበር ሰሚ ችልት በህግ የተሰጠው ሥልጣን ባለመሆኑ በዚህ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በማስረጃ አመዛዘን ረገድ የሰጠውን ዲኝነት እንደገና ለመመርመርና፤ አግባብነቱን ለማየት የሚቻል አይደለም።
ይሁን እንጂ በአሁን አመልካችና በሟች መካከል የነበረው የጋብቻ ግንኙነት በመኖሪያ ቦታ መለያየት የተነሳ ሳይቋረጥ ግንኙነቱ እንዲለ፤ እንደቀጠለ ነበር በማለት የአሁን አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ እና የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት ለሰጠው ውሳኔ ምርኩዝ አድርጎ የያዘው ማስረጃ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ ሰሚነት ሥልጣኑ ትችት ባሳረፈበት የሰነድ እና ገላጭ ማስረጃዎች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። የሟች እህት የሆኑትን እና የሟች ጏረቤትን የምስክርነት ቃል ሁለ የያዘ ነው። ለጉዲዩ አግባብነት ካለው የምስክርነት ቃል ውስጥ ሁለቱም በአካባቢው በእድር፣ እና በቤት ስራ ማህበር በባልና ሚስትነት እንደሚታወቁ፤ ሟች ሥራ ስላልነበራቸው ተጠሪዋ የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመለወጥ ከባለቤታቸው ጋር ባደረጉት ስምምነት ወደ ውጭ አገር ሄደው ሥራ በመስራት በሚልኩት ገንዘብ ቤት መስራታቸውን ሟችም ሲታመም ገንዘብ በመላክ ታስታምመው እንደነበር እስከ ሟች ዕለተ-ሞት በትዲር ሁኔታ ውስጥ እንደነበሩ በመግለጽ ያረጋገጡበት ይገኝበታል።
ስለዚህ የሰው ማስረጃ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ያለው የለም። ክርክርን ለማስረዲት የቀረበን ማስረጃ ከማስረጃው አግባብነት ተቀባይነት እና የማሳመን ብቃት አንጻር በማየት የማይቀበለው ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት ሳይመለከተው የቀረ ካልሆነ በቀር ክርክርን በማስረዲት የቀረበን የተከራካሪ ወገን ማስረጃ በዘፈቀደ ውድቅ ማድረግ እንደማይችል ስለማስረጃ አቀባበል በተደነገጉት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 257፣ 258 እና 259 ተመልክቷል። ይህም የተከራካሪ ወገንን የመደመጥ መብት ለማስከበር ሲባል የተዘረጋ ሥርዓት ነው። እንዱሁም የበታች ፍ/ቤት ወይም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በክርክርና ክርክርን ለማስረዲት የቀረበን፤ የተሰማን ማስረጃ አንድ በአንድ በማገናዘብ በመተቸት፤ የሚቀበለውንና የማይቀበለውን በመለየት ዲኝነት መስጠት እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 181 እና 182 በተመለከተው የፍርድ አፃፃፍ ሥርዓት ተደንግጓል። የበላይ ፍ/ቤትም ይህ ዲኝነት የፍርድ አፃፃፍ ስህተት የማስረጃ አቀባበል ሥርዓት ጉድለት መፈፀሙን የሥር ፍ/ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ የሚያስረዲና ሳይመረመርና ሳይታይ የታለፈው የማስረጃ ይዘት በመዝገቡ ላይ ሰፍሮ ከተገኘ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 242 መሰረት በዚሁ የመዝገብ ግልባጭ ላይ በመመርኮዝ አስፈላጊውን ዲኝነት መስጠት እንደሚቻልም ተመልክቷል።
ስለሆነም የአሁን አመልካችና የሟች የጋብቻ ግንኙነት ሳይቋረጥ እስከ ሟች ዕለተ ሞት ድረስ ግንኙነት የቀጠለ ስለመሆኑ የሥር የአ/አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰው ማስረጃ ያረጋገጠው የፍሬ ነገር ጉዲይ ስለመሆኑ ተገንዝበናል። ይህም ከሆነ በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የህግ አተረጓጎምና አፈጻጸም ማስፈን ይቻል ዘንድ እንደ አንድ ስልት ተቆጥሮ በወጣው በአዋጅ ቁጥር 454/97 ድንጋጌ መሰረት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች ተሰይመው የሰጡት የህግ ትርጉም በበታች ፍ/ቤቶች የአስገዲጅነት ኃይል ወይም ባህርይ የሚኖረው ትርጉም በተሰጠበት እና ዲኝነት እንዱሰጥበት በቀረበው ጉዲዮች መካከል የተነሳው የፍሬ ነገርና የህግ ጥያቄ የተመሳሰለ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በዚህ አዋጅ መሰረት የተጠቀሰውንና አስቀድሞ ትርጉም የተሰጠበትን በሰበር መ/ የተሰጠውን ውሳኔ ማየት እንደሚቻለው ሁለቱም ለ12 ዓመታት ተለያይተው እንደኖሩ ተጠሪም በውጭ ሀገር በመኖር ላይ እንዲለች ላላ ባል አግብታ ትኖር እንደነበር በክርክር ደረጃ የቀረበው ሳይጣራ የተሰጠ ውሳኔ ስለሆነ እንደገና ተጣርቶ ሉወሰን ይገባል በማለት ለሰጠው ዲኝነት እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በደፈናው የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት ትርጉም በሰጠባቸው "ላልች መዝገቦች" የሚለው አገላለጽ በሰበር መ/ የተሰጠውን ለመጥቀስ ተፈልጏ ከሆነም ተለያይተው የኖሩ ተጋቢዎች በየፉናቸው የየራሳቸውን ህይወት ስለመጀመራቸው ሟች ላላ ሚስት አግብተው ስለመኖራቸው ተረጋግጦ መሆኑ ሁለ ታይቶ ትርጉም የተሰጠበት ስለሆነ በፍሬ ነገር ረገድ በአሁን አመልካች በምንያ ገ/ስላሴ እና ተጠሪ ወ/ሪት መሰረት ዓለማየሁ መካከል ከተነሳው ክርክር ጋር የሚመሳሰል አይደለም። የሚመሳሰል ባለመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት ታይቶ ሉወሰን የሚችል አይደለም።
በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እና የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃ አቀባበል ሥርዓትና ከአዋጅ ቁጥር 454/97 አፈጻጸም ረገድ አንጻር ሲታይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የሚከተለውንም ውሳኔ ሰጥተናል።
በአብላጫ ድምፅ የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የሰጠው ፍርድ ፀንቷል።
ይህ የሰበር ክርክር ስላስከተለው ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.