No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ሐምዚያ ሼክ ኢብራህም ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አብዱ ኡስማኤል ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የአፈጻጸም ክስ የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ የአመልካች ባለቤት በነበረው በአቶ ዲውድ ዩሱፍ ላይ ያስፈረደውን ገንዘብ ለማስፈጸም ሲንቀሳቀስ በአወዲይ ከተማ የሚገኘውንና አመልካች የግላ ነው በምትለው መኖሪያ ቤት ላይ እንዱፈጸም በመታዘዙ፣አመልካች ጉዲዩን በመጀመሪያ ለተመለከተው በኦሮሚያ ብሓ/ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ሆና በመከራከር በዚህ ንብረት ላይ ሉፈጸም የማይገባ ስለመሆኑ ትዕዛዝ ያሰጠች ሲሆን፣ተጠሪ በበኩለ በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረብ እና ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የአመልካች ግማሽ ድርሻ ሳይነካባት በፍርድ ባለዕዲው ግማሽ ድርሻ ላይ እንዱፈጸም ያዘዘ በመሆኑ እና የክልለ የሰበር ሰሚ ችልትም ይሄንኑ ውሳኔ በማጽናቱ አመልካች የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት በማመልከቷ የቀረበ ነው።
አመልካች በቀን 06-10-2003 ዓ.ም በሶስት ገጽ በተጻፈ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለቻቸውን ነጥቦች በማንሳት ያቀረበች ሲሆን ፍሬ-ሀሳቡ፡-አመልካች እና የፍርድ ባለዕዲ እ.ኤ.አ. በ1993 ወይም በ1985 ዓ.ም የነበረንን ጋብቻ በሀሮማያ ወረዲ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ.815 ከፈረሰ በኋላ እ.ኤ.አ. በ24-5-94 ወይም በ1986ዓ.ም 4 የሀገር ሽማግላዎች መርጠን በተፈራረምነው የንብረት ክፍፍል ውል የአሁን አመልካች የአቶ ዲውድ ዩሱፍ ድርሻ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ሰጥቼ አሁን አፈጻጸም የቀረበበት ቤት ድርሻዬ ሁኖ ከ1986ዓ.ም. ጀምሮ የግላ ሆኖ ስጠቀምበት የቆየሁ ስለመሆኑ በተረጋገጠበት፣የፍርድ ባለዕዲ እና የፍርድ ባለመብት የክርክሩ ምክንያት የሆነውን ውል የተፈራረሙት ጋብቻችን ከፈረሰ እና ንብረት በሽማግላዎች ከተከፊፈልን ከበርካታ ዓመታት በኋላ በ1993 ዓ.ም ስለመሆኑ ግልጽ ሁኖ እያለ፣በፍርድ ባዕዲው እና በፍርድ ባለመብት መካከል በተፈራረሙት የመኪና ግዥ እና ሽያጭ ውል ላይ ሳልፈርም እና ንብረታችንን ቀደም ሲል ተከፊፍለን የተለያየን ስለመሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ በንብረቴ ላይ አፈጻጸም እንዱቀጥል መባለ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በሰጠው መልስ ለዕዲው መክፈያ እንዱውል የታዘዘው ቤት አሁንም በፍርድ ባለዕዲ ስም ያለ በመሆኑ፣የአመልካች የግል ንብረት ስለመሆኑ ያቀረባቸው አንድም ማስረጃ በላለበት ሁኔታ፣በፋዳራል የቤተሰብ ህጉም የንብረት ክፍፍልን የማጽደቅ ስልጣን ያለው ሽማግላዎች ሳይሆኑ ፍርድ ቤት ብቻ ስለመሆኑ ስለሚደነግግ፣ይፈጸም የተባለውም በራሷ ድርሻ ሳይሆን በፍርድ ባለዕዲው ድርሻ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
በዚሁ መሰረት ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ የአመልካች ትዲር በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የቀድሞ ባለቤታቸው በገቡት ዕዲ መነሻ ቀደም ሲል በክፍፍል ለአመልካች በደረሰ መኖሪያ ቤት ላይ ሉቀጥል ይገባል የመባለን አግባብነት ለመመርመር በሚል በመሆኑ ከዚሁ ቀደም ሲል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በአመልካች እና በፍርድ ባለዕዲው አቶ ዲውድ ዩሱፍ ጋር ያላቸው የጋብቻ ግንኙነት በፍቺ የፈረሰበትን ጊዜ በተመለከተ አመልካች በዚህ የሰበር አቤቱታቸው ላይ እ.ኤ.አ. በ1993 ነው በማለት ያቀረቡ ሲሆን በበታች ፍርድ ቤቶች ግን አመልካችም ራሳቸው ሲከራከሩ የነበሩት በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ በፍቺ የፈረሰው በቀን 16- 8-1993ዓ.ም በመዝ.ቁ.815 በኦሮማያ ወረዲ ሸሪአ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ እና የበታች ፍርድ ቤቶችም በፍሬ-ነገር ያረጋገጡት ነጥብ ይሄው በመሆኑ በዚህ የሰበር ሰሚ ደረጃ አመልካች ያነሱትን ክርክር ችልቱ የሚቀበለው ባለመሆኑ አልፈነዋል።
በዚሁ የክርክር ሂደትም በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡት ፍሬ-ነገሮች አመልካች እና የፍርድ ባለዕዲ አቶ ዲውድ ዩሱፍ በጋብቻ ተሳስረው የኖሩ ስለመሆኑ፣በግራቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻም በቀን 16-8-1993 ዓ.ም በወረዲ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በፍቺ የፈረሰ ስለመሆኑ፣የጋብቻ ፍቺ ውጤትን በተመለከተ ግራቀኙ ስምምነት ያደረጉ ሆኖ በፍርድ ቤት ግን ቀርቦ ያልጸደቀ ስለመሆኑ፣ እስከ አሁን ድረስም አከራካሪው ቤት በፍርድ ባለዕዲ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ እና በስሙም ግብር የሚከፈልበት ስለመሆኑ የተመለከቱት ነጥቦች ናቸው። በልላ በኩል የፍርድ ባለዕዲ አቶ ዲውድ ዩሱፍ ለአሁኑ ዕዲ ምክንያት የሆነውን እና በባንክ ዕዲ ተይዞ እያለ ለአሁን ተጠሪ ሽጦታል የተባለውን ተሽከርካሪ የሸጠው በቀን 26-4-1993ዓ.ም ስለመሆኑ፣ለአሁን አፈጻጸም ምክንያት የሆነውን ዕዲ ተጠሪ በፍርድ ባለዕዲው ላይ ያስፈረደው ደግሞ በቀን 18-7- 1995ዓ.ም ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ-ነገር ረገድ የተረጋገጡ ነጥቦች ናቸው።
ከላይ እንደተመለከተው በፍሬ-ነገር የተረጋገጡትን ነጥቦች ይዘን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ስንመለከት ለአሁን ዕዲ ምክንያት የሆነው ተሸከርካሪ የተገዛው በአመልካች እና በፍርድ ባለዕዲ መካከል የነበረው ጋብቻ ከመፍረሱ ከአራት ወራት በፉት በመሆኑ፣ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለዕዲው አቶ ዲውድ ዩሱፍን በዚሁ የተሸከርካሪ ግዢ ምክንያት በመክሰስ ያስወሰነበት በአመልካች እና በአቶ ዲውድ ዩሱፍ መካከል የነበረው ጋብቻ በፈረሰ በ2ኛ ዓመቱ በቀን 18-7- 1995ዓ.ም. ስለመሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም ግን የፍቺ ውጤትን በተመለከተ በህግ ተቀባይነት ያለው ህጋዊ ክፍፍል ስለመፈጸም ወይም አለመፈጸም በተመለከተ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ ክርክር ነጥብ ላይ አመልካች አጥብቃ የምትከራከረው በሸሪአ ፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በሽማግላዎች ዕርቅ በማድረግ የፍርድ ባለዕዲውን የአቶ ዲውድ ዩሱፍ ድርሻ ብር /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በመክፈል አከራካሪውን ቤት የግላ አድርጌዋለሁ በሚል ነው። ሆኖም የተደረገው የፍቺ ውጤት ስምምነት ምን ያህል የህግ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ መመልከት ተገቢ ነው። በዚህ ነጥብ ላይ የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.69/1995 እና 83/1996 አንቀጽ 110/5/ እንደዚሁም የፋ/የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ213/92 አንቀጽ 83/3/፣117 ስር በግልጽ እንደተደነገው የፍቺ ውጤት በስምምነት በሚያልቅበት ወይም በሽማግላዎች ወይም በባለሙያዎች በሚወሰንበት ጊዜ ውሳኔው ተፈጻሚነት የሚኖረው ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ ብቻ እንደሆነ፣ፍቺን እና የፍቺ ውጤትን በተመለከተ ውሳኔ የመስጠት እና የማጽደቅ ስልጣን የፍርድ ቤት ብቻ ስለመሆኑ እና ላላ ማንኛውም አካል በጉዲዩ ላይ ውሳኔ የመስጠትም ሆነ የማጽደቅ ስልጣን የላለው ስለመሆኑ አስገዲጅ በሆነ ቃል ተቀምጧል። በዚህም ጉዲይ አመልካች በስምምነት የንብረት ክፍፍል ያደረጉ ስለመሆናቸው ክርክር ያቅርቡ እንጂ ለፍርድ ቤት ቀርቦ የጸደቀ ወይም የተወሰነ ስለመሆኑ ያነሱት የክርክር ነጥብ የላለ ከመሆኑም በላይ በዚህ ነጥብ ላይ የተሰጠ ፍርድ የላለ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤት በፍሬ-ነገር ረገድ የተረጋገጠ ነጥብ ነው። አንድ የፍቺ ውጤት ደግሞ በህጉ አግባብ ለፍርድ ቤት ቀርቦ እስካልጸደቀ ድረስ በሽማግላዎች ፉት የተደረገ የንብረት ክፍፍል ስምምነት መኖሩን በማመላከት መከራከሪያ ማድረግ የማይቻል እና ህጉም ለእንደዚህ ዓይነት ስምምነት ጥበቃ የማያደርግ ስለመሆኑ ከላይ ከተመለከቱት የድንጋጌዎቹ ዓላማ፣ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም የተጠሪ የአፈጻጸም ሂደት የአመልካች ግማሽ ድርሻ ሳይነካ በፍርድ ባላዕዲው ግማሽ ድርሻ ላይ እንዱቀጥል መባለ የሚነቀፍበት አግባብ የለም ብለናል።
ባጠቃላይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የሰበር ሰሚ ችልት የተጠሪ የአፈጻጸም ክስ ሂደት የአመልካችን ግማሽ ድርሻ ሳይነካ በፍርድ ባለዕዲው በአቶ ዲውድ ዩሱፍ ግማሽ ድርሻ ላይ እንዱቀጥል በማለት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት በመዝ.ቁ.125214 በቀን 23-9-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ.93945 በቀን 26-5-2003 ዓ.ም በዋለዉ ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ጸንቷል።
ተጠሪ ያቀረበው አፈጻጸም የአመልካችን ግማሽ ድርሻ ሳይነካ በፍርድ ባለእዲዉ ግማሽ ድርሻ ላይ እንዱቀጥል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ሰኔ 06 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
No topics extracted.