No summary available.
ጥር 02 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አራጋው አበበ - ጠበቃ ደጉ መኮንን ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ራሓል ውብሸት - ጠበቃ ስንታየሁ በቀለ ጋር ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የባልና የሚስት የጋራ ሀብት ክፍፍልን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት ግራቀኙ የጋራ እና የግል በማለት ያቀረቡትን ክርክር በመስማት ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ፣ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በቃሉቲ ክ/ከተማ ክልል ውስጥ ገላን ሳይት ላይ የሕንጻ ቁ.133 ሆኖ የቤት ቁ.GA- B/33/01/11 የሆነውን ኮንደሚኒየም ቤት በተመለከተ ብቻ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት ሲያዝ በላልቹ ሀብቶች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ በማጽናት በመወሰኑ አመልካች የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት በማመልከታቸው የቀረበ ነው።
አመልካች ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለዋቸውን ነጥቦች ያቀረቡ ሲሆን በቀን 14-6-2003 ዓ.ም በሁለት ገጽ የተጻፈ የቅሬታ ፍሬ-ሃሳብ፡- በተሻሻለው የኢ.ፋ.ዳ.ሪ. የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 57 ድንጋጌ መሰረት ከጋብቻ በኋላ ያለግብይት በውርስ የተገኙ ንብረቶች በፍርድ ቤት እስካልተገለለ ድረስ የጋራ ንብረቶች ናቸው በማለት ውሳኔ መሰጠቱ፣በስር ፍርድ ቤት ክርክር የተነሳባቸው የባልና የሚስት ንብረቶች የትኞቹ የግል የትኞቹ የጋራ እንደሆኑ ያስረደልኛል ያልኳቸውን የሰው ምስክሮች እና በውርስ ንብረት ግምት የተገኘ ገንዘብ መሆኑን ያስረደልኛል በማለት በትዕዛዝ ይቅረብልኝ ያልኩት የጽሐፍ ማስረጃ አስቀርቦ ሳይመለከት ከፉል ውሳኔ በማለት መወሰኑ፣በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.182(2) መሰረት ዲኝነት ሳይጠየቅ የንግድ ቤት ትርፍ አመልካች ከቤት ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ልታካፍላት ይገባል በማለት ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረምልኝ የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ ቀርበው መልስ እንዱሰጡበት ታዞ መልስ የሰጡ ሲሆን ሚያዚያ 3 ቀን 2003 ዓ.ም በሶስት ገጽ የሰጡት የመልስ ፍሬ-ሃሳብ፡- አመልካች በውርስ ያገኘው ንብረት የጋራ እንደተባለ በማስመሰል ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፤የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሰጡት ግን በውርስ ተገኘ የተባለውን ንብረት የጋራ ሀብት ነው በማለት ሳይሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ ውስጥ የተቀመጠው ገንዘብ በውርስ ያገኘሁት ንብረት ለልማት ተብል ሲፈርስ መንግስት የሰጠኝ የካሳ ገንዘብ ነው ያለውን ሆኖ ነገር ግን ማስረጃ ያላቀረበበትን ገንዘብ የሚመለከት በመሆኑ፣ይህም ፍርድ ያረፈው በውርስ የተገኘን ንብረት በሚመለከት ሳይሆን በውርስ ሀብት ምትክ ካሳ ሆኖ ተከፈለ በተባለው ጥሬ ገንዘብ ላይ በመሆኑ፣የውርስ ሃብት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ተገኘ የተባለውን ጥሬ ገንዘብ የግል ሀብቴ ነው በማለት ክርክር ማቅረብ የሚችለው ደግሞ በፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 58 መሰረት ንብረቱ የግል ይባልልኝ በማለት በፍርድ ቤት በማስገለል ብቻ በመሆኑ፣በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ ያለው ገንዘብ ቀደም ሲል በተጠሪ ስም ከተከፈተ በኋላ በአመልካች ጉትጏታ በሁለታችን ስም የተደረገና በሁለታችን ጣምራ ፊርማ ብቻ የሚንቀሳቀስ የጋራ ሀብታችን በመሆኑ፣ በልላ በኩል የሰላዲ ቁ. 2-95871 የሆነን መኪና በውርስ ሀብት ግምት በተገኘ ገንዘብ የተገዛ ነው በማለት አመልካች ያቀረበውን ክርክር በተመለከተ አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መኪና በውርስ ነው ያገኘሁት የሚል ክርክር ያላቀረቡ በመሆኑ፣መኪናውም ጋብቻችን ጸንቶ በነበረበት ወቅት በግብይት የተገኘ በመሆኑ እና የግል ስለመሆኑም በፍርድ ቤት የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 58 በሚያዘው መሰረት ያላስወሰነ በመሆኑ እየቀረበ ያለው ክርክር ተቀባይነት የላለው በመሆኑ፣የንግድ ቤትን ትርፍ በተመለከተም ባቀረብኩት የጋራ ሀብት ዝርዝር ውስጥ የጋራ ሀብታችን ነው በማለት ካቀረብኳቸዉ መካከል አንደ እና ዋነኛዉ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። የአመልካች የመልስ መልስም ቀርቧል።
በግራቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ከታያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ አመልካች በውርስ ያገኘሁት ንብረት በልማት ምክንያት ፈርሶ ካሳ የተከፈለኝ ነው ያለውን ገንዘብ የጋራ ሀብት ነው የመባለን አግባብነት እና ላልችንም ተያያዥነት ያላቸውን ነጥቦች ለመመርመር በሚል በመሆኑ የተያዘው ጉዲይ ከዚሁ ጭብጥ አኳያ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት በግራቀኙ መካከል አከራካሪ የነበሩ እና ውሳኔ ያገኙ እንደዚሁም በበታች ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ ያለ በርካታ የፍቺ ውጤትን የሚመለከቱ የሀብት ክርክር ያለ ሲሆን በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት እያከራከረ ያለው እና የዚህን የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ የሚያሻው አመልካች የውርስ ሀብትን መሰረት ባደረገ የካሳ ክፍያ አገኘሁት የሚለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ የሚገኝ ብር 276,320 (ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ብር)፣ አመልካች ከዚሁ የውርስ ሃብት ከተገኘ ካሳ ገንዘብ ላይ ቀንሼ የገዛሁት ተሸከርካሪ ነው የሚለት የሰላዲ ቁ.2-95871 አ.አ. የሆነው እና ከንግድ ቤት የሚገኝን ገቢ በተመለከተ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል።
በመጀመሪያ ደረጃ የንግድ ቤት ትርፍ በተመለከተ ተጠሪ በግልጽ ዲኝነት ባልጠየቁበት ሁኔታ መወሰኑ አግባብነት የለውም በማለት በአመልካች የቀረበውን ክርክር ስንመለከት ተጠሪ ባቀረቡት መልስ በግልጽ ዲኝነት የጠየቁበት ስለመሆኑ ከመከራከራቸውም በላይ በፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ስንመለከት ከንግድ ድርጅቱ የሚገኘውን ገቢ ከቤት ከወጣሁበት ቀን ጀምሮ ልካፈል ይገባል በማለት ዲኝነት የጠየቁ በመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ ዲኝነት ሳይጠየቅበት የተወሰነ ነው በማለት ከፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.182(2) አኳያ የተነሳው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም በዚህ ነጥብ ላይ አመልካች ያነሱት ቅሬታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ላላው የውርስ ሀብት መሰረት ባደረገ የካሳ ክፍያ የገዛሁት ተሸከርካሪ ነው በማለት አመልካች የሚያነሱትን ክርክር በተመለከተ ተሸከርካሪው ግራቀኙ በጋብቻ ተሳስረው ባለበት ወቅት የተገዛ ስለመሆኑ አላከራከረም። መኪናው በጋብቻ ወቅት የተገዛ ከሆነ ደግሞ በቤተሰብ ህጉ በግብይት ስለተገኙ ሀብቶች በሚመለከት ድንጋጌ የሚገዛ ስለመሆኑ ግልጽ ነው። በተሻሻለው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ.
የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 58 መሰረት ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ አንደ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘዉ ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሽጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግል ሀብቱ ይሆናል በማለት በንኡስ አንቀጽ አንድ ስር ሲደነግግ በዚሁ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር ሁለት ስር ደግሞ በዚህ አንቀጽ ንኡስ ቁጥር አንድ ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ይባልልኝ ብል አንደኛው ወገን ጥያቄ ሲያቀርብ እና ፍርድ ቤት ሲያጸድቀው ብቻ ነው በማለት ይደነግጋል። በዚህ ነጥብ ላይ አመልካች ተሽከርካሪው የግለ እንዱባልለት ለፍርድ ቤት በማቅረብ ያጸደቀ ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክር የለም። አመልካች በህጉ በተቀመጠው መሰረት በፍርድ ቤት በጋብቻ ወቅት የተገዛው ተሽከርካሪ የግላቸው እንዱባልላቸዉ አቅርበው ያስወሰኑት ነገር በላለበት ሁኔታ በዚህ የፍቺ ውጤት ክርክር ላይ የግል ሀብት ነው በማለት ያነሱት ክርክር አግባብነት የላለው ነው ብለናል። በዚህ ነጥብ ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች በጋብቻ ወቅት የተገዛውን የሰለዲ ቁ.2-95871 አ.አ. የሆነው ተሽከርካሪ የጋራ ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ አለ የተባለውን ገንዘብ በተመለከተ እንደሚከተለው መርምረናል። አመልካች ከበታች ፍርድ ቤቶች ጀምሮ እየተከራከረ ያለው ገንዘቡ የተገኘው በውርስ የተላለፈልኝ ንብረት በልማት ምክንያት በመፍረሱ የተነሳ የተከፈለኝ ካሳ ነው በማለት ነዉ። ተጠሪ በበኩላቸው ገንዘቡ የጋራችን ነው፣ቀደም ሲል በራሳቸው ስም የተከፈተ እና በኋላ ግን በአመልካች ጉትጎታ በሁላታችን ፊርማ ብቻ እንዱንቀሳቀስ ያደረግነው የጋራ ሀብታችን ነው በማለት ይከራከራለ። አመልካች በበታች ፍርድ ቤት ይሄንን ያስረደልኛል የሚለትን ማስረጃዎች እንደቆጠሩና ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል በፍርድ ቤት ውሳኔ ያላስገለልክ በመሆኑ የሚያመጣው ለወጥ የለም በማለት ያለፊቸው ስለመሆኑ በቅሬታቸው አመላክተዋል። ችልቱም በዚህ ነጥብ ላይ የተነሳውን ክርክር እንደመረመረው አመልካች በተጠቀሰዉ ንግድ ባንክ አለ የሚለት በቀጥታ ከውርስ ሀብቱ የካሳ ክፍያ የተገኘ ነው በማለት በመሆኑ በፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 58 መሰረት በጋብቻ ወቅት በግብይት እንደተገኘ ንብረት በመቁጠር ቀደም ሲል የግልህ ስለመሆኑ ያላስገለልክ በመሆኑ በማስረጃ እንዱጣራ የሚፈቀድበት አግባብ የለም መባለ ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም አመልካች እየተከራከሩ ያለት በግብይት ስለተገኘው ሀብት ሳይሆን በቀጥታ ከውርስ ሀብቶች ለልማት ተብል በመፍረሱ ምክንያት ከተከፈለኝ ካሳ የተገኘ ነው በማለት በመሆኑ በግብይት ስለተገኙ ንብረቶች በሚመለከት በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 58 ስር የሚሸፈን አይደለም ብለናል። የአመልካች ክርክር የሚሸፈነው ከጋብቻ በኋላ በዉርስ በግለ ያገኘው ወገን የግል ንብረቱ ሆኖ ይቀጥላል የሚለውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 57 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም በዚህ ነጥብ ላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን ድንጋጌ በመጥቀስ አከራካሪ የሆነው ገንዘብ የውርስ ሀብት ስለመሆን ወይም አለመሆን አመልካች የማስረዲት መብት እንደላለው በመቁጠር መታለፈ ተቀባይነት የለውም ብለናል። አመልካች በዚህ ነጥብ ላይ ለማስረዲት ማስረጃ የቆጠረ ስለመሆኑ በቅሬታውም ያመላከተ ከመሆኑም በላይ በበታች ፍርድ ቤቶችም የተጠየቀ እና ፍርድ ቤቶቹ ቀድሞ በፍርድ ቤት የግለ ስለመሆኑ ባላስወሰነበት ሁኔታ የማስረጃዎቹ መሰማት የሚያመጣው ለውጥ የለም በማለት የታለፈ ስለመሆኑ ከውሳኔው መረዲት ይቻላል።
በዚሁ መሰረት ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ አለ የተባለው ጥሬ ገንዘብ የግል ሀብት ወይም የጋራቸዉ ሀብት ስለመሆን ወይም አለመሆን ግራቀኙ ባላቸው ማስረጃ ሉያጣራ ሲገባ ሳያጣራ ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የለውም። አመልካች ገንዘቡ የግል ስለመሆኑ ለማስረዲት የቆጠራቸውን ምስክሮች እና እንዱቀርቡለት የጠየቃቸውን የጽሐፍ ሰነድች በመስማት እና በማስመጣት እንደዚሁም የተጠሪን የማስተባበያ ማስረጃ በመስማት እና ፍርድ ቤቱም ለፍትሕ አሰጣጥ ተገቢ ነው የሚለውን ማስረጃ በመስማት ውሳኔ መስጠት ሲገባው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የቤተሰብ ህግ ድንጋጌ በመጥቀስ ማለፈ አግባብነት የላለው በመሆኑ እና የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የተፈጸመውን ስህተት ሳያርም ማለፈ ትክክለኛ አካሄድ ያለመሆኑን ተገንዝበናል። ባጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች በተጠቀሰው የንግድ ባንክ ያለውን ጥሬ ገንዘብ በተመለከተ ተገቢዉን ማጣራት ሳያደርጉ የደረሱበት መደምደሚያ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተዉን ዉሳኔ ሰጥተናል።
የፋደ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ. ቁ. 103132 በቀን 7-6-2003ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 78970 በቀን 7-4-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት አከራካሪ በሆኑት የሰለዲ ቁጥሩ 2-95871 አ.አ. የሆነ እና የንግድ ድርጅት ገቢን በተመለከተ የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ የሚገኘውን ጥሬ ገንዘብ በተመለከተ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.103132 በቀን 7-6-2003ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 78970 በቀን 7-4-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት የውሳኔ ክፍል በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሸሯል።
በጋብቻ ወቅት በግብይት የተገኘ ንብረት የግል ነው ተብል በፍርድ ቤት ካልተወሰነ በስተቀር የጋራ ሀብት ነው ተብል መወሰኑ እና ከጋራ የንግድ ድርጅት የተገኘ ገቢ የጋራ ነዉ መባለ በአግባቡ ነው ብለናል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪል ቅርንጫፍ የሚገኘውን ጥሬ ገንዘብ በተመለከተ የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ በመስማት እና ለፍትሕ አሰጣጡ አስፈላጊ ነው የሚለውን ማስረጃ በመስማት ገንዘቡ የጋራ ወይም የግል ስለመሆኑ በተመለከተ ተገቢዉን ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በዚህ ነጥብ ላይ ብቻ ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። በዚህ ችልት ውሳኔ ካገኙት ዉጪ ያለትን በተመለከተ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ አልተነካም።
በዚህ ችልት በቀን 25-6-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰጥቶ የነበረዉ የዕግድ ትዕዛዝ የሰለዲ ቁ. 2-95871 አ.አ. የሆነውን ተሽከርካሪ እና የንግድ ቤቱን ገቢ በተመለከተ ጉዲዩ እልባት ያገኘ በመሆኑ ተነስቷል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.