No summary available.
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ፍቅረ ዱን ሰይፈዱን - ጠበቃ ቴዎፍልስ ክፍለ ወንጌል ቀረበ ተጠሪዎች፡- 1- አበራ ለማ 2- ወ/ሮ ጋዱሴ ለማ ቀረበች 3- ወ/ሮ ጠጅቱ ለማ 4- ፍቃደ ለማ 5- ወ/ሮ ገላዬ ለማ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸምን መነሻ ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው አመልካች ሲሆን ፣ ክሱን የመሰረተው በ6-8-2001 ዓ.ም በተደረገው የሽያጭ ውል በብር 3ዐ,ዐዐዐ ቤት ሸጠውልኛል ባላቸው ገላዩ ለማ እና በቀለ ለማ በተባለት ሰዎች ላይ ነው። በወቅቱ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ክርክሩን ከሰማ በኋላ በውለ መሰረት ይፈጸም በማለት ውሣኔ ሰጥቶ እንደነበር እና በኋላ ደግሞ የአሁኖቹ ተጠሪዎች መቃወሚያ በማቅረባቸው መዝገቡ እንደገና ተንቀሳቀሶ ክርክር መስማቱን ከመዝገቡ ተመልክተናል። የአሁኖቹ ተጠሪዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መቃወሚያ ያቀረቡት የሽያጭ ውል የተደረገበት ቤት የእኛም የውርስ ድርሻ ያለበት በመሆኑ ከእኛ ስምምነት ውጪ የተደረገው ውል ይፍረስልን በማለት ነው። ፍ/ቤቱም የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ ፣ የቀድሞውን ውሣኔውን አፅንቶአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን የሰማ ሲሆን ፣ በመቀጠልም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አፅንቶአል። በመጨረሻም በወረዲው ፍ/ቤት ተቃዋሚ የነበሩት እነ አበራ ለማ ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ በማቅረባቸው በዚህ ደረጃ ክርክሩ የተሰማ ሲሆን ፣ ችልቱም የሽያጭ ውለን በማፍረስ ግራ ቀኝ ወገኖች ውለ ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት ይመለሱ በማለት ወስኖአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ታሕሣሥ 21 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን በማስቀረብ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው የቤት ሽያጭ ውለ እንዱፈርስ በሚል የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
አመልካች ከእሱ ጋር የቤት ሽያጭ ውል አድርገዋል የሚላቸውን ሰዎች የከሰሰው በሟች ወንድማቸው /አውራሻቸው/ ስም የሚገኘውን ቤት ስመሃብት እንዱያዛውሩለት ፤ ቤቱንም እንዱያስረክቡት እንዱወሰንለት ስለመሆኑ ለዚህ ሰበር ችልት ከአቀረበው የአቤቱታ ማመልከቻ ጭምር ለመገንዘብ ችለናል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕግ ቁጥር 358 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ መቃወሚያ ያቀረቡት ሰዎችም የሟች ወንድምና እህቶች እንደሆኑም አላከራከረም።
ተቃዋሚዎቹ መቃወሚያ ያቀረቡት ውለ የተደረገበትን ቤት ስመሃብት በአመልካች እንዱዛወር በማለት በተሰጠው ውሣኔ ላይ ቢሆንም፤ የጠየቁት ዲኝነት ግን ውለ እንዱፈርስ ይወሰንልን የሚል ነው። መቃወሚያው የቀረበለት የወረዲው ፍ/ቤትም ውለ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይፈርስም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ እንዲከራከረ እና በመጨረሻም ውለ አይፈርስም የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ የቀድሞውን ውሣኔ እንዲፀና ከሰጠው ውሣኔ ይዘት ተገንዝበናል።
በዚህ ውሣኔ ላይ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ያለት መቃወሚያ አቅራቢዎች ብቻ ናቸው።
አመልካች የውለ መፍረስ ወይም አለመፍረስን በሚመለከት ክርክር የሚደረግበት አግባብ ወይም ሥርዓት የለም በማለት የበኩለን ይግባኝ አላቀረበም። የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ውለ ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይፈርስም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ክርክሩን የሰማው በዚህ ምክንያት ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ የተፈጸመ የክርክር አመራር ስህተት የለም። ይህ የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልትም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት የሚመረምረው ከዚህ አንፃር እንጂ አመልካች መጀመሪያ አቅርቦት ከነበረው የውል ይፈጸምልኝ ወይም የስም ይዛወርልኝ ክስ አንፃር አይደለም።
አመልካች የሽያጭ ውል አድርጌበታለሁ የሚለው ቤት ተመዝግቦ የሚገኘው በሻጮቹ ስም እንዲልሆነ ከላይ ተመልክተናል። አመልካቹ ውለን አደረግሁ የሚለው ሻጮች ሆነው የቀረቡት ሰዎች የቤቱ ባለሃብት /ሟች/ ብቸኛ ወራሾች እኛ ነን ብለውኛል። የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትም አሳይተውኛል በማለት ስለመሆኑ ከሰበር አቤቱታ ማመልከቻው ለመገንዘብ ችለናል። እንደምንመለከተው ሻጭ የተባለት ሰዎች የሟች ወንድም እና እህት ከመሆናቸው ባለፈ በውርስ ሃብቱ ላይ ክፍፍል ስለመደረጉም ሆነ ቤቱ የውርስ ሃብት መሆኑ ቀርቶ ወደ ሻጮቹ ስለመዛወሩ አመልካች አላረጋገጠም። ውለን ያደረገው በዚህ መልክ ጥርት ያለ እና ግልጽ የሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ መሰረት በማድረግ /በመያዝ/ አይደለም። የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ውለ ፈራሽ ነው ለማለት የቻለውም ቤቱ የወራሾች የጋራ ሃብት ነው በማለት ነው። በበኩላችንም እንደምናየው የሰበር ችልቱ ከዚህ የተለየ መደምደሚያ ላይ መድረስ ነበረበት የምንልበት ምክንያት የለም።
ውርሱ ወይም የውርሱ ሃብት የውርሱ አከፊፈል እስኪፈጸም ድረስ በወራሾቹ መካከል ሳይነጣጠል እንደሚቆይ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1060/1/ ተደንግጎአል። የጋራ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ባልተከፊፈለት የውርስ ንብረቶች ላይ ያላቸው መብትም በፍትሐብሕር ሕጉ በአንቀጽ 8 ስለጋራ ባለሃብትነት፣ በአላባ ስለመጠቀም እና ስለላልች ግዙፍ መብቶች በማመላከት በተቀመጡት ድንጋጌዎች መሰረት እንደሚወሰን በዚሁ ቁጥር 1ዐ6ዐ/2/ ተመልክቶአል። በዚህ አግባብ የወራሾቹ ሁለ የጋራ ሃብት የሆነውን ንብረት ለመሸጥ፣ ለማስተላለፍ፤ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግልት ለመለወጥ የጋራ ባለንብረቶቹ ሁለ ስምምነት አስፈላጊ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1262 ተደንግጎአል። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው አመልካች የቤት ሽያጭ ውለን የተፈራረመው የጋራ ባለሃብት የሆኑትን ሰዎች ሁለ ስምምነት ሳያገኝ ነው። ውለ እንዱፈርስ ጥያቄ ያቀረቡት ስምምነታቸውን ያልሰጡት ላልች የጋራ ባለሃብቶች በመሆናቸው ውለ እንዱፈርስ በመወሰኑ ሕጉ በአግባቡ ተተርጉሞአል ነው ማለት የሚቻለው ። በመሆኑም አቤቱታው የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የምንልበት አግባብ የለም። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ. ጥቅምት 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቶአል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
የግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.