No summary available.
ታህሳስ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ በቀለ ቱፊ - ከጠበቃ ደጀኔ ታደሰ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ባዩሽ እሽቴ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት የክስ ማመልከቻ መነሻ ነው። የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው በባንክ ውስጥ ከገባው ገንዘብ ውስጥ በትዲር ጊዜ ወጥቶ ለአመልካች አባት ገንዘባቸው በአመልካች የተሰጠ ሆኖ እያለ እና በኦሮሚያ ክልል ለገዲዱ ግድብ ማዞሪያ አካባቢ የሚገኙ ሁለት የመኖሪያ ቤቶች የሶስተኛ ወገን ንብረቶች መሆናቸው ተገልፆ እያለ የጋብቻ ውጤቶች ናቸው ተብለው የጋራ ንብረቶች ናቸው በማለት አመልካችና ተጠሪ እኩል እንዱካፈለ በሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ሲለ አመልካች ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዲዩ አመጣጥም ሲታይ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ ተጠሪ የጋራ ናቸው የሚሎቸውን ንብረቶች አይነታቸውንና ብዛቸውን በመለየት ዘርዝረው አቅርበዋል። በዚህ ዝርዝር ውስጥም እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚያከራክሩት ንብረቶች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ቅርንጫፍ በአመልካች ስም በነበረው የሂሳብ ቁጥር ውስጥ የነበረ ብር 455,485.00 (አራት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር) እና በኦሮሚያ ክልል ለገዲዱ ግድብ ማዞሪያ አካባቢ የሚገኙት ሁለት መኖሪያ ቤቶች ሲሆኑ አመልካች በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር በእነዚህ ንብረቶች ላይ የሰጡት መከላከያ መልስ ከጥሬ ገንዘቡ ውስጥ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) ከባንኩ በጋብቻ ጊዜ ወጥቶ የአመልካች አባት ንብረት በመሆኑ በአመልካች መሰጠቱንና በአጠቃላይ ገንዘቡ በትዲር ጊዜ የወጣ በመሆኑ አመልካች እንደማይጠየቁበት የሚገልጽ ሲሆን አሁን የሚያከራክሩትን ቤቶችን በተመለከተ ደግሞ የአመልካች አባት ለልጅ ልጆቻቸው እንዱሆኑ የገዟቸው እንጂ የአመልካችና የተጠሪ የጋብቻ ውጤት ያለመሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ በበኩላቸው ደግሞ ጥሬ ገንዘቡን አመልካች ያላግባብ መውሰዲቸውን በመግለጽ ለትዲር ጥቅም ያለመዋለን ጠቅሰው እንዱሁም ቤቶቹ የጋራ ናቸው በማለት ተከራክረዋል። እነዚህን አከራካሪ ንብረቶችን በተመለከተ ክርክሩ በዚሁ መልኩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ጉዲዩን አጣርቶ በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር ውድቅ አድርጎ ንብረቶቹ የጋራ ስለሆኑ ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጥሬ ገንዘቡ የአመልካች አባት በመሆኑ ከባንክ በትዲር ጊዜ ወጥቶ በአመልካች የተወሰደ ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ አመልካች ግማሹን ለተጠሪ እንዱከፍለ ተብል መወሰኑም ሆነ ቤቶቹን በተመለከተ የሶስተኛ ወገኖች ንብረቶች መሆናቸው ተገልጾ እያለ አመልካችና ተጠሪ እኩል እንዱካፈለ ተብል መወሰኑ በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎችን ከቤተሰብ ሕጉ ጋር ባላገናዘበ ሁኔታ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ግራ ቀኙ በትዲር ውስጥ እያለ ከባንክ ወጪ የተደረገን ብር እና በሶስተኛ ወገን ስም ያለ ንብረት ይካፈለ መባለ በአግባቡ ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በአከራካሪ ንብረቶች ላይ የተሰጠው ውሳኔ ማስረጃውንና ሕጉን መሰረት ያደረገ መሆኑን ዘርዝረው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ሲለ የተከራከሩ ሲሆን አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መሰረት ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አኳያ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ የፈረሰው ጥቅምት 02 ቀን 2002 ዓ.ም. እንደሆነና እንደዚሁም ለዚህ ሰበር ችልት ለቀረበው ክርክር ምክንያት የሆነው ጥሬ ገንዘብ ከባንኩ የወጣው መጋቢት 10፣14፣16 ቀን 2001 ዓ.ም.
መሆኑን ነው። ከገንዘቡ ውስጥ አመልካች ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) ከባንኩ በትዲር ጊዜ ያወጡት መሆኑን ሳይክደ አጥብቀው የሚከራከሩት ገንዘቡ የአመልካች አባት በመሆኑ ከባንክ አውጥተው ለአባታቸው የሰጡ በመሆኑና በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሚያዚያ 23 ቀን 2000 ዓ/ም ስምምነት ሲደረግም ገንዘቡ ከባንክ ስለመኖሩ ሳይጠቀስ መታለፈ ገንዘቡ የጋራ ንብረት ያለመሆኑን ያሳያል በማለት ነው። ይሁን እንጂ አመልካች አለ የሚለት የሚያዚያ 23 ቀን 2000 ዓ/ም ስምምነት በግራ ቀኙ የንብረት ክርክር ላይ በታች ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው የማስረጃው ክብደት ተመዝኖ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት ስለሚገለጽ ይህንን ማስረጃ መሰረት አድርጎ የሚቀርበው የአሁኑ ክርክር የሚሆነው የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዘና ጉዲይ ነው። ጉዲዩ የፍሬ ነገር ማጣራትና የማስረጃ ምዘና ጉዲይ ከሆነ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት በዚህ ችልት የሚታይ ጉዲይ አይሆንም። ምክንያቱም የማስረጃ ምዘና መሰረታዊ የሆነ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ጉዲይ አይደለምና ነው። በዚህም ምክንያት አመልካች ሚያዚያ 23 ቀን 2000 ተደረገ የተባለውን ስምምነት መሰረት አድርገው ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
የሚያዚያ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ስምምነት ተቀባይነት ያጣበት ምክንያት በዚህ ችልት ላታይ የሚችል አይደለም ከተባለ በጋብቻ ውጤቱ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል።
በዚህም መሰረት አመልካች ብዛቱ ብር 455,485.00 (አራት መቶ ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር) የጋራ ስለመሆኑ ሚያዚያ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. በተደረገው ስምምነት አልተገለጸም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ስምምነቱ በበታች ፍርድ ቤቶች በማስረጃነቱ ተመዝኖ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ በዚህ ችልት ተቀባይነት የሚያገኝበት አግባብ የለም። ላላው አመልካች ጥሬ ገንዘቡን ከባንክ ማውጣታቸውን ሳይክደ ለተጠሪ ላካፍል አይገባም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ገንዘቡ የላላ ሰው በመሆኑ ከባንክ አውጥቼ ሰጥቼአለሁ የሚል ነው። ነገር ግን ገንዘቡ ትዲሩ ጸንቶ ባለበት ጊዜ በአመልካች ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የነበረና አመልካች ከባንኩ አውጥተው ለአባታቸው የሰጡት መሆኑ ያልተካደ ከመሆኑም በላይ ለትዲር ጥቅም ውሎል የሚል ክርክር አመልካች ያላቀረቡ በመሆኑ በትዲር ጊዜ የነበረ ንብረት የጋራ ስለመሆኑ ሕጉ ግምት የሚወስድበት ጉዲይ ስለሆነ የአመልካች ክርክር ሕጋዊ መሰረት የለውም። አመልካች ገንዘቡን ለላላ ሰው አሳልፈው መስጠታቸው እስካልተካደ ድረስ ገንዘቡ በትዲር ጊዜ ከባንክ በመውጣቱ ብቻ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ ሕጉ ግምት የሚወስድበትን አግባብ አመልካች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ምክንያት የለም። በትዲር ጊዜ ገንዘቡ ወይም ንብረቱ ከወጣ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ ሕጉ ግምት የሚወስደው የጋራ ንብረትን ለላላ ሰው አሳልፍ መሰጠቱ የተረጋገጠበትን ሁኔታ ሁለ ስላለመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 85-93 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነውና።
በመሆኑም ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) አመልካች ከባንክ አውጥተው ለአባታቸው መስጠታቸውን ካለመካዲቸውም በላይ አመልካች የዚሁ ገንዘብ ባለቤት ናቸው የሚሎቸው አባታቸውም የገንዘቡ ባለቤት የሆኑበት አግባብ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ግማሹን የማይከፍለበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ ሆኖ አግኝተናል።
ላላው ብር 55,485.00 (ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር) የሚመለከት ሲሆን ይህ ገንዘብም ትዲሩ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ከባንክ መውጣቱ ያልተካደ ሲሆን አመልካች ይህንኑ የገንዘብ መጠን ለላላ ሰው መስጠታቸውን አልገለፁም። በጋብቻ የተፈራ ገንዘብ ትዲሩ ጸንቶ ባለበት ጊዜ ወጪ መሆኑ ከተረጋገጠ ለትዲር ጥቅም እንደዋለ የባልና ሚስትን ሃብት ስለማጣራት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 85-93 ካለት ድንጋጌዎች አንጻር የሕግ ግምት መውሰድ ይቻላል። በዚህ የሕግ ግምት ተጠቃሚ የሆነ ወገንም ንብረቱ በጋብቻ ጊዜ የተሸጠ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከሆነ በትዲር ጊዜ የወጣ መሆኑን ካስረዲ በቂ ሲሆን ላላው ወገን ደግሞ ጋብቻው በፍቺ በፈረሰ ጊዜ ከንብረቱ የሽያጭ ገንዘብ ወይም የጋራ የሆነ ላላ ጥሬ ገንዘብ በሙለ ወይንም በከፉል የሚገኝ መሆኑን ወይም ያላግባብ አንደኛው ተጋቢ ያባከነው መሆኑን በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካስረዲ የሽያጩ ገንዘብ ወይም ላላ የጋራ የሆነ ጥሬ ገንዘብ በጋብቻ ጊዜ ለጋራ ጥቅም ውሎል የሚለውን የሕግ ግምት እንዲፈረሰ ይቆጠራል።
አመልካች ለክርክሩ መነሻ ምክንያት ከሆነው ጥሬ ገንዘብ ውስጥ ብር 55,485.00 (ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) በጋብቻ ጊዜ ከባንክ የወጣ መሆኑን በማስረዲት የሽያጩ ገንዘብ ለጋራ የትዲር ጥቅም እንደዋለ ሕጉ ለወሰደው ግምት ተጠቃሚ ሆነዋል። በልላ በኩልም ተጠሪ ጋብቻው በፈረሰ ጊዜ ይኸው ጥሬ ገንዘብ በሙለ ወይንም በከፉል በአመልካች እጅ እንደሚገኝ ወይም አመልካች ያላግባብ የወሰደት ስለመሆኑ ያላስረደ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልፅ ያሳያል። እንዱህ ከሆነ ተጠሪ የሕግ ግምቱን ማፍረስ አልቻለም። በመሆኑም አመልካች የብር 55,485.00 (ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር) ግማሽ ለተጠሪ እንዱመልሱ የሚገደደበት ሕጋዊ ምክንያት በላለበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
ላላው አመልካች የሚከራከሩበት ነጥብ በኦሮሚያ ክልል ለገዲዱ ግድብ ዙሪያ አካባቢ ይገኛለ የተባለትን ሁለት መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ነው። አመልካች እነዚህ ቤቶችን ለተጠሪ ላካፍል አይገባም የሚለት ቤቶቹ የላላ ሶስተኛ ወገን ንብረቶች ናቸው በሚል ነው። እነዚህ ሶስተኛ ወገኖች የሚባለት ደግሞ ከአመልካችና ከተጠሪ አብራክ የተወለደ ልጆች ሲሆን ቤቶቹን ለእነዚህ ሕጻናት ገዙ የሚባለት የአመልካች አባት ናቸው። ይሁን እንጂ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ቤቶቹ የጋብቻ ውጤት ያለመሆናቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ያላቀረቡ መሆኑን አረጋግጧል፣ በአመልካች ምስክሮችም ጭምር ያለመመስከሩንም ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ በግልፅ አስቀምጧል። ይህ ፍሬ ነገር በይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሙለ በሙለ ተቀባይነት አግኝቷል። እንደዚሁም አመልካች የቤቶቹ ባለቤቶች የሚሎቸው ወገኖች ወይም በእነርሱ በሕጉ አግባብ የተወከለ ሰዎች በሕጉ አግባብ ያቀረቡት ክርክርም የለም። በመሆኑም ቤቶቹ የላላ ሶስተኛ ወገን ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ አመልካች ቤቶቹ የጋራ አይደለም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሚያገኝ ሆኖ አላገኘነውም።
በትዲር ጊዜ በጋራ የተገኘ እና የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ስለመኖሩ የተረጋገጠ ማናቸውም ንብረት የባልና ሚስት የጋራ ስለመሆኑ ሕጉ ግምት የሚወስድበት ጉዲይ መሆኑን ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀፅ 63(1) ድንጋጌ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው።
በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ተሻሽል ሉወሰን የሚገባው ሆኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዲር 15 ቀን 2003 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 103845 በ27/07/2003 በትእዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች የብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) ግማሽ ገንዘብና በኦሮሚያ ክልል ለገዲዱ ግድብ ዙሪያ አካባቢ የሚገኙትን ሁለት መኖሪያ ቤቶችን ለተጠሪ እንዱያካፍለ ተብል መወሰኑ ተገቢ ነው ብለናል።
ብር 55,485.00 (ሃምሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) አመልካች ለተጠሪ ሉያካፍለ አይገባም ብለናል።
በላልች ንብረቶች ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.