No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - ትእግስት አሰፊ ቀረበች ተጠሪ፡- ወ/ሮ እመቤት ቱርፋ - ወኪል አደፍርሰው ዘውዳ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በብድር የተወሰደን ገንዘብ ለማስመለስ የቀረበውን ክስ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ፣ ክሱ የተመሰረተው ባልና ሚስት በሆኑት አቶ አደፍርሰው ዘውዳ እና በአሁኑዋ ተጠሪ ላይ ነው። ተከሣሾች ገንዘቡን የወሰደት ለእህል ንግድ ሥራ እንደሆነ እና በወቅቱ አጠናቀው ባለመክፈላቸው በቀሪ የሚፈለግባቸውን ገንዘብ ከእነ ወለደ እንዱከፍለት ይወሰንለት ዘንድ አመልካች ጠይቆአል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም የተከሣሾችን የመከላከያ ክርክር ከሰማ በኋላ፣ የአሁንዋን ተጠሪ /ሚስት/ በብድር ውለ ላይ ስለመፈረምዋ አልተረጋገጠም በማለት ከእዲው ነፃ አድርጎአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምለት ዘንድ ጠይቆአል። እኛም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ተጠሪ በብድር የተወሰደውን ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም የተባለው በሕጉ አግባብ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ይህን ጭብጥ ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር ፤ አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ተጠሪ የተከሰሰችው ከባለቤትዋ ጋር በመሆን እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል። ባለቤትዋ የሆነው አቶ አደፍርሰው ዘውዳ ዕዲው ይመለከተዋል ተብል በፍ/ቤት ተወስኖበታል። ተጠሪ ስትከራከር የቆየችው ባለቤቴ ገንዘቡን አልተበደረም በማለት ሳይሆን፣ በብድር ውለ ላይ አልፈረምኩም በማለት ነው። ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም በፊርማው ላይ ብቻ በመመሥረት እና ይህንኑ በላብራቶሪ አስመርምሮ የመጣለትን ውጤት እንደብቸኛ እና ፍጹማዊ የሆነ ማስረጃ በመቁጠር ተጠሪን ከእዲው ነፃ አድርጎአል። አመልካች ከፊርማው በተጨማሪ ውለ ሲፈረም የነበሩ እማኞች በምስክርነት እንዱሰሙለት ስለመጠየቁም ከመዝገቡ ተመልክተናል። ፍ/ቤቱ ግን ክሱን የሰማው ፊርማውን በተመለከተ የመጣለትን የላብራቶሪ ውጤት እንደብቸኛ ማስረጃ በመቁጠሩ ምስክሮቹን አልሰማም። በልላም በኩል ብድሩ የተወሰደው ለንግድ ሥራ ነው። የተጠሪ ባለቤት ነጋዳ ነው። በመሆኑም ጉዲዩ በንግድ ሕግ ቁጥር 19 ከተቀመጠው ድንጋጌ ጋር ተገናዝቦ ይታይልኝ በማለት ከአመልካች ለቀረበው ክርክርም ዋጋ አልሰጠም። አመልካች የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው በማስረጃው አቀባበል እና በንግድ ሕጉ የተመለከተውን ድንጋጌ አተረጓጎም በሚመለከት ነው። ተጠሪም ሁለቱን ነጥቦች መሰረት በማድረግ ክርክርዋን /መልስዋን/ አቅርባለች።
እንደምናየው አቶ አደፍርሰው ዘውዳ እና ተጠሪ ባልና ሚስት ስለመሆናቸው አላከራከረም።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ገንዘብ በብድር የተወሰደው ለእህል ንግድ ሥራ እንደሆነ እና አቶ አደፍርሰው ዘውዳም ነጋዳ ስለመሆኑም እንደዚሁ ክርክር የተነሳበት አይደለም። ተጠሪ እዲው አይመለከተኝም የምትለው ባለቤቴ /አቶ አደፍርሰው ዘውዳ/ ከአመልካች የተበደረው ገንዘብ የለም፣ ወይም የተበደረው ለንግድ ሥራ ማስኬጃ አይደለም፤ ወይም ደግሞ ነጋዳ አይደለም በማለት ሳይሆን፣ የኔ ስምምነት እስከላለ ድረስ ከብር 500/ አምስት መቶ ብር/ በላይ ለሆነው ብድር ተጠያቂ አይደለሁም፣ በብድር ውለ ላይ አልፈረምኩም፣ በንግድ ሕግ ቁጥር 19 የተቀመጠው ድንጋጌ በተሻሻለው የፋዳራል ቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ተሽሮአል የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ነው።
አመልካች ከሥር ጀምሮ እየተከራከረ ያለው ተጠሪም ከባለቤትዋ ጋር በመሆን በብድር ውለ ላይ ፈርማለች። ፊርማውን በሚመለከት ከባለሙያ የተሰጠው አስተያየት ብቻውን በብድር ውለ ላለመስማማቷ /ላለመፈረሟ/ ብቸኛ እና የተሟላ ማስረጃ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። በብድር ውለ ላይ አልፈረመችም የሚባል እንኳን ቢሆን በንግድ ህጉ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት ዕዲው እስዋንም ይመለከታል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪን ከእዲው ነፃ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም። ውሣኔው ሕግን መሰረት ያደረገ አይደለም በማለት ነው።
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍ/ቤትም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ተጠሪን ከእዲው ነፃ ያደረጉአት በብድር ውለ ላይ ያለው ፊርማ የእሷ ስለመሆኑ በባለሙያ ሉረጋገጥ አልቻለም በማለት እና ይህ ከባለሙያ የመጣውን አስተያየት እንደብቸኛ ማስረጃ በመውሰድ ነው። ፍ/ቤቶቹ ላልቹን የአመልካች ማስረጃዎች አልሰሙም ወይም የባለሙያው አስተያየት ከላልች ማስረጃዎች ጋር በማገናዘብ አልመዘኑም። የተካደን ፊርማ ለማጣራት የባለሙያ አስተያየት መጠየቁ አግባብ አይደለም የሚባል አይደለም። በልላ በኩል ደግሞ የአንድ ሰው ፊርማ በተለያዩ ምክንያቶች ሉለዋወጥ የሚችልበት ሁኔታም ስለሚኖር ላልች ተጨማሪ ማስረጃዎች ሳይሰሙ እንደበቂና ብቸኛ ማስረጃ ተደርጎ መወሰደ አግባብ አይሆንም። ይህ የሰበር ችልትም እነዚህን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስግባት በሰበር መ/ በሰጠው ውሣኔ ፊርማን በሚመለከት የሚቀርበው የባለሙያ አስተያየት እንደመጨረሻ ማስረጃ /conclusive evidence/ ተደርጎ ሉወሰድ አይገባም እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ፊርማውን በሚመለከት ከባለሙያ የቀረበላቸውን አስተያየት ብቻ መሰረት በማድረግ መወሰናቸው ተገቢ አይደለም። ይህ እንግዱህ በዚህ አግባብ የሚታይ ሲሆን ፣ ቀጥል መታየት ያለበት ተጠሪ በብድር ውለ ተዋዋይ አልነበረችም ቢባልስ ከእዲው ከነጭራሹ ነፃ ነች ወይም እዲው እሷን አይመለከትም ወደሚለው ድምዲሜ ከመደረሱ በፉት ሉመረመር የሚገባው የሕግ ነጥብ የለም ወይ? የሚለው ነው።
ተደጋግሞ እንደተገለጸው ብድሩ የተወሰደው ለንግድ ሥራ ማስኬጃ ነው። የሚነግደው ባል ወይም ሚስት የተዋዋለው እዲ እንደባልና ሚስት ዕዲ እንደሚቆጠር በንግድ ሕግ ቁጥር 19 ተደንግጎአል። በዚህ የንግድ ሕግ ድንጋጌ የባልና ሚስት ዕዲን በተመለከተ የተደነገገው የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 659 ተጠቅሶአል። በልላ በኩል ደግሞ በፍትሐብሕር ሕጉ መጽሐፍ ተካቶ የነበረው የቤተሰብ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 213/92 በመሻሻለ ወይም እራሱን የቻለ የተሻሻለ የፋዳራል ቤተሰብ ሕግ በመውጣቱ በአሁኑ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 659 የተቀመጠው ድንጋጌ ስለባልና ሚስት የጋራ ዕዲን በሚመለከት ለሚቀርበው ክርክር አወሳሰን በዋቢነት ሉጠቀስ አይችልም። በንግድ ሕጉ የተቀመጠው ድንጋጌ ቁጥር 19 ግን በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ተሽሮአል። የሚባልበት የሕግ አግባብ የለም። በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግም ቢሆን በአንቀጽ 70 ስለባልና ሚስት ዕዲ በሚመለከት የተደነገገ በመሆኑ ልባል የሚችለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 659 የተቀመጠው ድንጋጌ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 7ዐ ተተክቶአል ነው። ከባል ወይም ከሚስት በግል የሚጠየቅ ዕዲ ከባለዕዲው ተጋቢ የግል ሃብት ፣ የግል ሃብቱ ዕዲውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከጋራ ሃብታቸው እንደሚከፈል በተጠቀሰው አንቀጽ 7ዐ/1/ የተመለከተ ሲሆን ፣ ዕዲው የመጣው ለባልና ሚስቱ ትዲር ጥቅም ከሆነ ደግሞ ከጋራ ሃብታቸው ፣ የጋራ ሃብታቸው ዕዲውን ለመሸፈን በቂ በማይሆንበት ጊዜ ከባል ወይም ከሚስት የግል ሃብት እንደሚከፈል በንኡስ አንቀጽ 2 ተደንግጎአል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ዕዲ በብድር የተወሰደው ባልናሚስቱ ለሚተዲደሩበት የንግድ ሥራ ማካሄጃ ነው። ቀደም ሲል እንዲመለከትነው የተጠሪ ክርክር ዕዲውን ያመጣው ባለቤቴ ነው ከማለት ባለፈ የንግድ ሥራው የጋራ መተዲደሪያችን አይደለም የሚል አይደለም። በበኩላችን እንደምንገነዘበው ከአመልካች ባንክ በብድር የተወሰደውን ገንዘብ የባልናሚስቱ የጋራ መተዲደሪያ ለሆነው የንግድ ሥራ እንዱውል የተወሰደ በመሆኑ የባልና ሚስቱ የጋራ ዕዲ ነው። በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪን ከወዱሁ ከዕዲው ነፃ በማድረግ የሰጡት ውሣኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ አይደለም። አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ተጠሪን የመክሰስ መብት የለውም በማለት በመ. ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና ይህን ውሣኔ በማፅናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. የካቲት 1ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ክስ የቀረበበት ገንዘብ ብር 348,024.54 /ሶስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሃያ አራት ብር ከሃምሣ አራት ሣንቲም/ የባልና ሚስቱ /የአቶ አደፍርሰው ዘውዳ እና የተጠሪ/ የጋራ ዕዲ በመሆኑ ተጠሪ ከዕዲው ነፃ የምትሆንበት ምክንያት የለም ብለናል። በዚህ መሰረትም ገንዘቡን ከነወለደ ተጠሪ ከባለቤትዋ አቶ አደፍርሰው ዘውዳ ጋር በመሆን እንድትከፍል ወስነናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ። ውሣኔው ዛሬ ታሕሣሥ 18 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በችልት ተነገረ ። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.