No summary available.
ሕዲር 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ፍቅሬስላሴ እሽቴ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዋጋዬ ጋይም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኗ ተጠሪ በአመልካች ላይ ሚያዚያ 17 ቀን 2002 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የክሱ ይዘትም ከአመልካች ጋር ከ22/05/1968 ዓ/ም ጀምሮ ተጋብተው ሲኖሩ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 05 ክልል ውስጥ የቤት ቁጥር 504 የሆነውን ቤት በጋራ እንዲፈሩ እንዱሁም ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ተለያይተው በመኖራቸው የተነሳ ጋብቻቸው በራሱ ጊዜ እንደፈረሰ ገልጸው በጋብቻ ወቅት በጋራ አፈራነው ያለትን ቤት በተመለከተ የክፍፍል ውሳኔ እንዱሰጥላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም ከተጠሪ ጋር ጋብቻ መስርተው የቆዩ መሆኑ የማይካድ መሆኑን፣ቤቱን ግን በጋብቻ ወቅት በጋራ ስለመፈራቱ ተጠሪ ያቀረቡት ማስረጃ የላለ መሆኑን፣ቀደም ብል ፍርድ ቤት ቀርቦ በነበረው ጉዲይም በፍቺ ጥያቄው ላይ የተሰጠ ውሳኔ የላለ መሆኑንና አመልካችና ተጠሪ ሳይራራቁ እየተጠያየቁ እንደሚኖሩ እንዱሁም ግራ ቀኙ ተነጋግረው በግል መፍትሄ ለጉዲዩ ለመስጠት እንደሚችለ ገልፀው ተከራክረዋል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮና ቤቱን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ማጣሪያ ማስረጃ እንዱቀርብ ከአደረገ በሁዋላ አመልካችና ተጠሪ ጋብቻ የመሰረቱት ጥር 22 ቀን 1968 ዓ.ም. መሆኑን፣አከራካሪው ቤት የተሰራው ደግሞ በ1974 ዓ/ም መሆኑን መረጋገጡን፣አመልካች ቤቱን ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ከመፈጸሙ በፉት ወይም ተለያይተው መኖር ከጀመሩ በሁዋላ ያፈሩት ስለመሆኑ ያላስረደ መሆኑ መረጋገጡን በመዘርዘር ቤቱ የጋራ ነው በማለት እኩል እንዱካፈለ ሲል በሕጉ የተመለከተውን የአከፊፈል ሥርዓት በመግልጽ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካችና ተጠሪ ለረዥም አመታት ተለያይተው የኖሩ በመሆኑ የፍቺ ውሳኔ አይሰጥም ተብል በስር ፍርድ ቤት በመ/ ውሳኔ ከተሰጠ በሁዋላ የፍቺ ውጤት የሆነው ንብረት ላይ ግን ክፍፍለ ይቀጥላል ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለት ጉዲዩ በይርጋ የሚታገድ ነው ተብል እንዱወስንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በአመልካችና በተጠሪ መካከል በመ/ ላይ ጋብቻ የለም ተብል ተወስኖ እያለ በዚሁ ጉዲይ የፍቺ ውጤት የሆነው የንብረት ክፍፍል በተጠሪ በኩል በመቅረቡ ምክንያት የስር ፍርድ ቤት የቤት ቁጥር 504 የሆነ የጋራ ሃብት ነው በማለት እኩል እንዱካፈለ ሲል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።ከዚኅም በኋላ ተጠሪ በክርክር ላይ እንዲለ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው በመገለፁ ለወራሾቻቸው በጋዜጣ ጥሪ የተደረገላቸው ቢሆንም አልቀረቡም።እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት የመ/ ቀርቦ የግራ ቀኙ ክርክር እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ በ22/05/1968 ዓ.ም. ጋብቻ ፈፅመው አከራካሪው ቤት በ1974 ዓ.ም. የተሰራ መሆኑን፣አከራካሪውን ቤት አመልካች ከጋብቻ በፉት የሰሩት ወይም ከተጠሪ ጋራ በስምምነት ተለያይተው መኖር ከጀመሩ በሁዋላ ያፈሩት ንብረት ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ የላለ መሆኑን፣ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በመ/ በሆነው የፍቺ ጥያቄ አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ ሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ግራ ቀኙ ተለያይው መኖር ከጀመሩ ረዥም ጊዜ መሆኑ መረጋገጡን በምክንያትነት በመያዝ ጋብቻው በራሱ ጊዜ የፈረሰ በመሆኑ የፍቺ ጥያቄ የሚቀርብበት ጉዲይ አይደለም በማለት ጥቅምት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. በዋለው ችልት መወሰኑን፣ከዚህም በሁዋላ ተጠሪ የጋራ ንብረት ነው ያለትን አከራከሪውን ቤት ለመካፈል ይወሰንላቸው ዘንድ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ በልላ መዝገብ (በመ/) በሆነው ለስር ፍርድ ቤት አቅርበው አመልካች እንዱቀርቡ ተደርጎ ግንቦት 07 ቀን 2001 ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት የመከላከያ መልስ የፍቺ ውሳኔ በላለበት ሁኔታ የንብረት ክፍፍል የሚቀርብበት አግባብ የለም በማለት መከራከራቸውን ነው።በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት የፍቺ ውሳኔ በላለበት ሁኔታ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ በሕጉ ከተዘረጋው ሥርዓት ውጪ ከመሆኑም በላይ ጉዲዩ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ሲሆን ተጠሪ ደግሞ የስር ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ጋብቻው በራሱ ስለፈረሰ በፍርድ ቤት የሚሰጥ የፍቺ ውሳኔ የለም በማለት መወሰኑ የጋብቻውን ውጤት ከመጠየቅ የማይከለክል ነው፣ይርጋውን በተመለከተ ደግሞ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያላነሱት ሰበር ሰሚ ችልት ሲደርሱ ሉያነሱ የሚችለበት ሥርዓት የለም በማለት በጽሁፍ ክርክር ወቅት ተከራክረዋል።እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የስር ፍርድ ቤትን ዋና መዝገብ በመመልከትና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ ጉዲዩን መርምረነዋል።
በመሰረቱ ጋብቻ በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በተግባር ተጋቢዎች ተለያይተው በየፉናቸው የራሳቸውን ህይወት መኖር ከቀጠለ ሉፈርስ እንደሚችል ከተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 76 ድንጋጌና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀፅ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ከሰጠበት የመ/ ውሳኔ መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።ጋብቻ ከላይ በተመለከተው የቤተሰብ ሕጉ ድንጋጌ ወይም የሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ከፈረሰ የጋብቻ ውጤት የሆነው ንብረት በፍርድ ቤት ውሳኔ መፍትሓ የማያገኝበት ምክንያት የለም። ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በራሱ ጊዜ የፈረሰ ነው ተብል በስር ፍርድ ቤት በመ/ ውሳኔ ማግኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን ይህ ውሳኔ ግን የጋብቻ ውጤትን በተመለከተ በፍርድ ቤት የዲኝነት ጥያቄ ከማቅረብ የሚከለክልበት የሕግ አግባብ የለም። ምክንያቱም የጋራ ንብረት ጥያቄ የግድ በፍርድ ቤት የፍቺ ውሣኔ ከተሰጠ በሁዋላ መቅረብ ያለበት ጉዲይ ስለመሆኑ የቤተሰብ ሕጉ አያሳይም።ስለሆነም ፍቺው ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጪ በሆነ መንገድ በተግባር የተከናወነ (Defacto divorce)መሆኑ የጋብቻውን ውጤትን በተመለከተ በፍርድ ቤት ዲኝነት ከመጠየቅ የማይከለክል ሲሆን ዋናውና መታለፍ የላለበት ነገር የክፍፍለ ጥያቄ በሕጉ በተዘረጋው የጊዜ ገደብ ውስጥ መቅረቡ መረጋገጡ ላይ ነው። በልላ አገላለፅ በተግባር ፍቺ ያከናወኑ ተጋቢዎች የጋብቻውን ውጤት በተመለከተ ለፍርድ ቤት ክፍፍለን ማቅረብ ያለባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1677(1) እና 1845 ስር በተመለከተው የአስር አመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ላሆን ይገባል።የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ከጋብቻ መፍረስ በሁዋላ በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ ቀሪ መሆን ያለበት መሆኑን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ ላይ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታልና። ይርጋውን ተመለከተ ደግሞ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው የሚለው ወገን በስርዓቱ መሰረት በግልፅ አንስቶ መከራከር የሚጠበቅበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234(1(ሐ)) እና 244(2(ሰ)) ድንጋጌዎች ያሳያለ። ይርጋን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በራሱ ሉያነሳው የማይችለው ጉዲይ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1856(2) ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የመከላከያ መልስ ሥርአቱን ጠብቀው የይርጋን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አላቀረቡም።አመልካች በስር ፍርድ ቤት አንስተው የተከራከሩት መሰረታዊው ነጥብ የፍቺ ውሣኔ ላሰጥ አይገባም ተብል በፍርድ ቤት ከተወሰነ በሁዋላ የጋብቻ ውጤት ላይ ክስ መመስረት ሕጋዊ አግባብነት የለውም የሚል ብቻ ነው።ይህ ደግሞ ይርጋውን አንስተው መከራከራቸውን የሚያሳይ አይደለም።ስለሆነም አመልካች በስር ፍርድ ቤት ሥርአቱን ጠብቀው ያላነሱትን የይርጋ ክርክር በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሚያነሱበት አግባብ የላለ መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329(1) ድንጋጌ ያስገነዝባል።ሲጠቃለልም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም.
ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 13 ቀን 2002 ዓ.ም.
በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የአምስት የማይነበብ ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.