No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 06 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ብርሃኑ ከፍያለው ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ሮማን ይርጋ/ 11 ሰዎች/
ጉዲዩ በፍርድ ቤት የተቋቋመ የውርስ አጣሪ አበል መጠን ሉወሰን የሚችልበትን ሕጋዊ አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው ወ/ሮ ሮማን ይርጋ ፣ ወ/ሮ ቅድስት ይርጋ እና ወ/ሮ ቆንጂት ይርጋ አመልካች ፣ አቶ መስፍን ይርጋ ደግሞ ተጠሪ ፣ እነ አቶ ተፈሪ ይርጋ ስድስት ሰዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ ሁነው በተካሄደው የሟች አቶ ይርጋ እንደታ የውርስ ንብረት ማጣራት ክርክር ሲሆን የውርስ ይጣልራልኝ ጥያቄ ያቀረቡት የስር አመልካቾች እነ ወ/ሮ ሮማን ይርጋ ሶስት ሰዎች ናቸው። ጥያቄው የቀረበለት የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤትም የአሁኑን አመልካች የውርስ ሃብቱን ለማጣራትና ለማስተዲደር የሾሟቸው ሲሆን አመልካች የውርስ ሃብቱን አጣርተው የውርስ ሃብት ሪፕርቱን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። ሪፕርቱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በተጣራው የውርስ ሪፕርት ላይ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዱሰጡበት አድርጓል። በውርስ ሪፕርቱ ከተካደት ጉዲዮች አንደ የውርስ አጣሪው የስራ ዋጋ መጠንን የሚመለከት ሲሆን ውርስ አጣሪው ላጣሩት የውርስ ስራ ከጠቅላላው ንብረት 5% ይገባኛል በማለት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የቀረበው የውርስ አጣሪ ስራ ዋጋ መጠን ከተጣራው የውርስ ንብረት መጠን አንፃር ሲታይ የተነጋነነ ነው፣ ከወራሽነትም የሚተናነስ አይደለም፣ ወራሾች እያንዲንዲቸው ተጠይቀውም እያንዲንዲቸው ብር 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ ለመክፈል ፈቃደኞች መሆናቸው ተረጋግጧል የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ ለአመልካች እያንዲንዲቸው ብር ሶስት ሺህ ፣ በጠቅላላው ብር 3ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ /ሰላሳ ሺህ ብር/ እንዱከፈላቸው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ባጭሩ የውርስ ማጣራቱና የውርስ ንብረት ማስተዲደሩን ተግባር ለማከናወን የሚያስፈልገውን የሥራ ዋጋ አስመልክቶ ከተጠሪዎች መካከል ስምንቱ አስቀድመው በስምምት መጠንኑ የቆረጡ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ፍርድ ቤቱ መጠኑ የተጋነነ ነው በማለት መቀነሱ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ፣1711 ፣ 959 ድንጋጌዎች አኳያ ጉዲዩ ያልታየ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ውሣኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም ሉጣራ የሚገባው የሕግ ነጥብ መኖሩ ታምኖበት ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጏላቸው ተጠሪዎች ቀርበው የተወሰኑት ከአመልካች ጋር የ5% ስምምነት ማድረጋቸውን በማመን መልስ ሲሰጡ የተወሰኑት ደግሞ ከአመልካች ጋር ያደረጉት ስምምነት የላለ መሆኑን በመግለፅ በእየራሳቸው በኩል ተገቢው እንዱወሰን ተከራክረዋል። አመልካች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የስር ፍርድ ቤት የአጣሪውን የአገልግልት ዋጋ መጠን በመቀነስ የሰጠው የውሣኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም ?የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
በመሰረቱ የውርስ አጣሪ መሆን የሚችለው፡- ያለኑዛዜ ወራሽ የሆነ ሰው፣ ይህም ልጅ፣ ልጅ ከላለ ወላጅ ፣ ወንድም እህት፣ በኑዛዜ ጠቅላላውን የሟች ንብረት እንዱወርስ ኑዛዜ የተደረገለት ሰው፣ አካለመጠን ያልደረሱ ወይም በህግ የተከለከለ ህጋዊ ወራሾች ሞግዚት፣ በወራሾች ስምምነት የሚመረጥ ሰው፣ ወራሾች ካልተስማሙ በፍ/ቤት የሚመረጥ ውርስ አጣሪ፣ ወይም (…) በኑዛዜ የሚመረጥ የውርስ አጣሪ ነው። የውርስ አጣሪው ዋና ዋና ስራዎች ደግሞ፣ ሟቹ አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግ ወራሾቹ እነማን እንደሆኑ መለየት ፣ የውርስ ሀብት ማስተዲደር፣ መክፈያቸው የደረሰውን የውርስ ሀብቶች መቀበል ፣ እዲዎችን መክፈል ፣ ሟች በኑዛዜው ያደረጋቸውን ስጦታዎች ኑዛዜው ተቀባይነት ያገኘ ከሆነ መክፈልና የሟች ኑዛዜ እንዱፈፀም አስፈላጊውን ሁለ ማድረግ ፣ ሟች ኑዛዜ ያልተወ ከሆነ የሟች ያለኑዛዜ ወራሾችን በመለየት የኑዛዜውን ድልድል እንዳት እንደሆነ ለወራሾች ማሣወቅ ፣ እና በአጠቃላይ ላልች ስራዎችን ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 946-1125 ድረስ ያለትን እንደ አግባብነታቸው መስራት ነው። በዚህ መልኩ በሕጉ የተሰጡትን ስራዎች የሚያከናውን የውርስ አጣሪ የስራውን አገልግልት ዋጋ የሚያገኝበት አግባብም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 959 ስር ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አጣሪው በሟቹ በተወሰኑት ሁኔታዎች /ውለታዎች/ መሰረት ወይም በወራሾቹ ወይም በዲኞቹ መካከል በተደረገ ስምምነት የሚሰራው ሥራ የሚያረጋግጥለት ከሆነ አንድ የአገልግልት ዋጋ ለማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ ተደንግጓል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ የሚቻለው የአጣሪው የአገልግልት ዋጋ ሉወሰን የሚችለው አጣሪው ከሟች፣ ወይም ከዳኞች መካከል በሚደርገው ስምምነት ሁኖ የሚሰራው ስራ አረጋጋጭ ሁኖ ሲገኝ መሆኑን ነው። በመሆኑም የሥምምነቱ መኖር ብቻውን አሳሪ የሚሆንበት አግባብ የላለ ሲሆን የማጣራቱ ስራ ክብደቱ ፣ ውስብስብነቱ ከወሰደው ጊዜና ድካም አንፃር እየታየ የአገልግልት መጠኑ የሚወሰን መሆኑንና ይህም ለፍርድ ቤቱ በሕጉ የተሰጠ ስልጣን መሆኑን የድንጋጌው መንፈስና ይዘት ከውርስ ማጣራት ስራ መሰረታዊ ዓላማ ጋር ተዲምሮ ሲታይ የሚያስገነዝበን ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ የምንችለው ሁኖ አግኝተናል።
No topics extracted.
አመልካች ለክርክራቸው መሰረት ያደረጉት ስምምነቱን መኖሩንና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ድንጋጌን ሲሆን በእርግጥ በሕግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች ሁለ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የሕግን ያህል አስገዲኝነነት ኃይል ያላቸው መሆኑን ተጠቃሹ ድንጋጌ የሚያሳየን ጉዲይ ሁኖ ይህ ድንጋጌ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1711 አና 959 ድንጋጌዎች ጋር ተጣምሮ ሲታይ የስምምነቱ መኖር ብቻውን ስምምነቱ ሕጋዊ ጥበቃ እንዱደረግለት የሚያደርግ ሲሆን ስምምነቱ የውርስ ማጣራቱ ስራው ክብደቱና ውስብስብነቱ እየታየ የአጣሪው የአገልግልት ዋጋ መጠን በፍርድ ቤት የሚወሰንበት ሕጋዊ አግባብ ያለ ከመሆኑ ጭምር ሲታይ የአመልካች ክርክር ሕጋዊ መሰረት የላለው መሆኑን የሚያስገነዝብ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በተያዘው ጉዲይ የስምምነቱ መኖር ያለመኖር በራሱ ክርክር ያስነሳ ከመሆኑም በተጨማሪ ከወራሾች መካከል ሁለቱ ስምምነቱ ላይ ፈቃዲቸውን ያልገለፁ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ሥልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች በሚገባ የተረጋገጠ ጉዲይ ሲሆን እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በቀረበው ክርክርም ስምምነቱ መኖሩን ያመኑት የተወሰኑት ተጠሪዎች ብቻ መሆናቸው፣ የውርስ ንብረቱ ክፍፍለ እስከሚፈፀም ድረስ እንደ አንድ የተለየ ንብረት የሚቆጠርና ሳይነጣጠል የሚቆይ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐ6ዐ/1/ ድንጋጌ ከተቀመጠው መርህ እና የውርስ አጣሪውን የአገልግልት ዋጋ ለመቀነስ ፍርድ ቤት በሕጉ ስልጣን የተሰጠው ከመሆኑ አንፃር ሲታይ ከወራሾች መካከል የተወሰኑት ስምምነት ማድረጋቸው የውርስ አጣሪውን የአገልግልት ዋጋ መጠኑን በግል ለያይቶ መወሰን የግድ አስፈላጊ ነው ብል ለመደምደም የማያስችል ነው።
አመልካች ከውርስ ንብረቱ ተገኘ ከተባለው ብር 5,498,400.00 ውስጥ 5% ይገባኛል ያለት የተጋነነ እና ከወራሽነት የማይተናነስ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ግምት የወሰደበት ሲሆን አመልካች በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የስራውን አድካሚነት እና በራሳቸው ጥረት የተነሳ ከውርስ ንብረቱ ይፈለጋል ተብል በግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ተጥል የነበረውን የግብር መጠን ማስቀረታቸውን ፣ በንብረት ጥበቃ ወቅትም የፈፀሙትን ተግባር ሁለ በመዘርዘርና በምክንያትነት በመጥቀስ ክፍያው የተጋነነ ነው ልባል የሚችል አይደለም በማለት ያቀረቡት ክርክር የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ ድንጋጌዎች አንጻር ሲታይ በዚህ ችልት ሉጣራና ሉመዘን የሚችል ካለመሆኑም በላይ በፍ/ብሕ/ቁጥር 959 ድንጋጌ መሰረት ለስር ፍርድ ቤት ከተሰጠው ፈቃድ ስልጣን አንጻር ተቀባይነት ሉሰጠው የሚችል ሁኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ የአጣሪው የአገልግልት ዋጋን በተመለከተ በተወሰኑት ወራሾችና በአጣሪው መካከል ስምምነት ቢኖርም በክርክሩ የተረጋገጡትን የተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶችን በመያዝ ፍርድ ቤት የአገልግልት ዋጋ መጠኑን ለመቀነስ የሚችል መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 959 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያሳይ በመሆኑና በተያዘው ጉዲይም በዚህ አግባባም የአጣሪው የአገልግልት ዋጋ መጠን የተወሰነ በመሆኑ በውሣኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 23 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 12 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በትዕዛዝ የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በፍርድ ቤት የተሾመ የውርስ አጣሪ የአገልግልት ዋጋን በተመለከተ አጣሪው የሚሰራው ስራ የሚያረጋግጥለት መሆኑን በመመርመር ፍርድ ቤት የመቀነስ ስልጣን አለው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።