No summary available.
ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ኢትዮ ቴላኮም ተጠሪዎች፡- 1.ትዕግስት ሙለዓለም 2. መስፍን ምስጌ 3. እቴነሽ ወጋዬሁ 4. ከተማ ዋና 5. ዱላወርቅ ግርማ 6. ጽጌረዲ አዱሱ 7. ሰናይት ማዘንጊያ 8. ትዝታነሽ በራዩ 9. ጌትነት መሀሪ 10. አንተነህ አጋር 11. መስፍን ምትኩ 12. ሂሩት ሚዳቅሳ 13. ብርቱካን በረሳ 14. መንበረ ወንድማገኝ 15 .ተስፊዬ ማሞ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ ለሰበር መነሻ የሆነው ክርክር የተጀመረው በአሁን የሰበር ተጠሪዎች ከሳሽነት በሐዋሳ ከተማ የመ/ደ/ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበር። ክሱም ተከሳሽ የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የመዋቅር ለውጥ አድርጌአለሁ በሚል የስራ ውላችንን ሲያቋርጥ የስንብት ክፍያ ብቻ በመክፈል ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ሳይኖር የ15 ቀናት ደመወዝ ሳይከፍል ያዘገየ በመሆኑ ያልከፈለውን ደመወዝና በአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 38 መሰረት ክፍያ ለዘገየበት የ3 ወር ደመወዝ እንዱከፍልና የስራ ልምድ የምስክር ወረቀት እንዱሰጠን ይወሰንል የሚል ነው።
ተከሳሽም በፍሬ ጉዲዩ ላይ በሰጠው መልስ ተከሳሽ በመዋቅር ለውጥ ምክንያት ሰራተኞችን ስመድብ ከሳሾች በምደባው ባለመካተታቸው ክፍያ በጠየቁት ወቅት በስራ ላይ አልተገኙም፣ የ15 ቀናት ደመወዝ አልተከፈለንም ለሚለትም ስራ የሰሩ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ የለም፣ ለከሳሾች በተሰጣቸው የስንብት ደብዲቤ ከእዲ ነጻ ለመሆናቸው ክሉራንስ በማቅረብ ክፍያ እንዱቀበለ ከመገለጹም በላይ በማስታወቂያና በግል ስልካቸው ጭምር የተዘጋጀላቸውን ክፍያ እንዱወስደ ተደርጓል። ስለሆነም ተከሳሽ የታመነውን ክፍያ በመክፈል የሚፈለግብኝን ግዳታ የተወጣሁ ስለሆነ ስራ ስለመስራታቸው ባልተረጋገጠበት የ15 ቀናት ደመወዝና ለዚሁ አከራካሪ ለሆነ ክፍያ ክፍያ ዘግይቷል በሚል የ3ወር ደመወዝ ሉከፈላቸው ስለማይገባ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም ብሎል።
ጉዲዩን የመረመረው የመ/ደ/ፍርድ ቤትም በሰጠው ፍርድ የስራ ውለ በተቋረጠበት ወቅት ለ15 ቀናት ከሳሾች ስራ ላይ ስለመሆናቸው መዝገቡ የሚያስረዲ ሲሆን ተከሳሽ ድርጅትም በእነዚህ ቀናት ከሳሾች ስራ ያልሰሩ ስለመሆናቸው የሚያስረዲ ማስረጃ ባለማቅረቡ እስከ ሐምል 06 ቀን 2003 ዓ.ም. ድረስ ሥራ ላይ የቆዩበትን የ15 ቀናት ደመወዝ ሉከፍል ይገባል በሚል የወሰነ ሲሆን፣ ለዚሁ አከራካሪ ለሆነው ክፍያ የ3 ወር ደመወዝ ክፍያ ለዘገየበት በቅጣት መልክ እንዱከፍል የጠየቁት ግን ተቀባይነት የለውም ብሎል።
በስር ከሳሾች ይግባኝ ጠያቂነት ጉዲዩን የመረመረው የከተማው ከፍተኛው ፍርድ ቤት በበኩለ በሰጠው ፍርድ የሐምል ወር የ15 ቀናት ደመወዝ በሐምል ወር መክፈል ሲገባው ሳይከፍል በማዘግየት በነሐሴ ወር የከፈለ ስለመሆኑ የሰነድ ማስረጃዎች ስለሚያሳዩና መልስ ሰጪው ክፍያውን ለማዘግየቱ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ስለመኖሩ ስላላስረዲና ሰራተኞቹ በስራ ላይ በተባለው ጊዜ ያልነበሩ መሆን አለመሆናቸውን በበቂ ማስረጃ የማስረዲት ሸክም የመልስ ሰጪው ሆኖ እያለ ይህንኑ ስላላረጋገጠ ክፍያው ለዘገየበት የ2ወር ደመወዝ ለእያንዲንዲቸው ሉከፍል ይገባል በሚል የስር የመ/ደ/ፍርድ ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፍርድ በይግባኝ የቀረበለት የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም የይግባኝ ባዩን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 337 መሰረት በመዝጋት ይግባኝ ባዩን በማሰናበቱ አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት አቅርቧል።
ሰበር አቤቱታም አመልካች በዋናነት የጠቀሰው የቅሬታ ነጥብ፡- በሰራተኛ ምደባና ቅነሳ መሀል ባለት ጊዜያት ሰራተኛው በሥራ ገበታ ላይ ለመገኘቱ ጊዜ ተወስድ ከተረጋገጠ በኋላ ለተሰናበቱት ሰራተኞች የስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና እና የዓመት ዕረፍት ክፍያ በአንድ ጊዜ ከተፈጸመላቸው በኋላ የ15 ቀናት ክፍያ አጠራጣሪና አከራካሪ በመሆኑ ምክንያት ክፍያው የቆየ ሆኖ ሳለ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ክፍያው ዘግይቷል በሚል ለተጠሪዎች የ2 ወር ደመወዝ እንዱከፈላቸው የወሰነውም ሆነ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ይህንኑ ያጸናው የቅጣት ክፍያን ዓላማ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ተገቢነት የለውም የሚል ነው።
የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ አመልካች በስር ፍርድ ቤቶች በተደረገው ክርክር በክሱ በተጠቀሱት ቀናት ተጠሪዎች ስራ አልሰሩም ከማለቱ በስተቀር በማስረጃ ማረጋገጥ ባለመቻለ ምክንያት ክፍያ ላዘገየበት የሁለት ወር ደመወዝ እንዱከፍል የስር ከፍተኛና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የወሰኑት በአግባቡ ስለሆነ ይጽናልን ብለዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም፡- አመልካች የ15 ቀናት ደመወዝ በጊዜ ባለመክፈለ የተነሳ ክፍያ ለዘገየበት ለተጠሪዎች የ2 ወር ደመወዝ እንዱከፍላቸው የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የወሰኑት በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች ድርጅት ባደረገው የአሰራር ለውጥ ምክንያት ሰራተኞቹን ሲቀንስ ተጠሪዎችም ከስራ የተቀነሱ ስለመሆናቸው መዝገቡ የሚያመለከት ሲሆን በቅነሳው ምክንያት ከስራ ውጪ ለተደረጉ ሰራተኞችም የተለያዩ ክፍያዎችን ከፍል እንዲሰናበታቸው ገልጾ የሚከራከር ሲሆን ተጠሪዎችም ቢሆኑ በህጉ መሰረት አመልካች የተለያዩ ክፍያዎችን የከፈላቸው ስለመሆኑ የሚያምኑት ጉዲይ ነው። ዋናው የሚያከራከራቸው ጉዲይ ግን የስራ ውለ ሲቋረጥ የ15 ቀናት ደመወዝ አመልካች በህጉ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ መክፍል ሲገባው ክፍያውን አለመፈጸሙ ነው። አመልካች ለክፍያው አለመፈጸም በስር ፍርድ ቤት እንደምክንያት የጠቀሰው ተጠሪዎቹ በእነዚህ ጊዜያት ስራ አልሰሩም የሚል ሲሆን ስራ ስለመስራታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ደግሞ የከተማው የመ/ደ/ፍርድ ቤት በውሳኔው ገልጿል። የመ/ደ/ፍርድ ቤትም ክፍያው የዘገየ መሆኑ ቢረጋግጥም ክፍያው አከራካሪ ነው ወደሚለው ድምዲሜ በመድረስ ተጠሪዎች እንዱከፈላቸው የጠየቁትን የቅጣቱን ገንዘብ ሳይቀበል ያለፈ ቢሆንም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ግን ተጠሪዎች ስራ ያልሰሩ ስለመሆናቸው የማስረዲት ሸክም የአመልካች ነው በሚል ክፍያውን አመልካች ማዘግየቱ ስለተረጋገጠ የ2 ወር ደመወዝ እንዱከፍል ሲል ወስኖበታል። በስር ፍርድ ቤቶች በተረጋገጠው ፍሬ ነገር መሰረት ደግሞ አመልካች ላልች ክፍያዎችን ከፍል የ15 ቀናት ደመወዝ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 36 መሰረት በ7 የስራ ቀናት ውስጥ አለመክፈለ ግልጽ ነው።
አመልካች የ15 ቀናት ደመወዝ ያልከፈለው ደግሞ ከፍያው አከራካሪ በመሆኑ ምክንያት ነው።
በአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 37 ስር እንደተመለከተው አሰሪው ያመነውን ክፍያ በመፈጸም አከራካሪ የሆነ ክፍያን እስከሚጣራ ድረስ ማዘግየት የሚችል ስለመሆኑ ከድንጋጌው መረዲት የሚቻል ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 38 መሰረትም አሰሪው በቅጣት እስከ 3 ወር ድረስ የሚደርስ የሰራተኛውን ደመወዝ ያህል ቅጣት ሉከፍል የሚገደደው ከቁጥጥር ወጪ የሆነ ምክንያት ሳይኖር ወይም በአንቀጽ 37 በተደነገገው መሰረት የሚያከራክር ክፍያ በላለበት ከቅን ልቦና ወጪ ሰራተኛውን ለመጉዲት ተነሳስቶ ክፍያውን ማዘግየቱ ሲረጋገጥ ነው። በዚህ በተያዘው ጉዲይ ግን አመልካች የስንብት ክፍያ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና ላልች ክፍያዎችን ሳያዘገይ ለተጠሪዎች መክፈለን መዝገቡ የሚያመለከት ሲሆን ዘግይቷል የተባለውም 15 ቀናት ደመወዝ ብቻ ነው። በመሆኑም የስር ከፍተኛና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ለ15 ቀናት ተጠሪዎች ስራ ባለመስራታቸው የተነሳ በህጉ በተወሰነው የጊዜ ገደብ አከራካሪው ክፍያ ሳይከፈል ቀርቷል ሲል እየገለጸ ባለበት የክፍያ ጊዜ በመዘግየቱ ብቻ እንደበቂ ምክንያት በመውሰድና አመልካች ላልች ክፍያዎችን ሁለ ስለመፈጸሙ ግንዛቤ ውስጥ ባለማስገባት በአንቀጽ 38 መሰረት ክፍያ ለዘገየበት ለእያንዲንዲቸው የ2 ወር ደመወዝ እንዱከፈላቸው የወሰኑት በአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 37 ስለአከራካሪ ክፍያ የተደነገገውን መሰረት ያደረገ ካለመሆኑም ላላ በአዋጁ አንቀጽ 38 የተቀመጠውን የገንዘብ ቅጣት ዓላማ ባላገናዘበ መልኩ ስለሆነ ክፍያ ለዘገየበት ለተጠሪዎች የ2 ወር ደመወዝ እንዱከፈላቸው የሰጡት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በማግኘታችን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የሐዋሳ ከተማ የከ/ፍርድ ቤት በመ/ቁ/11103 በቀን13/03/2004 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ፣ እና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 55825 በቀን 21/03/2004 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348 (1)መሰረት አሻሽለናል።
አመልክች ለተጠሪዎች የ15 ቀናት የደመወዝ ክፍያ ላዘገየበት ለእንዲንዲቸው የ2 ወር ደመወዝ እንዱከፍላቸው የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡትን የውሳኔ ክፍል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 348 (1) መሰረት ሽረናል። ስለሆነም ክፍያ ላዘገየበት ለተጠሪዎች የሚከፍላቸው ክፍያ የለም ብለናል።
የስር ፍርድ ቤቶች ለተጠሪዎች አመልካች የ15 ቀን ደመወዝ እንዱከፍላቸውና የስራ ልምድ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ሲለ የሰጡትን የውሳኔ ክፍል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት አጽንተናል።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል ።
No topics extracted.