No summary available.
ጥር 15 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አበበች አደኛ በራሳቸውና በህጻን ረቂቅ ተክለ ስም - ከጠበቃ ሒጎስ አብርሃ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- በስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የተንዲሆ ቤቶች ልማት ፔሮጀክት ጽ/ቤት- የቀረበ የለም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በስራ ላይ በደረሰ የሞት አደጋ ምክንያት ለጥገኞች የሚከፈል ክፍያ ጋር በተያያዘ የተነሳ ክርክር ሲሆን የተጀመረው በፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት በአሁኑ አመልካች ከሳሽነት ነዉ። ቀርቦ የነበረው ክስ ባለቤታቸውና የህጻን ረቂቅ ተክለ አባት የነበሩት አቶ ተክለ አያኖ በተከሳሽ ዘንድ በጊዜያዊ ሰራተኝነት ተቀጥረው ከመጋቢት 16 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምረው ብር 6,710 የወር ደመወዝ እየተከፈላቸው ይሰሩ እንደነበረ፣ መስከረም 07 ቀን 2000 ዓ.ም ወደ ስራ ቦታቸው በተከሳሽ መኪና በመጓዝ ላይ እያለ በደረሰ አደጋ መሞታቸውን፣ ተከሳሽ በህጉ መሰረት ተገቢውን ክፍያ ለመፈጸም ፍቃደኛ መሆኑን በ26-6-2000 ዓ.ም በጻፈው ደብዲቤ ገልጾ የነበረ ቢሆንም ግንቦት 1 ቀን 2000 ዓ.ም በባንክ በኩል ለከሳሽ የከፈለው ግን ብር 27,051 ብቻ መሆኑን፣ ተከሳሽ በፋዳራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 94(2) እና አዋጅ ቁ.262/94 አንቀጽ 46 መሰረት ለሟች ተተኪዎች የሟቹን የዓመት ደመወዝ በአምስት ተባዝቶ ካሳ የመክፈል ግዳታ ያለበት መሆኑን፣ በዚህ መሰረት ከከፈለው ላላ የሚቀርበትን ብር 375,549 እንዱከፍል ተጠይቆ በ22-9-2000 ዓ.ም በጻፈው መልስ ፈቃደኛ ያለመሆኑን ማሳወቁን ገልጸው ተከሳሽ ይሄንን ቀሪ የካሳ ክፍያ ከየካቲት 30 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድና ከክሱ ወጪዎች ጋር እንዱከፍል እንዱወሰንበት የሚል ነው። ተጠሪ በቀረበው ክስ ላይ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በሰጠው መልስ የፍርድ ቤቱ ስልጣን ተነስቶ ውድቅ ተደርጎ የታለፈ ስለመሆኑ ተመልክቶ በፍሬ-ጉዲዩ ላይ የተሰጠው የመልስ ፍሬ-ሃሳብ፡- በእርግጥ ሟችን በጊዜያዊ ሰራተኝነት ቀጥሯቸው በኤርታላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የኮንስትራክሽን እና ኦፉስ ኢንጅነሪንግ መምሪያ ኃላፉ ሆነው ሲሰሩ እንደነበረ በመግለጽ ሟች የሞቱት ያልተፈቀደላቸውን የሰ.ቁ.3- 27289 የሆነ ፍርድ ፑክአፔ መኪና እያሽከረከሩ ከአዱስ አበባ ወደ ደብቲ ሲጓዙ በደረሰባቸው የመገልበጥ አደጋ መሆኑን፣ ሟች የተቀጠሩት ባላቸው የምህንድስና ሙያ እንጂ በሹፋርነት ያለመሆኑን፣ ሟች ይዘውት የነበሩውን መኪና የተረከቡት አቶ ሞገስ ጀንበሩ የተባለ ሹፋር ቢሆኑም ሟች መኪናውን ከሹፋሩ ነጥቀው አዱስ አበባ ውስጥ ሲጠቀሙበት ከቆዩ በኋላ በራሳቸዉ አሽከርካሪነት 4 የፔሮጀክቱን ሰራተኞች ጭነው ወደ ደብቲ ሲጓዙ መኪናዋ አቅጣጫ ስታ ከመንገድ ወጥታ መገልበጧን፣ ሟች በራሳቸው ስህተት በፈጠሩት አደጋ ተከሳሽ ተጠያቂ ስለማይሆን፣ በአገራችን ባለው የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት በሚወስኑት ህጎች እንዱሁም በአዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 47(ሐ) በተቀመጠው ትርጉም መሰረት በሟች ላይ የደረሰው ጉዲት በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ልባል የማይችል በመሆኑ በህጉ ላይ ለተተኪዎች ይከፈላል ተብል የተወሰነውን ካሳ ከሳሾች የመጠየቅ መብት የላላቸው በመሆኑ፣ ጉዲቱ በስራ ላይ የደረሰ ባይሆንም ሟች ከዚህ በፉት በቋሚነት በተለያየ ቦታ ያገለገለ መሆኑን ከግምት በማስገባት ከብር 100,000 በላይ ሰራተኞችን አስተባብሮ ለከሳሽ የከፈለ መሆኑን ገልጾ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዱሆን በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ እና የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማት ሟች የሞቱት በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን በመመርመር ውሳኔ ሰጥቷል። በዚሁ መሰረት በዚሁ የበታች ፍርድ ቤት የተረጋገጡት ፍሬ-ነገሮች አደጋው በደረሰ ጊዜ ሟች ያሽከረክሩት የነበረው መኪና በእርግጥ ከፔሮጀክቱ ጽ/ቤት ለበዓል ወደ አዱስ አበባ ሲመጡ ይዘውት ያልመጡ እና ላላ ተሸከርካሪ በመያዝ የመጡ ስለመሆኑ፣ አዱስ አበባ የሚሉንየም በዓለን አሳልፈው ወደ ስራ ቦታ ሉመለሱ ሲዘጋጁ የስራ አስኪያጁ መኪና በመበላሸቱ ሟች ይዘውት የመጡት መኪና ለስራ አስኪያጁ ተሰጥቶ አደጋው የተከሰተበት መኪና በዚህ ሂደት ሉይዝ እንደቻለ፣ ቀድሞ ሟች ይዘውት የመጡት መኪና በኃላፉነታቸው የተሰጣቸው እና አሁን አደጋው የተከሰተበት መኪና ደግሞ ከኃላፉው ጋር በመቀያየር ሂደት ሟች እጅ የገባ ስለመሆኑ፣ ሟችም ወደ ስራ ቦታቸው ደብቲ ሲሄደ 4 የፔሮጀክቱን ሰራተኞች ይዘው በመጓዝ ላይ እያለ በአደጋው ምክንያት ህይወታቸው ሉያልፍ ስለመቻለ ናቸው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት ከላይ የተመለከቱትን ፍሬ-ነገሮች ካጣራ በኋላ ጉዲቱ የደረሰው በስራ ላይ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ከፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 47(2)(ሐ) አኳያ መርምሮታል። የተሰጠውም ውሳኔ የዚህ ድንጋጌ ይዘት “…….መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች አገልግልት እንዱሰጥ በመደበው የማጓጓዣ አገልግልት በመጓዝ ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዲት……” ከሆነ ብቻ በመሆኑ፣ አደጋዉ የደረሰበት ሰራተኛ ይጓዝ የነበረው መስሪያ ቤቱ “…for the common use….” እየተጠቀመ ባለበት ወቅት እንጂ በዚህ ጉዲይ ሟች ለግለ መጠቀሚያ በቀጥታ ተሰጥቶት ወይም ከላላ ባለስልጣን ጋር ተቀያይሮ ሲያሽከረክር የደረሰን አደጋ አይመለከትም፣ አደጋውን ያደረሰው መኪና ተጠሪ ለሰራተኞች መጓጓዣ እንዱያገለግል በመደበው የጋራ መጓጓዣ ሳይሆን በስራ ኃላፉነታቸው የተነሳ እንዱጠቀሙበት በግል የተሰጣቸውን መኪና ሲያሽከረክሩ የደረሰ አደጋ በመሆኑ በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ልባል ስለማይችል ከሳሾች በጠቀሱት ህግ ላይ ከደረሰ ጉዲት ጋር በተያያዘ ጊዜያዊ ሰራተኛ ሲሞት ለተተኪዎች የሚከፈለውን ካሳ ተጠሪ እንዱከፍል አመልካች ለመጠየቅ መብት የላቸውም የሚል ነው። በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ግራ ቀኙ ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የፋ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች ጥቅምት 15 ቀን 2003 ዓ.ም በሁለት ገጽ በተጻፈ አቤቱታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያለዋቸውን ነጥቦች ያነሱ ሲሆን ፍሬ-ሃሳቡ፡- ሟች አደጋው የደረሰባቸው መስሪያ ቤቱ በመደበላቸው መኪና እየተጓዙ ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ በጋራ ለሰራተኞች አገልግልት የተመደበ ካልሆነ በኃላፉነታቸው ለሟች የተመደበን መኪና ለሰራተኞች በጋራ የተመደበ ባለመሆኑ በስራ ላይ እንደደረሰ አደጋ አይቆጠርም ወደሚለው መደምደምያ መደረሱ የድንጋጌውን ይዘት ያላገናዘቡ ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ሟች 4 የፔሮጀክቱ ሰራተኞችን በመያዝ ወደ ስራ ቦታቸው በመጓዝ ላይ እያለ የደረሰ አደጋ በመሆኑ የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት ታርሞ በክሳችን የተመለከተው ክፍያ እንዱፈጸምልን የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በቀን 17-5-2003 ዓ.ም በሁለት ገጽ በተጻፈ መልስ የሰጠ ሲሆን ፍሬ-ሃሳቡ፡ድርጅታችን በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚተዲደር ስለመሆኑ ከዚህ በፉት ይሄ የፋ/ሰበር ሰሚ ችልት በመዝ.ቁ.38250 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠ በመሆኑ፣ በዚህ ጉዲይ የፋ/መንግስት ሰራተኞች አዋጅን መሰረት በማድረግ ውሳኔ መሰጠቱ አግባብነት የላለው በመሆኑ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በተመለከተ ደግሞ ሟች የስራ መሪ በመሆኑ ይሄንንም መሰረት በማድረግ ክስ ሉያቀርብ የማይችል በመሆኑ፣ ሟች አዱስ አበባ ካለው መኖሪያ ቤታቸው ድርጅቱ ወደ አዘጋጀላቸው ደብቲ ወደ ሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በመጓዝ ላይ እያለ የደረሰ አደጋ በመሆኑ በስራ ላይ እንደደረሰ አደጋ የማይወሰድ በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት የተከራከሩ ሲሆኑ በዚሁ መልሳቸው 2ኛ ገጽ ላይ መስቀለኛ ይግባኝ በማለት የተጻፈ ሲሆን ተገቢውን ስነስርዓት በመጠበቅ የቀረበ ባለመሆኑ ታልፍአል። አመልካችም የመልስ መልስ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ላይ በሟች እና ተጠሪ መስሪያ ቤት መካከል የቅጥር ውል ሲደረግ በስራ ላይ በሚደርስ ጉዲት ምክንያት ለሚከፈለው ክፍያ ተፈጻሚነት ያለው ህግ አዋጅ ቁ.262/94 በአዋጅ ቁ.515/99 እንደተሻሻለው ስምምነት ያለ በመሆኑ በዚሁ ስምምነት መሰረት ክፍያ እንዱፈጸምልን በማለት ተከራክረዋል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል።
ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ የአመልካች ባለቤት(ሟች) የሞቱት በስራ ላይ በደረሰ ጉዲት አይደለም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ከፋ/መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 47(2)(ሐ) አኳያ ለመመርመር በሚል በመሆኑ ከዚሁ ጭብጥ አኳያ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመጀመሪያ ደረጃ በግራ ቀኙ መካከል ባለው ክርክር አግባብነት ያለው የህግ ማዕቀፍ እና ጉዲዩን ለመመልከት ስልጣን ያለውን አካል በተመለከተ በበታች ፍርድ ቤቶች በተደረገው ክርክር ተጠሪ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ እና የፋዳራል መንግስት ሰራተኞቸ አዋጅ በመጥቀስ በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ያለመሆኑን ከመከራከር ውጪ አዋጆቹ በግራ ቀኙ ባለው ክርክር ላይ ተፈጻሚነት የላላቸው ስለመሆኑ ያነሳው ነጥብ ስለመኖሩ የሚያመለክት ነገር የለም። በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ ባቀረበው ክርክር ደግሞ በአንድ በኩል የተጠሪ ጽ/ቤት ውስጥ የሚነሳው ተመሳሳይ አለመግባባት የሚታየው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ስለመሆኑ ከዚህ በፉት ይሄ የሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን አስገዲጅ የህግ ትርጉም በመጥቀስ በፋ/መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላታይ እንደማይገባ ሲከራከር በልላ በኩል ደግሞ ሟች የስራ መሪ መሆኑን በመጥቀስ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ በዚህ ክርክር ላይ ተፈጻሚነት የላለው መሆኑን ተከራክሯል። በተጨማሪም አመልካች ቀደም ሲል ጉዲዩን ለፋዳራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት አቅርበው ጉዲዩን የመመልከት ስልጣን የላለው መሆኑን በማመልከት ክሱን የዘጋ ስለመሆኑ ከክርክር ሂደቱ መገንዘብ ይቻላል።
አመልካች በበኩላቸው ክሳቸውን ሲያቀርቡ በግራ ቀኙ መካከል ባለው የስራ ውል መሰረት ተገቢው ክፍያ እንዱፈጸምላቸው ተገቢውን ዲኝነት በመክፈል ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል።
በዚሁ መልኩ ሟች የተቀጠረው በኮንስትራክሽንና ኦፉስ ኢንጂነር መምሪያ ኃላፉ ሆኖ በጊዜያዊነት መሆኑ ያላከራከረ በመሆኑ የስራ መሪ ልባል የሚችል የስራ መደብ ላይ የተቀጠረ በመሆኑ በሟች እና ተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው የስራ ውል ደግሞ ለህግ እና ሞራል ተቃራኒ ነው የሚል ክርክር ያልተነሳ በመሆኑ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገ ስምምነት ደግሞ በተስማሙት አካላት መካከል ህግ ሆኖ የሚያገለግል ስለመሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁ.1731 የሚያስገነዝበን በመሆኑ ከዚሁ በሟች እና በተጠሪ ጽ/ቤት መካከል ተደርጎ በነበረው ስምምነት መሰረት የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት ተመሳሳይ አለመግባባቶች ሲከሰቱ ማለትም በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ስለመሆን አለመሆኑ ለመወሰንም ሆነ የካሳ አከፊፈልን በተመለከተ ሉፈቱ የሚገባቸው በፋ/የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሰረት መሆን እንዲለበት በግራ ቀኙ በተደረገው የስራ ውል አንቀጽ 5 ስር በግልጽ በማመልከት የስምምነታቸው አካል አድርገውታል። በዚሁ መሰረት የተረጋገጡትን ፍሬነገሮች ይዘን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ስንመለከት የበታች ፍርድ ቤቶች በሟች ላይ የደረሰው አደጋ በስራ ላይ የደረሰ አይደለም ወደሚለው መደሚደሚያ የደረሱት አደጋውን ያስከተለው መኪና ሟች ይዞት የመጣው ተሸከርካሪ የስራ አስኪያጁ መኪና በመበላሸቱ ለስራ አስኪያጁ እንዱሰጥ ተደርጎ በዚህ መቀያየር ሂደት በእጁ የገባ ስለመሆኑ እና ሟች ለሚሉኒየም በዓል የተሰጠውን እረፍት ጨርሶ ወደ ስራ ቦታው እየተመለሰ ባለበት ወቅት የተከሰተ አደጋ መሆኑን በፍሬ-ነገር ተቀብለው እያለ መኪናው በጋራ ለሰራተኞች የተመደበ ባለመሆኑ በሚል ነው። የፋ/መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 47(2)(ሐ) ስንመለከት መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች አገልግልት እንዱሰጥ በመደበው የመጓጓዣ አገልግልት በመጓዝ ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዲት በማለት ከሚደነግግ ውጪ አንድ ሰራተኛ ባለው ኃላፉነት በግለ ተሸከርካሪ ተሰጥቶት እየተገለገለበት ባለበት ሁኔታ የተከሰተን አደጋ አይጨምርም ማለት ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በህጉ በግልጽ ከተመለከተው የድንጋጌው ይዘት ውጪ የደረሱበት መደምደሚያ አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም በበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡት ፍሬ-ነገሮች ሟች ህይወቱ ሉያልፍ የቻለው በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ስለመሆኑ የሚያረጋግጡ ሁነው እያለ በስራ ላይ የደረሰ አደጋ አይደለም መባለ ተቀባይነት ያለው ባለመሆኑ በሟች ላይ የደረሰው የሞት አደጋ በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ነው ብለናል።
የካሳውን መጠን በተመለከተ ሟች የተቀጠረው በጊዜያዊነት በመሆኑ እና በፋ/የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ የተቀመጠውና ለጊዜያዊ ሰራተኛ ተፈጻሚነት ያለው የካሳ ክፍያ በግራ ቀኙ የስራ ውል መሰረት በተመሳሳይ ተፈጻሚነት ሉኖረው እና በዚህ የካሳ ክፍያ መጠን ላይ የተነሳ ክርክር የላለ በመሆኑ እና ለዚህም አግባብነት ያለው ድንጋጌ የአዋጅ ቁ.515/99 አንቀጽ 94(2) እና አዋጅ ቁ.262/94 አንቀጽ 46(2)(5(ለ)) በመሆኑ ከዚሁ አኳያ ተሰልቶ ለአመልካች የጉዲት ካሳ ክፍያ ሉከፈላቸው ይገባል ብለናል። ግራ ቀኙ ባደረጉት የቅጥር ውል መሰረት የውላቸው አካል ባደረጉት እና በዚህ መልኩ አለመግባባት ሲፈጠር ተፈጻሚነት እንደሚኖረው በተስማሙት ድንጋጌ መሰረት የካሳውን መጠን ማስላት ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት በስራ ላይ በደረሰ ጉዲት የሞተው ሰራተኛ ጊዜያዊ ተቀጣሪ ከሆነ የአንድ ዓመት ደመወዙ በአምስት ተባዝቶ ለተተኪዎች በጉዲት ካሳ መልክ እንደሚከፈል ያመለክታል። በልላ በኩል የሟች የወር ደመወዝ 6,710 (ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አስር ብር) ስለመሆኑ ያከራከረ ነጥብ አይደለም። በመሆኑም (6,710 x 12)5 = 402,600 ብር (አራት መቶ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ብር) ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ የካሳ ክፍያ መጠን ውስጥ ቀደም ሲል አመልካች 27,051 ብር (ሃያ ሰባት ሺህ ኃምሳ አንድ ብር) በተጠሪ መስሪያ ቤት የተከፈላቸው ስለመሆኑ ያመኑ በመሆኑ ይሄው ገንዘብ ሲቀነስ ቀሪ ክፍያ 402,600 – 27,051 = 375,549 ብር (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር) ይሆናል ማለት ነው። በዚሁ መሰረት የተጠሪ ድርጅት ለአመልካች 375,549 ብር (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር) እንዱከፍል ብለናል።
ባጠቃላይ በሟች ላይ የደረሰው የሞት አደጋ በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች በስራ ላይ የደረሰ አደጋ አይደለም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. በቀን 10-12-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.122319 መጋቢት 7 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽሯል።
በሟች አቶ ተክለ አያኖ ላይ የደረሰው የሞት አደጋ በስራ ላይ የደረሰ ጉዲት ነው ብለናል።
በመሆኑም የተጠሪ ድርጅት ለሟች ተተኪዎች (ለአመልካች) ብር 375,549 (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር) እንዱከፍላቸው ብለናል።
No topics extracted.