No summary available.
ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1- ወ/ሮ ጥሩሰው ጥላሁን የቀረበ የለም 2- ወ/ሮ ቦጋለች አስፊው ቀረቡ 3- እነ ወ/ሮ ብዙነሽ ካሣ / ወ/ሮ ብዙነሽ ካሣ እና እማኋይ ድንቁ ቢሆነኝ / ቀረቡ ተጠሪ፡- ሲቪል ወርክስ አማካሪ መሃንዱሶች ኃ/የተ/የግል ማህበር ጠበቃ ዜና ደባስ ቀረቡ መዝገቡ ከሰ/መ/ ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የሞት ጉዲት ካሣ የሚጠይቅበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሣሸ የነበሩት የአሁኑ አመልካቾች ሲሆኑ ተከሣሽ የአሁኑ ተጠሪ ነበር። ከሣሾች ክሳቸውን ያቀረቡት በተለያዩ መዛግብት ሲሆን በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱት አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘቱ ባለቤታቸውና የተፀነሰው ልጅ አባት የሆኑት ኢንጂነር ዲዊት ኃ/ማርያም በተጠሪ ድርጅት በኮንስትራክሽን መሐንዱስትነት የስራ መደብ በወር ብር 12,675 ደመወዝና በመስክ ስራ ሲመደቡ ደግሞ በቀን 2ዐዐ ብር አበል እየተከፈላቸው ለመስራት ተቀጥረው ስራውን በመስራት ላይ እንዲለ ተጠሪ መስሪያ ቤት በሚቆጣጠረው በቀይ አፈር ቱርሚ የመንገድ ስራ ኘሮጀክት አብሯቸው እንዱሰሩ ከተመደቡት ከኢንጂነር ለሉት ታምራት ጋር የካቲት 23 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም በመስክ መኪና በሾፋር ወደ ኘሮጀክቱ ቦታ ሄደው የተጠሪን ስራ እየሰሩ ሳለ የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም የተጠሪ ሹፋር በሚያሽከረክረው መኪና የሄደበትን የመቆጣጠር ስራ ለማከናወን ኦሞራቴ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን ድልድይ ተመልክተው ሲመለሱ ደሞኮ ከተማ ሉደርሱ ሁለት ኪል ሚትር ሲቀር መኪናው ተንሸራቶ አሸዋ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ለመውጣት ሲሞክር ደራሽ የጎርፍ ውሃ ደርሶ ተሽከርካሪውን ከእነ ተሳፊሪዎች ይዞ በመሄደ የተነሳ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ሕይወቱ ሉያልፍ እንደቻለ ገልጸው በሚስትነታቸውና ከሟች የጸነሱት ልጅ በአዋጁ መሰረት የሚገባቸው ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። በተራ ቁጥር ሁለት የተጠቀሱት አመልካች ባቀረቡት ክስ ልጃቸው የሆነችው ሟች ኢንጂነር ለሉት ታምራት በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ ደመወዝ 4ዐ55.50 /አራት ሺህ ሃምሳ አምስት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ እና አበል በቀን አንድ መቶ ብር እየተከፈላቸው በመስራት ላይ እንዲለ የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም በስራቸው ላይ እንዲለ በደረሰባቸው አደጋ የሞቱ መሆኑን በመግልፅ የጉዲት ካሣ እና የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። በተራ ቁጥር ሶስት የተጠቀሱት አመልካቾች ደግሞ የወ/ሮ ብዙነሽ ካሣ ባለቤት የህፃን ናሆም ወላጅ አባት፣ የእማኋይ ድንቁ ቢሆነኝ ልጅ የሆኑት ሟች ኢንጅነር ደምስ ወርቁ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው በወር ብር 11,135.00 የመስክ አበል ብር 27ዐ.00 እየተከፈላቸው በመስራት ላይ እንዲለ በየካቲት 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም ከእነ ኢንጂነር ዲዊት ኃ/ማርያም ጋር በደረሰባቸው አደጋ የሞቱ መሆኑን ገልጸው በሕጉ መሰረት የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም በውሃ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው መሃንዱሶች ሰራተኞቹ መሆኑን ሳይክድ አደጋው የደረሰው ከተመደቡበት የስራ ቦታ ወደ ላላ ቦታ በራሳቸው ፍላጎት ስራ በላለበት እሁድ ቀን በመሄድ ሲመለሱ የደረሰ አደጋ በመሆኑ በስራ ላይ እንደደረሰ አደጋ ሉቆጠር አይችልም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮችን ከሰማ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ሟቾች ሕይወታቸው በአደጋ ምክንያት ባለፈበት ጊዜ ከተጠሪ ጋር የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የነበራቸው መሆኑን ተጠሪ ያለመካደንና በማስረጃም መረጋገጡን ከገለጸ በሁዋላ አደጋው የደረሰው ግን ሟቾች በስራ ላይ በነበሩበት ጊዜ ሳይሆን ከስራ ቀንና ቦታ ውጪ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል ፣ አመልካቾች ሟቶች የሞቱት በስራ ላይ ሆነው ስለመሆኑ የማስረዲት ግዳታቸውን አልተወጡም በማለት ደምድሞ ክሱን ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተናጠል አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ባለመስማማት ሲሆን አመልካቾች አቤቱታቸውን በተለያዩ መዛግብት ያቀረቡ ቢሆንም የሁለም አመልካቾቹ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት ግን ሟቾች በተጠሪ መኪና እና ሹፋር ኦሞራቴ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን ድልድይ ተመልክተው ሲመለሱ ጉዲቱ የደረሰባቸው ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 95 እና 97 ስር ላይ በስራ ላይ ስለሚደርስ አደጋ የተቀመጠውን የሕጉን መንፈስ ባግባቡ ሳይመለከቱ አደጋው የደረሰው በስራ ላይ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት ክሱን ውድቅ ማድረጋቸውን ከሕግ ውጪ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ በሟቾች ሞት ምክንያት ለአመልካቾች ካሣ የመክፍል ኃላፉነት አለበት? ወይስ የለበትም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦም በሁለም መዛግብት በሰጠው የጽሐፍ መልስ ሟቾች ሰራተኞቹ መሆናቸውን ሳይክድ አደጋው በደረሰበት እለት ግን የስራ ቀን ካለመሆኑም በላይ ሟቾች ሉመለከቱት የሄደበት ድልድይ ሟቾች እንዱሰሩ ከተመደቡበት ሳይት ውጪ በልላ አቅጣጫ ያለና በእለቱም ሟቾቹ እንዱመለከቱት ከአሰሪው ተገቢው ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ሟቾቹ በራሳቸው ፍላጎት ሄደው ድልድዩን ተመልክተው ሲመለሱ አደጋው የደረሰ በመሆኑ አደጋው በስራ ላይ የደረሰ ነው ልባል እንደማይችልና ኃላፉነት የለበትም ተብል መወሰኑ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ሲል ተከራክሯል። አመልካቾች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታዎቹ መነሻ ከሆኑት ውሣኔዎች እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ሟቾች አደጋው በደረሰበት እለት በመስክ ስራ ላይ የነበሩ መሆኑን ሳይክድ አጥብቆ የሚከራከረው አደጋው የደረሰው ሟቾቹ ከተጠሪ ፈቃድና እውቅና ውጪ በሆነ ሁኔታ ተጠሪ በአማካሪነት በተቆጣጣሪ መሃንዱስነት ከሚሰራበት ቦታ ውጪ ወደአለው በኦሞራቴ ወንዝ ላይ የሚሰራውን ድልድይ ለመመልከት ሄደው ሲመለሱ አደጋው የደረሰ በመሆኑ በስራ ላይ እንደደረሰ አደጋ አይቆጠርም በማለት መሆኑን አመልካቾች ደግሞ ሟቾች በተጠሪ ትዕዛዝ ወደ ቀይ አፈር ቱርሚ የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ለመስክ ስራ መሄዲቸው የተረጋገጠና ወደ ኦሞራቴ ወንዝ ድልድይ ጉብኝት የሄደትም በተጠሪ ሹፋርና መኪና እንዱሁም በወቅቱ የመስኩ ስራ ኃላፉ ከነበሩት ሰው ጋር ጭምር በመሆኑ አደጋው በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ነው በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋጧቸው ነጥቦች ደግሞ ሟቾች በተጠሪ ድርጅት ተቀጥረው የሚሰሩ መሆናቸውን አደጋው ደረሰ የተባለበት እለት እሁድ ሁኖ የእረፍት ቀን መሆኑን ፣ በዚህ እለት ሟቾች በተጠሪ ድርጅት መኪና አሞራቴ ወንዝ ላይ በልላ ድርጅት የሚሰራውን ድልድይ ለመመልከት ሄደው ሲመለሱና ደመኮ ከተማ ለመድረስ ሁለት ኪል ሜትር ሲቀራቸው የተሳፈሩበት መኪና አዋሽ ወንዝ ውስጥ ገብቶ የጎርፍ ደራሽ ውሃ የወሰዲቸውና ለህልፈት የዲረጋቸው መሆኑን ሟቾች ከተመደበቡት የመስክ ስራ ቦታ ውጪ ወደ ሚገኘው ወደ ኦሞራቴ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ጉብኝት የሄደት ከተጠሪ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ኖሮ ሳይሆን በራሳቸው ፍላጎት ስለመሆኑ ነው። በመሆኑም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ከተሰጠው ስልጣን አንጻር ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጧቸውን ፍሬ ነገሮችን እንዲለ በመቀበል የሚኖረው ሚና በሕጉ አተረጓጎም ረገድ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ ስህተት ካለ ማረም ነው። ከዚህ አንፃር በሕጉ ረገድ ያለውን ጉዲይ ተመልክተናል።
በመሰረቱ በስራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ማለት በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ /occupational injury/ ወይም በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ /occupational disease/ እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 95/2/ በግልፅ ተመልክቷል። የአዋጁ አንቀጽ 97 ደግሞ በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ማለት ማንኛውም ሰራተኛ ሥራውን በማከናወን ሳለ ወይም ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሱ ወጭ በሆነ ምክንያት ወይም ስራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት በአካለ ወይም በአካለ ማንኛውም ክፍል ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት ጉዲት በሚደርስበት ጊዜ እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶበታል። በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ማለት ደግሞ ሰራተኛው የአሰሪውን ትዕዛዝ በስራ ላይ እና በስራ ሰዓት ሲፈጽም የደረሰበት ጉዲት ፣ ሰራተኛው ከስራው በፉት ወይም በኋላ ወይም ስራው ለጊዜው ተቋርጦ በነበረበት ጊዜ በስራው ቦታ ወይም በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የደረሰበት ጉዲት ፣ ሰራተኛው ወደ ስራ ቦታ ወይም ከስራ ቦታው ድርጅቱ ለሰራተኞች አገልግልት እንዱሰጥ በመደበው መጓጓዣ በመጓዝ ላይ በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዲት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀፅ 97 ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። በመሆኑም የአሰሪው ሒላፉነት በስራ ምክንያት ለሚመጡ ጉዲቶች የተወሰነ ስለመሆኑ ድንጋጌዎቹ ያስረዲለ። በዚህም መሰረት በአዋጁ የጉዲት ካሣ ለመጠየቅ የሚቻለው ጉዲቱ በስራ ምክንያት የመጣ ሁኖ በስራ ሰዓት ፣ በስራ ቦታና ከስራው ጋር ግንኙነት ባለው አጋጣሚ የተከሰተ መሆኑ በሚገባ ሉረጋገጥ ይገባል ። በመሆኑም የአዋጁ አንቀፅ 96 እና 97 ድንጋጌዎች ጠቅላላ ይዘት ሲታይ ደግሞ አሰሪው በስራ ላይ ሉደርስ የሚችለውን አደጋ የመከላከል እርምጃ የመውሰድ ፣ አደጋው በሕጉ በተቀመጠው ትርጉም መሰረት በስራ ላይ ከደረሰ ደግሞ ካሣ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ያስገነዝባል። በአዋጁ አንቀፅ 95 ድንጋጌ መሰረት የካሣ ክፍያ ጥያቄ የሚያቀርበው ወገን ጉዲቱ የደረሰው በአንቀፅ 97 በተመለከተው አኳኋን በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት መሆኑንና እንደዚሁም በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ቅርብና ቀጥተኛ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት መኖሩን /proximate cause and effect relationship/ ማስረዲት እንደሚጠበቅበት ይታመናል። በልላ በኩል የአሰሪው አላፉነት በጥፊት ላይ ያልተመሰረተ /strict/ ስለሆነ ካሣ ጠያቂው ወገን በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ማሳየት ብቻ እንጂ ከዚህ አልፍ የጉዲት አድራሹን ወይንም የአሰሪውን የአእምሮ ሁኔታ /state of Mind/ ማስረዲት እንደማይጠበቅበት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 96 ስር ከተመለከተው ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ሟቾች በተጠሪ መስሪያ ቤት ተቀጣሪ ሰራተኞች መሆናቸውና በመስክ ላይ እያለ በደረሰባቸው አደጋ ሕይወታቸው ማለፍ እና ይኸው አደጋ የደረሰው ደግሞ በተጠሪ ተመድበው በሚሰሩበት የሥራ ቦታና ሰዐት ሳይሆን ከዚህ ውጪ በራሳቸው ፍላጎት በአካባቢው በልላ ድርጅት የሚሰራውን የድልድይ ግንባታ ለመመልከት ሄደው ድልድዩን ተመልክተው ሲመለሱ መሆኑን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። አደጋው የደረሰው ከስራ ሰዓትና ከስራ ቦታ ውጪ ከስራው ጋር ግንኙነት በላለው አጋጣሚ እና ከአሰሪው ትዕዛዝ ሳይኖር መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋገጠ ደግሞ ተጠሪ በአሰሪነቱ ለጉዲቱ ኃላፉ የሚሆንበት ምክንያት የላለ መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 95፣ 96 እና 97 ድንጋጌዎች ይዘት ያሳያል። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካቾች የሞቱት በስራ ላይ በደረሰ አደጋ አይደለም በማለት የካሣ ክፍያ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ ሕዲር 01 ቀን 2003 ዓ.ም በመ/ ሕዲር 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ፣ በመ/ ሕዲር 01 ቀን 2003 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በመ/ የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. ፣ በመ/ የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት በድምጽ ብልጫ ጸንቷል።
ሟቾች ሕይወታቸው ያለፈው በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ባለመሆኑ ለአመልካቾች የሚከፈል የካሣ ክፍያ የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሣኔ ግልባጩ ከሰ/መ/ ጋር ይያያዝ ብለናል።
የሀሣብ ልዩነት እኛ ስማችን በሶስተኛ ተራ ቁጥር እና በአራተኛው ተራ ቁጥር የተሰየምነው ዳኞች አብላጫው ድምፅ ሟችዎች ህይወታቸው ያለፈው በሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ባለመሆኑ ለአመልካቾች የሚከፈል የካሣ ክፍያ የለም በማለት በሰጠው ውሣኔ የማንስማማ በመሆኑ በሀሣብ ተለይተናል።
ከአብላጫው ድምፅ የምንለይባቸው ምክንያቶች የሚከተለት ናቸው።
ተጠሪ ከኢትዮጵያ መንገድች ባለሥልጣን ጋር ባደረገው የሥራ ውል ከቀይ አፈር አስከቱርሚ ያለውን መንገድ ለመገንባት የሥራ ተቋራጭነት ውል የተዋዋለ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪ በውል የተረከበውን የመንገድ ሥራ ለማከናወን የቀጠራቸውን ሰራተኞችና የግንባታ መሣሪያዎች እንዱያስተዲድርለትና የመንገድ ሥራ ኘሮጀክቱን በበላይነት እንዱመራለት ሟች ኢንጅነር ደምሴ ወርቄን የቀይ አፈርቱርሚ የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መድቦት የነበረ መሆኑ ግራ ቀኙ በሥር ፍርድ ቤትም ሆነ በሰበር በተደረገው ክርክር ያልተካደና የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው። ተጠሪ ለመንገድ ሥራ ኘሮጀክቱ በመደባት የመለያ ቁጥር 3-43639 መኪና የትራንስፕርት አገልግልት እያገኙ እያለ “ወራባ” ከተባለው ወንዝ በደራሽ ጎርፍ ውሀ የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ተወስደው ህይወታቸው ካለፈው አራት ሰዎች ውስጥ አንደኛው ማለትም ኢንጅነር ደምሴ ወርቄ የቀይ አፈርቱርሚ የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ የነበረ ነው ኢንጅነር ደምሴ ወርቄ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 2/ሐ/ እንደተሻሻለ በተደነገገው መሰረት የድርጅቱ /የተጠሪ/ ሥራ መሪ ናቸው።
ላልቹ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ማለትም ኢንጅነር ዲዊት ሀይለማርያም ኢንጅነር ለሉት ታምራትና የተጠሪ ሰራተኞች መሆናቸው ተረጋግጧል። በእኛ እምነት ሟች ኢንጅነር ዲዊት እና ኢንጅነር ለሉት የሞት አደጋ የደረሰባቸው ሥራ በመሥራት ላይ እያለ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ኢንጅነር ዲዊትና ኢንጅነር ለሉት ወደ “አምራቴ” ወንዝ የመስክ ሥራ ጉብኝት ለማድረግ የሄደት በአሰሪው /በተጠሪው/ ትዕዛዝ በተሰጣቸው የሥራ ስምሪትና ትዕዛዝ መሰረት ነው ወይስ አይደለም ? የሚለው ነጥብ መመለስ አለበት። የቀይ አፈር ቱርሚ የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር ደምሴ ወርቄ ተጠሪ በተቋራጭነት የሚሰራውን የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ስኬታማ በሆነ መንገድ ለመሥራት አስፈላጊ ነው የሚለውን ሥራ እንዱሰሩና ከሙያቸው ጋር ተያያዥነት ያለውን የመስክ የሥራ ጉብኝት እንዱያደርጉ በሥሩ የሚገኙትን ሰራተኞች የማሰማራት ሥልጣን እንዲለው ይገመታል። ከዚህ በተጨማሪ የኘሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ካለት ሰራተኞች የተወሰኑትን ብቻ ለይቶ ከመደበኛ የሥራ ቀናት ፣ ከመደበኛ የሥራ ሰዓትና ከመደበኛው የሥራ ቦታ ውጭ ለሥራ ሉያሰማራና የመስክ የሥራ ጉብኝት እንዱያደርጉ የማድረግ ሥልጣንና ኃላፉነት እንደሚኖረው የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ልዩ የሥራ ባህሪና በግንባታው ሥራ መስክ የዲበሩ የአሰራር ልምድችን በተለይም ስለግንባታ አካሄድ የወጣውን የሥራ መመሪያ በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
ተጠሪ የኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ለነበረው ለኢንጅነር ደምሴ ወርቄ የሰጠው ሥልጣንና ኃላፉነት ሰራተኞችን ለሥራ የማሰማራትና ለሥራው አፈፃፀም ጠቀሜታ ያለው የመስክ የሥራ ጉብኝት እንዱያደረጉ ለማድረግ የሚያስችለው እንደነበር የማስረዲት ግዳታ ያለበት ሲሆን ተጠሪ ይህንን የማስረዲት ግዳታውን አልተወጣም። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ከመደበኛው የሥራ ቀናት ከመደበኛ የሥራ ሰዓትና ከመደበኛ የሥራ ቦታ ውጭ የድርጅቱን ሰራተኞች ለሥራ የማሰማራትና የመስክ የሥራ ጉብኝት እንዱያደርጉ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን ያልነበረው መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረበም እንጅ ማስረጃ ቢያቀርብ እንኳን በሥራ አስኪያጅ ሥልጣን ላይ ተጠሪ የጣለውን ገደብ የኘሮጀክቱ ሰራተኞች በጠቅላላውና ሟችዎች ኢንጅነር ዲዊትና ኢንጅነር ለሉት በግልፅ እንዱያውቁት ያደረገ መሆኑንና ሟችዎች ሥራ አስኪያጅ ከሥራ ከመደበኛ ሥራ ቀናቶች ከመደበኛ የሥራ ሰዓታቸውና ከመደበኛ የሥራ ቦታቸው ውጭ እንዱሰማሩና የመስክ የሥራ ጉብኝት እንዱያደርጉ የማዘዝ ሥልጣን እንደላለው የሚያውቁ መሆኑን የማስረዲት ግዳታና ሀላፉነት አለበት። ተጠሪ ይህንን የማስረዲት ግዳታውን ያልተወጣ መሆኑን በሥር ፍርድ ቤት ከቀረበው ክርክርና በሰበር ከቀረበው ክርክር ለመገንዘብ ይቻላል።
ተጠሪ የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጅ በነበረው የኢንጅነር ደምሴ ወርቄ ሰራተኞችን ከመደበኛ የሥራ ቀናቶች ውጭ ለሥራ የማሰማራት ሥልጣንና ኃላፉነቱ የተገደበ መሆኑን አላስረዲም። አንድ ሰራተኛ በሥራ ውለና በሥራ ደንቡ መሰረት በአሰሪው የሚሰጠውን የሥራ ስምሪትና ትዕዛዝ የመፈፀም ግዳታ ያለበት መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13 ንዐሰ አንቀፅ 2 በግልፅ ተደንግጓል። ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ኢንጅነር ለሉት የካቲት 23 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ከቀይ አፈርቱርሚ ኘሮጀክት ውጭ “በአሞራቴ” ወንዝ ላይ በመሰራት ላይ የነበረውን ድልድይ ከቦታው ድረስ በመሄድ የሙያ የመስክ የሥራ ጉብኝት ያደረጉ መሆኑን አመልካቾች ያልካደትና የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው። ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ኢንጅነር ለሉት ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጭ በእረፍት ቀናቸው ከመደበኛ የሥራ ቦታቸው ውጭ የሚገኘው በአሞራቴ ወንዝ ላይ እየተሰራ የነበረውን ድልድይ ለማየት የሄደት ተጠሪን በመወከል የመንገድ ሥራ ኘሮጀክቱን በኃላፉነት ሲመራ የነበረው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱን መኪና እና ሹፋር በማንቀሣቀሥና ሥራ አስኪያጅም አብሮ በመጓጓዝ እንደሆነ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
የመስክ ጉብኝቱ የኘሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ሟችዎች በእረፍት ቀናቸው ከመደበኛ የሥራ ቦታ ውጭ የመሥክ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ተጠሪ በተቋራጭነት የያዘውን የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ስኬታማ በሆነ መንገድ ለመሥራት ጠቃሜታ እንዲለው አምኖበትና አውቆት እንደዚሁም የድርጅቱ ሥራ መሪ የመስክ የሥራ ጉብኝቱ ተካፊይ ሆኖበት የተከናወነ ነው።
ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ሟች ኢንጅነር ለሉት በደራሽ ጎርፍ ውሀ የተወሰደት ከመደበኛ የሥራ ቦታቸው ከቀይ አፈርቱርሚ ኘሮጀክት ክልል ውጭ ሣይሆን በመደበኛ የሥራ ቦታቸው በተለይም ከመኖሪያ ሰፈራቸው በሁለት ኪል ሜትር ዕርቀት በሚገኘው “ወራባ” በተባለው ወንዝ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው። ሟችዎች በእረፍት ቀን ከመኖሪያ ሰፈራቸው ወጥተው በአሞራቴ ወንዝ ላይ እየተሰራ የነበረውን ድልድይ ለመጎበኘት የተጓዙትና ከዚያም በኋላ ከሄደበት የመስክ የሥራ ጉብኝት ተመልሰው በቀይ አፈርቱርሚ ኘሮጀክት ክልል ውስጥ በደራሽ ጎርፍ የተወሰደት የተጠሪ የሥራ መሪና የመንገድ ሥራ ኘሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በነበረው ኢንጅነር ደምሴ ወርቄ ተግባራዊ እንዱሆን ባደረገው የመስክ የሥራ ጉብኝትና በሰጠው የሥራ ስምሪት ትዕዛዝ መሰረት ነው። ሟችዎች በእረፍት ቀናቸው የመስክ የሥራ ጉብኝት እንዱያደርጉ የኘሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ የሰጠው የሥራ ስምሪት በአሰሪው ማለትም በተጠሪ እንደተሰጠ የሥራ ሥምሪት ትዕዛዝና የመስክ የሥራ ጉብኝት የሚቆጠር መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 2/ሐ/ ድንጋጌዎች ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 2188 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብና ህጋዊ ውጤት ለመረዲት ይቻላል።
በመሆኑም አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካች ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ሟች ኢንጅነር ለሉት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 2 በሚደነግገው መሰረት ከአሰሪያቸው /ከተጠሪ/ በእረፍት ቀናቸው ከመደበኛ የሥራ ቦታቸው ውጭ እንዱያከናውኑ የተሰጣቸውን የመስክ ሥራ ጉብኝት ትዕዛዝ አከናውነው ሲመለሱ በቀይ አፈርቱርሚ ኘሮጀክት ክልል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 2 ፣ አንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 2/ሐ/ እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2188 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት የማስረዲት ግዳታቸውን ተወጥው እያለ የሥር ፍርድ ቤት ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ሟች ኢንጅነር ለሉት በሥራ ላይ እያለ አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን አመልካቾች አላስረደም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ከላይ የዘረዘርናቸውን ሁኔታዎችና የህግ ድንጋጌዎች ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚል ሀሣብ አለን።
ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ሟች ኢንጅነር ለሉት አሰሪያቸው /ተጠሪ/ ኘሮጀክቱን በበላይ ኃላፉነት ይመራ በነበረው ሥራ አስኪያጅ የተሰጣቸውን የመስክ ሥራ ስምሪትና የመስክ ሥራ ጉብኝት በማክበር በእረፍት ቀናቸው ከመደበኛ የሥራ ቦታው ውጭ የሚገኘውን “የአሞራቴ” ወንዝ ላይ የሚሰራውን ድልድይ ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ በቀይ አፈርቱርሚ የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ክልል ውስጥ በደራሽ ጎርፍ ተወሰደው የሞት አደጋ ደርሶባቸዋል ። አንድ ሰራተኛ ከሥራ ቦታው ወይም ከመደበኛ ሥራ ሰዓት ውጭም ቢሆን የአሰሪውን ትዕዛዝ ሥራ ላይ ሲያውል በነበረበት ጊዜ የደረሰበት ጉዲት በሥራ ላይ የደረሰ ጉዲት እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 97 ንዐስ አንቀፅ /ሀ/ በግልፅ ተደንግጓል። ሟችዎች የመስክ የሥራ ጉብኝት በማድረግ በእረፍት ቀናቸው አይተውት የተመለሱት በአማራቴ ወንዝ ላይ እየተሰራ ያለው ድልድይ ከሟችዎች የመደበኛ የሥራ ቦታ ክልል ውጭ የሚገኝ መሆኑን በመመልከት ብቻ የበታች ፍርድ ቤቶች አደጋው በሥራ ላይ የደረሰ አይደለም በማለት የሰጡት ትርጉምና የደረሱበት መደምደሚያ ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ሟች ኢንጅነር ለሉት በኘሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ የተሰጣቸውን የሥራ ስምሪትና ትዕዛዝ በመፈፀም ላይ እያለ አደጋው የደረሰ መሆኑን ያላገናዘበና የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 97 ንዐስ አንቀፅ /ሀ/ የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።
በመሆኑም አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካቾች ሟች ኢንጅነር ዲዊትና ሟች ኢንጅነር ለሉት በእረፍት ቀናቸው እንዱያከናውኑ በአሰሪያቸው/ በተጠሪ/ የተዘጋጀውን የመስክ ሥራ ጉብኝት በማከናወን ላይ እያለ “ወራባ ” ተብል በሚጠራው ወንዝ በገጠማቸው በደረሰ የጎርፍ ውሀ ተወሰደው የሞት አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን የማስረዲት ግዳታቸውን የተወጡ በመሆኑ አንደኛ አመልካችና ሁለተኛ አመልካቾች በሟችዎች መሞት ለደረሰባቸው ጉዲት ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 110 መሰረት ተጠሪ ካሣ እንዱከፍላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 3 ንዐስ አንቀፅ 2/ሐ/ ፣ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2188 ንዐስ አንቀፅ 1 ፣ የአዋጅ አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 2 እና የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 97 ንዐስ አንቀፅ /ሀ/ መሰረት ያደረገ ህጋዊ ጥያቄ ነው በማለት በሀሣብ ተለይተናል።
የመንገድ ሥራ ግንባታን በኃላፉነት የሚመራ ሥራ አስኪያጅ በልላ የሥራ ተቋራጭ በመሰራት ላይ የሚገኝ ድልድይ በአካል ተገኝቶ መጎብኘት ሙያዊ ልምድ መቅሰሙና ላልች ባለሙያዎችም የሙያ ልምድ የሚያገኙበትን የመስክ የሥራ ጉብኝት ማመቻቸቱ በግንባታ ኘሮጀክት የሥራ አመራር ሂደት ያልተለመደና የአመራር ጉድለትና ጥፊት መሆኑን ተጠሪ ያቀረበው ማስረጃ እንደላለ ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል። በመሆኑም ሟች ኢንጅነር ደምሴ ወርቄ የተጠሪ የሥራ መሪ ሆኖ የመንገድ ኘሮጀክት ሥራ በሀላፉነት ሲመራ በእረፍት ቀኑ ጭምር ሥራውን በትጋት በመፈፀም ላይ እያለ የሞት አደጋ የደረሰበት መሆኑን ከላይ በዝርዝር የገለፅናቸው ዝርዝር ጉዲዮች ያሣያለ። ስለሆነም ሶስተኛ ተጠሪዎች ሟች ኢንጅነር ደምሴ ወርቄ የተጠሪን የመንገድ ሥራ ኘሮጀክት ሥራ በትጋት ሲመራና በእረፍት ቀኑ ሲሰራ የሞት አደጋ የደረሰበት በመሆኑ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 110 መሰረት ካሣ እንዱከፈላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የሥራ ውለን መሰረት ያደረገና ህጋዊ ጥያቄ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ሉሻርና ተጠሪ ለአመልካቾች ካሣ እንዱከፍል ሉወሰንበት ይገባል በሚል ዕምነት በሀሣብ ተለይተናል።
No topics extracted.