No summary available.
ሐምል 20 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሪመምበር ዘ ፐረሰት ኮሚዩኒቲ - ጠበቃ ለሜሳ ያደታ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዘውድነሽ ማሞ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/1996"ን" መሰረት አድርጎ የቀረበን የግል የስራ ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀረመው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በአዲማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የአመልካች የክስ ይዘትም ባጭሩ ሲታይ ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ውል ግንኙነት ከሕግ ውጪ የተቋረጠባቸው መሆኑን ጠቅሰው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍሎቸውና የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የተጠሪ የስራ ድርሻ ሕጻናትን መንከባከብ ሲሆን ከምትንከባከባቸው ሕጻናት ውስጥ ፍፁም ወርቁ የሚባለውን ደብድባ ሰውነቱ እስኪላጥ ድረስ ጉዲት ማድረሷ በመረጋገጡ የተፈጸመ ስንብት በመሆኑ ሕጋዊ ስለሆነ የሚከፈላት ክፍያ የለም ሲል ተከራክሯል።የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና የሰነድ ማሰረጃ መርምሮ ህፃኑ መደብደቡ ቢረጋገጥም ድብደባውን የፈፀሙት ተጠሪ ስለመሆናቸው አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ብል አመልካች ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች ሉከፍሎቸው ይገባል በማለት የክፍያዎችን አይነትና መጠን ለይቶ ወስኗል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩና ተደበደበ የተባለው ሕፃን ቀርቦ ከተሰማ በኋላ ተጠሪ ድርጊቱን መፈጸማቸው ተረጋግጧል ተብል ስንብቱ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27(2)፣14(2)(ሀ)) እና 27(1(ረ)) መሰረት ሕጋዊ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ተሽሯል። ከዚህ በኋላም ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሽሮ የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በሚንከባከቡት ሕፃን ላይ በድብደባ ተግባር ጉዲት ያደረሱ ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የሻረው ያላአግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት እንዱቀርብ ከተደረገ በኋላ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም የአመልካች የስንብት እርምጃ ሕገ ወጥ ነው ተብል ለተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፍል መወሰኑ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገነዘብ የተቻለው አመልካች ድርጅት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል የህጻናት እንክብካቤ የሚገኝበት መሆኑንና የተጠሪ ስራም ሕጻናትን መንከባከብ መሆኑን፣ተጠሪ ከአመልካች ጋር የመሰረቱት የስራ ውል ሉቋረጥ ችሎል በማለት አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ ፍጹም ወርቁ የተባለ ሕፃን ላይ በድብደባ ተግባር ጉዲት አድርሰዋል በሚል መሆኑንና ይህንኑ ክርክሩን ለማስረዲትም የሰነድ ማስረጃዎችን ማቅረቡን፣ የወረዲው ፍርድ ቤትና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ተጠሪ ለድርጊቱ ተጠያቂ ሉሆኑ አይችለም ወደሚለው ድምዲሜ ደርሰው ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ለማለት የቻለት ድርጊቱን ተጠሪ ስለመፈጸማቸው አመልካች አምነዋል በማለት ያቀረበው ሰነድ ቢኖርም ተጠሪ በፍርድ ቤት ሲቀርቡ ሰነደን ክደው የተከራከሩ በመሆኑና የህክምና ማስረጃውም ጉዲቱ በተጠሪ ስለመድረሱ ያረጋግጣል ልባል የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት መሆኑን፣የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን ድብደባው ተፈፅሞበታል የተባለውን ሕጻን አስቀርቦ ጉዲቱ በተጠሪ የደረሰበት ስለመሆኑ በማረጋገጥ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ የሻረው መሆኑን ነው።
እንግዱህ ከላይ ከተገለፀው የፍርድ ቤቶች የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት መገንዘብ የሚቻለው በሕፃኑ ላይ አካለ ላይ ጉዲት የደረሰበት መሆኑ በሁለም ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ሁኖ ጉዲቱ በምን ምክንያት ነው የደረሰው? በሚለው ጥያቄ ላይ ግን የተለያየ ድምዲሜ ፍርድ ቤቶቹ የያዙ መሆኑን ነው።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን በሕፃኑ ላይ ጉዲቱ እንዳት ደረሰ? ለሚለው ጥያቄ ሕፃኑን በችልት በማስቀረብ ሰምቶ ጉዲዩን በአግባቡ አጣርቶ ተጠሪ ጉዲቱን ስለማድረሳቸው አረጋግጧል።የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ግን በወረዲው ፍርድ ቤት የቀረቡትን የሰነድ ማሰረጃዎችን መሰረት በማድረግ ተጠሪ ጉዲቱን አድርሰዋል ለማለት የሚቻል አይደለም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠውን የሕፃኑን ቃል በመተው ነው።ይህ ደግሞ ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ለ)) እና በክልለ ሕገ መንግስት አንቀፅ 64(2(ሐ) እንዱሁም በክልለ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 141/2000 አንቀፅ 31 የተሰጠውን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም ስልጣን ባግባቡ ያላገናዘበ ነው። የሰበር ችልቱ ፍሬ ነገርን ማጣራት ወይም ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የላለው መሆኑን ከተጠቃሽ ሕጎች ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ ይቻላልና።በመሆኑም ድብደባውን ማን አደረሰው የሚለው ጥያቄ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባለው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረጋግጦ እያለ ይኸው ፍሬ ነገር በክልለ ሰበር ሰሚ ሳይታይ መታለፈ በህጋዊ ምክንያት ያለመሆኑን ተገንዝበናል።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕፃኑን በራሱ ተነሳሽነት አስቅረቦ መስማቱም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 345(1) መሰረት ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ሲል ተጨማሪ ማስረጃ ማስቀረብ እንደሚችል በሕጉ የተሰጠውን ስልጣን መጠቀሙን ያሳያል ከሚባል በስተቀር በማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ደንብ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ፈጽሟል ለማለት የሚቻልበት ምክንያት የለም።የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህጻኑ የተደበደበውና ጉዲቱ የደረሰበት በተጠሪ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ የተከተለው መንገድ ሕጋዊ ነው፣ጉዲቱም በተጠሪ በተፈፀመው የድብደባ ተግባር የደረሰ ነው ከተባለ ይህ ጥፊት አንድን ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የሚያስችል ምክንያት መሆን ያለመሆኑን መመልከቱ ተገቢ ይሆናል።ማናቸውም ሰራተኛ ሕይወትና ንብረትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ድርጊት መፈፀም ሕገ ወጥ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 14(2(ሀ))ስር የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 27(1(ቀ)) ስር ደግሞ በአንቀጽ 14(2) ስር የተመለከቱትን ሕገ ወጥ ድርጊቶችን መፈፀም የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ በግልጽ ተመልክቷል።በመሆኑም ተጠሪ በሚንከባከቡት ሕፃን ላይ የድብደባ ተግባሩን መፈፀማቸው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደረገው የፍሬ ነገር ማጣራትና የማስረጃ ምዘና የተረጋገጠ ሁኖ በሕፃኑ ላይ ደረሰ የተባለው ጉዲትም ሲታይም ሕይወቱን ለአደጋ ሉያጋልጥ የማይችል ነው ልባል የሚችልበትን ሕጋዊ ምክንያት የላለ ስለመሆኑ ተገንዝበናል። ስለሆነም አመልካች ከስራ የተሰናበቱት በአዋጁ አንቀፅ 27(1(ቀ)) ድንጋጌ በመሆኑ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ልባል የሚችልበት አግባብ የለም።በዚህም ምክንያት የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ ለሰበር ችልቱ በሕጉ ተለይቶ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ከመሆኑም በላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 345 መሰረት ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን ስልጣን ያላገናዘበና በውጤቱም የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1(ቀ)) ድንጋጌን የጣሰ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው በሕጉ አግባብ ስለሆነ ስንብቱ ሕጋዊ ነው ብለናል።አመልካች ከተጠሪ ደመወዝ ብቻ በመቁረጥ ሲያጠራቅም የነበረ የፔሮቪደንት ፈንድ ካለ ይህንኑ ተጠሪ ከመጠየቅ ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.