No summary available.
ሐምል 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አኪኮ ቦዱዋይዝ ኃ/የተ/የግል ማህበር - ጠበቃ አቶ ጌታቸው ወንድሙ ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ገረመው አበበ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው የአሁን አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው ህግ በደነገገው መሰረት ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክርና በማስረጃ ከተረጋገጠው የፍሬ ነገር ጉዲይ ጋር በማገናዘብ ለይቶ ለመወሰን ሲባል ነው።
በዚህ ጉዲይ የአሁን ተጠሪ ሥራዬን በአግባቡ እየተወጣሁ እያለ አሰሪው ወደ ላላ የሥራ መደብ ተዛውረሃል በአዱሱ የስራ መደብ ሄደህ ሥራ በማለት በቃል ሲገልጽልኝ፤ በተዛወርኩበት ቦታ ሥራዬን በኃላፉነት በአግባቡ እንድወጣ የዝውውር ደብዲቤ ይድረሰኝ በማለት በመጠየቄ በጥበቃ ኃላፉው ተገድጄ እንድወጣ ተደርጓል። በዚህም የተነሣ የሥራ ውለ የተቋረጠ ስለሆነ ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ የሚገባኝ ልዩ ልዩ ክፍያ እንደ ህጉ ይፈፀምልኝ በማለት ዲኝነት ስጠይቅ፤
የአሁን አመልካች በበኩለ ከአሰሪነቴ በመነጨ ሥልጣን ሰራተኛው በልላ የሥራ መደብ ተዛውሮ እንዱሰራ፤ የዝውውር ደብዲቤ በቀጣይነት እንደሚደርሰው በሥራ ኃላፉው ግልፅ ትዕዛዝ ቢደርሰውም ሥራ አልጀመረም። በዚህም የተነሳ በቀድሞው የሥራ ቦታ ሉያቆያቸው የሚችል ምክንያት የላለ መሆኑ ተገልፆ ወደ መደብ የሥራ ቦታቸው እንዱሄደ ሲነገራቸው ሥራቸውን በፈቃዲቸው ለቀው ሄደዋል በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙ የሥራ ውል የተቋረጠው በሰራተኛው ፈቃደኝነት ወይስ በአሰሪው አነሳሽነት? የሚለውን በአከራካሪ ነጥብነት ይዞ በጉዲዩ ላይ ማስረጃ ሰምቷል። በተሰማው ማስረጃ መሰረትም አሰሪው ሰራተኛውን የድርጅቱ የሥራ ቦታ በሆነ በልላ ቦታ ተዛውሮ እንዱሰራ በቃል መገለፁንና ሰራተኛውም ዝውውር በፅሁፍ ይድረሰኝ በማለት ሲጠይቅ እንደነበር አሰሪውም በድርጅቱ የጥበቃ ኃላፉ አማካኝነት ሰራተኛው ተገድ እንዱወጣ ያደረገ መሆኑንና ሰራተኛውም ልብ አድርጉ እያለ ተገድ ወጥቶ መሄደን ከዚያም ወደ ሥራ ቦታ ሉመለስ ያልቻለ መሆኑን በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ እንደሆነ ከውሳኔው ግልባጭ ተረድተናል። ስለሆነም አመልካች ሰራተኛው ወደ ተዛወረበት ቦታ አልሄድም በሚል ምክንያት ሥራውን በገዛ ፈቃደ ለቋል የሚለው ክርክሩ በማስረጃው የተረጋገጠውን ጉዲይ መሰረት ያደረገ ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል ለግራ ቀኙ ክርክር መነሻ የሆነው የዝውውር ጉዲይ እንደሆነ በማስረጃ ከመረጋገጡም በላይ ሁለቱንም ወገኖች ያለያያቸው ነጥብ አይደለም። የተለያዩበት ነጥብ አመልካች እንደ አሰሪነቴ የዝውውር እርምጃውን በቃል ትዕዛዝ አስተላልፋያለሁ፤ በቀጣይም የዝውውር ደብዲቤ እንደሚደርሰው እየተገለፀለት ወደ ምድብ ሥራው መሄድና ሥራ መጀመር ሲገባው ይህንን አላደረገም የሚለውን በማስቀደም በሰራተኛው በኩል ጥፊት እንዲለ ለማሳየት ሲል ክርክሩን አቅርቧል።
ይሁን እንጂ ሰራተኛው የተዛወረበት ክፍል ከቦታም ሆነ ከሥራ መደብ አንፃር ሲታይ ቀድሞ ተመድቦ ይሰራበት ከነበረው የሥራ አድራሻም ሆነ የሥራ መደብ የተለየ ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ሲሆን፤ አመልካች ለዚህ ያቀረበው ማስተባበያ ክርክር የለም። ይህም ከሆነ አሰሪው የዝውውሩን እርምጃ በቃል በማስተላለፍና የሚያስገድድ አጣዲፉ ሁኔታ መኖሩን ካላስረዲ በቀር የዝውውር እርምጃውን በቃል አስተላልፋያለሁ፤ በቀጣይም በደብዲቤ እገልፃለሁ ማለቱ የአስተዲዲሪነት ሥልጣኑን በዘፈቀደ ለማከናወን ከመሻት የመነጨ ምክንያት ነው ከሚባል በቀር የእርምጃውን ህጋዊነት አያሳይም። ተጠሪም ይህ የዝውውር ውሳኔ በቃል መሆኑ ቀርቶ በፅሁፍ ይደረግልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ ተዛውሮ እንዱሄድ ከተገለፀለት የሥራ አድራሻ እና የሥራ መደብ አንፃር የአንድ መ/ቤትን አግባብ የሆነ የዝውውር አፈፃፀም ተከትል ያቀረበው የመብት ጥያቄ ነው የሚያሰኝ እንጂ የአሰሪውን ትዕዛዝ ላለመፈፀም ያደረገው ተግባር ሆኖ አይገኝም።
በመሆኑም ለግራ ቀኙ ውዝግብ የሆነው ምክንያት አሰሪው በእራሱ በፈፀመው ያልተገባ ተግባር እንደሆነ መረዲት ችለናል።
አሰሪው የወሰድኩት እርምጃ ህጋዊ መሰረት ያለው ነው በሚል ያመነበት ቢሆን እንኳ ተጠሪ ወደ አዱሱ የስራ ቦታ ሄድ ሥራ ባለመጀመሩ ምክንያት የሥራ ደንቡ እና ህጉ በሚፈቅደው ቅደም ተከተለ የጠበቀ አስተዲደራዊ እርምጃ መወሰድ ከሚችል በቀር ሰራተኛውን የጥበቃ ኃላፉ በሆነው አማካኝነት ከስራ ቦታ አስገድድ እንዱወጣ በማድረጉ በእራሱ እጅ የመዲኘት ተግባሩ ላላው ህጋዊ መሰረት የላለው እርምጃ ሆኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም የሥራ ውለ ሉቋረጥ የቻለው ከላይ በተገለፁት ምክንያቶች በሰራተኛው ፈቃድ ሳይሆን ሰራተኛው/የአሁን ተጠሪ/ ደንቡን ባልጠበቀ ዝውውር ምክንያት ለመሄድ እቸገራለሁ በማለት ተገቢው እንዱፈፀም በመጠየቁ ምክንያት አሰሪው ከሥራ ቦታው በድርጅቱ ጥበቃ ሰራተኛ አማካኝነት አስገድድ በማስወጣቱ ህገ-ወጥ ድርጊት ሆኖ ስለተገኘ የሥር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ህጉ ከደነገገው ውጭ የተፈፀመ ነው በሚል የሰጡት ዲኝነት በማስረጃ የተረጋገጠውን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በስንብቱ አግባብነት ዙሪያ ክርክር ከማቅረቡ በፉት በክፍያው ጉዲይ ላይ ያነሳው ክርክርም የለውም።
በዚህ ሁለ ምክንያት በበታች ፍ/ቤቶች አመልካች በወሰደው ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ሳቢያ የሥራ ውለ የተቋረጠ መሆኑን ተገንዝበው የሰጡት ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ባለማግኘታችን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በጉዲዩ ላይ ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ በ29/3/2004 ዓ.ም የሰጠውና የመጨረሻ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
ከዚህ በፉት በዚህ የሰበር መዝገብ ሚያዝያ 13 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ እንዱነሳ ብለናል። ይፃፍ።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክር የተነሳ የደረሰውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.